Other

ለምጽ፣ ለምጻም

መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን፣ “ለምጽ” የተለያዩ የቆዳ በሽታዎችን ያመለክት ነበር። አንድ ሰው ከእነዚህ የቆዳ በሽታዎች በአንዱ ከተያዘ ርኵስ ተብሎ ይቆጠር ነበር።

  • “ለምጻም” የሚባለው ለምጽ ያለበት ሰው ነው።
  • “ለምጻም” በለምጽ የተያዘ ሰው ወይም የአካል ክፍልን የሚገልጽ ቃል ነው።
  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ለምጻሞች ከሌሎች ሰዎች ተለይተው ከሰፈር ወይም ከከተማ ውጪ እንዲኖሩ ይደረግ ነበር።

ላም፣ ጥጃ፣ ወይፈን፣ ከብት

“ከብት” የሚለው ሳር የሚበሉ በዋነኛነት ደረጃ ለሚሰቱት ሥጋና ወተት ሰዎች የሚያረቧቸው ባለ አራት እግር የእርሻ እንስሳት ናቸው። እንዲህ ካሉት እንስሳት እንስቷ “ላም” ስትባል፣ ተባዕቱ፣ “ወይፈን” ከእነርሱ የሚወለደው፣ “ጥጃ” ይባላል።

  • በአንዳንድ አገሮች ባሕል መሠረት ሰዎች ከብቶችን በተለያዩ ዕቃዎች ይለዋወጣሉ። አንዳን ድጊዜ ወንዱ ማግባት ለፈለጋት ልጃገረድ ወላጆች በትሎሽ መልክ ከብት ይሰጣል።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የአይሁድ ሕዝብ ከብቶችን በተለይም፣ ቀይ ጊደር በመባል የምትታወቀውን መሥዋዕት ያቀርቡ ነበር።
  • “ጊደር” ገና ጥጃ ያልወለደች ላም ናት።
  • “በሬ” ሞፈር ቀንበር በመሸከም ለእርሻ ሥራ የሚያገለግል ከወይፈን ከፍ ያለ የቤት እንስሳ ነው።

ላከ፣ መላክ

“ላከ” አንድ ሰው ወይም አንድ ነገር ወደ ሌላ ቦታ እንዲሄድ ማድረግ ማለት ነው። አንድን ሰው፣ “መላክ” አንድን ነገር እንዲያደርግ ወይም አንድን ተልዕኮ እንዲፈጽም መናገር ወይም ማዘዝ ማለት ነው

  • ሰዎች የሚላኩበት ራሱን የቻለ ዓላማ ይኖራል። ብዙ ጊዜ የሚላከው ሰው የተላከበትን ጉዳይ የመፈጸምና የማስፈጸም ኅላፊነትም ይሰጠዋል
  • “ዝናብ ላከ” ወይም፣ “መዐት ላከ” የተሰኙት ሐረጎች፣ “እንዲመጡ ማድረግ” የሚል ትርጉም አላቸው። ይህ ዐይነቱ አነጋገር ጥቅም ላይ የሚውለው እግዚአብሔር እነዚህ ነገሮች እንዲሆኑ በሚያደርግበት ጊዜ ነው
  • “ቃል ላከ” ወይም፣ “መልእክት ላከ” በተሰኙት አነጋገሮች ውስጥ፣ “ላከ” ጥቅም ላይ በሚውልበት ጊዜ፣ ለሌሎች የምንናገረው ቃል ወይም መልእክት ሰጠን የሚል ትርጉም ይኖረዋል
  • ለአንድ ሰው አንድ ዓይነት እንስሳ ወይም አንድ ነገር መላክ፣ እነዚያን ነገሮች ለሰውየው መስጠት ማለት ነው፤ ብዙውን ጊዜ እነዚህን ነገሮች ለተቀባዩ ለማድረስ ጥቂት ጉዞ ማድረግ ያስፈልግ ይሆናል

ሌባ፣ ሌቦች፣ ወንበዴ

“ሌባ” ወይም፣ “ወንበዴ” ገንዘብ ወይም ንብረት ከሌሎች የሚሰርቅ ሰው ነው። በብዙ ቁጥር ሲሆን፣ “ሌቦች” ይሆናል።

  • አብዛኛውን ጊዜ ሌቦች አንድን ነገር ሳይታሰብ ለመውሰድ በማድባት ምቹ ጊዜ ይጠብቃሉ። ብዙውን ጊዜ የሚያደርጉት እንዳይታይ ጨለማን ተገን ያደርጋሉ።
  • አንዳንዴ “ወንበዴ” የሚለው ቃል ሌሎችን የሚጎዳ ሰው የሚል ትርጕም ይኖረዋል። ከኢየሱስ ጋር የተሰቀሉት ሰዎች “ወንበዴዎች” ወይም፣ “ወንጀለኞች” ተብለዋል።
  • ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ አዲስ ኪዳን ሰይጣንን ለመሰቅ፣ ለመግድልና ለማጥፋት የሚመጣ ሌባ ብሎታል። ይህም ማለት የሰይጣን ዕቅድ ሰዎች ለእግዚአብሔር መታዘዝ እንዲያቆሙ ማድረግና እግዚአብሔር ያዘጋጀላቸውን መልካም ነገር እንዳይቀበሉ ከእነርሱ መስረቅ ነው ማለት ነው።
  • ሌባ ስዎች ባልጠበቁት ጊዜ እንደሚመጣ፣ ኢየሱስም ሰዎች ባልጠበቁት ጊዜ ይመጣል። እርሱ የሚመጣው በድንገትና ሳይታሰብ ስለሆነ የእርሱን ተመልሶ መምጣት ዘወትር እንዲጠባበቁ ኢየሱስ ለተከታዮቹ ተናግሮአል።

ልሳን

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ልሳን” በርካታ ምሳሌያዊ ትርጕሞች አሉት።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በጣም የተለመደው የዚህ ቃል ምሳሌያዊ ትርጕም፣ “ቋንቋ” ወይም፣ “ንግግር” የተሰኘው ነው።
  • “ልሳን” የተለመደውን ሰዎች በዚህ ምድር የሚጠቀመቡበትን ቋንቋ ሊያመለክት ይችላል።
  • ይህ ቃል መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠው ልዕለ ተፈጥሮአዊ ቋንቋ ሊያመለክትም ይችላል።
  • “የእሳት ልሳን” የተሰኘው አገላለጽ የእሳት፣ “ነበልባል” ማለት ነው።
  • “ልሳኔ (አንደበቴ) ሐሤት አደረገ” ወይም፣ “ሐሰተኛ ልሳን፣ ምላስ” የተሰኙትን የመሳሰሉ ሌሎች ምሳሌያዊ አገላለሦች የሰውን ሁለንተና ወይም የሰውን ድምፅ ወይም ንግግር ያመለክታሉ።

ልዑል፣ ልዕልት

“ልዑል” የሚባለው የንጉሥ ልጅ ነው። ሌሎችን መሪዎች ለማመልከትም ጥቅም ላይ ይውላል። “ልዕልት” የንጉሥ ልጅ ናት።

  • “ልዑል” የሚለው ብዙውን ጊዜ ገዢን፣ መሪን፣ ወይም ሥልጣን ያለውን ሌላ ሰው የሚያመለክት አጠቃላይ ቃል ነው።
  • አብርሃም ከነበረው ሀብትና ታላቅነት የተነሣ በመካከላቸው እየኖረ በነበረ ጊዜ ኬጢያውያን፣ “ልዑል” በማለት ጠርተውታል።
  • ኢየሱስም፣ “የሰላም ልዑል/አለቃ” እና፣ “የሕይወት ልዑል/አለቃ” ተብሏል።
  • ሐዋርያት ሥራ 2፡36 ላይ ኢየሱስ፣ “ጌታና ክርስቶስ” ተብሏል፤ ሐዋርያት ሥራ 5፡31 ላይ ደግሞ፣ “ልዑልና አዳኝ” ተብሏል፤ ይህም፣ “ጌታ” እና፣ “ልዑል” የሚለውን ተጓዳኝ ያሳያል።
  • ትንቢተ ዳንኤል ውስጥ፣ ስለ “ፋርስ አለቃ” እና፣ ስለ፣ “ግሪክ አለቃ” በተሰጠው ገለጻ ጥቅም ላይ የዋለው፣ “ልዑል” የሚለው ቃል ሲሆን፣ በእነዚህ አካባቢዎች ሥልጣን ወይም ኀይል የነበራቸውን ክፉ መናፍስት የሚያመለክት ሊሆንም ይችላል።
  • ትንቢተ ዳንኤል ውስጥ፣ የመላእክት አለቃ ሚካኤል፣ “ልዑል” ተብሏል።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰይጣንም አልፎ አልፎ፣ “የዚህ ዓለም አለቃ/ልዑል” ተብሎአል።

ልዕልት

የአንድ አገር ሴት ገዢ ወይም የንጉሥ ልጅ ልትሆን ትችላለች። ማዳፈን “ማዳፈን” የሚለው ቃል አንድ ነገር ማጥፋት ወይም መርካት የሚፈልግን ነገር ማስቆም ማለት ነው።

  • ብዙውን ጊዜ ቃሉ ጥቅም ላይ የሚውለው ጥምን ካለ ማርካት ጋር ተያይዞ ነው።
  • እሳት ማጥፋትን ለማመልከትም ይውላል።

ሐሜት

ሐሜት ከሰዎች በስተጀርባ ሆነው እነርሱ በተመለከተ የሚናገሩት አፍራሽና አሉታዊ ቃል ነው። ብዙውን ጊዜ በእንዲህ ያለ መልኩ የተነገረው እውነት ሆኖ አይገኝም።

  • ሰዎች ላይ እውነት ያልሆነ ወሬ ማውራትና ማስወራት ትክክል እንዳይደለ አዲስ ኪዳን ይናገራል። ሐሜትና ስም ማጥፋት የዚህ ዓይነቱ አሉታዊ ንግግር ምሳሌ ናቸው።
  • እነርሱ ላይ የተወራው ወሬ የግላቸውና በምስጢር መያዝ የነበረበት በመሆኑ ሐሜት የተወራበትን ሰው ወይም ሰዎች ይጎዳል።

ሐምራዊ

“ሐምራዊ” የሰማያዊና የቀይ ቅልቅል የሆነ ቀለም ስም ነው። ልብስን በዚህ ቀለም ማቅለም በጣም ውድና ሰፊ ጊዜ የሚጠይቅ በመሆኑ ሐምራዊ ልብስ የሀብት፣ የከበሬታና የንጉሣዊነት ምልክት ተደርጎ ይወሰድ ነበር።

  • በጥንት ዘመን ሐምራዊ በጥቂቱ የሚገኝና በጣም ውድ ልብስን ማቅለሚያ ቀለም ስለ ነበር የነገሥታትንና የሌሎች ከፍተኛ ባለ ሥልጣኖችን ልብስ ለማቅለም ነበር ጥቅም ላይ የሚውለው።
  • ሐምራዊ ቀለም ከባሕር ቀንድ አውጣ ዐይነት ፍጡር ነበር የሚወጣው። ቀለሙን ለማውጣት ቀንድ አውጣውን መጨፍለቅ ወይም በሕይወት እያሉ እንዲለቁት በማድረግ ነበር። ይህ ደግም ጊዜና ጉልበት የሚጠይቅ ሂደት ነው።
  • እርሱ የአይሁድ ንጉሥ ነኝ በማለቱ ኢየሱስ ከመሰቀሉ በፊት የሮም ወታደሮች ኢየሱስ ላይ ለማፌዝ ሐምራዊ ልብስ አልብሰውት ነበር።
  • የፊልጵስዩስ ነዋሪ የሆነችው ሊድያ ሐምራዊ ጨርቅ በመሸጥ የምትኖር ሴት ነበረች።

ሐሤት

ሐሤት በደስታን በፍስሐ መሞላት፣ እጅግ በጣም ደስ መሰኘት ማለት ነው፥

  • ብዙውን ጊዜ ቃሉ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ባደረገው መልካም ነገር በጣም ደስ መሰኘትን ነው።
  • “በጣም ደስ መሰኘት” ወይም፣ “በደስታ መሞላት” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

ሐሰተኛ ነብይ

ሐሰተኛ ነብይ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከእግዚአብሔር ያልተቀበለውን መልእክት ከእግዚአብሔር እንደተቀበለ የሚናገር ሰው ነው።

  • የሐሰተኛ ነብያት ትንቢት አይፈጸምም።
  • ሐሰተኛ ነብያት በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ ከሚለው ጋር የሚቃረን መልእክት ያስተምራሉ።
  • ይህ ቃል፣ “በሐሰት በእግዚአብሔር ስም የሚናገር ሰው” ወይም፣ “የሐሰተኛ አምላክ ነብይ” በማለት መተርጎም ይቻላል።

ሕልም

ሕልም ሰዎች ተኝተው እያለ የሚያዩት ወይም አእምሮአቸው ውስጥ የሚለማመዱት ነገር ነው።

  • ብዙ ጊዜ ሕልሞች በእውን ያሉ ይመስላሉ ግን አይደለም።
  • አንዳንዴ እግዚአብሔር ሰዎችን በሕልም ያስተምራል። አስፈላጊ ከሆነም በቀጥታ በሕልም ይናገራል።
  • ከመጸሐፍ ቅዱስ እንደምንመለከተው እግዚአብሔር ወደ ፊት የሚሆነውን የሚያመለክት ሕልም ለሰዎች ይሰጣል።
  • ሕልም ከራእይ የተለየ ነው። ሕልም ሰዎች ተኝተው እያለ የሚያዩት ሲሆን፣ ብዙ ጊዜ ግን ራእይ የሚያዩት ነቅተው እያለ ነው።

ሕዝብ

ሕዝብ የሚባለው በአንድ ዐይነት መንግሥታዊ አስተዳደር የሚመራ የሰዎች ስብስብ ነው። ብዙውን ጊዜ በዘር፣ በነገድ፣ በቋንቋና በሌሎችም ባሕርዮች የሚመሳሰሉ ሰዎችን ያካትታል።

  • “ሕዝብ” የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ ግልጽ የሆነ ባሕልና ክልልንም ያካትታል።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ እስራኤላውያንን፣ ፍልስጥኤማውያንን፣ አሦራውያንን፣ ባቢሎናውያንን፣ ሮማውያንንና ግሪኮችን ጨምሮ ብዙ ሕዝቦች ተጠቅሰዋል።
  • ሕዝብ አገርንም ሊያመለክት ይችላል፤ ግን ሁሌ አይደለም። አንዳንዴ ይበልጥ አጠቃላይ ሲሆን፣ በተለይ ደግሞ በብዙ ቁጥር ጥቅም ላይ ሲውል የሚያመለክተው የሰዎችን ስብስብ ነው። በማንኛውም ጊዜ ዐውዱ የቀረበትንሁኔታ ማጣራቱ አስፈላጊ ነው።

ሕጋዊ

ሕጋዊ የሆነ ነገር አሳሪ ከሆነው ደንብ ወይም ሕግ መሠረት የተደረገ ወይም ከእርሱ ጋር የሚስማማ ማለት ነው።

  • መጽሐፍ ውስጥ አንድ ነገር፣ “ሕጋዊ” ነው ከተባለ በእግዚአብሔር ገብረ ገባዊ ሕግ ወይም በሙሴ ሕግና ሌሎች የአይሁድ ሕጎች ተፈቅዷል ማለት ነው።
  • “ሕጋዊ” የሚለውን ለመረርጎም ሌሎች አማራጮች፣ “የተፈቀደ” ወይም፣ “እንደ የእግዚአብሔር ሕግ” ወይም፣ “ከሕጋችን ጋር የሚስማማ” ሊባል ይችላል።

ሕግ፣ ሥርዐት (መርሕ)

ሕግ ሆን ተብሎ በጽሑፍ የሰፈረና ሥልጣን ባለው አምላክ የሚያስፈጽመው መደበኛ መመሪያ ነው። ሥርዐት (መርሕ) ውሳኔዎችን ለማድረግ መመሪያ ወይም መመዘኛ ነው።

  • የአንድ ሰው ምግባር የሚመራ ደንብ ወይም እምነት ለማመልከት “ሕግ” እና፣ “መርሕ” የተሰኙት ቃሎች ጥቅም ላይ መዋል ይችላሉ።
  • ይህ የሕግ፣ “ትርጕም” ከሙሴ ሕግ የተለየ ነው።
  • አጠቃላዩን ሕግ ለማመልከት ታስቦ ከሆነ፣ “ሕግ” የሚለው ቃል፣ “መርሕ” ወይም፣ “መደበኛ መመሪያ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

ሕግ፣ አፍራሽ፣ ዐመፃ

“ዐመፃ” ለማንኛውም ሕግ ወይም ደንብ አለመታዘዝ ማለት ነው። ሕግ አፍራሽነት፣ “ዐመፃ” ሊባል ይችላል።

  • ሕግ አፍራሽ ዐመፀኛና ለእግዚአብሔር ሕግ የማይታዘዝ ነው።
  • በመጨረሻው ዘመን ክፉ ነገር ለማድረግ ሰይጣን ስለሚጠቀምበት፣ “የዐመፅ ሰው” ወይም፣ “ዐመፀኛው” ስለ ተባለ ሰው ጳውሎስ ይናገራል።

መለመን፣ ልመና

“መለመን” አንድ ነገር እንዲደረግ ወይም እንዲሰጥ አጥብቆ መጠየቅ ማለት ነው። “ልመና” የሚለው የሚያመለክተው የመለመንን ተግባር ነው።

  • ብዙውን ጊዜ ልመናያ ሰው ከባድ ችግር ውስጥ መሆኑን ወይም እግዚአብሔር አንድን ሰው እንዲረዳ አጥብቆ መፈለግን ያመለክታል።
  • ምሕረት እንዲደረግላቸው ወይም ጉዳያቸው ፍርድ እንዲያገኝላቸው ሰዎች ንጉሥን ወይም ገዢን ይለምናሉ።
  • ይህን ቃል ለመተርጎም፣ “መጠየቅ” ወይም. “መወትወት” የተሰኙ ቃሎችም ያገለግላሉ።
  • “መለመን” የሚለውን ቃል፣ “አስቸኳይ ጥያቄ” ወይም፣ “አጥብቆ ማሳሰብ” ማለትም ይቻላል።

መለመን፥ ለማኝ

“መለመን” አንድን ነገር አጥብቆ መጠየቅ ማለት ነው። ብዙውን ጊዜ ገንዘብ ወይም እንጀራ መጠየቅን ይመለከታል።

  • “ለማኝ” ከሰዎች ገንዘብ ወይም እንጀራ ለመጠየቅ መንገድ ዳር የሚቀመጥ ወይም የሚቆም ወይም ከቦታ ቦታ የሚዘዋወር ሰው ነው
  • ብዙውን ጊዜ ሰዎች አጥብቀው አንድን ነገር ሲፈልጉ፥ ይለምናሉ፤ የለመኑት ነገር እንደሚሰጣቸው ግን አያውቁም። ይህ፥ “መወትወት” ወይም፥ “አጥብቆ መጠየቅ” ተብሎ መተርጎም ይችላል
  • የሚናገርው ገንዘብ ወይም እንጀራ መጠየቅን አስመልክቶ ከሆን፥ “ገንዘብ መጠየቅ” ወይም፥ “እንጀራ መጠየቅ” ወይም፥ “ዘወትር አንድን ነገር መጠየቅ” ተብሎ መተርጎምም ይቻላል።

መለከት

“መለከት” ሙዚቃ ለመጫወት ወይም ዐዋጅ ለማሰማት ወይም ሕዝብን ለስብሰባ ለመጥራት ጥቅም ላይ የሚውል መሣሪያ ነው።

  • ብዙውን ጊዜ መለከት የሚሠራው ከብረት፣ ከባሕር እንስሳ ቅርፊት ወይም ከከብት ቀንድ ነበር።
  • ሰዎች ለጦርነት እንዲሰበሰቡና በእስራኤል ሕዝባዊ ስብሰባ ጊዜ መለከት መነፋቱ የተለመደ ነበር።
  • በመጨረሻው ዘመን የእግዚአብሔር ቁጣ ምድር ላይ እንደሚወርድ ለማስታወቅ መላእክት መለከት እንደሚነፉ የዮሐንስ ራእይ ይናገራል።

መለየት፣ የመለየት ችሎታ

“መለየት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው አንድን ነገር መረዳትን በተለይም ያ ነገር ትክክል ወይም ስሕተት መሆኑን በሚገባ መረዳትን ነው።

  • የመለየት ችሎታ አንድን ነገር ወይም ሁኔታ አስመልክቶ መረዳትና አስተዋይ ውሳኔ ላይ መድረስን ያመለክታል።
  • ጥበብና መልካም ዳኝነት ሲኖር ማለት ነው።

መልበስ፣ ለበሰ

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ከዋ፣ “ለበሰ” አንድ ነገር፣ “ተቀዳጀ” ወይም አንድ ነገር ታጠቀ ወይም በአንዳች ሁኔታ ዝግጁ ሆነ ማለት ነው። አንድ ነገር፣ “መልበስ” አንድ ዐይነት ፀባይ ወይም ባሕርይ አዳበረ ማለት ነው።

  • የምትለብሱት ልብስ ውጫዊ አካላችሁን እንደሚሰፍንና ለሰው ሁሉ እንደሚታይ፣ አንድ ዓይነት ባሕርይ፣ “ስትለብሱም” ሌሎች ሰዎች በቀላሉ ያዩታል። “ትሕትናን መልበስ” ሰው ሁሉ በቀላሉ እንዲያየው ተግባራችሁና አናኗራችሁ ሁሉ ትሕትናን የሚያንጸባርቅ ይሆናል።
  • “ከላይ ኃይል መልበስ” ሲባል ከላይ የሚመጣ ኃይል መቀበል ማለት ነው።
  • ቃሉ፣ “እፍረት መከናነብ” ወይም፣ “ውርደት ልበሱ” የተሰኙትን የመሳሰሉ አሉታዊ ነገሮችን ለማመልከትም ይጠቅማል።

መልእክተኛ

መልእክተኛ የሚባለው ለሌሎች የሚናገረው ወይም የሚያደርሰው ነገር የተሰጠው ሰው ነው።

  • በጥንት ዘመን በጦርነት ቦታ እየተደረገ ያለውን በከተማ ላሉ ሰዎች ለመንገር ከጦርነቱ ቦታ መልእክተኛ ይላክ ነበር።
  • መልአክ ለሰዎች መልእክት እንዲያደርስ እግዚአብሔር የሚልከው ልዩ ዐይነት መልእክተኛ ነው። አንዳንድ ትርጕሞች፣ “መልአክ” የሚለውን፣ “መልእክተኛ” ብለውታል።
  • ነቢይ የእግዚአብሔርን ትምህርት፣ ማስጠንቀቂያና ሌሎችንም ነገሮች ለሰዎች የሚሰጥ ወይም የሚያደርስ ሰው ነው።
  • መጥምቁ ዮሐንስ የመሲሑን መምጣትና እርሱን እንዲቀበሉ ሰዎችን ለማዘጋጀት ከኢየሱ አስቀድሞ የሚመጣ መልእክተኛ ተብሏል።
  • የኢየሱስ ሐዋርያት ወደ ሰዎች በመሄድ የእግዚአብሔር መንግሥትን ለሰዎች የሚያካፍሉ መልእክተኞቹ ናቸው።

መሐላ

በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት አንዳች ነገር ለማድረግ የሚሰጥ ውል ያለው ተስፋ ቃል ነው። መሐላ የሚያደርግ ሰው የሰጠውን ተስፋ የመፈጸም ግዴታ አለበት።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “መሐላ” ቃል መግባት ማለት ነው።
  • “በ . . . መማል” ከተባለ መሐላው የሚደረግበት መሠረት ወይም ሥልጣን እንዲሆን የአንድን ሰው ስም በመጥራት በይፋ መናገር ማለት ነው።
  • አንዳንዴ ቃሉ፣ “መሐላ መማል” በሚል መልኩ ይቀርባል።
  • የጉድጓድ ውሃ አጠቃቀምን በተመለከተ ኪዳን ለማድረግ አብርሃምና አቢሜሌክ ተማምለው ነበር።
  • ከአብርሃም ዘሮች መካከል ለልጁ ለይስሐቅ ሚስት እንዲፈልግለት አብርሃም አገልጋዩን ቃል አስገብቶት ወይም አስምሎት ነበር።
  • ለሕዝቡ የገባውን ተስፋ ለመፈጸም እግዚአብሔር ራሱ ምሎ ነበር።
  • በዚህ ዘመን፣ “መሐላ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የሚውልበት ሁኔታ እንዲሁ ከንቱ ቃል መናገር ሲሆን፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትርጕም ጋር አይስማማም።

መመለስ

“መመለስ” ወደ ኋላ መመለስ፣ ወይም አንድን ነገር መልሶ መስጠት ማለት ነው።

  • ወደ አንድ ነገር መመለስ፣ እንደ ገና ያንን ነገር ማድረግ መጀመር ማለት ነው።
  • እስራኤላውያን ወደ ጣዖት አምልኮአቸው ሲመለሱ፣ እንደ ገና እነርሱ ማምለክ ጀምረዋል ማለት ነው።
  • ወደ እግዚአብሔር ተመልሰዋል ከተባለ ንስሐ ገብተዋል፤ እንደ ገና ያህዌን ማምለክ መጀመራቸውን ያመለክታል።
  • ከአንድ ሰው የወሰድነውን ወይም የተቀበለውን ርስት ወይም ንብረት የምንመልስ ከሆነ ያንን ርስትና ንብረት ለመጀመሪያው ባለቤቱ መልሰን እንሰጣለን ማለት ነው።
  • “መመለስ” የሚለውን፣ “ወደ ኋላ መሄድ” ወይም፣ “መልሶ መስጠት” ወይም፣ “ያንኑ ማድረግ መጀመር” በማለት መተርጎም ይቻላል።

መመለስ፣ ተመለሰ፣ ወደ ኋላ አለ

  • “መመለስ” ወይም፣ “ወደ ኋላ” ማለት አቅጣጫን መለወጥ ወይም ሌላው አቅጣጫ እንዲለውጥ ማድረግ ነው።
  • “ተመለሰ” እያደገ የነበረውን ተወ ወይም ችላ አለ ማለት ነው።
  • “ወደ ኋላ ማለት” – “ጭልጥ ብሎ መሄድ” ወይም ሌላው እንዲሄድ ማድረግ ማለት ነው።
  • “ወደ . . . መመለስ/መዞር” አንድን ሰው ፊት ለፊት ማየት ማለት ነው።
  • “ተመልሶ መሄድ” ወይም፣ “ጀርባ አዙሮ መሄድ” – “ሮቆ መሄድ” ማለት ነው።
  • “ወደ ኋላ መመለስ” – “አንድን ነገር እንደ ገና ማድረግ” ማለት ነው።
  • ከ . . . መመለስ” - ማለት፣ “ያንን ነገር ማድረግ ማቆም” ማለት ነው።

መመላለስ

መመላለስ የሚለው ቃል ብዙ ጊዜ በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ከዋለ፣ “መኖር” ማለት ነው።

  • “ሄኖክ” አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ” ማለት ሄኖክ በጣም ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ ኖረ ማለት ነው።
  • “በመንፈስ መመላለስ” እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና እርሱን የሚያከብር ነገር ለማድረግ በመንፈስ ቅዱስ መመራት ማለት ነው።
  • በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወይም በእግዚአብሔር፣ መንገድ “መመላለስ” ትእዛዞቹን በመፈጸምና ፈቃዱን በማድረግ መኖር ማለት ነው።
  • እግዚአብሔር በሕዝቡ መካከል፣ “እመላለሳለሁ” ሲል በመካከላቸው እኖራለሁ፤ ከእነርሱ ጋር ግንኙነት ይኖረኛል ማለቱ ነው።
  • “በተቃራኒ መመላለስ” ከአንድ ሰው ወይም ነገር በሚጻረር መልኩ መኖር ማለት ነው።
  • “ከ . . . ኋላ መመላለስ” አንድን ነገር አጥብቆ መፈለግ ማለት ነው። ሌላው የሚያደርገውን ማድረግ ማለትም ይሆናል።

