3 1 “ከዚያ ወደ ሰሜን ዞረን ወደ ባሳን ግዛት ሄድን፡፡ የዚያ አካባቢ ንጉስ ዐግ፣ በኤድራይ ከተማ እኛን ለመውጋት ወታደሮቹን ሁሉ ይዞ ከደቡብ አቅጣጫ ዘመተብን፡፡ 2ያህዌ እንዲህ አለኝ፣ ‹እርሱን አትፍራው፣ ምክንያቱም እርሱንና ወታደሮቹን ሁሉ እንዲያሸንፉ ምድራቸውንም ሁሉ እንዲወርሱ እኔ ለወታደሮችህ አቅም እሆናለሁ፡፡ የሂሴቦን ገዢ በሆነው በአሞር ህዝብ ወገን ንጉስ በሴዎን ላይ ያደረስክበትን በእርሱም ላይ አድርግ፡፡