1 2 1ማናቸውም የመዋለጃ ብልቱ የተኮላሸ ወንድ የያህዌ ህዝብ ሆኖ አይቆጠርም፡፡ 2ማንኛውም ከህግ ውጭ የተወለደ ሰው ወይም የዚህ ሰው ትውልድ እስከ አስር ትውልዱ ድረስ፣ የያህዌ ህዝብ ሆኖ አይቆጠርም፡፡ 3 4 3ከአሞን ወይም ሞአብ ወገን የሆነ እስከ አስር ትውልዱ ድረስ የያህዌ ህዝብ ተደርጎ አይቆጠርም፡፡ 4ለዚህም አንዱ ምክንያት፣ አባቶቻችሁ ከግብጽ ተነስተው ወደ ከነዓን ሲጓዙ መሪዎቻቸው ምግብና ውሃ ሊሰጧቸው አልወደዱም ነበርና ነው፡፡ ሌላው ምክንያት በመስጴጦምያ በፐቶር ውስጥ ይኖር ለነበረው ለቢያር ልጅ ለበልዓም እናንተን እስራኤላዊያንን እንድረግም ገንዘብ ከፍለው ነበር፡፡ 5 6 ነገር ግን ያህዌ አምላካችን በለዓምን አልሰማውም፤ ይልቁንም፣ በልዓም አባቶቻችሁን እንዲባርክ አደረገው፣ ምክንያቱም ያህዌ አባቶቻችሁን ይወድ ነበር፡፡ 6እስራኤል አገር ሆኖ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ፣ እነዚህ ሁለት የህዝብ ወገኖች እንዲበለጽጉ የሚያደርግ አንዳች ነገር አታድርግ፡፡ 7 8 ነገር ግን ከኤዶም ወገን ማንንም አትናቅ፣ ምክንያቱም እነርሱ እንደ እናንተ የይስሃቅ ዘር ናቸው፡፡ ግብጻዊ የሆኑትን ሰዎችም አትናቅ፣ ምክንያቱም አባቶችህ በመጀመሪያ በግብጽ ሲኖሩ በሚገባ ተቀብለዋቸው ነበር፡፡ 8አሁን በመካከልህ የሚኖሩ ከኤዶምና ከግብጽ የመጡ የልጅ ልጆች የያህዌ ህዝብ ተደርገው ሊቆጠሩ ይችላሉ፡፡ 9 10 11 ወታደሮችህ በጦርነት ወቅት በአንድ ቦታ በሰፈሩ ጊዜ፣ እግዚአብሔር እንዳይቀበላቸው የሚያደርግ ደስ የማያሰኝ ስራ አይስሩ፡፡ 10አንድ ወታደር በሌሊት የዘር ፍሬውን በማፍሰሱ ምክንያት እግዚአብሔር የማይቀበለው ሆኖ ቢገኝ፣ በቀጣዩ ጠዋት ከሰፈር ይወጣና ቀኑን በዚያ ይቆይ፡፡ 11ነገር ግን በዚያን ዕለት ምሽት ላይ ሰውነቱን ይታጠብ፣ ፀሐይ ስትጠልቅ ወደ ሰፈር መመለስ ይፈቀድለታል፡፡ 12 13 14 12ወታደሮችህ ከሰፈር ውጭ የሚጠቀሙበት የመጸዳጃ ሥፍራ ይኑራቸው፡፡ 13ከጠላቶችህ ጋር ለመዋጋት ስትወጣ ከመሳሪያዎችህ ጋር በትርም አብረህ ያዝ ይህም መጸዳዳት ስትፈልግ በብትሩ ጉድጓድ ትቆፍራህ፣ ከተጸዳዳህ በኋላ ጉድጓዱን በበትሩ አፈር ታለብሰዋህ፡፡ 14ያረፍክበትን ሰፈር ለአምላካችን ለያህዌ ደስ የሚያሰኝ አድርገህ መጠበቅ አለብህ፣ ምክንያቱም እርሱ በሰፈርህ አንተን ሊጠብቅና ጠላቶችህን እንድታሸንፍ ሊያበቃህ ከአንተ ጋር ነው፡፡ ያህዌ እንዲተውህ የሚያደርግ አንዳች የሚያሳፍር ነገር አታድርግ፡፡ 15 16 15ከጌታቸው ያመለጡ ባሮች ወደ አንተ መጥተው እንድትጠብቃቸው ቢጠይቁህ፣ ወደ ጌታቸው አትመልሳቸው፡፡ 16በመረጡት ማናቸውም ከተማ፣ በአንተ መሃል እነዲቆዩ ፍቀድላቸው፣ ደግሞም አትበድላቸው፡፡ 17 18 ማንኛውም እስራኤላዊ ወንድ ወይም ሴት በመቅደስ አመንዝራ እንዲሆኑ አትፍቀድ፡፡ 18እንዲሁም፣ ማንም ሰው ከዝሙት ያገኘውን ገንዘብ ወደ ያህዌ ቤተ መቅደስ እንዲያመጣ አትፍቀድ፣ ያንን ገንዘብ ለእርሱ በመሃላ ለማምጣት ቃል ገብተው ቢሆን እንኳን አትቀበላቸው ያህዌ ዝሙት አዳሪነትን ይጠላል፡፡