መመሪያ

መመሪያ በተወሰነ ማኅበረሰብ ውስጥ ያሉ ሰዎች የሚያከብሩት ሕዝባዊ ደንብ ወይም ትእዛዝና መመሪያ የሚሰጥ ሕግ ነው።

  • አንዳንዴ ለዘመናት ጥቅም ላይ በመዋሉ ተቀባይነት ያገኘ ባሕልም መመሪያ ይሆናል።
  • በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት መመሪያ እስራኤላውያን እንዲያደርጉት እግዚአብሔር ያዘዘው ነገር ነው። አንዳንድ ነገሮችን ለዘለቄታው እንዲያደርጉ አዟቸዋል።
  • “መመሪያ” የሚለው ቃል፣ “ሕዝባዊ ዐዋጅ” ወይም፣ “ደንብ” ወይም፣ “ሕግ” በማለት መተርጎም ይቻላል።

መመደብ፥ ተመደበ

“መመደብ” ወይም፥ “መደበ” የሚለው ቃል የተወሰነ ተግባርን እንዲፈጽም አንድን ሰው መሾምን ያመለክታል

  • ንጉሥ ሳኦል ከእስራኤል ወታቶች ጎበዝ የሆኑትን በወታደርነት እንዲያገለግሉ እንደሚመድባቸው ነቢዩ ሳሚኤል አመልክቶ ነበር።
  • ሙሴ እያንዳንዱ የእስራኤል አሥራ ሁለት ነገድ ከነዓን ውስጥ የሚኖርበትን ምደ ድርሻ መድቦለት ነበር
  • በብሉይ ኪዳን ሕግ መሠረት አንዳንድ የእስራኤል ነገዶች በካህንነት፥ በእጅ ባልሙያነት፥ በመዘምራንነትና በግንበኝነት ይመደቡ ነበር።
  • በዐውዱ መሠረት፥ “መመደብ” የሚለው ቃል፥ “መስጠት” ወይም “መሾም” ወይም “ለተወሰነ ዐይነት ተግባር መምረጥ” ብሎ መተርጎም ይቻላል
  • “ተመደበ” የሚለው “ተሾመ” ወይም፥ “አንድ ሥራ ተሰጠው” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል

መምራት፣ መመሪያ

“መምራት” እና፣ “መመሪያ” የተሰኙ ቃሎች የሚያመለክቱት አንድን ነገር እንዴት ማድረግ እንደሚቻል ወይም መታዘዝ የሚገባ ሕግን አስመልክቶ ግልጽ የሆነ አቅጣጫ መመልከት ማለት ነው።

  • ለሕዝቡ እንዲያድሉ ኢየሱስ እንጀራውንና ዓሣውን ለደቀመዛሙርቱ በሰጠ ጊዜ ያንን እንዴት ማድረግ እንዳለባቸውም ግልጽ መመሪያ ሰጥቷቸው ነበር።
  • “መራ” የሚለው ቃል፣ “ተናገረ” ወይም፣ “መመሪያ ሰጠ” ተብሎ መተርጎም ይቻላል።
  • “መመሪያ” – “አቅጣጫ” ወይም፣ “ገለጻ” ተብሎ መተርጎም ይችላል።
  • ከያህዌ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ጥቅም ላይ ከዋለ፣ “መመሪያ” ትእዛዝ ወይም ደንብ የሚል ትርጉም ይኖረዋል።

መምሰል፣ አምሳል

እርስ በርስ የሚመሳሰሉ ሰዎች ወይም ነገሮች እርስ በርስ የሚጋሩዋቸው ነገሮች ይኖሯቸዋል።

  • አንድን ነገር፣ “መምሰል” ከዚያ ነገር ጋር አንድ መሆን፣ የጋራ የሆኑ ባሕርያትን መካፈል ማለት ነው።
  • ሰዎች በእግዚአብሔር “አምሳል” ተፈጥረዋል፣ ያም ማለት በእርሱ መልክ ተፈጥረዋል። የእርሱ ዐይነት ባሕርያት አላቸው ማለት ነው፥

መምሰል፣ አምሳል

እርስ በርስ የሚመሳሰሉ ሰዎች ወይም ነገሮች እርስ በርስ የሚጋሩዋቸው ነገሮች ይኖሯቸዋል።

  • አንድን ነገር፣ “መምሰል” ከዚያ ነገር ጋር አንድ መሆን፣ የጋራ የሆኑ ባሕርያትን መካፈል ማለት ነው።
  • ሰዎች በእግዚአብሔር “አምሳል” ተፈጥረዋል፣ ያም ማለት በእርሱ መልክ ተፈጥረዋል። የእርሱ ዐይነት ባሕርያት አላቸው ማለት ነው፥

መምከር

“መምከር” ጠንከር አድርጎ ማስጠንቀቅ ወይም ምክር መስጠት ማለት ነው።

  • ብዙውን ግዜ ፣ “መምከር” አንድን ሰው አንድ ነገር እንዲያደርግ ምክር መስጠት ማለት ነው።
  • በክርስቶስ አካል ውስጥ አማኞች ኅጢአትን እንዲያርቁና የተቀደሰ ሕይወት እንዲኖሩ እርስ በርስ መመካከር እንዳለባቸው ይማራሉ።
  • “መምከር” የሚለው ቃል “ኅጢያት እንዳያደርጉ ማበረታታት” ወይም “ኅጢያት እንዳያደርጉ ማስጠንቀቅ” ተብሎ መተርጎም ይቻላል።

መሠረት፣ መሠረተ

“መሠረተ” የሚለው ግሥ አንድ ነገር ላይ ሠራ ወይም ገነባ ማለት ነው። መሠረት አንድ ሕንፃ የሚያርፍበት ከታች ያለው አካል ነው።

  • ሕንፃውን በሙሉ መሸከም እንዲችል የአንድ ቤት ወይም ግንባታ መሠረት በጣም ጠንካራ መሆን አለበት።
  • “መሠረት” የሚለው ቃል የአንድ ነገር ጅማሬን ወይም አንድ ነገር የተፈጠረበትን ጊዜም ያመለክታል።
  • በምሳሌያዊ አነጋገር በክርስቶስ የሚያምኑ ክርስቶስ ራሱ የማእዘን ራስ ከሆነበት፣ በነቢያትና በሐዋርያት ትምህርት ላይ ከተመሠረተ ሕንፃ ጋር ተመሳስለዋል።
  • “የመሠረተ ድንጋይ” የመሠረቱ አካል የሆነ ድንጋይ ነው። መላውን ሕንፃ መሸከም የሚችሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ድንጋዮቹ፣ “የፈተናሉ” ወይም፣ “በተለያየ መከራ ያልፋሉ።”

መሣሪያ

  • “መሣሪያ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው አንድ ወታደር በጦርነት የሚዋጋበትንና ከጠላት ጥቃት ራሱን የሚከለክልበትን ትጥቅ ነው። መንፈሳዊ መሣሪያን ለማመልከትም በምሳሌያዊ መንገድ ጥቅም ላይ ይውላል።
  • ከወታደሩ መሣሪያዎች ጥቂቶቹ የራስ ቁር፥ ጋሻ፥ ጥሩር፥ ጉልበት መሸፈኛና ሰይፍ ናቸው።
  • በምሳሌያዊ መንገድ ሲጠቀምበት ቁሳዊ መሣሪያን በመንፈሳዊ ውጊያ እንዲረዳው እግዚአብሔር ለአማኝ ከሰጠው መንፈሳዊ መሣሪያ ጋር ያነጻጽረዋል
  • ኅጢአትንና ሰይጣንን እንዲዋጉበት እግዚአብሔር ለሕዝቡ ከሰጣቸው መንፈሳዊ መሣሪያ አንዳንዶቹ እውነት፥ ጽድቅ፥ የሰላም ወንጌል፥ እምነት፥ ድነትና መንፈስ ቅዱስ ናቸው
  • ይህም፥ “የወታደሩ ማጥቂያ” ወይም “መከላከያ የጦር ልብስ” ወይም “መከለያ ሽፋን” ወይም እንዲሁ “ መሣሪያዎች” ተብሎ መተርጎም ይቻላል።

መሥዋዕት፣ ቁርባን

“ቁርባን” (ስጦታ) የሚለው ለእግዚአብሔር ወይም ለጣዖት የተሰጠ ማንኛውንም ነገር የሚያመለክት አጠቃላይ ቃል ነው። መሥዋዕት በብዙ መልኩ ይመሳሰላል፤ ሆኖም በተለምዶ ከተገደሉ በኋላ ለእግዚአብሔር ወይም ለጣዖት የሚሰጡ ነገሮችን ያመለክታል

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምንመለከታቸው ቁርባኖችና መሥዋዕቶች እግዚአብሔርን ለማምለክ የተሰጡ ነበሩ
  • የተለያዩ ብዙ ዐይነት መሥዋዕትና ቁርባኖች እንዲያቀርቡ እግዚአብሔር ከስእራኤላውያን ይጠብቅ ነበር። ይህም እግዚአብሔር ኅጢአትን ይቅር እንዲል የሚቀርብ ቁርባንን፣ ስለ በረከቱ እግዚአብሔርን ለማመስገን የሚቀርብ ቁርባንን ይጨምራል። ከእነዚህ ቁርባኖች ጥቂቶቹ፣ “የሚቃጠል መሥዋዕት” – “የኅጢአት መሥዋዕት” – “የእህል መሥዋዕት” እና፣ “የመጠጥ መሥዋዕት” ናቸው
  • የመሥዋዕቶቹ ስም መሠረት የሚሆነው መሥዋዕት የሚሆነውን ነገርና መሥዋዕቱ የሚቀርብበት ዓላማ ነው
  • የሰዎችን ኅጢአት ፈጽሞ የሚያነጻ እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ያዘጋጀው መሥዋዕት ብቻ ነው። የእንስሳት ደም መሥዋዕት ያንን ማድረግ አይችልም

መርዳት፣ የተረዳ

“መረዳት” መረጃ መስማት ወይም መቀበልና ምን ማለት እንደሆነ መገንዘብ ማለት ነው።

  • “መረዳት” የሚለው ቃል፣ “ዕውቀትን” ወይም፣ “ጥበብን” ወይም አንድን ነገር እንዴት ማድረግ እንደሚቻል መገንዘብን ያመለክታል። የአንድን ሰው ስሜት ማወቅንም ይጨምራል።
  • በኤማሁስ መንገድ እየሄዱ በነበረ ጊዜ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ መሲሑን በተመለከተ የተነገሩ ቅዱሳት መጻሕፍትን ትርጕም እንዲረዱ አደረገ።
  • እንደ ዐውዱ አገባብ፣ “መረዳት” የሚለው፣ “ማወቅ” ወይም፣ “ማመን” ወይም፣ “መገንዘብ” ወይም፣ “ምን ማለት እንደሆነ ማወቅ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
  • ብዙ ጊዜ፣ “መረዳት” – “ዕውቀት” ወይም፣ “ጥበብ” ተብሎ ይተረጎማል።

መሰናከል

ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “መሰናከል” እየተራመዱ ወይም እየሮጡ እያል የመውደቅ ያህል መንገዳገድ ማለት ነው። ብዙውን ጊዜ በአንድ ነገር መደናቀፍን ያመለክታል

  • በምሳሌያዊ መልኩ፣ “መሰናከል” ኅጢአት ማድረግ ወይም ከእምነት መናወጥ፣ ወይም በኅጢአት ምክንያት የእምነት መዳከም ማለት ነው
  • “መሰናከል” በስደት የተጎዱትን ለማመልከት አንዳንዴ በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል

መሰናከያ፣ መሰናከያ ዐለት

“መሰናከያ” ወይም፣ “መሰናከያ ድንጋይ” አንድ ሰው ተደናቅፎ እንዲወድቅ የሚያደርግ ነገርን ያመለክታል

  • አዲስ ኪዳን ውስጥ ይህ ቃል ተሰናክሎ ውስጡ የወደቀ እንስሳ ላይ እንዲዘጋ ወጥመድን ወይም አሽክላን የሚያስፈነጥር ልምጭ ወይም ሌላ ነገር ያመለክታል
  • ምሳሌያዊ መሰናከያ አንድ ሰው በግብረ ገባዊ ወይም በመንፈሳዊ መልኩ እንዲወድቅ የሚያደርግ ማንኛውም ነገር ማለት ነው
  • በመሳሌያዊ መልኩ፣ “መሰናከያ” ወይም፣ “መሰናከያ ድንጋይ” አንድ ሰው በኢየሱስ እንዳያምን ወይም በመንፈሳዊ ሕይወቱ እንዳያድግ የሚያግድ ነገርን ያመለክታል
  • አብዝኛውን ጊዜ እንደመናከያ የሚሆነው አንድ ሰው ራሱ ወይም ሌላው የሚያደርገው ኅጢአት ነው
  • አንዳንዴ እግዚአብሔር ራሱ በእርሱ በሚያምፁ ሰዎች መንገድ ላይ መሰናከያ ያደርጋል

መሳም

አንድ ሰው ከንፈሮቹን አጥብቆ ሌላው ሰው ጉንጮች ወይም ከንፈሮች ላይ በማድረግ ፍቅሩን የሚገልጥበት ሁኔታ ነው፥

  • የአንዳንድ ባሕል ሰዎች ሰላምታ ሲሰጣጡ ወይም ሲሰነባበቱ እርስ በርስ ጉንጮቻቸውን ይሳሳማሉ።
  • መሳሳም ባልና ሚስትን በመሳሰሉ ሁለት ሰዎች መካከል ያለው ጥልቅ ፍቅር መገለጫ ነው።

መሳት፥ ሳተ፥ ወደ ስህተት ተመራ

“መሳት” እና “ሳተ” በእግዚአብሔር ፈቃድ ላይ መመፅ ማለት ነው። “ወደ ስህተት መመራት” ሌሎች ሰዎች ወይም ሁኔታዎች ለእግዚአብሔር ወዳለመታዘዝ እንዲመራቸው መፍቀድ ማለት ነው

  • “መሳት” የሚለው ቃል ግልጽ የሆነውን መንገድ፥ ወይም ሰላም ያለበትን ቦታ ትቶ በተሳሳተና አደገኛ በሆነ መንገድ የመሄድን ስዕል ይሰጣል
  • የእረኛቸውን ግጦሽ መስክ የሚተው በጎች፥ “ስተዋል(ኮብልለዋል)” እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን እርሱን ትተው ከኮበለሉ በጎች ጋር ያመሳስላቸዋል።

መስቀል

አንድን ነገር መስቀል ያንን ነገር ከመሬት በላይ ማንጠልጠል ማለት ነው።

  • በስቅላት የሚፈጸም ቅጣት ብዙውን ጊዜ ሰውዬው አንገት ላይ ገመድ በማጥለቅ መስቀያ ወይም የዛፍ ቅርንጫፍ ላይ ማንጠልጠል ነው። ይሁዳ ራሱን ያጠፋው በዚያ መልኩ ነበር።
  • የኢየሱስ መስቀል ላይ መሰቀል የተፈጸመው በሌላ መንገድ ነበር፤ ወታደሮቹ እጅና እግሮቹን በሚስማር ከቸነከሩ በኋላ ነበር ይተቸነከረበትን መስቀል ያቆሙት።

መስበክ

ስለ እርሱ ለማስተማርና ለእርሱ እንዲታዘዙ ለማሳሰብ ለተወሰኑ ሰዎች መናገር ማለት ነው።

  • ብዙውን ጊዜ ስብከት የሚደረገው አንድ ሰው ብዛት ላላቸው ሰዎች ነው።
  • “መስበክ” እና፣ “ማስተማር” ተመሳሳይ ቢሆኑም፣ አንድ አይደለም። ስብከት በዋናነት መንፈሳዊና ግብረ ገባዊ ነገሮችን በሕዝብ ፊት ማወጅንና ሰዎች ምላሽ እንዲሰጡ ማሳሰብን ያመለክታል። “ማስተማር” ለመመሪያ አጽንዖት መስጠት ማለትም እየተማረ ላለው ሰው ዕውቀት ወይም ሙያ ማካፈል ማለት ነው።
  • መጥምቁ ዮሐንስ፣ ኢየሱስና ሐዋርያቱ ንስሐ እንዲያደርጉና ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንዲገቡ ብዙ ጊዜ ለሰዎች ሰብከው ነበር።

መስከር፣ ሰካራም

መስከር የአልኮል መጠጥ አብዝቶ በመጠጣት አእምሮን መሳት ወይም ከተለመደው የተለየ ፀባይ ማሳየት ማለት ነው።

  • ሰካራም የሚባለው ብዙ ጊዜ የሚሰክር ሰው ነው። እንዲህ ያለው ሰው፣ “እልኮሊክ” ተብሎም ይጠራል።
  • አማኞች መንፈስ ቅዱስ እንዲገዛቸው እንጂ፣ መስከር እንደሌለባቸው መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
  • መጽሐፍ ቅዱስ መስከር ሞኝነት መሆኑንና ወደ ሌሎች ኃጢአቶችም እንደሚመራ ይናገራል።
  • መስከር የሚለውን ለመተርጎም ሌሎች መንገዶች፣ “መጠት ማብዛት” ወይም፣ “ከልክ በላይ መጠጣት” የተሰኙት ሊሆኑ ይችላሉ።

መስጠት (መፈጸም)፣ የተሰጠ (ፈጸመ)፣ ስጦታ

በዚህ አግባብ መሠረት፥ “መስጠት” ሲባል አንድን ነገር ለማድረግ መወሰን ወይም ቃል መግባት ማለት ነው።

  • አንድን ነገር ለማድረግ ቃል የገባ ሰው፣ ከዚያ አንጻር፣ “የተሰጠ” ሰው ይባላል።
  • ለአንድ ሰው አንዳች ዐይነት ተግባር፣ “መስጠት” ያንን ሰው ለዚያ ተግባር መወሰን ማለት ነው። ለምሳሌ ያህል በ2ቆሮንቶስ መልእክቱ ጳውሎስ፣ እግዚአብሔር ሰዎች ከእርሱ ጋር እንዲታረቁ የማድረግን አገልግሎት እግዚአብሔር፣ “ሰጥቶናል” ይላል።
  • “መፈጸም” እና፣ “ፈጸም” የተሰኙት ቃሎች ብዙውን ጊዜ ኃጢአትን፣ ዝሙትን፣ ወይም፣ መግደልን የመሳሰሉ መጥፎ ነገሮችን ማድረግን ያመለክታሉ።
  • “ተግባር ተሰጠው” የሚለው፣ “ያ ሥራ ለእርሱ ተሰጠ” ወይም ሥራው በአደራ ተሰጠውፋ ወይም በኃላፊነት ተሰጠው ተብሎ መተርጎምም ይችላል።
  • “መስጠት” የተሰኘው ቃል፣ “የተሰጠ ተግባር” ወይም፣ “ቃል መስጠት” ተብሎ መተርጎም ይችላል።

መሸከም

ቃል በቃል ከተወሰደ፣ “መሸከም” አንድን ነገር ራስ ላይ መጫን ማለት ነው። ይህ ቃል በርካታ ምሳሌያዊ ጠቀሜታዎችም አሉት።

  • በማኅፀንዋ ልጅ የተሸከመች ሴት ያረገዘች ሴት ማለት ነው።
  • “ሸክም መሸከም” አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ማለፍ ማለት ነው። ይህ አስቸጋሪ ሁኔታ አካላዊ ወይም ስሜታዊ መከራ ሊሆን ይችላል።
  • “ልጅ የአባቱን ኀጢአት ይሸከማል” ማለት፣ “አባቱ ለፈጸመው ኀጢአት ኀላፊነት አለበት” ወይም፣ “በአባቱ ኀጢአት ይቀጣል” ማለት ነው።

መሸፈኛ

“መሸፈኛ” ብዙውን ጊዜ የሚያመለክተው ራስን ለመሸፈን የሚያገለግለውን በጣም ስስ ልብስ ሲሆን፣ ራስና ፊት እንዳይታይ ይከልላል።

  • ያህዌ ፊት ከነበረ በኋላ እስራኤል የፊቱን ብርሃን እንዳያዩ ለመጋረድ ሙሴ ፊቱን በመሸፈኛ ሸፍኖ ነበር።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሴቶች ሕዝብ ባለበት ወይም ወንዶች ባሉበት ቦታ ሲሆኑ ራሳቸውንና ፊታቸውን ይሸፍኑ ነበር።
  • “ሸፈነ” የሚለው ግሥ አንድን ነገር እንዳይታይ አደረገ ማለት ነው።
  • አንዳንድ ትርጕሞች ቅድስተ ቅዱሳን መግቢያ ላይ ያለውን ግዙፍ መጋረጃ፣ “መሸፈኛ” ብለውታል። ይሁን እንጂ፣ እዚህ ላይ የሚያመለክተው በጣም ከባድ፣ ወፍራምና ግዙፍ ጨርቅ በመሆኑ፣ “መጋረጃ” የሚለው ቃል የበለጠ ትክክል ነው።

መሾም (ዕውቅና መስጠት)

መሾም ሲባል ወግ ባለው ሁኔታ ለተለየ ተግባር ወይም ድርሻ አንድን ሰው መለየት ማለት ነው። በዐዋጅ ደረጃ ሕግን ወይም ደንብን ማሳወቅ ማለትም ይሆናል።

  • “መሾም” የሚለው ቃል ካህን፣ አገልጋይ ወይም የሃይማኖት መምህር እንዲሆን ወግ ባለው መልኩ አንድን ሰው መርጦ ለዚሁ ተግባር መለየት ማለት ነው።
  • ካህናት እንዲሆኑ እግዚአብሔር አሮንና ልጆቹን ሾሟቸው ነበር።
  • ሃይማኖታዊ በዓልን ወይም ኪዳን መመሥርት ማለትም ይሆናል።
  • “መሾም” እንደ አውዱ ሁኔታ፣ “መለየት” ወይም፣ “ማዘዝ” ወይም፣ “ደንብ ማውጣት” ወይም፣ “መመሥረት” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

መቀበል

“መቀበል”የሚለው ቃል ለአንድ ሰው ወይም ሁኔታ ተገቢ ዕውቅና ወይም ይሁንታ ሲሰጠው ማለት ነው።

  • እግዚአብሔርን መቀበል እርሱ የተናገረው እውነት መሆኑን በሚያሳይ መልኩ መንቀሳቀስን ይጨምራል።
  • የእግዚአብሔርን አምላክነት የሚቀበሉ ሰዎች ለስሙ ክብር በሚያመጣ መልኩ ለእርሱ በመታዘዝ ያንን ያሳያሉ።
  • አንድን ነገር መቀበል ያንኑ ከሚያረጋግጥ ቃልና ተግባር ጋር እውነት መሆኑን መቀበል ማለት ነው።

መቀበል

“መቀበል” የተሰጠ ወይም የቀረበ ነገርን ተቀብሎ የራስ ማድረግ ማለት ነው።

  • “መቀበል” የበደልን ወይም የኀጢአትን ቅጣት መውሰድ ማለትም ይሆናል።
  • ሰውን፣ “መቀበል” የሚቻልበት ሁኔታም አለ። ለምሳሌ፣ እንግዶችን ወይም ጎብኚዎችን “መቀበል” በመልካም ሁኔታ እነርሱን ማስተናገድና በተቻለ መጠን ምቾታቸውን መጠበቅ ማለት ነው።
  • “የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ መቀበል”፣ መንፈስ ቅዱስን ወደ ሕይወታችን ማስገባትና በእኛና በእኛ በኩል እንዲሠራ መፍቀድ ማለት ነው።
  • “ኢየሱስን መቀበል” በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የእግዚአብሔርን ድንቅ ስጦታ መቀበል ማለት ነው።

መቀደስ፣ ቅድስና

መቀደስ ለአንድ ራሱን ለቻለ ዓላማ ወይም ተግባር አንድን ነገር መለየት ወይም መስጠት ማለት ነው።

  • ዳዊት ወርቁንና ብሩን ለጌት ቀደሰ።
  • ብዙውን ጊዜ፣ “ቅድስና” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ለተለየ ዓላማ አንድ ነገር የመለየት ደንብን ወይም ሥርዓትን ነው።
  • መሠዊያን የመቀደስ ሥርዓት ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ማቅረብንም ይመለከታል።
  • ያህዌን ብቻ እንዲያመልኩና የእርሱን ከተማ እንዲጠብቁ በአዲስ መልኩ ቃል በማስገባት እንደ ገና የተገነቡትን የኢየሩሳሌም ቅጥሮች በመቀደሱ ሂደት ነህምያ እስራኤላውያንን መራቸው። ይህም በሙዚቃ መሣሪያዎችና በዝማሬ የታጀበ ምስጋና ለእግዚአብሔር ማቅረብንም አካትቶ ነበር።
  • “መቀደስ” የሚለው ቃል “ለአንድ ዓላማ መለየት” ወይም፣ “አንድ የተለየ ተግባር ለመፈጸም መሰጠት” ተብሎ መተርጎም ይችላል።

መቀጣት፤ቁጣ

‘’መቀጣት’’ ወይም ‘’ቁጣ’’አንድ ነገር ወይም ሰወ ላይ ደስ አለመሰኘት፤መበሳጫትና መናደድ ማለት ነው፤

  • የሰዎች ቁጣ ብዙዉን ጊዜ ሃጢአትና ራስ ሚ ያለበት ቢሆንም አንዳንድ ግን የፍትህ መጉደልን ወይም ጭቆና ላይ በጽድቅ መቆጣት ሊሆን ይችላል።
  • የእግዚአብሔር ቁጣም እንዲሁ ሃጢአትን አስመልክቶ በጣም መከፋቱን ያመለክታል።
  • ለቁጣ ማነሣሣት የተሰኘው ሐረግ “ማስቆጣት ማለት ነው።

መቁረጥ

“መቁረጥ” የሚለው ቃል ማግለልን፣ ማስወገድን ወይም ከዋው ወገን መነጠልን ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውል የነበረ ፈሊጣዊ ቃል ነው። ከኀጢአት የተነሣ በመልኮታዊ ፍርድ መገደልን ሊያመለክትም ይችላል።

  • በብሉይ ኪዳን ዘመን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ማፍረስ ከእግዚአብሔር ሕዝብና ከእርሱ ፊት መቆረጥን ወይም መለየትን ያስከትል ነበር።
  • እርሱን ባለማምለካቸውና ለእርሱ ባለ መታዘዛቸው እንዲሁም የእስራኤል ጠላት ከመሆናቸው የተነሣ እስራኤል ያልሆኑ ሰዎችን እንደሚቆርጥ እግዚአብሔር ተናግሮአል።
  • መቁረጥ የሚለው ቃል እግዚአብሔር የወንግዙ ውሃ እንዳይወርድ ያደረገበትን ሁኔታ ለማመልከትም ጥቅም ላይ ውሏል።

መቃብር፣ የቀብር ቦታ

“መቃብር” እና፣ “የቀብር ቦታ” ሰዎች የሞተውን ሰው አካል የሚያኖሩበት ስፍራ ነው።

  • አይሁድ አንዳንዴ ዋሻዎችን እንደ መቃብር ይጠቀማሉ፣ አንዳንዴ በኮረብታ አንድ ወገን ያለውን ዐለት በመፈልፈል ዋሻ ይሠራሉ።
  • አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን መቃብሩን ለመዝጋት መቃብሩ በራፍ ላይ ትልቅና ከባድ ድንጋይ ማንከባለል የተለመደ ነበር።
  • መቃብር ወይም የቀብር ቦታ አካል መሬት ውስጥ የሚቀመጥበትን ቦታ ብቻ የሚያመለክት ከሆነ ይህን ለመተርጎም፣ “ዋሻ” ወይም፣ “ኮረብታ ላይ ያለ ጉድጓድ” ማለት ይቻላል።
  • “መቃብር” የሚለው ቃል በአጠቃላይና ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ እንደ ሞት ያለ ሁኔታ ውስጥ መሆንን ወይም የሞቱ ሰዎች ነፍሶች ያሉበትን ቦታ ያመለክታል።

መቃተት

“መቃተት” የሚለው ቃል ከአካላዊ ወይም ስሜታዊ ሕመም የተነሣ ከጥልቅ የሚወጣ አጭር ድምፅ ነው። ብዙውን ጊዜ መቃተት የሚገለጠው ያለ ምንም ቃል ነው።

  • አንድ ሰው ሐዘን ሲሰማው ሊቃትት ይችላል።
  • በከባድና አስጨናቂ ሸክም ምክንያት መቃተት ሊፈጠር ይችላል።
  • ይህን ቃል ለመተርጎም ሌሎች መንገዶች፣ “አጭር የስቃይ ድምፅ ማሰማት” ወይም፣ “ከጥልቅ የሚወጣ ሐዘን” የተሰኙት ሊሆኑ ይችላሉ።

