1“ምናልባት አንድሰው ያህዌ አምላካችን በሰጠህ ምድር በሜዳ ላይ ወድቆ ቢገኝና ማን እንደ ገደለው ባታውቅ፣ 2የአገርህ ሽማግሌዎችና ዳኞች የዚያ ሰው በድን ወደተገኘበት ስፍራ ይሂዱ፡፡ ቀጥሎም ከዚያ ስፍራ እየተነሱ ወደ እያንዳንዱ በቅርብ ወዳሉ ከተሞች ድረስ ያለውን ርቀት ይለኩ፡፡