18
ከሌዊ ወገን የሆኑ ካህናት ሁሉ፣ በእስራኤል አንዳች ርሰት አይቀበሉም፡፡ በምትኩ በሌሎች ሰዎች መስዋዕት ሆኖ ለያህዌ ከሚቀርበው የሚቃጠል መስዋዕት እና ለያህዌ ከሚቀርቡ ሌሎች መስዋዕቶች እንዲበሉ ይቀበላሉ፡፡ 2ሌሎች ነገዶች እንደሚሰጣቸው እነርሱ አንዳች መሬት አያገኙም፡፡ እነርሱ የሚቀበሉት የያህዌ ካህናት የመሆንን ክብረ ነው፤ ይህም እነርሱ ሊኖራቸው ይገባል ብሎ እርሱ የተናገረው ነው፡፡