መቃን

አንድን በር ደግፎ የሚይዝ በሩ ግናራ ቀኝ ላይ ያለ ቀጥ ያለ ጣውላ ነው።

  • እስራኤላውያን ከግብፅ ከመውጣቸው ጥቂት ቀደም ሲል አንድ በግ እንዲያርዱና የበራቸውን መቃን ደም እንዲቀቡ እግዚአብሔር ነግሮአቸው ነበር።
  • በብሉይ ኪዳን ዘመን የተቀረውን የሕይወት ዘመኑን ጌታውን ማገልገል የፈለገ ባርያ ጆሮውን የጌታው ቤት መቃኖች ላይ ያደርግና በወስፌ ወይም በሚስማር ይበሳ ነበር።
  • ይህ ቃል፣ “በሩ ግራና ቀኝ ላይ ያለ ጣውላ” ተብሎ መረትጎም ይችላል።

መቅለጥ

“መቅለጥ” የሚለው ቃል ሙቀት ሲነካው የአንድ ነገር ፈሳሽ መሆንን ያመለክታል። ምሳሌያዊ በሆነ መልካም ጥቅም ላይ ይውላል።

  • የጦር መሣሪያዎችን፣ ጌጣጌጦችንና ጣዖቶችን ለመሥራት ቅርጽ ወደሚያስይዛቸው ነገር እንዲፈስስ የተለያዩ የብረት ዐይነቶች እስኪቀልጡ ድረስ እሳት ላይ መሆን አለባቸው።
  • ሻማ ሲነድ ሰሙ ይቀልጥና ይንጠባጠባል። በጥንት ዘመን ብዙውን ጊዜ ደብዳቤዎች ጥቂት የቀለጠ ሰም ጫፋቸው ላይ በማፍሰስ ይታሸጉ ነበር።
  • ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ፣ “መቅለጥ” ልክ እንደ ቀለጠ ሻማ ለስላሳና ደካማ መሆን ማለት ነው።
  • “ልባቸው ቀለጠ” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ብዙውን ጊዜ ከፍርሃት የተነሣ በጣም ደካሞች ሆኑ ማለት ነው።
  • “እነርሱ ይቀልጣሉ” የሚለው ምሳሌያዊ አነጋገር ሌላው ትርጕም እንዲሸሹ፣ መገደድ ወይም ደካማነታቸው በመገለቱ በሽንፈት መሸሽ ማለት ነው።
  • “መቅለጥ” ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “ፈሳሽ መሆን” ወይም፣ “መፍሰስ” ወይም፣ “ፈሳሽ እንዲሆን ማድረግ” ተብሎ ይተረጎማል።
  • “መቅለጥ” የሚለውን ቃል ምስሌያዊ ሐሳብ፣ “መለስለስ” ወይም፣ “ደካማ መሆን” ወይም፣ “መሸነፍ” በማለት መተርጎም ይቻላል።

መቅሠፍት

መቅሠፍት የሚባለው ብዙ ሕዝብ ላይ ጉዳት ወይም ሞት የሚያስከትል በሽታ ወይም ሌላ ሁኔታ ነው።

  • ብዙ መቅሠፍቶች ተፈጥሮአዊ ምክንያት ሲኖራቸው አንዳንዶቹ ግን በኀጢአታቸው ምክንያት ሕዝብን ለመቅጣት ከእግዚአብሔር የተላኩ ናቸው።
  • እስራኤል ከግብፅ እንዲወጡ ፈርዖንን ለማስገደድ በሙሴ ዘመን እግዚአብሔር አሥር መቅሠፍቶች ግብፃውያን ላይ አምጥቶ ነበር።

መቅበር፣ ቀበረ፣ ቀብር፣ መቀበሪያ

“መቅበር” የሞተ ሰውን አካል ጉድጓድ ውስጥ ወይም ሌላ መቀበፊያ ቦታ ውስጥ ማኖርን ያመለክታል። “ቀብር” የሚለው ቃል አንድ ነገር የመቅበር ሥራ ሲሆን፣ አንድን ነገር ለመቅበር የሚያገለግል ቦታንም ያመለክታል።

  • ብዙውን ጊዜ ሰዎች የሞተ አካልን መሬት ውስጥ በማኖርና በኋላም በአፈር በመሸፈን ይቀብራሉ።
  • አንዳንዴ የሞተው አካል ከመቀበሩ በፊት የሬሳ ሳጥን ወይም ያንን የመሰሉ ነገር ውስጥ ያኖሩታል።
  • አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን ብዙውን ጊዜ የሞቱ ሰዎች ዋሻ ወይም ተመሳሳይ ቦታ ውስጥ ይቀመጡ ነበር። ኢየሱ ከሞቱ በኋላ አካሉ በጨርቅ ተጠቅልሎ ከድንጋይ በተፈለፈለ መቃብር ውስጥ ከተደረገ በኋላ መቃብሩ በትልቅ ድንጋይ ተዘጋ።
  • “የቀብር ቦታ” ወይም፣ “የቀብር ክፍል” ወይም፣ “የቀብር ዋሻ” ቃሎች በሙሉ የሞቱ አካል የሚቀመጥባቸው ቦታዎችን ያመለክታሉ።
  • ሌሎች ነገሮችም ይቀበራሉ፤ ለምሳሌ አካን ከኢያሪኮ ያለ አግባብ የወሰደውን ብርና ሌላም ነገር ቀብሮ ነበር።
  • “ፊቱን ቀበረ” የሚለው ሐረግ ብዙውን ጊዜ የሚያመለክተው፣ “ፊትን በእጆች መሸፈንን” ነው።
  • አንዳንዴ “መደበቅ” የሚለው ቃል አካን በኢያሪኮ የወሰደውን ነገር ሲደብቅ እንደ ሆነው፣ “መቅበር” ማለትም ይሆናል። ይህም ማለት የወሰደውን መሬት ውስጥ ቀበረው ማለት ነው።

መቅጣት፣ ቅጣት

“ቅጣት” ከፈጸመው ጥፋት የተነሣ አንድ ሰው ላይ አሉታዊ ውጤቶች ማድረስ ማለት ነው።

  • እስራኤል ባለ መታዘዛቸው ይልቁንም ሐሰተኛ አማልክት በማምለካቸው እግዚአብሔር ቀጥቷቸዋል።
  • ብዙውን ጊዜ እግዚአብሔር እስራኤልን ሲቀጣ እንደ ታየው የቅጣት ዓላማ ኀጢአት ማድረግን ማስቆም ነው።
  • ሰዎች ለፈጸሙት ኀጢአት ሁሉ ኢየሱስ ተቀጣ። ምንም እንኳ የሚያስቀጣ በደል ባይኖረትም ኢየሱስ የእያንዳንዱን ሰው ቅጣት በራሱ ተቀበለ።
  • “ያልተቀጣ” ወይም፣ “ያልተቆነጠጠ” የተሰኙት ፈሊጣዊ ንግግሮች በፈጸምው ጥፋት አንድን ሰው ሳይቀጡ መተውን ያመለክታል።

መበልጸግ/መከናወን፣ ብልጽግና፣ የበለጸገ

“መበልጸግ” አንድ ሰው ወይም ሕዝብ በሕይወታቸው ሲከናወኑ ወይም የተሳካላቸው ሲሆኑ ማለት ነው። ይህ መከናወን ቁሳዊ ወይም መንፈሳዊ ሊሆን ይችላል። “ብልጽግና” ሀብታምና ደኅና የመሆን ሁኔታ ነው።

  • ሰዎች በሕወትና በጤንነት ወይም በሀብት የተሳካላቸው ሲሆኑ በለጸገ ይባላል።
  • ብዙውን ጊዜ “ብልጽግና” የሚለው ቃል ገንዘብና ንብረትን በተመለከተ የተሳካላቸው መሆኑን ያመለክታል።
  • በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት፣ “የበለጸገ” የሚለው ቃል በመልካም ጤንነትና በልጆች መባረክንም ይጨምራል።
  • “የበለጸገ” ከተማ ወይም አገር ብዙ ሕዝብ፣ የተትረፈረፈ ምግብና፣ ብዙ ገንዘብ የሚያስገኝ ንግድና ሌሎች ተግባሮች የተሳካለት ማለት ነው።
  • አንድ ሰው ለእግዚአብሔር ትምህርቶች ሲታዘዝ በመንፈሳዊ ሕይወት እንደሚበለጽግ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። በደስታና ሰላምም ይባረካል። እግዚአብሔር ለሰዎች ሁሌም የተትረፈረፈ ቁሳዊ ሀብት ላይሰጣቸው ይችላል፤ ይሁን እንጂ፣ የእርሱን መንገድ ከተከተሉ ሁሌም በመንፈሳዊ ሕይወት ይባርካቸዋል።
  • እንደ ዐውዱ ሁኔታ፣ “መበልጸግ” የሚለው ቃል፣ “መንፈሳዊ ስኬት” ወይም፣ “በእግዚአብሔር መባረክ” ወይም፣ “መልካም ነገሮችን መለማመድ” ወይም፣ “መሳካት” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

መበቀል፥ በቀል፥ ብቀላ

“መበቀል” ወይም፥ “በቀል” እርሱ ላደርሰው ጉዳት ለመክፈል ሲባል አንድን ሰው መቅጣት ማለት ነው። የመበቀያ ወይም በቀል የተፈጸመበት ተግባር “ብቀላ” ይባላል

  • ብዙውን ጊዜ፥ “መበቀል” የሚለው ቃል ለተፈጸመው በደል ፍትሕ ሲደረግ ወይም የተበላሸው ሲስተካከል የማየት ፍላጎትን ያመለክታል
  • እግዚአብሔር መበቀል ካለበት ያንን የሚያደርገው ኃጢአትና ዐመፅን ለመቅጣት በመሆኑ ሥራው ጽድቅን መሠረት ያደረገ ነው የሚሆነው።

መበታተን፣ የተበተነ

መበታተን የሰዎችን ወይም የነገሮችን በተለያዩ አቅጣጫ መበታተን ያመለክታል።

  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ እርስ በርስ ተራርቀው በተለያየ ቦታ እንዲኖሩ ለማድረግ እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደሚበትን ይናገራል። እንዲህ የሚያደርገው በኀጢአታቸው እነርሱን ለመቅጣት ነው። ተራርቀውና ተለያይተው መኖራቸው በንስሐ እንዲመለሱና እንደ ገና እግዚአብሔርን ማምለክ እንዲጀምሩ ሊያደርጋቸው ይችላል።
  • አዲስ ኪዳን ውስጥ መበታተን የሚለው ቃል የሚያመለክተው ስደትን ለማምለጥ ቤታቸውን ትተው ወደ ተለያዩ ቦታዎች የሄዱ ክርስቲያኖችን ነው።
  • የተበተኑ የሚለውን፣ “በተለያዩ ቦታ ያሉ አማኞች” ወይም፣ “ወደ ተለያዩ አገሮች የሄዱ ሰዎች” ብሎ መተርጎም ይቻላል።

መብላት፣ መዋጥ፣ ጨርሶ ማቃጠል

ይህ ቃል የሚያመለክተው በአደገኛ ሁኔታ መብላትን ወይም ጨርሶ ማቃጠልን ነው።

  • ጳውሎስ ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ በዚህ ቃል በመጠቀም እርስ በርስ መጠፋፋት እንደሌለባቸው ማለትም በቃልም ሆነ በተግባር አንዳቸው ሌላውን ማጥቃት ወይም ማጥፋት እንደሌለባቸው አማኞችን አሰጠንቅቆ ነበር (ገላትያ 5፡15)።
  • መዋጥ የሚለው ቃል ምሳሌያዊ በሆን መልኩ ጥቅም ላይ ከዋለ አገሮች እርስ በርስ እንደሚጠፋፉት ወይም እሳት ቤቶችንና ሰዎች እንደሚያቃጥለው፣ “ጨርሶ ማጥፋት” ማለት ነው።
  • ይህ ቃል፣ “ሙሉ በሙሉ ማጥፋት” ወይም፣ “ጨርሶ መደምሰስ” ተብሎ መተርጎም ይችላል።

መብራት

መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ሰዎች ይጠቀሙበት የነበረው መብራት በሚነድበት ጊዜ ብርሃን የሚሰጥ ብዙውን ጊዜ እንደ ኀይል ሰጪ የሚያገለግል ዘይት የያዘ ዕቃ ነበር።

  • የዘይት መብራቶች ብዙውን ጊዜ ከሸክላ የሚሠሩ ዕቃዎች ነበር።
  • ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ መብራት የብርሃንና የሕይወት ምሳሌ ነው።

መብራት መያዣ

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “መብራት መያዣ” ክፍሉ ውስጥ ሁሉ እንዲያበራ መብራቱ የሚቀመጥበት ከእንጨት ወይም ከብረት የተሠራ ዕቃ ነው።

  • ለቤተ መቅደሱ የሚሠራው ልዩ መብራት መያዣ ሰባት መብራቶች የሚይዙበት ቦታ ነበሩት።
  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን መብራት ብዙውን ጊዜ የወይራ ዘይት ወይም ስብ የያዘ ከሸክላ የተሠራ ዕቃ ሲሆን ሲቀጣጠል ብርሃን የሚሰጥ ክር ወይም ፈትል ውስጡ ይደረግ ነበር።

መብዛት

“መብዛት” የሚለው በከፍተኛ ደረጃ በቁጥርና በመጠን ማደግን ያመለክታል።

  • “እንዲበዙ” እና ምድርን እንዲሞሉ እግዚአብሔር ለሰው ልጆችና ለእንስሳት ተናግሮአል። ይህ በዐይነት እነርሱን የመሰሉትን እንዲወልዱየተሰጠ ትእዛዝ ነው።
  • 5000 ሰዎችን መመገብ እንዲችል ኢየሱስ እንጀራዎቹና ዓሣዎቹ እንዲበዙ አደረገ። ሰው ሁሉ በልቶ እስኪጠግብ ድረስ የምግቡ መጠን መጨመሩን ቀጠለ።
  • ይህ ቃል፣ “በጣም መጨመር” ወይም፣ “በቁጥር ማደግ” ወይም፣ “ከቁጥር በላይ መሆን” ተብሎ መተርጎምም ይችላል።

መተርጎም፣ ትርጉም

“መተርጎም” እና፣ “ትርጉም” የተሰኙት ግልጽ ያልሆነ ነገርን መርዳትና ያንን ግልጽ ማድረግን ያመለክታል።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እነዚህ ቃሎች ብዙውን ጊዜ ጥቅም ላይ የዋሉት የሕልምን ፍቺ ግልጽ ከማድረግ ጋር በተያያዘ ነው።
  • የባቢሎን ንጉሠአንዳንድ ግራ የሚያጋቡ ሕልሞች ባለመ ጊዜ ምን ማለት እንደሆኑ እንዲተረጉምና ግልጽ እንዲያደርግ እግዚአብሔር ዳንኤልን ረዳው።
  • የሕልሙ “ትርጉም”፣ የሕልሙን መልእክት ግልጽ ማድረግ ነው። አንዳንዴ እነዚህ ትርጉሞች በጽሑፍ ይሰፍራሉ።
  • ከብሉይ ኪዳን እንደምንመለከተው ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር ወደፊት የሚሆኑ ነገሮችን ለሰዎች በሕልም ይገልጽ ነበር፤ ስለሆነም የእነዚህ ሕልሞች ትርጉም ትንቢት ነበር ማለት ነው።
  • “መተርጎም” የሚለው ቃል በተፈጥሮአዊው ዓለም እየሆን ያለውን መሠረት በማድረግ የአየሩ ሁኔታ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመትን የመሰለ የአንዳንድ ነገሮችን ምንነት መገመትን ለምግለጽም ጥቅም ላይ ይውላል።

መተኛት፥ ተኛ፣ አንቀላፋ

እነዚህ ቃሎች ከሞት ጋር የሚያያዝ ምሳሌያዊ ትርጉም አላቸው

  • “አንቀላፋ”- “ሞተ” የሚለው ተለዋጭ ዘይቤ ነው
  • “ከአባቶቹ ጋር አንቀለፋ” አባቶቹ እንደ ሞቱ እርሱም ሞተ ማለት ነው

መታሰቢያ፣ የመታሰቢያ ቁርባን

መታሰቢያ የሚለው ቃል አንድ ሰው ወይም አንድ ሁኔታ እንዲታሰብ የሚያደርግ ተግባር ወይም ነገር ማለት ነው።

  • “የመታሰቢያ ቁርባንን” ወይም፣ “መታሰቢያ ክፍል” ወይም፣ “የመታሰቢያ ድንጋይ” ከሚሉት ማየት እንደሚቻለው ይህ ቃል አንዳች ነገርን እንዲያስታውሱ የሚያደርጉ ነገሮችን የሚያመለክት ቅጽል በመሆንም ጥቅም ላይ ይውላል።
  • በብሉይ ኪዳን፣ “የመታሰቢያ ቁርባን” ይቀርብ የነበረው እግዚአብሔር ያደረገላቸውን እስራኤላውያን እንዲያስታውሱ ነበር።
  • ካህናት የአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች የተቀረጸባቸው የመታሰቢያ ድንጋዮች ያሉበት ልዩ ልብስ እንዲለብሱ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ተናግሮአል። ምናልባትም እግዚአብሔር ምን ያህል ለእነርሱ ታማኝ መሆኑን እንዲያስታውሱ ለማድረግ ይሆናል።
  • ለድኾች ያደርግ ከነበረው ችሮታ የተነሣ ቆርኔሌዎስ የተባለውን ሰው እግዚአብሔር እንዳከበረ ከአዲስ ኪዳን እናነባለን። ይህ መልካም ሥራው በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ ሆነ።

መታወቅ፣ የታወቀ

“የታወቀ” የሚለው ቃል ሰፊ ተቀባይነት ማግኘትፍንና ስመ ጥሩ የሆነ ሰውን ያመለክታል።

  • “የታወቀ” የሚለው ለረጅም ጊዜ ሰፊ ታዋቂነት ያተረፈ ዝነኛ ሰውን ያመለክታል።
  • “የታወቀ” የሚባል ሰው ብዙ ሰዎ የሚያውቀውና ከፍ ያለ ግምት የሚሰጠው ነው።
  • “የታወቀች” የምትባል ከተማ ብዙ ጊዜ በሀብትና በብልጥግናዋ ትታወቃለች።

መታዘዝ፣ ታዛዥ፣ ታዛዥነት

“መታዘዝ” ሥልጣን ያለው ሰው የሚፈልገውን ወይም እንዲደረግ የሚያዝዘውን መፈጸም ማለት ነው። “ታዛዥ” የተነገረውን ወይም የታዘዘውን የሚፈጽም ሰው ነው።

  • ሰዎች የአገር መሪዎች መንግሥት ወይም ድርጅት ለሚያወጧቸው ሕጎችም ይታዘዛሉ።
  • ልጆች ለወላጆቻቸው ይታዘዛሉ፣ ባርያዎች ለጌቶቻቸው ይታዘዛሉ፤ ሰዎች ለእግዚአብሔር ይታዘዛሉ፤ ዜጎች ለአገራቸው ሕጎችና ደንቦች ይታዘዛሉ።
  • ሕጉ ወይም ሥልጣን ያለው ሰው አንድ ነገር እንዳይደረግ ካዘዙ፣ ሰዎች ያንን ላለማድረግ መታዘዝ አልባቸው።
  • ይህን ቃል ለመተርጎም የሚጠቅሙ ቃሎች ወይም ሐረጎች፣ “የታዘዘውን ማድረግ” ወይም፣ “ትእዛዙን መከተል” ወይም፣ “እግዚአብሔር የተናገረውን ማድረግ” የተሰኙትንም ያካትታል።

መታደግ፣ ታዳጊ (የሚታደግ)

አንድን ሰው መታደግ እርሱን ማዳን ማለት ነው። ታዳጊ ከባርነት፣ ከጭቆና ወይም ከሌላ አደጋ ሰዎችን የሚታደግ ወይም ነጻ የሚያወጣ ነው።

  • በብሉይ ኪዳን ዘመን እነርሱን ለማጥቃት በመጡ ሌሎች ላይ እንዲዘምቱ በማድረግ እስራኤልን የሚጠብቁና የሚመሩ ታዳጊዎች እግዚአብሔር አስነሥቶ ነበር።
  • እነዚህ ታዳጊዎች፣ “መሳፍንት” ተብለውም ይጠሩ ነበር፤ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ያለው መጽሐፈ መስፍንት እነዚህ መሳፍንቶች እስራኤልን የመሩት መቼ እንደ ነበር በዝርዝር አስፍሮአል።
  • እግዚአብሔርም፣ “ታዳጊ” ተብሎአል። ከእስራኤል ታሪክ በሙሉ እንደምንመለከተው እርሱን ሕዝቡን ከጠላቶቻቸው ታድጎአቸው ወይም አድኖአቸው ነበር።

መታገሥ፣ ትዕግሥት (ጽናት)

መታገሥ ረጅም ጊዜ መቆየት ወይም አስቸጋሪ ነገርን መቋቋም ማለት ነው።

  • የፈተና ጊዜ ሲመጣ ተስፋ ሳይቆርጡ ጸንቶ መቆም ማለትም ነው።
  • “መታገሥ - “መቻል” – “በመከራና ስደት ውስጥ መጽናት” ማለት ነው።
  • “እስከ መጨረሻ ጽኑ” በማለት ለክርስቲያኖች የተሰጠው ማበረታቻ ምንም እንኳ ያንን ማድረጋቸው ከባድ መከራ ሊያመጣባቸው ቢችልም ለኢየሱስ መታዘዝ እንደሚገባቸው ያሳስባቸዋል።
  • “መከራን መታገሥ” ሲባል፣ “መከራን መለማመድ” ማለትም ነው።

መታጠቂያ

“መታጠቂያ” የሚለው ቃል አንዳች ነገር ዙሪያ የሚታሰር ነገርን ነው። ብዙ ጊዜ የሚያመለክተው ቀሚስ ወይም እጀ ጠባብ ወደ መሬት እንዳይወርድ ወገብ ላይ ለማሰር የሚያገለግል ቀበቶ ወይም ሻሽን ነው።

  • “ወገባችሁን ታጠቁ” የሚለው የተለመደ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አነጋገር እግሮቻችሁ በፍጥነት መራመድ እንዲችሉ የልብሳችሁን ጫፍ ቀበቶአችሁ ውስጥ ሸጉጡት ማለት ነው።
  • “መታጠቅ” በአንድ ነገር ዙሪያ መሄድ ማለትም ይሆልናል።
  • ወገባችሁን ታጠቁ” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ትርጕሙ በሚሠራበት ቋንቋ ተመሳሳይ ትርጕም በሚሰጥ ፈሊጣዊ አነጋገር ሊተረጎም ይችላል። ወይም ደግም ምሳሌያዊ ባልሆነ አነጋገር፣ “ራሳችሁን ለተግባር አዘጋጁ” ወይም፣ “ተዘጋጁ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

መነሣት፣ ተነሣ

በአጠቃላይ፣ “መነሣት” – “ብድግ ማለት” ወይም፣ “ወደ ላይ መውጣት” ማለት ነው።

  • ምሳሌያዊ በሆነ አነጋገር፣ “ተነሥ” ማለት አንድ ነገር ወደ መገኘት እንዲመጣ ወይም እንዲታይ ማድረግ ማለት ነው። አንዳች ነገር እንዲያደርግ ሰውን መሾም ማለትም ይሆናል።
  • አንዳንዴ፣ “ተነሥ” ማለት፣ “መመለስ” ወይም “እንደ ገና መሠራት” ማለትም ይሆናል።
  • “ከሞት ተነሣ” የሚለው ሐረግ ውስጥ ያለው፣ “ተነሣ” ልዩ ትርጕም አለው፤ የሞተው ሰው እንደ ገና ወደ ሕይወት ሲመጣ ማለት ነው፥
  • አንዳንዴ፣ “መነሣት” - አንድን ሰው ወይም ነገር ወደ ላይ ከፍ ማድረግን ያመለክታል።
  • መነሣት፣ ተነሣ፣ “ወደ ላይ መሄድ” ማለትም ይሆናል።
  • አንድ ሰው ወደ አንድ ቦታ ለመሄድ ከተነሣ፣ “ተንሥቶ ሄደ” ወይም፣ “ብድግ ብሎ ሄደ” ማለት ነው።
  • አንድ ነገር፣ “ተነሣ” ከተባለ፣ “ሆነ” ወይም፣ “መሆን ጀመረ” ማለት ነው።
  • ኢየሱስ ከሞት እንደሚነሣ አስቀድሞ ተናግሮ ነበር፤ ኢየሱስ ከሞተ ሦስት ቀን በኋላ መልአኩ፣ “ተነሥቶአል!” አለ።

መነፋት

“መነፋት” የሚለው ፈሊጣዊ ቃል የሚያመለክተው ትዕቢተኛ ወይም ዕብሪተኛ መሆንን ነው።

  • ይህ ቃል ከሌሎች እበልጣለሁ የማለት ዝንባሌን ወይም ስሜት ያመለክታል።
  • ብዙ መረጃዎች ወይም ሐቆችን ማወቅ ወደ መነፋት ወይም ወደ ትዕቢት ሊያደርስ እንደሚችል ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች ጽፏል።

መናቅ

“መናቅ” አንድ ሰው ወይም አንድን ነገር ለመቀበል አለመፈለግ ማለት ነው። እግዚአብሔርን መናቅ ለእርሱ መታዘዝ አለመፈለግ ነው።

  • “መናቅ” የሚለው፣ “በ . . . ለማመን አለመፈለግ” ማለትም ይሆናል።፥
  • እስራኤል የሙሴን አመራር በናቁ ጊዜ፣ በእውነቱ እግዚአብሔርን መናቃቸው ነበር።
  • ሐሰተኛ አማልክትን ማምለክ እስራኤል እግዚአብሔርን መናቃቸውን ያሳዩበት ዋናው መንገድ ነበር።
  • “መግፋት” የሚለው የዚህ የግሪክ ቃል በቃል ትርጕም ነው። ሌሎችን ቋንቋዎችም መናቅን ወይም ማመን አለመፈለግን የሚገልጡ ፈሊጣዊ ቃሎች ይኖራቸው ይሆናል።

መንቀጥቀጥ

“መንቀጥቀጥ” ከፍርሃት ወይም ከከባድ ጭንቀት የተነሣ መናወጥ ወይም፣ መንዘፍዘፍ ማለት ነው።

  • “በጣም መፍራት” ማለትም ይሆናል።
  • አንዳንዴ፣ “መንቀጥቀጥ” መሬቱን የሚያናውጥ ታላቅ ድምፅንም ያመለክታል።
  • በእግዚአብሔር ፊት ምድር እንደምትንቀጠቀጥ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ይህም ከፍርሃት የተነሣ በምድር የሚኖሩ ሰዎች ይንቀጠቀጣሉ ወይም ምድር ሯሷ ትንቀጠቀጣለች ማለት ነው።
  • እንደ ዐውዱ አገባብ “መፍራት” ወይም፣ “እግዚአብሔርን መፍራት” ወይም፣ “መራድ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

መንጋ

“መንጋ” በጎችንና ፍየሎችን ወይም በሬዎችንና ላሞችን ወይም አሳማዎችን ያመለክታል

  • መንጋ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ የአማኞች ኅብረትንም ያመለክታል።
  • ይህን መንጋ የሚመራና የሚመግብ እረኛ ይባላል።

መንግሥት

መንግሥት በንጉሥ የሚገዛ የሰዎች ቡድን ነው። ንጉሥ ወይም ሌሎች ገዦች የሚቆጣጠሩትና በሥልጣን የሚያስተዳድሩትንም አካባቢ ወይም ፖለታካዊ አገርንም ያመለክታል።

  • መንግሥት ማንኛውም ዐይነት መልክዓ ምድራዊ መጠን ሊኖረው ይችላል። ንጉሥ ሕዝብን፣ አገርን ወይም አንድ ከተማ ብቻ ሊገዛ ይችላል።
  • “መንግሥት” የሚለው ቃል፣ “የእግዚአብሔር መንግሥት” በተሰኘው ሐረግ መሠረት መንፈሳዊ ግዛትን ወይም ሥልጣንን ማመልከትም ይችላል።
  • እግዚአብሔር የፍጥረት ሁሉ ገዢ ቢሆንም፣ “የእግዚአብሔር መንግሥት” የሚለው ሐረግ በተለይ የሚያመለክተው በኢየሱስ ያመኑትና ለእርሱ ሥልጣን በተገዙት ላይ እርሱ ያለውን ገዢነት ወይም ሥልጣን ነው።
  • ሰይጣን በምድር ያሉ ብዙ ነገሮችን ለጊዜው የሚገዛበት፣ “መንግሥት” እንዳለው መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። የእርሱ መንግሥት ክፉ ነው፣ “ጨለማ” ተብሎ ይጠራል።

