15
1በየሰባት አመት መጨረሻ፣ ብድርን ሁሉ ትሰርዛለህ፡፡ 2የዕዳ ስረዛውን የምታደርገው እንደዚህ ነው እያንዳንዳችሁ ለወንድሞቻችሁ ለእስራኤላዊያን የሰጣችሁትን ብድር መሰረዝ ይኖርባችኋል፡፡ እንዲከፍልህ አትነዝንዘው፡፡ ይህን ማድረግ የሚኖርብህ ምክንያት ያህዌ በየሰባት አመቱ ዕዳ እንዲተው ስለደነገገ ነው፡፡ በዚያ አመት በመካከልህ የሚኖረውን እንግዳ የአንተ የሆነውን ልትጠይቀው ትችላለህ፣ ነገር ግን እስራኤላዊ ወገንህ ዕዳውን እንዲከፍልህ አትጠይቀው፡፡