6 “ያህዌ አምላካችን አስተምራችሁ ዘንድ ያዘዘኝ ትዕዛዛትና ህግጋት እንዲሁም ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፡፡ በምትገቡባትና በምትወርሷት ምድር እነዚህን ትጠብቋቸው ዘንድ ይፈልጋል፡፡ 2እርሱ እናንተ ታከብሩት ዘንድ ይፈልጋል፣ ለረጅም ዘመን ትኖሩ ዘንድ እናንተና ትውልዶቻችሁ እኔ ለእናንተ የሰጠኋችሁን እነዚህን ህግጋትና ደንቦች ሁልጊዜም እንድትጠብቁ ይፈልጋል፡፡