መንጠቅ፣ ነጠቀ

ብዙውን ጊዜ፣ “መንጠቅ” የሚለው ቃል ተአምራዊ በሆነ መንገድ እግዚአብሔር በድንገት አንድን ሰው ወደ ሰማይ ሲወስድ ነው።

  • “ነጠቀ” የሚለው ቃል በፍጥነት አንድ ሰው ላይ መድረስ ማለት ነው። ከዚህ ቃል ጋር ተመሳሳይ ትርጕም ያለው፣ “አስገድዶ መያዝ” የሚለው ነው።
  • ክርስቶስ ተመልሶ ሲመጣ እርሱን በአየር ለመቀበል ክርስቲያኖች በአንድነት እንደሚነጠቁ ጳውሎስ ይናገራል።
  • “ኃጢአቴ ያዘኝ” የተሰኘው ምሳሌያዊ አንጋገር፣ “የኃጢአቴን ውጤት እየተቀበልሁ ነው” ወይም፣ “ከኃጢአቴ የተነሣ እየተሰቃየሁ ነው” ወይም፣ “ኃጢአቴ ችግር አምጥቶብኛል” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

መንጠቅ፣ ንጥቂያ

“መንጠቅ” የሚያመለክተው አንድን ነገር፣ ብዙውን ጊዜ ደግሞ ለምግብ የሚሆን እንስሳን ማደንን ነው።

  • ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ ሲውል ጥቅሙን እንዲያጣ የተደረገውን፣ የእርሱ የሆነው አለአግባብ የተወሰደበትን ወይም በሌላ ኀያል በሆነ ሰው የሚጨቆን ሰውን ያመለክታል።
  • ሰዎች ላይ የሚፈጸም፣ “ንጥቂያ” እነርሱን በመጫን ወይም ከእነርሱ በመስረቅ የእነርሱን ጥቅም መውሰድ ማለት ነው።

መከራ

“መከራ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው መከራና ጭንቀት ያለበት አዳጋች ጊዜን ነው።

  • እየኖሩ ያሉት የኢየሱስን ትምህርት የሚቃወም ዓለም ውስጥ በመሆኑ ክርስቲያኖች በስደትና ማንኛውም ዐይነት መከራ ባለበት ሁኔታ ውስጥ እንደሚያልፉ አዲስ ኪዳን ይናገራል።
  • ከኢየሱስ ዳግም መምጣት በፊት እግዚአብሔር ለተወሰኑ ዓመታት ቁጣውን በምድር ላይ እንደሚያወርድ ሲያመለክት መጽሐፍ ቅዱስ፣ “ታላቁ መከራ” በሚል ቃል ይጠቀማል።
  • “መከራ” የሚለው ቃል፣ “ታላቅ የመከራ ጊዜ” ወይም፣ “ከባድ ጭንቀት” ወይም፣ “ጽኑ ስደት” በማለት መተርጎም ይቻላል።

መከራ ማድረስ፣ መከራ

“መከራ ማድረስ” አንድን ሰው ማሰቃየት ወይም መጉዳት ማለት ነው። “መከራ” ከዚህ የሚመጣ ሕመም፣ ስሜታዊ ሐዘን ወይም ሌላ ዐይነት ጉዳት ነው።

  • ከሐጢያታቸው ንስሐ እንደቡና ወደ እርሱ እንዲመለሱ ለማድረግ እግዚአብሔር ሕዝቡን መሕመም ወይም በሌላ ችግር መታ።
  • ንጉሣቸው እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ባለ መፈለጉ እግዚአብሔር የግብፅ ሕዝብ ላይ መከራ ወይም መቅሠፍት እንዲመጣባቸው አደረገ።

መከራ፣ መከራ መቀበል

“መከራ” እና፣ “መከራ መቀበል” የተሰኙት ቃሎች በሽታን፣ ስቃይን ወይም ሌሎች አዳጋች ነገሮችን የመሳሰሉ አስከፊ ነገሮች ማለት ነው

  • ሰዎች ሲሰደዱ ወይም ሲታመሙ መከራ ይደርስባቸዋል
  • አንዳንዴ ሰዎች ላይ መከራ የሚደርሰው ራሳቸው በፈጸሙት መጥፎ ነገር ሊሆን ይችላል፤ አንዳንዴ ግን በዓለም ካለው ኅጢአትና ስቃይ የተነሣ ሊሆን ይችላል
  • መከራ ስቃይን ወይም ሕመምን የመሰለ አካላዊ ጉዳት ሊሆን ይችላል። ፍርሃትን፣ ሐዘንና በቸኝነትን የመሰለ መንፈሳዊ ጉዳት ሊሆንም ይችላል

መከር

“መከር” የሚለው ቃል እህል፣ ፍራፍሬ ወይም አትክልት መሰብሰብን ያመለክታል።

  • በመደበኛ ደረጃ የመከር ጊዜ የሚመጣው እህል ፍሬ ሲያፈራ ነው።
  • እስራኤላውያን፣ “የመከር በዓል” ወይም፣ “የመሰብሰብ በዓል” የሚሉት በዓል ነበራቸው። ከመሰበሰበው እህል፣ አትክልት ወይም ፍራፍሬ የመጀመሪያውን ለእርሱ እንዲሰጡ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አዝዞአል።
  • በምሳሌያዊ አነጋገር፣ “መከር” የሚለው ቃል በኢየሱስ ያመኑ ሰዎችን ያመለክታሉ፣ ወይም መንፈሳዊ ዕድገትን ያመለክታል።
  • መከር መንፈሳዊ ባሕርያትን ይወክላል።

መካን(መኻን)

“መካን” መሆን ልጅ አለመውለድ ወይም ፍሬያማ አለመሆን ማለት ነው

  • መካን የሆነ አፈር ወይም መሬት ምንም ዓይነት ተክል ማብቀል አይችልም
  • መካን ሴት ልጅ መፅነስ ወይም መውለድ የማትችል ሴት ናት

መካከለኛ

መካከለኛ የሚባለው ሁለት ወገኖች አለመግባባትን አስወግደው ዕርቅ እንዲያደርጉ የሚረዳ ሰው ነው።

  • የእግዚአብሔር ቁጣ የኀጢአት ውጤት ነው፤ የኀጢአትም ቅጣት ሞት ነው። ከኀጢአት የተነሣ በእግዚአብሔርና በሕዝቡ መካከል የነበረው ቅርርብ ተቋረጠ። ኢየሱስ በእግዚአብሔር አብና በሕዝቡ መካከል ያለ መካከለኛ ነው፤ ለኀጢአታቸው ቤዛ በመሞት ተቋርጦ የነበረውን ቅርርብ አደሰ።

መክሰስ፣ክስ፣ከሳሽ

“መክሰስ”እና “ክስ” የተሰኙት ቃሎች በደል በማስረጉ አንድን ሰው መወቀስን ያመለክታል።ሌሎችን የሚከስ ሰው ከሳሽ ይባላል።

  • የሐሰት ክስ የሚባለው፣የአይሁድ መሪዎች በክፉ ተግባር እየሱስን በከሰሱ ጊዜ እንደሆነው አንድ ሰው ላይ እውነት ያልሆነ ክስ ሲቀርብ ነው።
  • አዲስ ኪዳን ውስጥ ባለው የዮሐንስ ራዕይ መሠረት ሰይጣን፣ “ከሳሽ”ተብሎ አል።

መክበብ፣ ከበበ

“መክበብ” የሚለው ቃል አጥቂ ሰራዊት ከተማን ሲከብና ምግብም ሆነ መጠጥ ወደዚያ እንዳይገባ ማድረግን ያመለክታል። አንድን ከተማን መክበብ እንቅስቃሴዋን መቆጣጠር ማለት ነው

  • ባቢሎናውያን እስራኤልን ለማጥቃት በመጡ ጊዜ ከተማው ውስጥ ያለውን ሕዝብ ለማዳከም ኢየሩሳሌምን ከበቡ
  • ከበባ በሚደረግበት ጊዜ ወደ ከተማዋ ቅጥሮች መሻገርና ከተማዋን መቆጣጠር እንዲችል ወራሪው ሰራዊት ቀስ በቀስ ዙሪያውን ካብ ይሠራ ነበር
  • “ከበባ ውስጥ” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር የጠላት ጦር የከበባት ከተማን ያመለክታል

መወሰን፣ ፍጻሜ

“መወሰን” የሚለው ቃል ወደ ፊት ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ያመለክታል። አንድ ሰው አንዳች ነገር እንዲያደርግ፣ “ተወስኖ” ከሆነ ያ ሰው ወደ ፊት የሚያደርገውን እግዚአብሔር ወስኖታል ማለት ነው።

  • እግዚአብሔር አንድን ሕዝብ ለጥፋት፣ ከወሰኑ ከኃጢአቱ የተነሣ እግዚአብሔር ያንን ሕዝብ ለመቅጣት ወስኖአል ወይም መርጦአል ማለት ነው።
  • ይሁዳ፣ ለጥፋት፣ “ተወስኖአል” ሲባል ከዐመጻው የተነሣ ይሁዳ እንደጠፋ በእግዚአብሔር ተወስኖአል ማለት ነው።
  • በመንግሥተ ሰማይም ይሁን በገሃነም እያንዳንዱ ሰው የመጨረሻና ዘላለማዊ ፍጻሜ እንዲኖረው ተወስኖአል።
  • የመጽሐፈ መክብብ ጸሐፊ የሰው ሁሉ ፍጻሜ አንድ ዐይነት ነው ሲል የኋላ ኋላ ሰዎች ሁሉ ይሞታሉ ማለቱ ነው።

መዋረድ፣ ውርደት

“ማረድ” አንድ ሰው እንዲያፍር ወይም እንዲሸማቀቅ ማድረግ ማለት ነው። ብዙውን ጊዜ ይህ የሚደረገው ሰዎች ፊት ነው።

  • አንድ ሰው እንዲያፍር ማድረግ፣ “ውርደት” ይባላል።
  • እግዚአብሔር አንድን ሰው ካዋረደ፣ ትዕቢተኛ ውድቀት እንዲደርስበት ያደርጋል፤ ያንን የሚያደርገው ትዕቢቱን እንዲጥል ሰውየውን ለመርዳት ነው።
  • “ማዋረድ” የሚለው፣ “ማሳፈር” ወይም፣ “ማሳቀቅ” ወይም፣ “ማስደንገጥ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

መዋረድ፣ ውርደት

“ማረድ” አንድ ሰው እንዲያፍር ወይም እንዲሸማቀቅ ማድረግ ማለት ነው። ብዙውን ጊዜ ይህ የሚደረገው ሰዎች ፊት ነው።

  • አንድ ሰው እንዲያፍር ማድረግ፣ “ውርደት” ይባላል።
  • እግዚአብሔር አንድን ሰው ካዋረደ፣ ትዕቢተኛ ውድቀት እንዲደርስበት ያደርጋል፤ ያንን የሚያደርገው ትዕቢቱን እንዲጥል ሰውየውን ለመርዳት ነው።
  • “ማዋረድ” የሚለው፣ “ማሳፈር” ወይም፣ “ማሳቀቅ” ወይም፣ “ማስደንገጥ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

መዋረድ፥ ውርደት

“መዋረድ” ክብርንና ተቀባይነት ማጣትን ያመለክታል።

  • አንድ ሰው ኃጢአት ካደረገ ውርድትና ክብርን ማጣት ያስከትልበታል።
  • “ውርደት” መጥፎ ሥራን ወይም ያንን ያደረገውን ሰው ያመለክታል።
  • አንዳንድ ጊዜ መልካም ያደረጉ ሰዎች ላይ ውርደት ወይም እፍረት የሚያስከትል ነገር ይደረግባቸዋል።
  • ለምሳሌ የኢየሱስ መስቀል ላይ መሞት የውርደት አሟሟት ነበር። እንዲህ ያለ ውርደት የደረሰበት ኢየሱስ መጥፎ ነገር በማድረጉ አልነበረም።
  • ውርደት የሚለውን ቃል አሳፋሪ ወይም፣ “ክብር የሚነፍግ” ብሎ መተርጎም ይቻላል።
  • ሐሰተኛ አማልክት በማምለካቸውና ክፉ በማድረጋቸው እስራኤላውያን ያህዌን አዋርደዋል።
  • ኢየሱስ አጋንንት ያደሩበት ሰው እንደ ሆነ በመናገር አይሁድ እርሱን አዋርደዋል።

መውቂያ፣ መውቃት

“መውቂያ” እና፣ “መውቃት” የተሰኙት ቃሎች የስንዴን ዘር ከተቀረው የስንዴው ክፍል የመለየት ሥራን ያመለክታሉ።

  • ገለባውንና አበቁን ከስንዴው መለየት እንዲቻል የሚወቃው እህሉ በመጀመሪያ በዱላ ይደበደባል፤ ወይም በሬዎች እንዲረማመዱበት ይደረጋል። ከዚያም ገለባው በነፋስ እንዲወሰድና እሁሉ ዐውድማው ላይ እንዲወድቅ እህሉና ገለባው ወደ አየር ይበተናል።
  • “ዐውድማ” እህል ለመውቃት የሚያገለግል ትልቅና ሰፊ ቦታ ነው።
  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን የነበረው ዐውድማ ሰፊና ዝርግ ዐለት ወይም እህሉን በመውቃት ከገለባው መለየት እንዲቻል ሰፊና በጣም የተጠቀጠቀ መሬት ነበር።
  • እህሉን በመደፍጠጥ ከገለባ ለመለየት፣ “መውቂያ ሰረገላ” ወይም፣ “መውቂያ መንኮራኩር” ጥቅም ላይ ይውል ነበር።
  • እህሉን መለየት እንዲቻል፣ “መውቂያ መዶሽ” ወይም፣ “መውቂያ ጣውላ” ጥቅም ላይ ይውል ነበር። ይህ የሚሠራው ከእንጨት ጣውላ ሲሆን በየጫፎቹ የሾሉ ብረቶች ነበርት።

መውጋት

“መውጋት” ስለት ባለው ሹል ነገር መውጋት ማለት ሲሆን፣ ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ሰውን በጣም ማሳዘንን ለማመልከትም ጥቅም ላይ ይውላል።

  • ኢየሱስ መስቀል ላይ ተሰቅሎ እያለ አንድ ወታደር ጎኑን በጦር ወጋው።
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንመለከተው አንድ ባርያ ነጻ ሲወጣና ከጌታው ጋር ለመሆንና እርሱን ለማገልገል ለመምረጡ ምልክት እንዲሆን ጆሮውን ይወጋ (ይበሳ) ነገር።
  • ጦር ልቧን እንደሚወጋት ማለትም በልጇ በኢየሱስ ላይ ከሚደርሰው የተነሣ ከባድ ሐዘን እንደሚደርስባት ስምዖን ለማርያም ነግሯት ነበር።

መያዝ

“መያዝ” አንድን ሰው ወይም አንድን ነገር በኅይል መያዝ ማለት ነው። ማሸነፍ ወይም ከቁጥጥር ሥር ማድረግ ማለትም ይሆናል

  • አንድ ከተማ በወታደራዊ ኅይል ከተያዘ ወታደሮቹ የተሸናፊውን ሕዝብ ሀብትና ንብረት ወታደሮቹ ይወስዳሉ
  • በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ሲውል፤ “ፍርሃት ያዘው” ከተባለ፣ ፍርሃት በድንገት ተቆጣጠረው ማለት ነው። “በድንገት ፈራ” ተብሎ መተርጎምም ይቻላል
  • አንዲት ሴት፣ “ምጥ ያዛት” ከተባለ ልጅ ከመውለዷ በፊት ድንገተኛና ከባድ ሕመም ተሰማት ተብሎ ሊተረጎም ይችላል
  • ይህ ቃል፣ “ተቆጣጠረው” ወይም፣ “ድንገት መጣበት” ወይም፣ “ወረረው” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል

መያዝ፣ ያዘ

“መያዝ” ሰው ላይ ወይም አንዳች ነገር ላይ ተቆጣጣሪ መሆን ማለት ነው። አብዛኛውን ጊዜ አንድ ነገር አሳድዶ መያዝንም ይጨምራል።

  • “ያዘ” የሚያመለክተው ኅላፊ ድርጊትን ነው።
  • የጦር ሰራዊት ጠላትን፣ “ያዘ” ከተባለ፣ ጠላትን በጦርነት አሸነፈ ማለት ነው።
  • አንድ አጥቂ እንስሳ ሰለባውን ከያዘ አሳድዶ እጁ አገባው ማለት ነው። አንድን ሰው ርግማን፣ “ደረሰበት” ወይም፣ “ያዘው” ከተባለ በርግማኑ የተባለው ሁሉ እርሱ ላይ ይፈጸማል ማለት ነው።
  • እንደ ዐውዱ ሁኔታ፣ “መያዝ” የሚለው ቃል፣ “ማሸነፍ” ወይም፣ “ከበታች ማድረግ” ወይም፣ “አፈፍ ማድረግ” ወይም፣ “አጠገቡ መድረስ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

መደምሰስ፣ ደመሰሰ

“መደምሰስ” እና፣ “ደመሰሰ” የሚለው ቃል ሰዎችን ወይም ነገሮችን ጨርሶ ማስወገድ ወይም ማጥፋትን የሚያመለክት ፈሊጣዊ ቃል ነው።

  • እነዚህ ፈሊጣዊ ቃሎች፣ ይቅር በማለትና ጨርሶ ማሰብ ባለ መፈለግ፣ የሰዎችን ኃጢአት “ሲደመስስ” ቀና በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።
  • ብዙዎን ጊዜ በኃጢአታቸው ምክንያት ሰዎችን በማጥፋት እግዚአብሔር “ሲደመስስ” ወይም፣ “ሲያስወግድ” ያለውን ሁኔታ ለማመልከት በአሉታዊ መልካም ጥቅም ላይ ይውላል።
  • መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎች ስም ከእግዚአብሔር ሕይወት መጽሐፍ “መደምሰሱን” ወይም፣ “መጥፋቱን” በተመለከተ ይናገራል፤ እንዲህ ሲሆን ሰውየው የዘላለም ሕይወት አያገኝም ማለት ነው።

መደረቢያ

መደረቢያ ከትከሻ እስከ ወገብ ወይም ጉልበት የሚደርስ ልብስ ነው።

  • መደረቢያ ከሸሚዝ ወይም እንደ ካባ ካለ ልብስ ጋር ይመሳሰላል።
  • መደረቢያ የሚለበሰው ከረጅም ቀሚስ ወይም ካባ በታች ነው።

መደነቅ፣ መገረም

እነዚህ ቃሎች “አንድ የተለየ ነገር በመደረጉ መደነቅን” ነው የሚያመለክቱት።

  • እነዚህ ቃሎች የተተረጎሙት፣ “በመደነቅ መመታት” ወይም፣ “ከራስ ውጪ መሆን” የሚል ሐሳብ ካላቸው የግሪክ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። እነዚህ ፈሊጣዊ አነጋገሮች አንድ ሰው በጣም መገረሙን ወይም መደንገጡን ያመለክታሉ። ሌሎች ቋንቋዎችም ይህን የሚገልጽ ፈሊጣዊ አነጋገር ሊኖራቸው ይችላል።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙውን ጊዜ የመደነቅ ወይም የመገረም ምክንያት ሲሆን የሚታየው እግዚአብሔር ብቻ ማድረግ የሚችለው ተአምር ነው።
  • ብዙውን ጊዜ የእነዚህ ቃሎች ትርጕም ፍጹም ያልተጠበቀና ይሆናል ተብሎ ያልታሰበ ነገር ከመሆኑ የተነሣ ግራ የመጋባት ስሜትንም ይጨምራል።
  • እነዚህን ቃሎች ለመተርጎም ሌሎች ቃሎች “በጣም መገረም” ወይም፣ “በጣም መደንገጥ” የሚሉት ሊሆኑ ይችላሉ።

መደነቅ፥ አክብሮት፥ አስፈሪ

“አክብሮት” የሚለው የመደነቅ ስሜትንና ታላቅነትን፥ ኅያልነትንና ባለ ግርማነትን በማየት የሚመጣ ጥልቅ አክብሮትን ያመለክታል

  • “አስፈሪ” የሚለው የፍርሃት ስሜትን የማሳድር ሰውን ወይም ነገርንና ሁኔታን ያመለክታል
  • ነቢዩ ሕዝቅኤል የእግዚአብሔርን ክብር ራእይ ሲያይ፥ “ፍርሃት” ወይም ፥ “ድንጋጤ” አድሮበት ነበር
  • ለእግዚአብሔር መገኘት ወይም ሐልምት የሰው ልጅ የሚያሳያቸው የተለመዱ ምላሾች መፍራት፥ ጎንበስ ማለት፥ መንበርከክ፥ ፊትን መሸፈንና መንቀጥቀጥ ናቸው።

መደፋት

“መደፋት” የሚለው ቃል ፊትን ወደ መሬት በማድረግ መዘርጋት ማለት ነው። በድንገት በጣም ዝቅ ብሎ ማጎንበስ ማለት ነው።

  • አንድ ሰው ፊት፣ “መደፋት” ወይም፣ “ራስን መድፋት” በዚያ ሰው ፊት በድንገት ራስን በጣም ዝቅ በማድረግ ፊትን ወደ መሬት መድፋት ማለት ነው።
  • ብዙውን ጊዜ እንዲህ የሚሆነው አንዳች ተአምራዊ ነገር ከመሆኑ የተነሣ ድንጋቴ፣ መደንቅና ፍርሃት ሲኖር ነው። ፊቱ ለሚደፉለት ሰው ያለውን ክብርና አድናቆትም ያመለክታል።
  • መደፋት እግዚአብሔር የሚመለክበትም መንገድ ነው። አንድ ተአምር ሲያደርግ እንደ ታላቅ መምህር እርሱን ለማክበር በምስጋናና በአምልኮ ብዙውን ጊዜ እንዲህ ያለ ምላሽ ይሰጡ ነበር።
  • እንደ ዐውዱ ሁኔታ፣ “መደፋት” የሚለውን ቃል፣ “ፊትን ወደ መሬት በማድረግ በጣም ዝቅ ብሎ ማጎንበስ” ወይም፣ “በፊቱ ፊትን ዝቅ አድርጎ ማምለክ” ወይም፣ “በመደነቅ ፊትን ወደ መሬት ዝቅ ማድረግ” ወይም፣ “ማምለክ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
  • “ራሳችንን አንደፋም” የሚለው ሐረግ፣ “አናመልክም” ወይም፣ “በአምልኮ ፊታችንን ዝቅ አናደርግም” ወይም፣ “ዝቅ ብለን አናመልክም” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

መገሠጽ

መገሠጽ በቃል ጠበቅ ያለ እርማት መስጠት ሲሆን፣ ብዙውን ጊዜ እንዲህ የሚደረገው ያንን ሰው ከኀጢአት ለመመለስ ነው።

  • ክርስቲያኖች ለእግዚአብሔር የማይታዘዙ ሌሎች አማኞችን መገሠጽ እንዳለባቸው አዲስ ኪዳን ያዝዛል።
  • ልጆቻቸው አልታዘዝም ካሉ ሊገሥጿቸው እንደሚገባ መጽሐፈ ምሳሌ ወላጆችን ያሳስባል።
  • ጠንከር ያለ ተግሣጽ የሚሰጠው በደል የፈጸመ ሰው ከዚያ የበለጠ ኃጢአት እንዳያደርግ ነው።
  • ይህ ቃል፣ “ጠንከር ያለ እርምት” ወይም፣ “ምክር” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

መገዛት፣ በመገዛት

ብዙውን ጊዜ፣ “መገዛት” የሚለው ቃል ፈቅዶና ወዶ ራስን በሌላው ሰው ሥልጣን ወይም መንግሥት ሥር ማድረግ ማለት ነው

  • በኢየሱስ የሚያምኑ ለእግዚአብሔርና ሥልጣን ላላቸው ሌሎች ሰዎች ራሳቸውን ያስገዛሉ
  • “አንዳችሁ ለሌላው ተገዙ” የሚለው መመሪያ በትሕትና ተግሣጽ መቀበልና ከራስ ይልቅ ለሌሎች ለሚያስፈልገው ነገር ትኩረት መስጠት ማለት ነው
  • “በመገዛት መኖር” ራስን በሌላው ሰው ሥልጣን ሥር ማድረግ ማለት ነው

መጋረጃ

መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን “መጋረጃ” የሚያመለክተው መገናኛው ድንኳንንና ቤተ መቅደሱን ለመሥራት ጥቅም ላይ ይውል የነበረውን ወፍራምና በጣም ከባድ ጨርቅ ነበር።

  • መገናኛው ድንኳን የተሠራው ከላይና ከጎን በተዘረጉ አራት ተደራራቢ መጋረጃዎች ነበር። እነዚህ መጋረጃዎች ከጨርቅ ወይም ከእንስሳት ቆዳ ይሠሩ ነበር።
  • የጨርቅ መጋረጃዎች በመገናኛው ድንኳን አደባባይ ዙሪያ ግድግዳ በመሆን ያገለግሉ ነበር። እነዚህ መጋረጃዎች ከተልባ እግር ማለትም ከናይለንም ይሠሩ ነበር።
  • በመገናኛው ድንኳንም ሆነ በቤተ መቅደሱ ግንባታ ሥራ በቅድስተ ቅዱሳኑና በተቀደሰው ቦታ መካከል በጣም ትልቅ የጨርቅ መጋረጃ ይደረግ ነበር። ኢየሱስ መስቀል ላይ በሞተ ጊዜ በተአምር ለሁለት የተቀደደው ይኸው መጋረጃ ነበር።

መግዛት

መግዛት በአንድ አገር ወይም በአንድ መንግሥትና ሕዝቡ ላይ ንጉሥ መሆን ማለት ነው። አንድ ንጉሥ የሚገዛው እርሱ በሕይወት እስካለ ድረስ ነበር።

  • የአጽናፈ ዓለሙ ፈጣሪ ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር መላውን ዓለም በንጉሥነቱ ይገዛል።
  • እርሱ ንጉሣቸው እንዳይሆን ሲፈልጉ እስራኤል የራሳቸው ንጉሦችን እንዲያነግሡ እግዚአብሔር ፈቀደ።
  • ኢየሱስ ክርስቶስ ሲመለስ መላውን ዓለም በንጉሥነት እንደሚገዛና ክርስቲያኖችም ከእርሱ ጋር እንደሚነግሡ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።

መግፋት

ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “መግፋት” ጉልበት በመጠቀም አንድን ነገር ማስወገድ ማለት ነው። የተለያዩ ምሳሌያዊ ጠቀሜታዎችም አሉት።

  • “በኀይል መግፋት” ማለት፣ “መናቅ” ወይም፣ “ለመርዳት አለመፈለግ” ማለት ነው።
  • “ወደ ታች መግፋት” – “መጨቆን” ወይም፣ “ማሳደድ” ወይም፣ “ማሸነፍ” ማለት ነው።
  • “አንድን ሰው ወደ ውጭ መግፋት” እርሱን ማራቅ ወይም ለዘለቄታው ማባረር ማለት ነው።
  • “ወደ ፊት መግፋት” ትክክል ወይም ተገቢ መሆኑን በቅጡ ሳይረዱ አንድን ነገር በማድረግ መቀጠል ማለት ነው።

መጠበቂያ ግንብ

“መጠበቂያ ግንብ” ጠባቂዎች እዚያ ላይ ሆነው ማንኛውንም አደጋ የሚመለከቱበት ቦታ እንዲሆን የተሠራ ረጅም ግንብ ነው። እነዚህ ግንቦች አብዛኛውን ጊዜ የሚሠሩት ከድንጋይ ነው።

