27
1ሙሴ፣ ከሌሎች የእስራኤል መሪዎች ጋር ሆኖ ለህዝቡ እንዲህ አለ፣ “ዛሬ ለእናንተ የምሰጣችሁን ትዕዛዛት ሁሉ ጠብቁ፡፡ 2በቅርቡ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግራችሁ አምላክህ እግዚአብሔር ሊሰጥህ ቃል ወደገባልህ ምድር ትገባለህ፡፡ በዚያ፣ ትላልቅ ድንጋዮችን አቁምና በኖራ ቀባቸው፡፡ 3አባቶቻችን ያመለኩት ያህዌ ሊሰጥህ ቃል ወደ ገባልህ ወደዚያች ለም ምድር ስትገባ በእነዚያ ድንጋዮች ላይ እነዚህን ህጎችና ትምህርቶች ጻፍባቸው፡፡