1ሁለት እስራኤላዊያን ተጣልተው ወደ ፍርድ ቤት ቢሄዱ፣ ምናልባት ዳኛው አንዱን ነጻ አድርጉ ሌላኛውን ጥፋተኛ ብሎ ይበይናል፡፡ 2ዳኛው ጥፋተኛው ሰው መቀጣት ይገባዋል ቢል፣ በፊቱ መሬት ላይ ተደፍቶ እንዲገረፍ ማዘዝ አለበት፡፡ ጥፋተኛው የሚገረፈው በሰራው ወንጀል መጠን ነው፡፡