  • እነርሱ ላይ ሆነው እህላቸውን ሌቦች ከመሰረቅና ከእንስሳት ለመጠበቅ ባለ ርስቶችም መጠበዚያ ግንብ ይሠራሉ።
  • ብዙውን ጊዜ ግንቡ ጠባቂዎቹ ከነቤተሰባቸው የሚኖርበት ክፍሎችም ይኖሯቸዋል፤ በዚህ ሁኔታ ለሊትና ቀን በጥበቅ ይተጋሉ።
  • ጠላት ከተማዋን ለማጥቃት ሲመጣ ማየት እንዲቻል የከተማ መጠበቂያ ግንቦች ከከተማዋ በጣም ከፍ እንዲል ተደርጎ ይሠራል።
  • መጠበቂያ ግንብ ከጠላቶች የመጠበቅና ከለላ የማግኘት ምሳሌ ነው።

መጠየቅ

“መጠየቅ” መረጃ የሚጠይቅ ማለት ነው።

  • ብሉይ ኪዳን ሰዎች ከእግዚአብሔር ለመጠየቃቸው በርካታ ምሳሌዎች አሉት።
  • አንድ ንጉሥ ወይም የመንግሥት ባለሥልጣን መንግሥታዊ ሰነዶችን መመርመርን አስመልክቶ ይህ ቃል ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።

መጠጊያ

“መጠጊያ” የሚለው ቃል ዋስትናና ጥበቃ ያለበትን ቦታን ወይም ሁኔታን ያመለክታል። “መጠቢያ” ከዝናብ ወይም ከአደጋ የሚከልል ነገር ነው።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር ሕዝቡ ጥበቃ፣ ጥንቃቄና ሰላም የሚያገኙበት መጠጊያ እንደ ሆነ ተነግሯል።
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ “የመጠጊያ፣ የመማጸኛ ከተማ የሚለው ቃል ሳያስበው ሰው የገደለ ሰው፣ የበቀል ጥቃት እንዳይደርስበት በፍጥነት በመሄድ የሚጠለልባቸውን ከተሞች ያመለክታል።
  • ብዙውን ጊዜ ለሰዎች ወይም ለእንስሳት ከለላ የሚሆን ሕንፃ ወይም ጣራ፣ “መጠጊያ” ተብሎ ይጠራል።
  • እንግዶቹ ከእርሱ ቤት ጣራ በታች “የተጠጉ” መሆናቸውን ሎጥ ከተናገረው መመልከት እንደሚቻለው፣ “መጠጊያ” – “መከለያ” ማለትም ይሆናል። ሎጥ እንዲህ ያለው በእርሱ ቤት እስካሉ ድረስ ምንም ጉዳት እንደማይደርስባቸው ለማመልከት ነው።

መጠጊያ፥ መጠለያ

“መጠጊያ” የሚለው ቃል ዋስትናና ጥበቃ ያለበትን ቦታን ወይም ሁኔታን ያመለክታል። “መጠለያ” ከዝናብ ወይም ከአደጋ የሚከልል ነገር ነው።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር ሕዝቡ ጥበቃ፣ ጥንቃቄና ሰላም የሚያገኙበት መጠጊያ እንደ ሆነ ተነግሯል።
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ “የመጠጊያ፣ የመማጸኛ ከተማ የሚለው ቃል ሳያስበው ሰው የገደለ ሰው፣ የበቀል ጥቃት እንዳይደርስበት በፍጥነት በመሄድ የሚጠለልባቸውን ከተሞች ያመለክታል።
  • ብዙውን ጊዜ ለሰዎች ወይም ለእንስሳት ከለላ የሚሆን ሕንፃ ወይም ጣራ፣ “መጠጊያ” ተብሎ ይጠራል።
  • እንግዶቹ ከእርሱ ቤት ጣራ በታች “የተጠጉ” መሆናቸውን ሎጥ ከተናገረው መመልከት እንደሚቻለው፣ “መጠጊያ” – “መከለያ” ማለትም ይሆናል። ሎጥ እንዲህ ያለው በእርሱ ቤት እስካሉ ድረስ ምንም ጉዳት እንደማይደርስባቸው ለማመልከት ነው።

መጥረቢያ

  • መጥረቢያ ዛፍን ወይም እንጨትን ለመቁረጥና ለመፍለጥ የሚያገለግል መሣሪያ ነው
  • ብዙውን ጊዜ መጥረቢያ ረጅም የእንጨት እጀታ(መያዣ) እና ጫፉ ላይ የተያያዘ ብረት ይኖረዋል
  • በእናንተ አካባቢ መጥረቢያ የሚመስል ሌላ መሣሪያ ካላችሁ “መጥረቢያ” የሚለውን ቃል ስትተረጉሙ የዚያን መሣሪያ ስም ማስገባት ትችላላችሁ
  • ይህ ቃል መተርጎም የሚችልባቸው ሌሎች መንገዶች፥ “ዛፍ መቁረጫ መሣሪያ” ወይም “ብረት ያለበት የእንጨት መሣሪያ” ወይም፥ “ረጅም እጀታ ያለው እንጨት መቁረጫ መሣሪያ” የተሰኙትንም ይጨምራል
  • ከብሉይ ኪዳን ከምናየው አንድ አጋጣሚ አንድ የመጥረቢያ ብረት ወንዝ ውስጥ ወድቆ ነበር፤ ስለዚህ ያ የመጥረቢያ ብረት ከእንጨት እጅታው የሚላቀቅ ዓይነት ነበር ቢባል የተሻለ ይሆናል

መጥረግ፣ ጠረገ

“መጥረግ” እና፣ “ጠረገ” የሚሉት ቃሉች አብዛኛውን ጊዜ የሚያመለክቱት መጥረጊያ በመጠቀም ቆሻሻና የማይፈለግ ነገር ማስወገድ በፍጥነት መንቀሳቀስን ነው። እነዚህ ቃሎች ማሳሌያዊ ትርጉምም አላቸው

  • አንድ ሰራዊት በድንገትና በፍጥነት ሁሉንም በሚያዳርስ እንቅስቃሴ ለማመልከት ጠረገ የሚለው ምሳሌያዊ አነጋገር ጥቅም ላይ ይውላል
  • ለምሳሌ ኢሳይያስ አሦራውያን የይሁዳን መንግሥት፣ “ጨርሶ እንደሚጠረጉ” በትንቢት አመልክቶ ነበር። ይህም ይሁዳን ይይዛሉ፤ ደግሞም ያጠፋሉ ማለት ነው
  • “መጥረግ” የሚለው ቃል በፍጥነት እየሄደ ያለ ውሃ ነገሮችን እየገፋ በኅይል ማስወገዱን ለማመልከትም ጥቅም ላይ ይውላል
  • አንድ ሰው፣ “ጥርግ አለ” ከተባለ ያ ሰው ላይ ከዐቅሙ በላይ የሆነ ድንገተኛ ነገር ደርሶበታል ማለት ነው

መጨረስ

ቃል በቃል ሲወሰድ እስኪያልቅ ድረስ አንድን ነገር መጠቀም ማለት ሲሆን በርካታ ምሳሌያዊ ትርጕሞችም ይኖሩታል።

  • መጸሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “መጨረስ” የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ ነገሮችን ወይም ሰዎችን ማጥፋት ይመለከታል።
  • እሳት ነገሮችን እንዲጨርስ (እንደሚበላ) ሲነገር ዐመድ እስከሆኑ ድረስ እቃጥሎ ይፈጃቸዋል ማለት ነው።
  • እግዚአብሔር፣ “የሚባላ እሳት” ተብሏል፤ ይህ ኃጢአት ላይ ያለውን ቊጣ የሚገልጽ ነው። ቊጣው በንስሐ ይማይመለሱ ኃጢአተኛ ላይ ከባድ ቅጣት ያመጣል።
  • ምግብ መጨረስ እስኪያልቅ ድረስ መብላት ወይም መጠጣት ማለት ነው።
  • “ምድሪቱን በላ” የሚለው ሐረግ፣ “ምድሪቱን አጠፋ” ተብሎ መተርጎም ይችላል።

መጨቆን፣ ጭቆና፣ ጭቋኝ

“መጨቆን” እና፣ “ጭቆና” በከፍተኛ ደረጃ ሰዎችን መበደልን ያመለክታል። “ጨቋኝ” ሰዎችን የሚጨቁን ሰው ነው።

  • “ጭቆና” የሚለው ቃል በተለይ የሚያመለክተው ኅይልና ሥልጣን ያላቸው ሰዎች ሰዎችን የሚበድሉበትን፣ ከኅይላቸው ወይም ከአገዛዛቸው ሥር ያሉትን ባርያዎች የሚያደርጉበትን ሁኔታ ነው።
  • “የተጨቆኑ” የሚለው በጣም የተበደሉ ወይም መከራ የደረሰባቸውን ሰዎች ያመለክታል።
  • የእስራኤል ጠላቶች የሆኑ መንግሥታትና ገዢዎቻቸው የእስራኤልን ሕዝብ ጨቁነዋል።

መጮኽ

“መጮኽ” እንባ አውጥቶ ማልቀስ ወይም ጭንቅ ውስጥ ያለ ሰው የሚያሰማው ጥሪ ሊሆን ይችላል።

  • “መጮኽ” ርዳታ በመፈለግ መጣራት ወይም ጮኽ ብሎ ድምፅን ማሰማት ማለት ነው።
  • ይህ ቃል፣ “በአስቸኳይ መጣራት” ወይም፣ “ርዳታ መጠየቅ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
  • “ወደ አንተ እጮኻለሁ” የሚለው፣ “እንድትረዳኝ አንተን ጠራሁ” ወይም፣ “በመከራዬ እንድትደርስልኝ አንተን ጠራሁ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

መጽናት፣ ጽናት

መጽናት፣ ምንም እንኳ ረጅም ጊዜ ቢወስድና በጣም አስቸጋሪም ቢሆን በእምነት ወይም የተሰጠውን ሥራ በመፈጸም መቀጠል ማለት ነው።

  • መጽናት፣ በከባድ መከራ ወይም ሁኔታ ውስጥ እንኳ ቢሆን የክርስቶስን በመሰለ መንገድ ተግባርንም መቀጠል ማለትም ይሆናል።
  • ጽናት፣ ምንም አዳጋች ቢሆን ሰዎች ማድረግ ያለባቸውን እንዲያደርጉ የሚያስችል ባሕርይ ነው።
  • እዚህ ላይ “ግትር” የሚለውን ቃል እንዳትጠቀሙ መጠንቀቅ አለባችሁ፤ ብዙ ጊዜ ይህ አሉታዊ ትርጕም ነው የሚኖረው።

መጽደቅ፣ ጽድቅ

“መጽደቅ” እና፣ “ጽድቅ” የተሰኙት ቃሎች በደለኛውን ሰው ምንም በደል እንዳልፈጸመ አድርጎ መቀበል ማለት ነው። ሰዎችን ማጽደቅ የሚችል እግዚአብሔር ብቻ ነው።

  • እግዚአብሔር ሰዎችን ሲያጸድቅ ኀጢአታቸውን ይቅር ይላል፤ ምንም ኀጢአት እንዳልሠሩ ያደርጋቸዋል። ንስሐ የሚያደርጉትንና እርሱ እንደሚያድናቸው በኢየሱስ የሚተማመኑትን ኀጢአትኞች እግዚአብሔር ያጽድቃቸዋል።
  • “መጽደቅ” እግዚአብሔር የሰውን ኀጢአት ይቅር ማለቱንና ያ ሰው በእርሱ ፊት ንጹሕ መሆኑን መናገሩን ያመለክታል።

መፅነስ፣ ፅንስ

ብዙዎን ጊዜ “መፅነስ” እና፣ ፅንስ” የተሰኙ ቃሎች የሚያመለክቱት ልጅ ማርገዝን ነው። ያረገዙ እንስሳትን ለማመልከትም ጥቅም ላይ ይውላል።

  • “ሕፃን መፅነስ” የሚለው ሐረግ “ማርገዝ” ተብሎ ወይም ይህን ለማመልከት ተቀባይነት ባለው ሌላ መንገድ መተርጎም ይችላል።
  • ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያለው፣ “ፅንስ” የሚለው ቃል፣ “የእርግዝና ጅማሬ” ወይም፣ “እርጉዝ የመሆን ሂደት” ተብሎ መተርጎም ይችላል።
  • እነዚህ ቃሎች ዐሳብን፣ ዕቅድን ወይም ተግባርን የመሳሰሉ ነገሮችን መፍጠር ወይም ማሰብንም ሊያመለክቱ ይችላሉ። እነዚህን እንደ ዐውዱ መሠረት፣ “ማሰብ” ወይም “ማቀድ” ወይም፣ “መፍጠር” ብሎ መተርጎም ይቻላል።
  • አንዳንዴ ይህን ቃል ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ እንጠቀምበታለን፤ ለምሳሌ “ምሦትም ከፀነሰች በኋላ” እንደሚለው፤ እንዲህ ማለት ክፉ ምኞት አእምሮ ውስጥ ሲፈጠር ውይም ክፉ ምኞት ወድ ልብ ሲመጣ ነው።

መፈለግ፣ ፈለገ

“መፈለግ” አንድን ሰው ወይም አንድን ነገር መሻት ማለት ነው። ኅላፊው ግሥ፣ “ፈለገ” የሚለው ነው። አንድን ነገር ለማድረግ “አጥብቆ መሞከር” ወይም፣ “ከባድ ጥረት ማድረግ” ማለትም ይሆናል

  • አንድን ዕድል፣ “መፈለግ” ወይም፣ “መሻት” አንድን ነገር ለማድረግ፣ “ጊዜ ለማግኘት መሞከር” ማለት ነው
  • “ያህዌን መፈለግ” ማለት፣ “ያህዌን ለማወቅና ለእርሱ መታዘዝን ለመማር ጊዜንና ጉልበትን መስጠት” ማለት ነው
  • “ከለላ መፈለግ” – “ከአደጋ የሚከልላችሁን ሰው ወይም ቦታ አጥብቆ መፈለግ” ማለት ነው
  • “ፍትሕ መፈለግ” – “ሰዎች እውነተኛና ትክክለኛ ፍርድ ሲያገኙ ለማየት ማንኛውንም ጥረት ማድረግ” ማለት ነው
  • “እውነትን መፈለግ” – “እውነቱ የትኛው እንደሆነ ለማወቅ ጥረት ማድረግ” ማለት ነው
  • “ሞገስ መፈለግ” – “መወደድን መፈለግ” ወይም፣ “አንድ ሰው እንዲረዳችሁ መፈለግ” ማለት ነው

መፈወስ፣ ፈወሰ

መፈወስ የሰው ቁስል፣ ሕመም ወይም ዕዐይነ ስውርነትና የመሳሰሉ ጉድለቶች ከእንግዲህ እንዳይኖሩ ማደረግ ነው። ወይም የታመመውን ወይም ዐቅም ያጣውን ሰው እንደ ገና ጤነኛ ማድረግ ነው።

  • የተፈወሰ ሰው ደኅና ሆኖአል ማለት ነው።
  • ተፈጥሮአዊ ፈውስ የሚሆነው ቀስ በቀስ ነው።
  • ብዙውን ጊዜ ተአምራዊ ፈውስ የሚሆነው አቅጽበት ነው፤ ለምሳሌ ጴጥሮስ ሽባውን ሰው ወዲያውኑ መራመድ እንዲችል እንዳደረገው።

መፋታት፣ ፍቺ

መፋታት ጋብቻ የሚቋረጥበት ሕጋዊ አሠራር ነው። ፍቺ ያደረጉ ባልና ሚስት ከእንግዲህ ትዳር ውስጥ አይደሉም ማለት ነው።

  • የመፋታት ቃል በቃል ትርጕሙ፣ “መለያየት” ወይም፣ “ማሰናበት” ማለት ሲሆን፣ ሌሎች ቋንቋዎችም እንዲህ ያሉ ፈሊጣዊ አነጋገሮች ይኖሩዋቸዋል።
  • “የፍቺ ጽሑፍ” የሚለው፣ “ባልና ሚስቱ መለያየታቸውን የሚያመለክት ሰነድ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

መፍረስ፣ ፍርስራሽ

አንድ ነገር፣ “ማፍረስ” ያንን ነገር ማበላሸት፣ ማጥፋት፣ መደምሰስ፣ ወይም ከጥቅም ውጪ ማድረግ ማለት ነው። “ፍርስራሽ” እንዲፈርስ ከተደረገው ነገር የቀረ ክምር ነው።

  • የእግዚአብሔር ቀን፣ ዓለም ላይ የሚፈረድበትና ዓለም የሚቀጣበት “የመፍረስ ቀን” እንደ ሆነ ነቢዩ ሰፎንያስ ተናግሯል።
  • እግዚአብሔርን የማይፈሩ ሰዎች ጥፋትና መፍረስ እንደሚጠብቃቸው መጽሐፈ ምሳሌ ያመለክታል።
  • እንደ ዐውዱ ሁኔታ፣ “መፍረስ” የሚለውን፣ “ማጥፋት” ወይም፣ “ማበላሸት” ወይም “ከጥቅም ውጪ ማድረግ” ወይም፣ “መስበር” ብሎ መተርጎም ይቻላል።
  • እንደ ዐውዱ ሁኔታ “ፍራሽ” ወይም “ፍርስራሽ” – “ክምር” ወይም፣ “የፈራረሱ ሕንፃዎች” ወይም፣ “የተደመሰሰ ከተማ” ወይም፣ “ውድመት” ወይም፣ “ስብርባሪ” ወይም “ጥፋት” በማለት መተርጎም ይቻላል።

መፍጠር፣ ፍጥረት፣ ፈጣሪ

“መፍጠር” አንድን ነገር ማድረግ ወይም ሕልውና እንዲኖረው ማድረግ ማለት ነው። የተፈጠረ ነገር “ፍጥረት” ይባላል። በመላው አጽናፍ ያለውን ወደ ሕልውና ያመጣ እርሱ በምሆኑ እግዚአብሔር፣ “ፈጣሪ” ይባላል።

  • ይህ ቃል እግዚአብሔር ዓለምን መፍጠሩን ለማመልከት ጥቅም ላይ ከዋለ ፍጥረትን እም ኀበ አልቦ ወይም ከምንም አስገኝቷል ማለት ነው።
  • ሰዎች ነገሮችን የሚፈጥሩት ቀድሞውኑ ከነበሩ ነገሮች ነው።
  • ሰላምን ማስገኘትን ወይም ንጹሕ ልብን መፍጠርን የመሳሰሉ ረቂቅ ነገሮችን ለማመልከት አንዳንዴ፣ “ፈጠረ” የሚለው ቃል በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።
  • “ፍጥረት” መጀመሪያ እግዚአብሔር ማንኛውንም ነገር ሲፈጥር የሆነውን የዓለምን ካለ መኖር ወደ መኖር መምጣት ሊያመለክት ይችላል። ወይም ደግም እግዚአብሔር የፈጠረውን ማንኛውንም ነገር ሁሉ ሊያመለክት ይችላል። አንዳንዴ፣ “ፍጥረት” በተለይ ዓለም ውስጥ ያሉ ሰዎችን ያመለክታል።፥

ሙሽራ (ሙሽሪት)

ሙሽሪት የወደፊት ባልዋ ከሚሆነው ሙሽራ ጋር ለመጋባት የጋብቻ ሥርዓት ላይ ያለች ሴት ናት።

  • ሙሽራ የተሰኘው ቃል በኢየሱስ የሚያምኑ አማኞችን ማለትም ቤተ ክርስቲያንን ለማመልከት ጥቅም ላይ የሚውል ተለዋጭ ዘይቤ ነው።
  • ኢየሱስ፣ “የቤተ ክርስቲያን ሙሽራ” በሚል ተለዋጭ ዘይቤ ተጠርቷል።

ሙሽራ (ወንድ)

ጋብቻ ሥርዓት ላይ ያለ ሙሽራ ሙሽራዪቱን የሚያገባው ሰው ነው።

  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን በአይሁድ ባሕል ሥርዓቱ ሁሉ ማዕከል የሚያደርገው የእርሱን ሙሽሪት ለመውሰድ የሚመጣው ሙሽራ ላይ ነበር።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኢየሱስ፣ “ለሙሽሪት” ማለትም ለቤተ ክርስቲያን የሚመጣ ሙሽራ ተብሎ ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ተጠርቷል።
  • ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሙሽራው ከእነርሱ ጋር እያለ ደስ እንደሚላቸው እርሱ ሲሄድ ግን የሚከፋቸው ሚዜዎች መስሎአቸዋል።

ማልቀስ፣ ለቅሶ

“ማልቀስ” እና፣ “ለቅሶ” የተሰኙት ቃሎች ጥልቅ የሐዘን መገለጫዎች ሲሆኑ፣ ብዙውን ጊዜ የሚያያዙት ሰው ሲሞት ከሚደረግ ሐዘን ጋር ነው። ብዙ ባሕሎች ሐዘንና ትካዜያቸውን የሚገልጡበት ውጫዊ እንቅስቃሴን ይጨምራል።

  • እስራኤላውያንና በጥንት ዘመን የነበሩ ሌሎች ሕዝቦች ለቅሶዋቸውን የሚገልጡት ጮኽ ብሎ በሚሰማ ዋይታ ወይም እንጉርጉሮ ሲሆን፣ በአብዛኛው አሁን ያሉ ሕዝቦች ከሚያደርጉት ጋር ይመሳሰላል።
  • ብዙውን ጊዜ ሰውየው ከሞተበት ጊዜ አንሥቶ መቃብር ውስጥ ከገባ ጥቂት ጊዜ በኋላ ድምፃቸውን አሰምተው ዋይ እንዲሉ አልቃሾች ይቀጠሩ ነበር። አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ አልቃሾች ሴቶች ነበሩ።
  • መደበኛው የለቅሶ ጊዜ ሰባት ቀን ሲሆን፣ እስከ ሰለሣ ቀን (ሙሴና አሮን ሲሞቱ እንደ ተደረገው) ወይም እስከ ሰባ ቀን ድረስ (ያዕቆብ ሲሞት እንደ ተደረገው) ይቆይ ነበር።
  • መጽሐፍ ቅዱስ በኀጢአት ምክንያት ስለ “ማልቀስ” ሲናገር ይህን ቃል በምሳሌነት ይጠቀማል። ኀጢአታችን ምን ያህል እግዚአብሔርን፣ ራሳችንንና ሌሎች ሰዎችን ምን ያህል እንደ ጎዳ በማሰብ ጥልቅ የሐዘን ስሜትንም ይጨምራል።

ማሕፀን

“ማሕፀን” እናቱ ውስጥ ያለ ሕፃን የሚኖርበት ነው።

  • አንዳንድ ቋንቋዎች ማሕፀን ለማለት “ሆድ” በተሰኘው ቃል ይጠቀማሉ።

ማመፅ፣ ዐመፀኛ

ማመፅ ሥልጣን ላይ ላለ ሰው አለመገዛት ማለት ነው። ለአለቃ አለመታዘዝ ማለትም ነው።

  • እነርሱ ላይ ሥልጣን ያላቸው እንዲያደርጉ ያዘዟቸውን ሰዎች ማድረግ ካልፈለጉ ልብ ውስጥ ዐመፅ ይፈጠራል።
  • ሰዎች በቀጥታ ባለ ሥልጣኖችን ከተቃወሙ ወይም አንታዘዝም ካሉ በገሃድ የሚታይ ዐመፅ ይፈጠራል።
  • ማመፅ የሚለው ቃል ንጉሣቸው ወይም መሪያቸው ላይ ጦርነት የሚያነሡ ሰዎችንም ይመለከታል። ሰዎች እንዲህ የሚያደርጉት ንጉሥ ወይ መሪው መሪው በትክክል እያስተዳደረ አይደለም በማለት ሲያስቡ ነው።

ማረሻ

“ማረሻ” አንድን ቦታ ለዘር ለማዘጋጀት መሬቱን ሥርዓት ባለው መልኩ ለመቆፈር የሚያገለግል የእርሻ መሣሪያ ነው።

  • ማረሻ ጠለቅ ብሎ መሬቱን ለመቆፈር የሚረዳ ሹል ጫፍ አለው። ትልሙን ማስተካከል እንዲቻል ገበሬው የሚይዘው እጀታ አለው።
  • ብዙውን ጊዜ ማረሻ የሚጎተተው በሁለት በሬዎች ወይም ሌሎች እንስሳት ነው።
  • ጫፉ ላይ ብረት ወይም ሌላ ሹል ነበር ከመግባቱ ውጪ አብዛኛውን ጊዜ ማረሻ የሚሠራው ከጠንካራ እንጨት ነው።

ማረድ፣ ታረደ

“ማረድ” ሰውን ወይም እንስሳን መግደል ማለት ነው። ብዙ ጊዜ ግን በኅይል ወይም በአሰቃቂ ሁኔታ መግደልን ነው የሚያመለክተው

  • “የታረዱ” የሚለው ቃል፣ “የታረዱ ሰዎችን” ማለት የተገደሉ ሰዎችን ያመለክታል
  • እንስሳትን ወይም ብዙ ሰዎችን የሚመለከት ከሆን ብዙውን ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውለው፣ “ጭፍጨፋ” የተሰኘውን ቃል ነው
  • “መግደል” በሚለው ቃል መጠቀምም ይቻላል

ማረድ፣ ታረደ

“ማረድ” ሰውን ወይም እንስሳን መግደል ማለት ነው። ብዙ ጊዜ ግን በኅይል ወይም በአሰቃቂ ሁኔታ መግደልን ነው የሚያመለክተው

  • “የታረዱ” የሚለው ቃል፣ “የታረዱ ሰዎችን” ማለት የተገደሉ ሰዎችን ያመለክታል
  • እንስሳትን ወይም ብዙ ሰዎችን የሚመለከት ከሆን ብዙውን ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውለው፣ “ጭፍጨፋ” የተሰኘውን ቃል ነው
  • “መግደል” በሚለው ቃል መጠቀምም ይቻላል

ማር፣ የማር እንጀራ

ማር ንቦች ከአበባ የሚሠሩት ጣፋጭና ሙጫነት ያለው የሚበላ ነገር ነው። የማር እንጀራ ንቦቹ ማሩን የሚያኖሩበት እንደ ሰም ያለው ቅርጽ ነው።

  • እንደ ዐይነቱ ማር ቢጫማ፣ ወይም ቡኒ ዐይነት መልክ ይኖረዋል።
  • በጣም ጣፋጭ ወይም በጣም አስደሳች ነገርን ለመወከል አንዳንዴ ማር በምሳሌያዊ አነጋገር ጥቅም ላይ ይውላል። አንዳንዴ ያ ጣፋጭና አስደሳች ነገር “ማር” ነው ሲባል፣ ሌላ ጊዜ፣ “እንደ ማር” ይባላል።
  • አንዳንዴ ማር የዛፍ ሽንቁርን ወይም ንቦቹ መኖሪያ የሚያደርጉትን ዱር ቦታ ውስጥ ሁሉ ሊገኝ ይችላል። ሰዎች ለመብል ወይም ለመሸጥ ንቦች ያነባሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጥቀሰው ማር ግን የዱር ማር ሊሆን ይችላል።
  • በጦርነት ጊዜ ኀይልና ብርታት ለማግኘት የሳኦል ልጅ ዮናታን ጫካ ውስጥ ያገኘውን የዱር ማር በላ።
  • አንድ ጊዜ ሳምሶን የሞተ አንበሳ ውስጥ ማር አግኝቶ ነበር።
  • በረሐ በነበረ ጊዜ መጥምቁ ዮሐንስ አንበጣና ማር ይበላ ነበር።

ማርከስ

“ማርከስ” ቅዱስ የሆነ ነገርን ማቆሸሽ፣ መበከል ወይም አለማክበር ማለት ነው።

  • ቅዱስ የሆነ ነገር ወይም ሰው ርኩስ ሊሆን አይችልም፤ ይልቁን ቅዱስ ባልሆንና ክብር በማይሰጥ ሁኔታ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።
  • የረከሰ ሰው ቅዱስ ያልሆነና እግዚአብሔርን የማያከብር ነገር የሚያደርግ ነው።
  • “ማርከስ” የሚለው ግስ፣ “ቅድስናን መንፈግ”፣ “ክብር ማሳጣት” ወይም፣ “በኀጢአት እግዚአብሔርን ማሳዘን” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
  • እንደ ዐውዱ አገባብ፣ “ማርከስ” የሚለው ቃል እንደ ቅጽል፣ “ክብር የማይሰጥ” ወይም፣ “መንፈሳዊ ያልሆነ” ወይም የረከሰ ተብሎ መተርጎም ይችላል።

