5 ሙሴ የእስራኤልን ህዝብ ሁሉ ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፣ ‹እናንተ የእስራኤል ህዝቦች ሆይ፣ ዛሬ እኔ ለእናንተ የምሰጣችሁን ህጎችና ድንጋጌዎች ሁሉ አድምጡ፡፡ በልባችሁ ጠብቋቸው እነርሱንም ለመታዘዝ እርግጠኞች ሁኑ፡፡ 2በሲና ተራራ በነበርንበት ጊዜ፣ ያህዌ አምላካችን ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፡፡ 3ነገር ግን ይህ ቃል ኪዳን ለአባቶቻችን ብቻ የተሰጠ አልነበረም፡፡ እርሱ አሁን በህይወት ላለነው ጭምር ሰጥቶናል፡፡