19

1ያህዌ አምላካችን ከሚሰጥህ ምድር በዚያ ይኖሩ የነበሩ ሰዎችን ካጠፉ በኋላ፣ አንተም እነርሱን ከከተሞቻቸው ካስወጣኋቸው በኋላ በቤቶቻቸው መኖር ስትጀምር፡ 2አምላክህ የሰጠህን ምድር በሶስት ክፍሎች ትከፍለዋለህ፡፡ ከዚያም በእያንዳንዱ ክፍል አንድ ከተማ ትመርጣለህ፡፡ ሰዎች ወደ እነዚያ ከተሞች በቀላሉ መግባት እንዲችሉ መልካም መንገዶችን ትሰራህ፡፡ 3ሰውን የገደለ ሰው ከእነዚያ ከተሞች ወደ አንዱ መሸሸ ይችላል፡፡