ማርከስ፣ መርከስ

“ማርከስ” እና፣ “መርከስ” የተሰኙት ቃሎች መበከልን ወይም በከፍተኛ ደረጃ መቆሸሽን ያመለክታሉ። አንድ ነገር ከአካላዊ፣ ከግብረ ገባዊ ወይም ከሃይማኖታዊ ሥርዓት ጋር በተያያዘ ርኵስ ተብሎ ሊጠራ ይችላል።

  • እርሱ፣ “ርኵስ” ወይም “ያልተቀደሰ” ያለውን በመብላት ወይም በመንካት ራሳቸውን እንዳያረክሱ እግዚአብሔር እስራኤላይውያንን አስጠንቅቆ ነበር።
  • የሞቱ አካሎችና ተላላፊ በሽታዎችን የመሳሰሉ ነገሮችን እግዚአብሔር ርኵሳን ብሏቸዋል፤ እነርሱን የሚነኩ ሰዎች ይረክሳሉ።
  • ከዝሙት ኃጢአት እንዲርቁ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አዞአል። ይህ ኃጢአት ያረክሳችዋል፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጡ ያደርጓቸዋል።
  • የተወሰኑ ሥርዓቶችን በመፈጸም እንደ ገና ንጹሕ እስኪሆን ድረስ ለጊዜውም ቢሆን ሰውን የሚያረክሱ ከአካል የሚወጡ ነገሮች ነበር።
  • አዲስ ኪዳን ውስጥ አንድን ሰው በእውነት የሚያረክሱት ኃጢአተኛ ዐሳብና ተግባር እንደ ሆኑ ኢየሱስ አስተምሮአል።

ማርከስ፣ ማጉደፍ

ለአምልኮ ጥቅም ላይ ማዋል በማይቻልበት ሁኔታ የተቀደሰ ቦታን ወይም ነገርን መጉዳት ወይም መበከል ማለት ነው።

  • ለአንድ ነገር አክብሮትን አለማሳየት ብዙውን ጊዜ ያንን ነገር ማርከስ ወይም ማጉደፍ ማለት ነው።
  • ለምሳሌ ቤተ መንግሥታቸው ውስጥ ለግብዣ በመጠቀም አረማውያን ነገሥታት ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የተወሰዱ የተለየ ክብር ያላቸው ዕቃዎችን አርክሰዋል ወይም አጉድፈዋል።
  • በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ የነበረውን መሠዊያ ለማርከስ ወይም ለማጉደፍ ጠላቶች የሞተ ሰው አጥንት ተጠቅመው ነበር።
  • ይህ ቃል፣ “ቅድስና መንፈግ” ወይም፣ “ክብር መንፈግ” ወይም “ማቆሸሽ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

ማሰላሰል

“ማሰላሰል” የሚለው ቃል ጊዜን ወስዶ ስለ አንድ ነገር በጥንፍቃቄና በጥልቀት ማሰብ ነው።

  • ብዙውን ጊዜ ቃሉ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጥቅም ላይ የዋለው ስለ እግዚአብሔርና ስለ ትምህርቱ ማሰብን ለማመልከት ነው።
  • መዝሙር 1 “ቀንና ሌሊት” የእግዚአብሔርን ሕግ የሚያሰላስል ሰው እጅግ እንደሚባረክ ይናገራል።

ማሳሳት፣ መሳት፣ ስሕተት፣ አሳሳች

“ማሳሳት” እውነት ያልሆነ ነገር እንዲታመን ማድረግ ነው። ሌሎችን የማሳሳት ተግባር “ማሳት” ይባላል።

  • “ስሕተት” የተሰኘው ሌላ ቃልም እንዲሁ እውነት ያለሆነ ነገር እንዲታመን ማድረግ ነው።
  • ሐሰትን እንዲያምኑ የሚያደርግ ሰው “አሳሳች” ነው። ለምሳሌ ሰይጣን፣ “አሳሳች” ተብሎ ተጠርቷል። እርሱ የሚቆጣጠራቸው ክፉ መናፍስትም አሳሳቾች ናቸው።
  • እውነተኛ ያልሆነ ሰው፣ ተግባር ወይም መልእክት፣ “አሳሳች” ተብሎ ሊጠራ ይችላል።
  • “ማሳት” እና፣ “ስሕተት” የተሰኙት ቃሎች ተመሳሳይ ትርጕም ቢኖራቸውም ጥቅም ላይ የሚውሉበትን መንገድ በተመለከተ መጠነኛ ልዩነት አላቸው።
  • “አሳሳች” እና “አሳች” የተሰኙት ገላጭ ቃሎች ተመሳሳይ ትርጕም አላቸው፤ በተመሳሳይ ዐውድ ጥቅም ላይ ይውላሉ።

ማሳደድ፣ ስደት

አንድን ሰው ማሳደድ ደጋግሞ ማጥቃት ወይም እርሱ ላይ የጭካኔ ተግባር መፈጸም ነው።

  • አንድን ሰው ብቻ፣ ትንንሽ ቡድኖችን ወይም ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎችን ማሳደድ ይቻላል።
  • እርሱ የሚያስተምረውን ባለ መቀበላቸው የአይሁድ ሃይማኖት መሪዎችና የሮም መንግሥት ክርስቲያኖችን አሳድደዋል። ይሁን እንጂ፣ አማኞች ስለ ኢየሱስ መስበካቸውንና ማስተማራቸውም አልተዉም፤ ቤተ ክርስቲያንም እያደገች ሄደች።
  • “ማሳደድን” ለመተርጎም ሌሎች ቃሎች፣ “መበደል” ወይም፣ “ማንገላታት” ወይም፣ መጨቆን” ወይም፣ “በጥላቻ መነሣት” የተሰኙት ናቸው።

ማስተማር፣ አስተማሪ

“ማስተማር” ከዚያ በፊት የማያውቁትን መረጃ ለሰዎች መናገርን ያመለክታል። ብዙውን ጊዜ መረጃው የሚሰጠው ወግ ባለው ወይም ስልታዊ በሆነ መንገድ ነው

  • አስተማሪ የሚያስተምር ሰው ነው
  • ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን ሰዎችን ስለ እግዚአብሔር የሚያስተምር ሰው በሚጠራበት የአክብሮት አጠራር፣ “መምህር” ይሉት ነበር
  • መምህሩ የሚሰጠው ቃል እንዳንዴ፣ “ማስተማር” የተሰኘው ቃል ትርጉም ሲሆን፣ ስለ እግዚአብሔር ተከታታይ ትምህርቶችን ማስተማርን ያመለክታል

ማስጠንቀቂያ/መሸበር

ማስጠቀቂያ የሚጎዳቸውን ነገር አስመልክቶ ሰዎችን ማሳሰብ ማስጠንቀቅ ማለት ነው።መሸበር አደገኛ ወይም ስጋት ያለውን ነገር በተመለከተ በጣም መጨነቅና መፍራት ማለት ነው።

  • ሞዓባውያን የይሁዳን መንግሥት ለማጥቃት እያቀዱ እንደ ነበር ሲሰማ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ በጣም ተሸበረ።
  • በመጨረሻው ቀን ጥፋት እየደረሰ መሆኑን ሲሰሙ መሸበር እንደሌለባቸው ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ተናገረ።
  • “የማስጠንቀቂያ ደወል” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ማስጠንቀቅ ማለት ነው። በጥንት ዘመን ሰዎች መለከት ወይም ደወል የመሳሰሉ ነገሮችን ድምጽ በማሰማት የማስጠንቀቂያ ያስተላልፉ ነበር። የማስጠንቀቂያ ድምጽ ማሰማት ለሰዎች ስለ አደጋ መናገር እነርሱም ሌሎችን እንዲያስጠነቅቁ፥ ማድረግንም ይጨምራል።

ማቅ

ማቅ ከፍየል ወይም ከግመል ጠጉር የሚሠራ ልብስ ነው። ይህ ዐይነቱ ልብስ ሻካራና የሚኮሰኩስ ነበር።

  • ብዙውን ጊዜ ማቅ የሚለበው ለቅሶን፣ ሐዘንንና መዋረድን ለማሳየት ነበር
  • ራስ ላይ ዐመድ መነስነስ ወይም ዐመድ ላይ መቀመጥም እንዲሁ የለቅሶና የውርደት ምልክት ነበር
  • “ማቅ ለብሶ፣ ዐመድ ነስንሶ” የሚለው ሐረግ የሐዘንና የንስሐ ባሕላዊ መገለጫን ያመለክታል

ማበረታታት

መበረታታት የሚለው የሚያመለክተው በቃልም ሆነ በተግባር ሌሎች እንዲጽናኑ፣ ተስፋ እንዲኖራቸው፣ ድፍረትና ጽናት እንዲኖራቸው ማድረግን ነው።

  • ተመሳሳዩ ቃል፣ “መምከር” የሚለው ሲሆን የተስሳተውን ነገር በመተው መልካምና ትክክል የሆነውን ነገር እንዲያደርጉ ሰዎችን ማደፋፈር የሚል ትርጕም አለው።
  • ሐዋርያው ጳውሎስና ሌሎች የአዲስ ኪዳን ሐዋርያት እርስ በርስ እንዲበረታቱና አንዳቸው ሌላውን በፍቅር እንዲያገለግሉ ክርስቲያኖችን አስተምረዋል።

ማበራየት፣ ማበጠር

“ማበራየት” እና፣ “ማበጠር” ለምግብ የሚሆነውን እህል ከማይፈልጉ ነገሮች መለየት ማለት ነው። ስሞችን መለየትን ወይም መክፈልን አስመልክቶ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁለቱም ቃሎች በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ውለዋል።

  • ማበራየት ነፋስ ገለባውን እንዲወስደው እህሉንና ገለባውን ወደ አየር በመበተን እህልን ከማይፈለገው ገለባ መለየት ማለት ነው።
  • “ማበጠር” የሚባለው ድንጋይን ጠጠርን የመሳሰሉ የማይፈለጉ ነገሮች ከእህሉ እንዲለዩ የተበራየውን እህል በወንፊት ማበጠር ማለት ነው።
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ ጻድቃንን ከኀጢአተኞች የሚለይ አስቸጋሪ ሁኔታን ለማመልከት፣ “መበራየት” እና፣ “ማበጠር” የተሰኙት ቃሎች ጥቅም ላይ ውለዋል።
  • እርሱንም ሆነ ሌሎች ደቀ መዛሙርት በእምነታቸው ፈተና እንደሚገጥማቸው ለማመልከት አንድ ጊዜ ኢየሱስ፣ “ማበጠር” በሚለው ቃል ተጠቅሞ ነበር።

ማባከን፣ ጠፍ ምድር

አንድን ነገር ማባከን በቸልታ መወርወር፣ ወይም ያለ አግባብ መጠቀም ማለት ነው። “የባከነ” የጠፋ ወይም ከጥቅም ውጪ የሆነ ነገርን ያመለክታል።

  • “ጠፍ ምድር” የተደመሰሰችና ማንም የማይኖርባት ከተማን የመሰለ ባዶነትን ያመለክታል።
  • ከተማን “ጠፍ ማድረግ” ጨርሶ መደምሰስ ማውደም ማለት ነው።

ማነሣሣት፣ መተንኮስ

“ማነሣሣት” ወይም፣ “መተንኮስ” አንድ ሰው አሉታዊ ምላሽ እንዲሰጥ ወይም አሉታዊ ስሜት እንዲያድርበት ማድረግ ማለት ነው።

  • አንድን ሰው ለቁጣ ማነሣሣት ያ ሰው እንዲቆጣ የሚያደርገውን ነገር መፈጸም ማለት ነው። ይህ ቃል፣ “ማስቆጣት” ወይም፣ “ማናደድ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
  • “አታነሣሡት” የሚለው፣ “አታስቆጡት” ወይም፣ “አታናድዱት” ወይም፣ “እንዲቆጣባችሁ አታድርጉ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

ማክበር

አንድ ሰው ወይም ነገር ምን ያህል ታላቅና አስፈላጊ መሆኑን ማሳየት ወይም መናገር ማለት ነው። ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “ክብር መስጠት” ማለት ነው።

  • እርሱ ስላደረገው ድንቅ በመናገር ሰዎች እግዚአብሔርን ማክበር ይችላሉ።
  • ለእርሱ ክብር በሚያስገኝ መንገድ በመኖርና እርሱ ምን ያህል ታላቅና ቸር መሆኑን በማሳየት እግዚአብሔርን ማክበርም ይችላሉ።
  • መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ራሱን አከበረ ሲል ብዙውን ጊዜ በተአምራቱ አማካይነት አስደናቂ ታላቁነቱን አሳየ ማለቱ ነው።
  • የወልድን ፍጹምነት፣ ውበትና ታላቅነት ለሰዎች በመግለጥ እግዚአብሔር አብ እግዚአብሔር ወልድን ያከብራል።
  • በክርስቶስ የሚያምን ሁሉ ከእርሱ ጋር ይከብራል። ከሞት በሚነሡበት ጊዜ ክብሩን እንዲያንጸባርቁና ለፍጥረት ሁሉ ጸጋውን ለማሳየት ይለወጣሉ።

ማወቅ፣ ዕውቀት፣ ማሳወቅ

“ማወቅ” አንድን ነገር መረዳት ወይም አንድን ሐቅ መገንዘብ ማለት ነው። “ማሳወቅ” አንድን መረጃን ለሌሎች መናገር ማለት ነው።

  • “ዕውቀት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሰዎች የተረዱትን ወይም የተገነዘብትን ነገር ነው። በመንፈሳዊውና በቁሳዊው ዓለም ያሉ ነገሮችን ማወቅንም ይመለክታል።
  • እርሱን ማወቅ እንዲችሉ እግዚአብሔር ለሰዎች እውነትን ገልጧል።
  • እርስ በርስ ከምንነጋገረውና ሌሎችን በተመለከተ ከሚኖረን ግንዛቤ የተነሣ ሰዎችን እናውቃለን።
  • በሚገባ በመመልከትና በማጥናት ሳይንስን፣ ሥነ ጥበብንና ሌሎች የሕይወት ገጽታዎችን በተመለከተ እውነትን እናውቃለን።
  • የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ ማለት እርሱ ያዘዘውን መገንዘብና አንድ ሰው ምን ማድረግ እንዳለበት እንደሚፈልግ መረዳት ነው።
  • “ሕጉን ማወቅ” እግዚአብሔር ያዘዘውን መገንዘብ ወይም እግዚአብሔር ለሙሴ በሰጠው ሕግ ምን እንዳስተማረ መረዳት ማለት ነው።
  • አንዳንዴ፣ “ዕውቀት” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ መንገድ መኖርንም ከሚጨምረው፣ “ጥበብ” ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ሆኖ ይነገራል
  • “የእግዚአብሔር ዕውቀት” አንዳንዴ፣ “የያህዌ ፍርሃት” ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ሆኖ ይነገራል።

ማወጅ፣ ዐዋጅ

“ማወጅ” እና “ዐዋጅ” የተሰኙት ቃሎች የሚያመለክቱት ሰው ሁሉ እንዲያውቀው ተፈልጎ በግልጽ በአደባባይ ለሕዝብ የሚነገር ሲሆን፣ እንዲህ የሚደረገው ለጉዳዩ አጽንዖት ለመስጠት ታስቦ ነው።

  • “ዐዋጅ” ለተነገረው አጽንዖት መስጠት ብቻ ሳይሆን፣ ዐዋጁን ለተናገረ ሰው ትኵረት ውስጥ ያስገባል።
  • ለምሳሌ በብሉይ ኪዳን ዘመን ብዙውን ጊዜ ከእግዚአብሔር የመጣ መልእክት፣ “የያህዌ ዐዋጅ” ወይም፣ “ያህዌ እንዲህ በማለት ያውጃል” የሚል መቅድመ ነገር ይሰጠው ነበር። ይህ አባባል እየተናገር ያለው ያህዌ ለመሆኑ አጽንዖት ይሰጣል። መልእክቱ የመጣው ከያህዌ መሆኑ ምን ያህል አስፈላጊ ወይም ጠቃሚ መሆኑን ያመለክታል።

ማወጅ፣ ዐዋጅ

አንድን ነገር በሕዝብ ፊት እና በድፍረት መናገር ወይም ማሳወቅ ማወጅ ይባላል።

  • ብዙውን ጊዜ መጸሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ማወጅ” የሚለው እግዚአብሔር ያዘዘውን በግልጽ መናገርና እርሱ ምንኛ ታላቅ መሆኑን ለሌሎች መናገር ነው።
  • ከአዲስ ኪዳን እንደምንመለከተው ሐዋርያት በተለያዩ ከተሞችና አካባቢዎች ላሉ ብዙ ሰዎች የኢየሱስን የምሥራች ቃል ተናግረዋል።
  • “ማወጅ” የሚለው ቃል ነገሥታት የሚያወጧቸውን ደንቦች ወይም ክፉ ነገርን በአደባባይ ማውገዝ ያመለክታል።
  • “ማወጅ” የሚለውን ለመተርጎም፣ “ማሳወቅ” ወይም፣ “በግልጽ መስበክ” ወይ፣ “በአደባባይ መናገር” በተሰኙ ቃሎች መጠቀም ይቻላል።
  • “ዐዋጅ” የሚለው ቃል፣ “ማስታወቂያ” ወይም፣ “ሕዝባዊ ስብከት” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

ማውደም፣ ውድመት

“ማወደም” ወይም፣ “ውድመት” የተባለው ቃል ንብረትን፣ ምድርን ወይም ሌላ ጠቃሚ ነገርን ጨርሶ ማጥፋትን ያመለክታል። ብዙውን ጊዜ በዚያ ምድር የሚኖሩ ሰዎችን መቆጣጠርን ወይም ጨርሶ ማጥፋትንም ይጨምራል።

  • ቃሉ የሚያመለክተው በከፍተኛ ደረጃ የተፈጸመ ጥፋትን ነው።
  • ለምሳሌ እዚያ ይኖሩ ከነበሩ ሰዎች ኀጢአት የተነሣ እግዚአብሔር የሰዶም ከተማን በማውደም ሕዝቡን ቀጣ።
  • “ውድመት” የተሰኘው ቃል ትጣትን ወይም ጥፋትን ተከትሎ የሚመጣ ታላቅ ሐዘንንም ይጨምራል።

ማውጣት፣ ማባረር

አንድ ነገር ወይም አንድን ሰው፣ “ማውጣት” ወይም፣ “ማባረር” ያ ነገር ወይም ሰው ከዚያ እንዲሄድ ማስገደድ ማለት ነው።

  • “ማውጣት” – “መወርወር፣ መጣል” ከተሰኘው ጋር ተመሳሳይ ነው። መረብ መጣል፣ መረቡን ባሕር ውስጥ መወርወር ማለት ነው።
  • ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ አንድን ሰው፣ “ማውጣት” ወይም፣ “ማባረር” ያ ሰው እዚያ እንዳይኖር መከልከል ወይም ማስገደድ ማለት ነው።

ማዳፈን

“ማዳፈን” የሚለው ቃል አንድ ነገር ማጥፋት ወይም መርካት የሚፈልግን ነገር ማስቆም ማለት ነው።

  • ብዙውን ጊዜ ቃሉ ጥቅም ላይ የሚውለው ጥምን ካለ ማርካት ጋር ተያይዞ ነው።
  • እሳት ማጥፋትን ለማመልከትም ይውላል።

ማድላት፣ አድልዎ

“ማድላት እና፣ “አድልዎ” የተሰኙ ቃሎች፣ አንዳንድ ሰዎችን ከሌሎች የበለጠ ማቅረብ ወይም ከሌሎች የተለየ ነገር ማድረግን ያመለክታል።

  • ይህ ከአድሎአዊነት ጋር ይመሳሰላል፤ አድሎአዊነት ሰዎች ሀብታም ወይም የተሳካላቸው ስለሆኑ ብቻ ለሌሎች የማናደርገውን ለእነርሱ ማድረግ ማለት ነው።
  • ሀብት ላላቸው ወይም ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ላሉ ሰዎች እንዳናደላ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል።
  • ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ እግዚአብሔር ያለ ምንም አድልዎ ለሰዎች በቅንነት እንደሚፈርድ ይናገራል።

ማገለገል፣ አገልግሎት

አንድን ሰው ማገለገል ለእርሱ የሚጠቅመውን ማድረግ ማለት ነው። አንድ ሰው ሌላውን የሚያገለግለው፣ ተገድዶ ወይም ማገልገል ስለፈለገ ብቻ ሊሆን ይችላል

  • “ማገልገል” - ለሌላው ሰው፣ “መታዘዝ” ወይም፣ ለእርሱ፣ “መሥራት” ማለት ነው
  • እግዚአብሔርን “ማገለገል” – “እግዚአብሔርን መምለክና ለእርሱ መታዘዝ” ወይም “እርሱ የሰጠውን ሥራ መፈጸም” ማለት ነው
  • “ማዕድ ማገልገል” ማዕድ ዙሪያ ለተቀመጡ ሰዎች ምግብ ማቅረብ ማለት ነው
  • ስለ እግዚአብሔር ለሌሎች የሚያስተምሩ ሰዎች ለእግዚአብሔርና ለሚያስተምሯቸው ሰዎች አገለጋዮች ናቸው

ማጎንበስ፣ ጎንበስ ማለት

ማጎንበስ ለአንድ ሰው ክብርን ለማሳየት በትሕትና ከወገብ እጥፍ ማለት ነው። “ጎንበስ ማለት” በጣም መታጠፍ ወይም በጣም ዝቅ ብሎ መንበርከክ ማለት ሲሆን፣ ብዙውን ጊዜ ግንባርንና እጆችን መሬት ላይ ማድረግንም ይጨምራል።

  • ሌሎች ገለጻዎች፣ “ጉልበትን ማጠፍ” (ማለት መንበርከክ)፣ “ራስን ዝቅ ማድረግ” (ማለት አክብሮትን ወይም ሐዘንን ለማሳየት ራስን በትሕትና ወደ ፊት ዘንበል ማለትን) ይጨምራል።
  • ጎንበስ ማለት የጭንቀት ወይም የሐዘን ምልክትም ይሆናል። በጣም “ጎንበስ ያለ” ሰው ወደ መጨረሻ የዝቅተኝነት ደረጃ ወርዷል ማለት ነው።
  • አንድ ሰው ነገሥታትንና ሌሎች መሪዎችን በመሳሰሉ ከፍ ያለ ደረጃ ወይም ከፍ ያለ ሥልጣን ባላቸው ሰዎች ፊት ሲቀርብ ብዙውን ጊዜ ጎንበስ ይላል።
  • በእግዚአብሔር ፊት ማጎንበስ እርሱን የማምለክ መገለጫ ነው።
  • ከተአምራቱና ከትምህርቱ የተነሣ እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣ መሆኑን ሰዎች ሲገነዘቡ ኢየሱስ ፊት ማጎንበሳቸውን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
  • መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን አንድ ቀን ኢየሱስ ሲመጣ ሰዎች ሁሉ እርሱን ለማምለክ ይንበረከካሉ።

ማጨድ፣ አጫጅ

ማጨድ እህልን የመሳሰሉ ነገሮች ማምረት ማለት ነው። እህል የሚያመርት ሰው አጫጅ ይባላል።

  • ምሳሌያዊ በሆነ አነጋገር እህል ማጨድ የኢየሱስን የምሥራች ለሰዎች መናገርና እነርሱን ወደ እግዚአብሔር ቤተ ሰብ ማምጣትን ያመለክታል።
  • “ሰው የዘራውን ያጭዳል” ከሚለው አባባል ማየት እንደሚቻለው የአንድን ሰው የሥራ ውጤትን ለማመልከትም ጥቅም ላይ ይውላል።

ማጽናት፣ ማረጋገጥ፣ ማጽኛ

“ማጽናት” የሚለው ቃል አንድ ነገር እውነት ወይም እርግጥ ወይም አስተማማኝ መሆኑን መናገር ወይም መመልከት ማለት ነው።

  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ ከእነርሱ ጋር የገባውን ኪዳን እንደሚያጸና እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይናገራል። ይህም ማለት ለእነርሱ የገባውን ቃል እንደሚጠብቅና እንደሚፈጽም መናገሩ ነው።
  • አንድ ሰው የጻፈውን ማጽናት እርሱ የጻፈው እውነት መሆኑን መቀበል ማለት ነው።
  • የእምነት “ማጽኛ” እውነት መሆኑን በሚያረጋግጥ መልኩ ለሰዎች የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ማስተማር ማለት ነው።
  • “በመሐላ ማጽናት” አንድ ነገር እውነተኛ አስተማማኝ መሆኑን ጠንከር አድርጎ መናገር ወይም መማል ማለት ነው።
  • ማጽናት የሚለውን የመተርጎም፣ “እውነት መሆኑን መናገር” ወይም፣ “አስተማማኝነቱን መግለጥ” ወይም፣ “ከዚያ ጋር መስማማት” ማለት ይቻላል። በዐውዱ መሠረትም፣ “ማረጋገጥ” ወይም፣ “ቃልን መስጠት” ማለት ይቻላል።

ማጽናናት፣ አጽናኝ

“ማጽናናት” እና “አጽናኝ” የተሰኙት ቃሎች አካላዊም ይሁን ጉዳት ያደረሰባቸው ሰዎች መርዳትን፣ አይዞአችሁ ባይነትን ነው የሚያመለክተው።

  • ሌሎችን የሚያጽናና ሰው፣ “አጽናኝ” ይባላል።
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ “አጽናኝ”እግዚአብሔር ለሕዝቡ ምን ያህል ቸር እና አፍቃሪ መሆኑና በመከራቸውም እንደሚረዳቸው ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል።
  • በመንፈስ ቅዱስ በኩል እግዚአብሔር ሕዝቡን እንዲያጽናና አዲስ ኪዳን ይናገራል። መጽናናትን የተቀበሉ መጽናናት መከራ ለደረሰባቸው ሌሎች ሰዎች ያንኑ መጽናናት መስጠት ይችላሉ።
  • “የእስራኤል አጽናኝ” የተሰኘው ገለጻ ሕዝቡን ለመታደግ የሚመጣውን መሲሕ ያመለክታል።
  • ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን፣ በእርሱ የሚያምኑት ሰዎችን የሚረዳ፣ “አጽናኝ” ብሎታል።

ማፌዝ፣ መቀለድ፣ መዘበት።

“ማፌዝ” “መቀለድና” እና፣ “መዘበት” የተባሉት ቃሎች ሁሉ የሚያመለክቱት በሚጎዳ መልኩ ሌሎችን መሳቂያ መሳለቂያ ማድረግን ነው።

  • ማፌዝ እነርሱን ለማሳፈር ወይም ንቀንትን ለማሳየት ሲባል የሰዎችን ቃልና እንቅስቃሴ አስመስሎ መነርና መንቀሳቀስንም ይጨምራል።
  • ቀይ ልብስ ሲያለብሱትና እንደ ንጉሥ እያከበሩት እንደ ሆነ ሲያስመስሉ የሮም ወታደሮች ኢየሱስ ላይ እየቀለዱ ነበር።
  • ከራሱ መላጣነት የተነሣ የተወሰኑ ወጣቶች ኤልሳዕ ላይ ቀልደውና አፊዘው ነበር።
  • “መዘበት” የሚታመን ወይም ጠቃሚ ተደርጎ በማይገመት ሐሳብ ላይ መቀለድና ማፌዝን ያመለክታል።

ምሕረት፣ ይቅርታ ማድረግ

“ምሕረት” ይቅር ማለትና ስል ተፈጸመው ኀጢአት አለመቀጣት ማለት ነው።

  • ምንም እንኳ እኛ ኀጢአተኞች ብንሆንም በሞቱ መሥዋዕትነት በኩል ኢየሱስ ክርስቶስ ለዘላለም በገሃነም እንዳንቀጣ ምሕረት አደረገለን።
  • በሕጉ መሠረት ባለ ሥልጣኖችም ለወንጀለኞች ምሕረት ማድረግ ይችላሉ።

ምሥጢር፣ የተደበቀ እውነት

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን፣ “ምሥጢር” የማይታወቅ ወይም ለመረዳት የሚያዳግት አሁን ግን እግዚአብሔር የገለጠውን ነገር ያመለክታል።

  • የክርስቶስ ወንጌል ባለፉት ዘመኖች ያልታወቀ ምሥጢር እንደ ነበር አዲስ ኪዳን ያመለክታል።
  • ምሥጢር ተብሎ ከተገለጠ ነገር አንዱ የአይሁድና የአሕዛብ በክርስቶስ አንድ መሆን ነበር።
  • ይህ ቃል፣ “የተሰወረ” ወይም፣ “የተደበቀ ነገር” ወይም፣ “ያልታወቀ ነገር” ተብሎ መተርጎም ይችላል።

