31

1ሙሴ ለእስራኤላዊያን ሰዎች ይህንን ሁሉ ተናግሮ ሲጨርስ፣ እንዲህ አለ፣ 2 “አሁን እኔ 120 አመቴ ነው፡፤ ከእንግዲህ እኔ ወደምትፈልጉበት ስፍራ ሁሉ መሄድ አልችልም፤ ስለዚህ የእናንተ መሪ ሆኜ መቀጠል አልችልም፡፡ በተጨማሪም፣ ያህዌ የዮርዳኖን ወንዝ እንደማልሻገር ነግሮኛል፡፡ 3ነገር ግን ያህዌ አምላካችን ከእናንተ ፊት ይሄዳል፡፡ በዚያ የሚኖሩ ህዝቦችን ምድራቸውን ትወርሱ ዘንድ እንድታጠፏቸው አቅም ይሆናችኋል፣ ያህዌ እንደነገረኝ ኢያሱ መሪያችሁ ይሆናል፡፡