1 እኔ አሁን ያህዌ አምላካችንን ብትታዘዘው አንተን የሚርክበትን መንገዶችና ባትታዘዘው አንተን የሚረግምባቸውን መንገዶች ነግሬሃለሁ፡፡ ነገር ግን ህግጋቱን አለመታዘዝ ብትመርጥ፣ አንድ ቀን እርሱ በሚበትንህ ምድር ትኖራለህ እናም ያን ጊዜ የነገርኩህን ታስታውሳለህ፡፡ 2ከዚያ፣ አንተና ልጆችህ ያህዌ አምላካችንን ማምለክ ብትጀምሩና ዛሬ ታደርገው ዘንድ ያዘዝኩህን ሁሉ በታማኝነት መታዘዝ ብትጀምር፣ 3እንደገና ይቅር ይልሃል፡፡ ከተበተንክበት አገር መልሶ ይሰበስብሃል፣ እንደገና ባለጸጋ ያደርግሃል፡፡