ምርመራ፣ ፈተና

“ምርመራ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው፣ “ማጣራትን” ወይም፣ መፈተንን ነው። አንድ ሰው በደለኛ ወይም ንጹሕ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚደረግ የማጣራት ወይም፣ የምርመራ ተግባር ነው። ምርመራ ወይም ፈተና ለመቋቋም የሚያዳግት ሁኔታ ሲሆን፣ ለዚያ በሚሰጠው ምላሽ አንድ ሰው ለተፈለገው ነገር ተገቢ ሊሆን ወይም ላይሆንን ይችላል።

  • አንድ ሰው በደል መፈጸም አለመፈጸሙን ለማረጋገጥ ፍርድ ቤት ውስጥ የክሱን ጭብጥ መስማት ምርመራ ወይም ፍተና ይባላል። ለዚህ የሚሆኑ ሌሎች ቃሎች፣ “ማጣራት” ወይም፣ “ማመዛዘን” የተሰኙት ሊሆኑ ይችላሉ።
  • በእግዚአብሔር በማመን መዝለቅ አለመዝለቃቸውን ለማረጋገጥ ብዙዎች መፈተናቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ እንመለከታለን። በተለያየ ምርመራ ወይም ፈተና ውስጥ ማለፋቸው ድብደባን፣ እስራትን ሌላው ቀርቶ ለእምነታቸው መሞትን እንኳ ያካተተ ነበር።

ምርኩዝ(በትር)

ምርኩዝ ሰዎች ሲራመዱ የሚጠቀሙበት ከእንጨት ወይም ከብረት የተሠራ ከዘራ ወይም በትር ነው

  • ያዕቆብ ባረጀ ጊዜ ለመራመድ የሚረዳው ምርኩዝ ይይዝ ነበር
  • ኅይሉን ለፈርዖን ለማሳየት እግዚአብሔር የሙሴን በትር እባብ አደረገ
  • በጎቻቸውን ለመምራት ወይም ሲወድቁ ለማንሣትና ርቀው ሲሄዱ ለመመለስ እረኞች በምርኩዝ ይጠቀማሉ። ምርኩዝ ጫፉ ቆልመም ያለ በመሆኑ ቀጥ ካለውና በጎቹን ለማጥቃት የሚመጣ አውሬ ከሚያባርርበት የእረኛ በትር የተለየ ነው

ምርኮ፣ ምርኮኛ

“ምርኮ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ከአገራቸው ርቀው ሌላ ቦታ እንዲኖሩ የተገደዱ ሰዎችን ያመለክታል።

  • ብዙ ጊዜ ሰዎች ለቅጣት ወይም በፖለቲካ ምክንያት ከአገር ውጪ እንዲኖሩ ይገደዳሉ።
  • በጦርነት የተሸነፉ ሰዎች ለእርሱ እንዲሠሩ ተብሎ አሸናፊው ሰራዊት አገር ውስጥ እንዲኖሩ ይወሰዳሉ።
  • የባቢሎን ምርኮ የሚባለው ብዙ የአይሁድ ዜጎች ከአገራቸው ተወስደው በባቢሎን እንዲኖሩ የተገደዱበት የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ነው።
  • “ምርኮኛ” የሚለው ቃል ከአገር ከወገናቸው ርቀው በባዕድ ምድር የሚኖሩ ሰዎችን ያመለክታል።

ምርኮኛ፣ ምርኮ

“ምርኮና” እና፣ “ምርኮ” የተሰኙ ቃሎች መኖር በማይፈልጉበት የባዕድ አገር እንዲኖሩ ሰዎችን መያዝ ወይም ማስገደድን ያመለክታሉ።

  • ከይሁዳ መንግሥት የነበሩ እስራኤላውያን ለ70 ዓመት የባቢሎን መንግሥት ምርኮኞች ሆነው ነበር።
  • ዳንኤልና ነህምያ ለባቢሎን ንጉሥ ይሠሩ የነበሩ እስራኤላዊ ምርኮኞች ነበሩ።
  • “ምርኮኛ መሆን” የተሰኘው ፈሊጣዊ አነጋገር ሌላውን ወገን መያዝን የሚያመልክት ሌላ አባባል ነው።
  • “ምርኮኛ ትሆናላችሁ” የሚለው አባባል፣ “እንደ ምርኮኛ ለመኖር ትገደዳላችሁ” ወይም፣ “እስረኞች ሆናችሁ ወደ ሌላ አገር ትወሰዳላችሁ” ተብሎ መተርጎም ይችላል።
  • ሐዋርያው ጳውሎስ ማንኛውንም ዐሳብ፣ “መማረክና” ለክርስቶስ እንዲታዘዝ ማድረግ እንዳለባቸው በምሳሌያዊ መልኩ ለክርስቲያኖች ይናገራል፥
  • አንድ ሰው የኃጢአት ምርኮኛ መሆን ስለሚችልበት ሁኔታም ይናገራል፤ ይህም ኃጢአት፣ “ይቆጣጠረዋል” ማለት ነው።

ምሳሌ

ምሳሌ ጥበብ ወይም እውነት የያዘ አጭር ዐረፍተ ነገር ነው።

  • በቀላሉ ለማስታወስና ለመድገም የሚቻሉ በመሆናቸው ምሳሌዎች ብርቱ ዐቅም አላቸው።
  • ብዙ ጊዜ ምሳሌ በዕለታዊ ሕይወት የሚገጥሙ ነገሮችን ያካትታል።
  • አንዳድን ምሳሌዎች ግልጽና ቀጥተኛ ሲሆኑ፣ ሌሎች ግን ለመረዳት የማዳግቱ ናቸው።
  • ንጉሥ ሰሎሞን በጥበቡ ይታወቃል፤ ከ1000 በላይ ምሳሌዎች ጽፏል።
  • ኢየሱስ ሲያስተምር ብዙ ጊዜ በምሳሌዎች ይጠቀም ነበር።
  • “ምሳሌ” የሚለውን ቃል ለመተርጎም ሌላው መንገድ፣ “የጥበብ ንግግር” የሚለው ሊሆን ይችላል።

ምስል፥ የተቀረጸ ምስል፥ የተቀረጸ ቅርጽ፥ በብረት የተሠራ ምስል

እነዚህ ቃላት በጠቅላላ ሀሰተኛን አምላክ ለማምለክ የተቀረጹን ጣኦታትን ለማመልከት የምንጠቀምባቸው ናቸው።


ምስክር፣ የዓይን ምስክር

“ምስክር” የሆነውን ነገር በግል የሚያውቅ ማለት ነው። ብዙውን ጊዜ ምስክር የሚባለው እውነት መሆኑን የሚያውቀውን የሚናገር ሰው ነው። “የዓይን ምስክር” እዚያ የነበረና የሆነውን ሁሉ በዓይኑ የተመለክተ ሰው ነው።

  • አንድን ነገር፣ “መመስከር” የሆነውን ነገር ማየት ማለት ነው።
  • ምስክር፣ ፍርድ ቤት ቀርቦ ሲሆን ያየውን ወይም የሰማውን ይመሰክራል።
  • ምስክሮች ስላዩትና ስለሰሙት እውነቱን መናገር ይጠበቅባቸዋል
  • እውነቱን የማይናገር ምስክር፣ “የሐሰት ምስርክ” ይባላል።
  • “በመካከላችን ይመስክር” ማለት በመካከላችን ስለ ተደረገው ውል ማስረጃ ይሁን ማለት ነው። ምስክሮች እያንዳንዱ ሰው የሚገባውን እያደረገ መሆኑን ያረጋግጣሉ።

ምስጋና

አንድ ሰው ማመስገን ለዚያ ሰው ያለንን አድናቆትና ክብር መግለጥ ማለት ነው።

  • እርሱ እጅግ ታላቅ በምሆኑና እንደ ዓለም ፈጣሪና አዳኝ ካደረጋቸው አስደናቂ ነገሮች የተነሣ ሰዎች እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ።
  • እግዚአብሔርን ማመስገን ስላደረገው ነገር እርሱን መወደስንም ይጨምራል።
  • ሙዚቃና ዝማሬ እግዚአብሔር ምስጋና የምናቀርብባቸው ናቸው። እግዚአብሔርን፣ “ማመስገን” ብዙውን ጊዜ እርሱን የማምለክ አካል ናቸው።

ምሽግ፣ መከላከያ፣ የተመሸገ

“ምሽግ” ወይም፣ “መከላከያ” የጠላት ወታደሮችን ጥቃት መከለከል እንዲቻል በሚገባ የታጠረ ወይም ከለላ ያለው ቦት ማለት ነው። “የተመሸገ” ከተባለ አንድን ከተማ ወይም ምሽግ ለመከላከል በጠንካራ ግንቦች ዐለቶችና ሌሎች ጠንካራ ነገሮች ማጠርን ያመለክታል

  • ጠንካራ ሕንፃዎች፣ መከላከያ አጥሮች ወይም ዐለታማ ገደሎችን የመሳሰሉ የተፈጥሮ መከላከያዎች ወይም ትልልቅ ተራሮች ምሽግ ወይም መከለከያ ሊሆኑ ይችላሉ
  • በምሳሌያዊ መልኩ፣ “ምሽግ” ሐሰተኛ አማልክትን የመሳሰሉ አንድ ሰው በስሕተት የሚታመንባቸው ነገሮች ማለት ነው
  • “የተመሸገ” የሚለው፣ “በሚገባ የተከለለ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል
  • “ምሽግ” ወይም፣ “መከላከያ” – “ጥበቃ የሚደረግለት ቦታ” ወይም፣ “ጠንካራ መከላከያ ያለው ቦታ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል

ምንጭ

ምንጭ በተፈጥሮው ከመሬት የሚፈልቅ ወይም የሌላ ዓይነት ወራጅ ውሃ መነሻ ቦታ ነው።

  • ይህ ቃል እግዚአብሔር የበረከት ምንጭ መሆኑን ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።
  • በዝመናችንም ለመጠጥ የሚሆን ውሃ የሚገኝባቸው ሰው ሠራሽ ጉድጓዶች ስላሉ በተፈጥሮ የተገኘውን ወራጅ ውሃ በሚያመለክት ቃል ወይም ሐረግ መጠቀሙ የተሻለ ይሆናል።
  • ዘካርያስ 13፡1፣ “በዚያን ቀን የዳዊትን ቤትና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች ከኃጢአትና ከርኵሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል” ይላል።
  • ማርቆስ 5፡29 ደም ደም ይፈስሳት ስለ ነበረችው ሴት ሲናገር፣ “የሚፈስሰው ደሟ (ምንጭ) ወዲያውኑ ቀመ” ይላል።

ምክር፣ መካሪ፣ አማካሪ

ምክር ማለት አንድ ሰው ማስተዋል ያለበት ውሳኔ እንዲያደርግ ተገቢውን ሐሳብ መስጠት ማለት ነው። መልካም “መካሪ” ወይም፣ “አማካሪ” ሰዎች ትክክልኛ ምርጫ ማድረግ እንዲችሉ አስፈላጊ ሐሳብ ይሰጣል።

  • ብዙ ጊዜ ነገሥታት የሕዝቡን ሕይወት የሚነኩ አስፈላጊ ነገሮችን በተመለከተ ትክክለኛ ውሳኔ እንዲያደርጉ የሚረዷቸው አማካሪዎች ነበሯቸው።
  • አንዳንድ የሚሰጠው ምክር መልካም ላይሆን ይችላል። ተገቢ ያልሀነ አንድ ርምጃ እንዲወሰድ ወይም ራሱንና ሕዝቡን የሚጎዳ ዐዋጅ እንዲያወጣ ክፉ መካሪዎች ንጉሡን ያሳስታሉ።
  • እንደ ዐውዱ ሁኔታ፣ “ምክር” ወይም “መካሪ” የተሰኙ ቃሎች፣ “ውሳኔ ለማድረግ የሚጠቅም ሐሳብ” ወይም፣ “ጠቃሚ አስተያየት” ተብሎ መተርጎም ይችላል።

ምድር፣ ምድራዊ

“ምድር” ሕይወት ያላቸው ሌሎች ነገሮችን ጨምሮ የሰው ልጆች የሚኖሩበትን ዓለም ያመለክታል።

  • ምድር ሲባል መሬትን ወይም አፈርን ሊያመለክት ይችላል።
  • ምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎችን ለማመልከት ይህ ቃል በምሳሌያዊ መንገድ ጥቅም ላይ ይውላል።
  • “ምድር ሆይ፣ ደስ ይበልሽ” እና፣ “ምድርንም ይገዛል” የተሰኙ አገላለጾች ይህ ቃል ጥቅም ላይ ከሚውልባቸው ምሳሌዎች ጥቂቱ ናቸው።

ምድጃ

ምድጃ መንደድ ያለበት ነገር የሚቀጣጠልበትና የሚነድበት ትልቅ ማንደጃ ነው።

  • በጥንት ዘመን አብዛኞቹ ምድጃዎች ጥቅም ላይ ይውሉ የነበረው ብረት ነክ ነገሮችን ለማቅለጥ ማብሰያ ድስቶችን፣ ጌጣጌጦችንና ጣዖቶችን የመሳሰሉ ነገሮችን ለመሥራት ነበር።
  • የሸክላ ውጤቶችን ለመሥራትም ምድጃዎች ይጠቅማሉ።
  • በታም የሞቀና የጋለ ነገርን ለማመልከትም ምድጃ እንደ ምሳሌ ያገለግላል።

ምጽዋት

“ምጽዋት” የሚለው ቃል ድኾችን ለመርዳት የሚሰጥ ገንዘብን፣ምግብን ወይም ሌሎች ነገሮችን ያመለክታል።

  • መጽዋት መስጠት ብዙውን ግዜ ጻድቅ ለመሆን ሃይማኖታቸው የሚጠይቀውን ነገር እንደ ማድረግ ይቆጠራል።
  • የሌሎችን ትኩረት ለመሳብ ሲባል ምጽዋት በሰዎች ፊት ምስጠት እንደሌለበት ኢየሱስ ተናግሮአል።
  • ይህ ቃል”ገንዘብ” ወይም “ለድኾች የሚሰጥ ስጦታ” ወይም “ድኾችን መርጃ ” ተብሎ መተርጎም ይቻላል።

ሞት፣ መሞት፣ ሞተ

እነዚህ ቃሎች አካላዊንም ሆነ መንፈሳዊ ሞትን ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላሉ። አካላዊ በሆነ መልኩ የሰውየው አካል መሥራትን ማቆሙን ያመለክታል። በመንፈሳዊ አንጋገር በኀጢአታቸው ምክንያት ሰዎች ከቅዱሱ እግዚአብሔር መለየታቸውን ያመለክታል።


ሟርት፣ ሟርተኛ፣ ሟርተኝነት

ሟርት እና ሟርተኛ የሚለው ቃል ልዕለ ተፈጥሮአዊ ከሆነው የመናፍስት ዓለም መረጃ ለማግኘት የሚደረግ መከራን ያመለክታል። ይህን የሚለማመድ ሟርተኛ ይባላል።

  • ሞራ ገላጭ፣ ጠጠር ጣይ፣ የዛር ወይም የውቃቢ አምልኮ ልምምድ ሁሉ ሟርተኝነት ነው።
  • ለእስራኤል ልጆች በሰጠው ትእዛዝ ምንም ዓይነት ሟርተኝነት ወይም ሟርት ተግባር እንዳይሳተፉ እግዚአብሔር ነግሮአቸው ነበር።
  • ሕዝቡ ከኡሪምና ከቱሚም መመሪያ እንዲቀበሉ እግዚአብሔር ፈቅዷል፤ ኡሪምና ቱሚም የከበሩ ድንጋዮች ሲሆኑ ለዚህ ዓላማ ሊቀ ካህኑ ይጠቀምባቸው ነበር። ከክፉ መናፍስት ማንኛውንም ዐይነት መመሪያ እንዲቀበሉ እግዚአብሔር ለሕዝቡ አልፈቀደም።
  • ጥንቆላ፣ መተትና አስማት እንዲሁም ድግምት የክፉ መንፈስ ተግባር ናቸው፤ እነዚህን ነገሮ ችንስዳንለማመድ እግዚአብሔር አዝዞአል።

ሟርት፣ ጥንቆላ

“ሟርት” ወይም “ጥንቆላ” አስማት በመጠቀም በክፉ መናፍስት ርዳታ አስደናቂ ነገሮችን ማድረግን ያመለክታል። በእነዚህ አስማታዊ ኅይሎች አስደናቂ ነገሮች የሚያደርገው ሰው ሟርተኛ ይባላል

  • ሰዎች አስማታዊ ኅይልና ሟርት በመጠቀም በሽተኛን መፈወስ፣ ሌላው ላይ ጉዳት እንዲደርስ ማድረግ ይችላሉ። ያም ሆኖ ግን፣ በክፉ መናፍስት ኅይል ስለሚጠቀም ማንኛውም የጥንቆላ ወይም የሟርት ዓይነት የተከለከለ ነው
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጥንቆላና ሟርት እንደ ዝሙት፥ ጣዖት ማምለክና ስርቆት ሁሉ ኅጢአት መሆኑን እግዚአብሔር ተናግሯል
  • “ጥንቆላ” እና፣ “ሟርት” የሚለውን፣ “የክፉ መናፍስት ኅይል” ወይም፣ “ሰይጣናዊ አሠራር” ፣ “የአስማት ሥራ” በማለት መተርጎም ይቻላል
  • “ሟርተኛ” የሚለው ቃል፣ “አስማት የሚሠራ” ወይም፣ “ደጋሚ” ወይም፣ “በክፉ መናፍስት ኅይል ተአምር የሚሠራ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል

ሥራ፣ ሠራተኛ

ማንኛውም ጉልበትን የሚጠቅይ ከባድ ልፋት ሥራ ይባላል።

  • ሥራ ጉልበት የሚያስፈልገው ማንኛውም ልፋት ሲሆን ብዙውን ጊዜ ከባድ ልፋት ያለበት መሆኑንም ያመለክታል።
  • ሠራተኛ በማንኛውም ዐይነት ተግባር የሚሳተፍ ሰው ነው።

ሥርዓት

ሥርዓት ሰዎች የሚኖሩበት መመሪያ የሚሆን በውል ጽሑፍ ላይ የሰፈረ ሕግ ነው

  • “ሥርዓት” የሚለው ቃል፣ “ደንብ” ወይም፣ “ትእዛዝ” ወይም፣ “ሕግ” ወይም፣ “ዐዋጅ” ከተሰኙት ጋር የሚመሳሰል ትርጉም አለው። እነዚህ ሁሉ እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሰጠውን መመሪያና ግዴታዎች ይጨምራሉ
  • ንጉሥ ዳዊት በያህዌ ሥርዓት ደስ እንደሚሰኝ ተናግሯል
  • “ሥርዓት” የሚለው ቃል፣ “የተለይ ትእዛዝ” ወይም፣ “ልዩ ትእዛዝ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል

ሩጫ፣ መሮጥ

ሩጫ፣ መሮጥ ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “ሩጫ” ከመራመድ ባለፈ በፍጥነት መንቀሳቀስ ማለት ነው

  • “ሽልማት እንደሚያገኝ ሰው መሮጥ” የሚለው ሐረግ፣ ሩጫ መሮጥን ከክርስትና ሕይወት ጽናት ጋር ያመሳስለዋል
  • “በትእዛዛትህ ሮጥሁ” በደስታና በሙሉ ልብ ለእግዚአብሔር ትእዛዞች መገዛት ማለት ነው
  • “ከሌሎች አማልክት ኋላ መሮጥ” - ሌሎች አማልክትን በማምለክ መጽናት ማለት ነው
  • “ወደአንተ እሮጣለሁ፤ አንተ ሰውረኝ” - መጠጊያና መሸሸጊያ ፍለጋ ቶሎ ወደ እግዚአብሔር መሄድ ማለት ነው

ራስ

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ራስ” በርካታ ምሳሌያዊ ትርጕሞች አሉት።

  • ብዙውን ጊዜ ይህ ቃል ሰዎች ላይ ባለ ሥልጣን መሆንን ያመለክታል፤ ለምሳሌ፣ “በሕዝቦች ላይ ራስ አደረግኸኝ” እንደሚለው ይህ፣ “የሕዝቦች መሪ አደረግኸኝ” ወይም፣ “ሥልጣን ሰጠኸኝ” ተብሎ መተርጎም ይችላል።
  • ኢየሱስ፣ “የቤተ ክርስቲያን ራስ” ተብሏል። የሰው ራስ የሰውነት ብልቶቹን እንደሚምራና አቅጣጫ እንደሚያስይዝ ሁሉ ኢየሱስም “የአካሉን” ማለትም የቤተ ክርስቲያን ብልቶች (አባሎች) ይመራል፤ አቅጣጫ ያስይዛል።
  • ባል የሚስቱ ራስ ወይም ባለ ሥልጣን መሆኑን አዲስ ኪዳን ያስተምራል። ሚስቱንና ቤተሰቡ የመምራትና አቅጣጫ የማስያዝ ኀላፊነት ተሰጥቶታል።
  • “በራሱ ላይ ምላጭ አያልፍም” የሚለው አገላለጽ፣ “ጠጉሩ አይቆረጥም ወይም አይላጭም” ማለት ነው።
  • “ራስ” የአንድን ነገር ጅማሬ ወይም ምንጭ ሊያመለክትም ይችላል፤ ለምሳሌ፣ “የመንገዱ ራስ” እንደሚለው።
  • ሰውየውን ሽማግሌ ነው ለማለት የሰውየው “ራሱ ግራጫ ነው” ሲባል ራሱን ብቻ ሳይሆን ሙሉውን ሰው ይወክላል፤ “የዮሴፍ ራስ” ዮሴፍን ያመለክታል።
  • “ደማቸው በራሱ ላይ ይሁን” ሲባል ለእነርሱ ሞት ኀላፊነቱን ይወስዳል፤ በዚያም ምክንያት ይቀጣል ማለት ነው።

ራስን መግዛት

ራስን መግዛት ኅጢአትን ላለማድረግ የራስን ፀባይና ሁለንተና የመቆጣጠር ችሎታ ማለት ነው

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ራስን መግዛት መልካም ጸባይ ማለትም ተገቢ ያልሆነ ሐሳብን፣ ንግግርንና ድርጊት ማስወገድ ማለት ነው
  • ራስን የመግዛት ችሎታ ያለው ሰው አንድ መጥፎ የማድረግ ሐሳብ ሲመጣበት ያንን እንዳያደርግ ራሱን መግታት ይችላል
  • ራስን መግዛት አንድን ክርስቲያን የሚያስችል የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ወይም ባሕርይ ነው

ራእይ

“ራእይ” የሚለው ቃል አንድ ሰው የሚያየውን ያመለክታል። በተለይ ደግሞ የሚያመለክተው መልእክት ለመስጠት ባልተለመደ ወይም ልዕለ ተፈጥሮአዊ መንገድ እግዚአብሔር ለሰዎች የሚያሳየውን ያመለክታል።

  • ብዙውን ጊዜ ራእይ የሚታየው ሳይተኙ ወይም ሳያንቀላፉ ነው። አንዳንዴ ግን ሰውየው ተኝቶ እያለ የሚያየው ሕልምም ራእይ ይባላል።
  • እግዚአብሔር ለሰዎች ራእይ የሚያሳየው በጣም አስፈላጊ ነገር ሊነግራቸው ነው። ለምሳሌ ጴጥሮስ አሕዛብን በሙሉ ልቡ መቀበል እንዳለበት ለመናገር እግዚአብሔር ራእይ አሳይቶት ነበር።

ርግብ፣ ዋኖስ

ርግብና ዋኖስ በጣም የሚመሳሰሉ የተለያየ መልክ ያላቸው ትናንሽ ወፎች ናቸው። ርግብ በምጠኑ ፈካ ያለች ስትሆን ወደ ነጭነት ትጠጋለች።

  • በአንድ ቋንቋዎች ሁለት የተለያዩ ስሞች ሲኖሯቸው፣ ሌሎች ግን ሁለቱንም በአንድ ስም ይጠሯቸዋል።
  • ርግብና ዋኖስ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ይቀርቡ ነበር፤ በተለይም ትልቅ እንስሳ መሥዋዕት ለማቅረብ ዐቅማቸው የማይፈቅድ ሰዎች እነዚህን ወፎች ነበር የሚያቀርቡት።
  • ርግብ ጎርፍ ሲጎድል የወይራ ቅጠል ይዛ ወደ ኖኅ መጣች።
  • ርግቦች ንጽሕናን፣ ጨዋነትንና ሰላምን ይወክላሉ።
  • ትርጕም በሚሠራበት ቋንቋ ርግብና ዋኖስ የማይታወቁ ከሆነ፣ “ርግብ ተብሎ የምትጠራ ትንሽ ወፍ” ወይም፣ “. . . የምትመስል (ያገሩን ወፍ) ትንሽ ወፍ” ብሎ መተርጎም ይቻላል።

ሮማን

ሮማን በሚበላ ቀይ ነገር የተሸፈኑ ብዙ ፍሬዎች ያሉት ጥብቅና ጠንካራን ሽፋን ያለው የፍራፍሬ ዐይነት ነው።

  • የውጪ ቅርፊት መልኩ ቀይማ ሲሆን፣ ዘሮቹን የሚሸፍነው ውስጠኛው ክፍል ቀይና ብልጭልጭ ነው።
  • ሮማን ሞቃትና ደረቅ የአየር ፀባይ ባላቸው በግብፅና ሌሎች አገሮች በጣም በብዛት ይበቅላል።

ሰላም፣ ሰላማዊ

ሰላም ምንም ዓይነት ግጭት ወይም ስጋት አለመኖር ማለት ነው።

  • ሰላም በስዎች መካከል ጦርነት ወይም ፀብ አለመኖርን ያመለክታል።
  • ከሰዎች ጋር ሰላም ማድረግ ከእነርሱ ጋር ውጊያ ወይም ግጭት እንዳይኖር ማድረግ ነው።
  • ሰላም በሰዎችና በሰዎች መካከል፣ በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል መልካም ግንኙነት መኖሩንም ያመለክታል።
  • የግል ሰላም ስጋት ወይም ፍርሃት የሌለበት የተረጋጋ አእምሮ መኖርን ያመለክታል።

ሰረገላ

በጥንት ዘመን ሰረገሎች በፈረሶች የሚጎተቱ ቀለል ያለ ክብደት ያላቸው ባለ ሁለት ተሽከርካሪ (ጎማ) መጓጓዣ ነበሩ።

  • ሰዎች ሰረገሎቹ ላይ በመቀመጥ ወይም በመቆም ሰዎች ለጦርነት ወይም ለመጓጓዣ ይጠቀሙባቸው ነበር።
  • በጦርነት ጊዜ ሰረገሎች ያሉት ሰራዊት በፍጥነትና በቀላሉ ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ ሰረገሎች በሌሉት ሰራዊት ላይ የበላይነት ይኖራቸው ነበር።
  • የጥንት ግብፃውያንና ሮማውያን በፈረሶችና በሰረገሎች በመጠቀም ይታወቁ ነበር።

ሰኮና

ሰኮና ግመልን፣ ላምና በሬን፣ ፈረሶችን፣ አህዮችን፣ በጎችና ፍየሎችን የመሳሰሉ አንዳንድ እንስሳት ታችኛውን የእግራቸውን ክፍል የሚሸፍን ጠንካራ ነገር ነው።

  • ሰኮና በምራመዱበት ጊዜ ለእንስሳቱ እግር ይከላከላል።
  • ሰኮናቸው የተከፈለና የሚያመስኩ እንስሳት ለመብላት ንጹሕ መሆናቸን እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ተናግሮአል።

ሰዓት

አንድ ነገር የተፈጸመው ምቼና እንዴት እንደ ነበር ከማመልከት በተጨማሪ፣ “ሰዓት” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለቻቸው በርካታ ምሳሌያዊ መንገዶች አሉ።

