16

በየዓመቱ በጸደይ ወቅት መግቢያ በአቢብ ወር የፋሲካን በዓል በማድረግ ያህዌ አምላካችንን አክብር፡፡ ያህዌ አባቶችህን ከግብጽ ባርነት ነጻ ያወጣቸው በዚያ ወር በምሽት ነበር፡፡ 2ያን በዓል ለማክበር፣ ያህዌ እርሱን እንድታመልከው ወደሚመርጠው ስፍራ ሂድ፣ እናም በዚያ ከቀንድ ከብቶችህ አንድ ወይፈን፣ ወይም ከበግህ የፋሲካ መስዋእት አቅርብ፡፡