  • አንድ ጊዜ፣ “ሰዓት” አንድ ነገር የሚደረግበትን መደበኛ ጊዜ ያመለክታል፤ ለምሳሌ፣ “የጸሎት ሰዓት” እንደሚለው።
  • ኢየሱስ መከራ የሚቀበልበትንና የሚሞትበትን ጊዜ አስመልክቶ፣ ምንባቡ “ሰዓቱ ደርሷል” ሲል እንደዚያ እንደሚሆን እግዚአብሔር ከብዙ ዘከን አስቀድሞ የወሰነው ትክክለኛ ጊዜ መጣ ማለት ነው።
  • “ሰዓት” የሚለው ቃል፣ “በዚያ ጊዜ” ወይም፣ “ያኔውኑ” ለማለትም ጥቅም ላይ ይውላል።
  • ምንባቡ፣ “ሰዓቱ” ዘገዬ ሲል ፀሐይ ወዲያውኑ የምትጠልቅበት የቀኑ የመጨረሻ ክፍል ማለት ነው።

ሰይፍ

ሰይፍ ለመቁረጥ ወይም ለመውጋት የሚያገለግል ጠፍጣፋ ስለት ያለ የጦር መሣሪያ ነው መያዣና ረጅም፣ ሾጠጥ ያለና ጫፉ ላይ ስለት አለው

  • በጥንት ዘመን የአንድ ሰይፍ ከ60 እስከ 91 ሳንቲ ሜትር ርዝመት ነበረው
  • አንዳንዱ ሰይፍ በሁለት ወገን ስለት ያለው በመሆኑ፣ “በሁለት በኩል የተሳለ” ተብሎ ይጠራል
  • የኢየሱስ ደቀመዛሙርት ራሳችንን መከላከያ ይሆነናል ብለው ያሰቡት ሰይፍ ነበራቸው። ጴጥሮስ የሊቀ ካህናቱን ባርያ ጆሮ በሰይፍ ቆርጦ ነበር
  • መጥምቁ ዮሐንስና ሐዋርያው ያዕቆብ ራሶቻቸው በሰይፍ ተቆርጠው ተገድለዋል

ሳንደል

ሳንደል ከእግር ታችኛው ክፍልና ከቁርጭምጭሚት ጋር በክር የሚታሰር ሰለል ያለ ጫማ ነው። ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ይጠቀሙበት ነበር

  • ሳንደል ንብረት መሸጥን የመሳሰሉ ሕጋዊ ውሎችን ለማጽናት ጥቅም ላይ ይውል ነበር። (ሩት 4፥7)፣ እንዲህ በሚሆንበት ጊዜ አንደኛው ወገን ሳንደሉን በማውለቅ ለሌላው ወገን ይሰጠው ነበር
  • ጫማን ወይም ሳንደልን ማውለቅ በተለይ በእግዚአብሔር ፊት ከሆነ የአክብሮትና የመገዛት ምልክት ነው
  • ዮሐንስ የኢየሱስን ጫማ ክር ለመፍታት እንኳ ብቁ እንዳልሆነ ተናግሮአል፤ በዚያ ዘመን ይህን ማድረግ በጣም ዝቅ ያለ አገልጋይ ወይም ባርያ ሥራ ነበር

ሴላ

ሴላ ብዙውን ጊዜ መዝሙር መጽሐፍ ውስጥ የሚገኝ የዕብራይስጥ ቃል ነው በርካታ ትርጉሞች ይኖሩት ይሆናል

  • ጉባኤው የተነገረውን ረጋ ብሎ እንዲያስብ ጥሪ ለማቅረብ የታሰበ፣ “ረጋ በል፤ አመስግን” ማለት ሊሆን ይችላል
  • መዝሙሮቹ የተጻፉት በጉባኤ እንዲዘመሩ በመሆኑ ዘማሪው ዝም እንዲልና የሙዚቃ መሣሪያው ብቻ እንዲጫወት ወይም አዳማጮቹ የመዝሙሩን ቃሎች በሚገባ እንዲያስቡ የሚያመለክት ሙዚቃዊ ቋንቋ ሊሆን ይችላል

ስቃይ

‘’ስቃይ” የሚለው ቃል ከባድ ህመምን ወይም ጭንቀትን ያመለክታል።

  • ስቃይ ሲባል አካላዊ ወይም ስሜታዊ ሕመም ወይም ጭንቀት ሊሆን ይችላል፤
  • ብዙውን ጊዜ ከባድ ስቃይ ወስጥ ያሉ ሰወች ያንን ራ ሁኔታቻው ላይ ያሳዩታል፤
  • ለምሳል ከባድ ሕመም ወይም ስቃይ ውስጥ ያለ ሰው ጥርሱን ይነክስ ወይም ይጮህ ይሆናል።
  • “ስቃይ” የሚለው ቃል ስሜታዊ ጭንቀት ወይም “ጥልቅ ሃዘን”ወይም ጽኑ ህመም ተብሎ መተርጎም ይቻላል።

ስቃይ

“ስቃይ” የሚያመለክተው ከፍተኛ መከራን ነው። አንድን ሰው ማሰቃየት ብዙውን ጊዜ በጭካኔ ከባድ መከራ እንዲደርስበት ማድረግ ነው።

  • አንዳንዴ፣ “ስቃይ” አካላዊ ሕመምና መከራን ያመለክታል። ለምሳሌ፣ የዮሐንስ ራእይ አውሬውን በሚያመልኩ ሰዎች ላይ በመጨረሻው ዘመን ስለሚደርሰው ስቃይ ይገልጻል።
  • መከራ ኢዮብ ላይ እንደ ደረሰው መንፈሳዊና ስሜታዊ ይዘት ሊኖረውም ይችላል።
  • የዮሐንስ ራእይ እንደሚነግረን እንደ አዳኝ በኢየሱስ የማያምኑ ሰዎች የእሳት ባሕር ውስጥ ዘላለማዊ መንፈሳዊ ስቃይ ይቀበላሉ።
  • ይህ ቃል፣ “ከባድ መከራ” ወይም፣ “አንድን ሰው በጣም ማሳመም ወይም፣ “ጭንቀት” በማለት መተርጎም ይቻላል።
  • ትርጕሙን ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ፣ “አካላዊ” ወይም፣ “መንፈሳዊ” የሚል ቃል መጨመር ያስፈልግ ይሆናል።

ስብሰባ(ጉባኤ)፥ መሰብሰብ

“ስብሰባ(ጉባኤ)” የሚለው ቃል ችግሮች ላይ ለመወያየት፥ ምክር ለመስጠትና ውሳኔ ለማሳለፍ በአንድነት የተሰበሰቡ ሰዎችን ያመለክታል

  • አንድ ስብሰባ በመደበኛነት የተደራጀ ሕጋዊነት ያለው አካል ሊሆን ይችላል ወይም ደግሞ ለተወሰነ ዓላማ ወይም ወቅት በአንድነት የሚገናኝ ጊዜያዊ የሰዎች ስብስብ ሊሆን ይችላል።
  • በብሉይ ኪዳን ዘመን፥ “የተቀደሰ ስብስባ (ጉባኤ)” የሚባል የተለየ ዐይነት ስብሰባ ነበር፤ ይህ የእስራኤል ሕዝብ ያህዌን ለመምለክ በአንድነት የሚገናኙበት ጊዜ ነበር።
  • አንዳንድ “ስብሰባ(ጉባኤ)” የሚለው ቃል በአጠቃላይ እንደማኅበረሰብ እስራኤላውያንን ያመለክታል።
  • ግዙፍ የጠላት ወታድሮች ክምችት አንዳንዴ “ስብሰባ(ጉባኤ) ተብሎ ይጠራል። ይህን ሰራዊት በማለት መተርጎም ይቻላል።
  • አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን ኢየሩሳሌምን በመሳሰሉ ዋና ዋና ከተሞች ይኖሩ የነበሩ 70 የአይሁድ መሪዎች ስብሰባ አንዳንድ ሕግ ነክ ጉዳዮችን ለመወሰንናበሰዎች መካከል ለተፈጠረ አለመግባባት መፍትሔ ለመስጠት ይሰበሰቡ ነበር። ይህ ስብሰባ ሳንሐድሪን ወይም “ሸንጎ” በመባል ይታወቅ ነበር።

ስንዴ

ስንዴ ሰዎች ለምግብ የሚያመርቱት እህል ነው።

  • ዘሩ የሚገኘው የስንዴው ተክል ጫፍ ላይ ነው።
  • ስንዴት ከታጨደ በኋላ ፍሬው ከገለባው ይለያል። ይህ ሂደት፣ “መውቃት” ይባላል።
  • ብዙውን ጊዜ የስንዴው ገለባ ወይም አገዳ ከብቶች እንዲተኙበት መሬት ላይ ይደረጋል።
  • ከስንዴው ጋር የሚበቅል ትንሽ ዘር እንክርዳድ ይባላል፤ ለምንም የሚጠቅም ስላልሆነ ይጣላል።
  • ሰዎች ስንዴውን ፈጭተው ዱቄቱን ዳቦ ለመሥሪያ ይጠቀሙበታል።

ሸንጎ፣ ምክር

ሸንጎ በጣም አስፈላጊ ጉዳዮችን በተመለከት ለመወያየት፣ ምክር ለመስጠትና ውሳኔ ለማሳለፍ የተሰበሰቡ ሰዎች ማለት ነው።

  • ሕገ ነክ የሆኑ ጕዳዮችን አስመልክቶ ውሳኔ ማሳለፍን ከመሳሰሉ ዓላማዎች አንጻር ብዙ ጊዜ ሸንጎ የሚቋቋመው ዕውቅና ባለውና ዘላቂነት ባለው መልኩ ነው።
  • ከፍ ያለ ሥልጣን የነበረው የአይሁድ ሸንጎ ሳንሔድሪን በመባል የሚታወቀው ነበር። ሳንሔድሪን ሊቃነ ካህናትን፣ ሽማግሎዎችን፣ ጸሐፍትን፣ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያንም የመሳሰሉ አይሁድ መሪዎችን የሚያካትት 70 አባሎች ነበሩት።
  • ወንጌልን በማስተማሩ የታሰረ ጊዜ ሐዋርያው ጳውሎስ የሮማውያን ሸንጎ ፊት ቀርቦ ነበር።
  • እንደ ዐውዱ ሁኔታ፣ “ሸንጎ” – “ሕጋዊ ጉባኤ” ወይም፣ “የፖለቲካዊ ጉባኤ” ተብሎ መተርጎም ይችላል።
  • “ሸንጎ ውስጥ መሆን” ታላላቅ ነገሮችን መወሰን የሚችል ስብሰባ ውስጥ መሆን ማለት ነው።

ሸክም

ሸክም ከባድ ጫና ነው። ቃል በቃል የጥንት እንስሳት የሚሸከሙትን ሸክም ያመልክታል። “ሸክም” የሚለው ቃል በርካታ ምሳሌያዊ ትርጕሞችም አሉት።

  • ሸምክ አንድ ሰው መፈጸም ያለበትን ከባድ ሥራን ወይም ጠቃሚ ኀላፊነትንም ማመልከት ይችላል። ከባድ ሸክም፣ “ተሸክሞአል” ወይም፣ “ከባድ ጫና ተጭኖታል” ማለት ይቻላል።
  • አንድ ጨካኝ መሪ ሕዝቡ ላይ ከባድ ሸክም ሊጭን ይችላል፤ ለምሳሌ ብዙ ግብር ወይም ቀረጥ እንዲከፍሉ በማስገደድ።
  • ሌላው ላይ ሸክም መሆን የማይፈልግ ሰው እዚያ ሰው ላይ ችግር መፍጠር አይፈልግም።
  • ኃጢአት የሚያስከትለው በደለኝነት ለዚያ ሰው ሸክም ነው።
  • “የጌታ ሸክም” የሚለው ምሳሌያዊ አገላለጽ አንድ ነቢይ ለእግዚአብሔር ሕዝብ ያለበትን፣ “የእግዚአብሔር ሸክም” ያመለክታል።
  • “ሸክም” የተሰኘው ቃል፣ በምንባቡ ዐውድ መሠረት፣ “ኃላፊነት” ወይም፣ “ተግባር” ወይም፣ “መልእክት” ተብሎ ሊተርጎም ይችላል።

ሽማግሌ

ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር ሕዝብ መሐል መንፈሳዊና ተግባራዊ መሪነት ኀላፊነት ያላቸው መንፈሳዊ ማስተዋል ያላቸው ስሞች ናቸው።

  • መጀመሪያ ላይ ይህ ቃል የተወሰደው ሽማግሌዎቹ የሚሆኑት በዕድሜያቸውና በሕይወት ልምዳቸው ከወጣቶች ይልቅ አስተዋይ የሆነ ስምች ስለ ነበሩ ነው።
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ ሽማግሌዎች ማኅበራዊ ፍትሕንና የሙሴ ሕግን በተመለከተ እስራኤላውያን በመምራት ያገለግሉ ነበር።
  • አዲስ ኪዳን ውስጥ የአይሁድ ሽማግሌዎች ማኅበረ ሰባቸውንና በመምራትና ሕዝባቸውን በመዳኘት ቀጥለው ነበር።
  • በጥንት ቤተ ክርስቲያን ክርስቲያን ሽማግሌዎች በየአካባቢው በነበረ የአማኞች ጉባኤ መንፈሳዊ አመራር ይሰጡ ነበር።
  • መንፈሳዊ ማስተዋል ያላቸው ወጣቶችም የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ይሆኑ ነበር።
  • ይህ ቃል፣ “በዕድሜ የገፉ ሰዎች” ወይም፣ “ቤተ ክርስቲያንን የሚመሩ መንፈሳዊ ማስተዋል ያላቸው ሰዎች” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

ሽብር፣ ማሽበር

“ሽብር” የሚለው ቃል በጣም የመፍራትና የመደንገጥ ስሜት ወይም አንድን ሰው ወይም ነገር በጣም መጥላት ማለት ነው።

  • በጣም የሚያስፈራ ወይም የሚያስጠላ ነገርም ሽብር ሊሆን ይችላል።
  • ወደ ፊት እየገሠገሠ ያለ አጥቂ ሰራዊት ጠላቶቹ ላይ ሽብር ያሳድራል።
  • አንድ ቀን እግዚአብሔር የሚያመጣው ፍርድ ጸጋውን የሚንቁትን ሁሉ ያሸብራል።
  • “የያህዌ ሽብር” የሚለው፣ “አስፈሪው የያህዌ ሕልሞች” ወይም፣ “አስፈሪው የያህዌ ፍርድ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
  • አንድን ሰው፣ “ማሸበር” እጅግ በጣም እንዲፈራ ማድረግ ማለት ነው።
  • “የሚያሸብር” ነገር ሁሉ ፍርሃትና ድንጋጤ ያመጣል።

ሽብር፣ ተሸበረ

“ሽብር” የሚለው ቃል ከፍተኛ የፍርሃት ወይም የድንጋጤ ስሜት ያመለክታል። ሽብር የሚሰማው ሰው፣ “ተሸበረ” ይባላል።

  • ሽብር ከተራ ፍርሃት የበለጠ ግልጽና በጣም ከባድ ነው።
  • ብዙውን ጊዜ አንድ ሰው ሲሸበር ይንቀጠቀጣል ወይም ይርበተበታል።

ቀረጥ

“ቀረጥ” ሰዎች እነርሱ ላይ ሥልጣን ላይ ላለው መንግሥት የሚከፍሉት ገንዘብ ወይም ዕቃ ነው

  • የሚከፈለው የቀረጥ ገንዘብ መጠን የሚወሰነው የዕቃው ዋጋ ወይም የሰውየውን ሀብት መሠረት በማድረግ ነበር
  • ቀረጥ ካልተከፈለ ያንን ገንዘብ ለማግኘት መንግሥት ሰዎች ወይም ሥራቸው ላይ ርምጃ ይወስዳል
  • “ቀረጥ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የሚውለው፣ “ቀረጥ መሰብሰብ” ወይም፣ “ቀረጥ መክፈል” በሚል ሐረግ ውስጥ ነው። “ለመንግሥት ገንዘብ መክፍል” ወይም፣ “የሚጠየቀውን መክፈል” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል
  • “ቀረጥ ሰብሳቢ” ሰዎች መክፈል ያለባቸውን ገንዘብ በመሰብሰብ ለመንግሥት የሚሠራ ሰው ነው

ቀረጥ ሰብሳቢ

የቀረጥ ሰብሳቢ ሥራ ከሰዎች የተቀበለውን ገንዘብ ለመንግሥት ማስተላለፍ ነበር

  • ኢየሱስና ሐዋርያቱ ባገለገሉበት ዘመን የሮም መንግሥት አይሁዳውያንን ቀረጥ ያስከፍል ነበር
  • ለሮም መንግሥት ቀረጥ ይሰበስቡ የነበሩ ሰዎች መንግሥት ከሚጠይቀው የበለጠ ገንዘብ ከሕዝቡ ይጠይቁ ነበር። ቀረጥ ሰብሳቢዎቹ ያንን ገንዘብ ለራሳቸው ይወስዱት ነበር
  • ሰዎችን በማታለላቸውና ለባዕዱ የሮም መንግሥት በመሥራታቸው አይሁድ ቀረጥ ሰብሳቢዎችን በጣም የባሰባቸው ኅጢአተኞች እንደሆኑ ይቆጥሩ ነበር። ለባዕድ መንግሥት መሥራታቸው የገዛ ሕዝባቸውን የካዱ አድርጓቸው ነበር

ቀስተኛ

  • “ቀስተኛ” የሚለው ቃል በቀስትና ደጋን የመጠቀም ችሎታ ያለውን ሰው ያመለክታል
  • በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቀስተኛ በሰራዎት ውስጥ ሆኖ ለመዋጋት ቀስትና ደጋን የሚጠቀም ወታደር ነው
  • ቀስተኛ በአሦራውያን ወታደራዊ ኅይል ውስጥ ሁነኛ ድርሻ ነበራቸው
  • አንዳንዶች ይህን ቃል በተመለከተ፥ “የደጋን ሰው” የሚል ቃል ይኖራቸዋል።

ቀንበር

“ቀንበር” ሁለት በሬዎች በአንድነት እንዲሠሩ ለማጣመር የሚረዳ ነገር ነው። “ቀንበር መሸከም” አንድ ዓይነት ኀላፊነት መሸከም ማለት ነው።

  • ቀነበር እንጨት ወይም ብረት ሲሆን ማረሻ ወይም ሰረገላ ለመጎተት ሁለት ወይም ከዚያ በላይ እንስሳትን ያጣምራል።
  • ቀንበር በርካታ ምሳሌያዊ ትርጕሞ አሉት።
  • ባርነትን፣ ጭቆናን ወይም በጨካኝ መሪ የሚመጣ ስደትን ሊያመለክት ይችላል።
  • ጋብቻን፣ ሥራን ወይም ጌታን ማገልገልን እንደ መሳሰሉት ለጋራ ዓላማ በአንድነት መሥራትንም ያመለክታል።

ቀንድ፣ ቀንዶች

ቀንዶች ላምና በሬ፣ በጎችና ፍየሎች የመሳሰሉ እንስሳት ራስ ላይ የሚበቅል ቋሚና ሹል ነገር ነው። ብርታትን፣ ኀይልን፣ ሥልጣንና ንጉሥነትን ለማመልከትም “ቀንድ” በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።

  • የበግ ቀንድ በአንዳንድ ሃይማኖታዊ ክብረ በዓላት ጊዜ የሚነፋውን፣ “ሸፋር” የተሰኙ የሙዚቃ መሣሪያ መሥሪያ ይሆናል።
  • ከናስ የተሠራው የዕጣን መሠዊያ ላይ በአራቱም አቅጣጫ የቀንድ ቅርጽ ያለው ነገር እንዲያደርጉ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ተናግሮአል። እነዚህ ነገሮች “ቀንዶች” ተብለው ቢጠሩም ትክክለኛ የእንስሳት ቀንዶች አልነበሩም።
  • ውሃ ወይም ዘይት ለመያዣ የሚያገለግለው ቀንድ መሰል ብልቃጥ አንዳንዴ፣ “ቀንድ” ተብሎ ይጠራል። የዘይት ብልቃጥ ሳሙኤል ዳዊት ላይ እንዳደረገው አንድን ንጉሥ ለመቀባት ያገለግላል።

ቃል

“ቃል” አንድ ሰው የተናገረውን ያመለክታል።

  • ለዚህ ምሳሌ የሚሆነን፣ “ቃሌን አላመንህምና” በማለት መልአኩ ለዘካርያስ የተናገረው ነው፤ እንዲህ ማለቱ፣ “የነገርሁህን አላመንህም” ማለቱ ነበር።
  • አብዛኛውን ጊዜ ይህ አንድን ቃል ብቻ ሳይሆን መላውን መልእክት ያመለክታል።
  • ብዙውን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ቃል”እግዚአብሔር የተናገረውን ወይም ያዘዘውን ሁሉ ይመለከታል፤ “የእግዚአብሔር ቃል” ወይም፣ “የእውነት ቃል” እንደ ተሰኙት።
  • አንዳንዴ፣ “ቃል” አጠቃላዩን ንግግር ያመለክታል፣ ለምሳሌ፣ “በቃልና በሥራ የበረታ እንደሚለው። ይህ “በንግግሩም ሆነ በጸባዩ ብርቱ የሆነ” ማለት ነው።
  • ይህ ቃል በጣም በተለየ ሁኔታ ጥቅም ላይ የዋለው ኢየሱስ፣ “ቃል” በመባሉ ነው።

ቃል መግባት

“ቃል መግባት” አንድ ነገር ለማድረግ ወይም ለመስጠት ተስፋ መስጠት ማለት ነው።

  • ከብሉይ ኪዳን እንደምንመለከተው የእስራኤል ባለ ሥልጣኖች ለንጉሥ ዳዊት ታማኝ ለመሆን ቃል ገብተው ነበር።
  • “ቃል መግባት” የሚለው ቃል ዕዳው እንደሚከፈል መያዣ እንዲሆን አንድን ነገር መስጠትን ወይም ተስፋ መስጠትንም ያመለክታል።
  • የተገባው ቃል ሲፈጸም እንደ መያዣ ተሰጥቶ የነበረው ዕቃ ለባለቤቱ ይመለሳል።

ቃርሚያ፣ መቃረም

ቃርሚያ አጫጆች የተዉትን ፍራ ፍሬ ወይም እህል ለመሰብሰብ እርሻ ወይም አትክልት ቦታ ውስጥ መሄድ ማለት ነው።

  • መበለቶች፣ ድኾችና መጻተኞች ምግባቸውን እንዲያገኙ ኋላ ኋላ እየሄዱ እንዲቃርሙ ይፈቅድላቸውል፤ ይህም ብዙ እህል ለመሰብሰብ ያስችላቸዋል።
  • ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የምትሆን፣ የሞተው ባሏ ዘመድ በሆነው ቦዔዝ እርሻ ውስጥ በነበሩት አጫጆች መካከል እንድትቃርም ተፈቅዶላት የነበረችው ሩት ናት።

ቅርጫት

“ቅርጫት” እርስ በርስ ከተጠላለፉ ነገሮች የሚሠራ መያዣን ያመለክታል

  • በብሉይ ኪዳን ዘመን ቅርጫት የዛፎች ልጥ(ቅርፊት)፥ ቅርንጫፎችና ሐረጎችን ከመሳሰሉ ጠንካራ የተክል ውጤቶች ይሠራ ነበር
  • ቅርጫት መንሳፈፍ እንዲችል ውሃ በማያስገባ ነገር ይሸፈን ነበር
  • ሙሴ ሕፃን ልጅ በነበር ጊዜ እናቱ ውሃ የማያስገባ ቅርጫት ሠርታ እንዲንሳፈፍ አባይ ወንዝ ውስጥ ጥላው ነበር
  • በዚህ ታሪክ “ቅርጫት” ተብሎ የተተረጎመው ቃል ኖኅ የሠራውን ጀልባ ለማመልከት “መርከብ” ከተባለው ቃል ጋር ተመሳሳይ ነው። በሁለቱም ዐውዶች ያለው የጋራ ትርጉም፥ “ የሚንሳፈፍ መያዣ ነገርን” ማመልከቱ ነው

ቅርጽ ማውጫ

ቅርጽ ማውጫ የሚባለው ከወርቅ፣ ከብርና ከሌሎች ፈሳሽ መሆን ከሚችሉ ነገሮች አንዳንድ ነገሮችን ለመሥራት የቅርጽ ማውጫውን ይዘው እንዲወጡ ለማድረግ ከእንጨት ቁራጭ፣ ከብረት ወይም ከሸክላ ተፈልፍሎ የሚሠራ ነገር ነው።

  • ቅርጽ ማውጫዎች ሌሎች ነገሮችንም ጨምሮ ጌጣጌጦችን፣ ሳህኖችንና የመመገቢያ ዕቃዎችን ለመሥራት ያገለግላሉ።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቅርጽ ማውጫዎች እንደ ጣዖት ያሉትን ሐውልቶችና የሐሰኛ አማልክት ማምለኪያ ነገሮችን ከመሥራት ጋር በተያያዘ ነው በዋናነት የተጠቀሱት።
  • ቅርጽ ማውጫው ውስጥ ማፍሰስ እንዲቻል በመጀመሪያ ወርቁ ወይም ብሩ በእሳት መቅለጥ አለበት።
  • አንድን ነገር መቅረጽ በመቅረጫው ወይም በእጅ በማበጀት ያ ነገር የተወሰን ቅርጽ ወይም ምስል ይዞ እንዲወጣ ማድረግ ነው።

ቅናት፣ መመኘት

ቅናት ያ ሰው ካለው ሀብት የተነሣ ወይም የሚደነዙ ችሎታዎች በለቤት ከመሆኑ የተነሣ ሌላውን ሰው መመቅኘት ማለት ነው። “መመኘት” ያ ሰው ያለውን ነገር ለራስ ለማድረግ አጥብቆ እስከ መፈለግ ድረስ በቅናት መነሣሣት ማለት ነው።

  • በሌላው ሰው ስኬት፣ ጥሩ ዕድል ወይም ሀብት መቅናት አሉታዊ የጸጸት ስሜት ነው።
  • መመኘት የሌላውን ሰው ሀብት ሌላው ቀርቶ የትዳር ጓደኛውን እንኳ የራስ ለማድረግ አጥብቆ መፍለግ ማለት ነው።

ቅን፣ ቅንነት

“ቅን” እና፣ “ቅንነት” የእግዚአብሔርን ሕግ እየተከተሉ መኖርን ያመለክታል።

  • የእነዚህ ቃሎች ትርጕም ቀጥ ብሎ መቆምንና በቀጥታ ወደ ፊት ማየትን የሚያካትት ሐሳብ አለው።
  • “ቀጥ ያለ” ሰው ለእግዚአብሔር ሕግ የሚታዘዝና ከእርሱ ፈቃድ የሚጋጭ ነገር የማያደርግ ሰው ነው።
  • “ታማኝነጥ” እና፣ “ጽድቅ” የተሰኙት ቃሎች ተመሳሳይ ትርጕም ያላቸው ሲሆኑ አንዳንዴ በተጓዳኝ ጥቅም ላይ ይውላሉ፤ ለመሳሌ፣ “ጻድቅና ቅን” እንደሚለው።

ቅድስት ከተማ

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ቅድስት ከተማ” የሚያመለክተው የኢየሩሳሌም ከተማን ነው።

  • በመጨረሻው ዘመን ቅድስት ከተማ የምትሆነው እግዚአብሔር በሕዝቡ መከከል የሚኖርባት አዲሲቱ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ናት።
  • ይህን ሐረግ በተቀረው ትርጕም ውስጥ “ቅዱስ” እና፣ “ከተማ” ለሚለው ጥቅም ላይ በዋሉት ቃሎች መተርጎም ይቻላል።

ቆጠራ

“ቆጠራ” የሚለው ቃል ሥርዓት ባለው መልኩ በአገሩ ወይም በመንግሥቱ ውስጥ ያሉ ሰዎች መቊጠርን ያመለክታል።

  • ብሉይ ኪዳን የእስራኤል ሰዎች እንዲቆጠሩ እግዚአብሔር በተለያየ ጊዜ አዝዞ እንደ ነበር መዝግቦአል፤ ለምሳሌ እስራኤል መጀመሪያ ከግብፅ ሲወጡና በኋላም ከነዓን ከመግባታቸው ጥቂት ቀደም ሲል።
  • ብዙውን ጊዜ ቆጠራ የሚደረገው ግብር የሚከፍሉ ምን ያህል ሰዎች እንደ ሆኑ ለማወቅ ነበር።
  • ለምሳሌ ከዘፀአት እንደምንመለከተው አንድ ጊዜ እያንዳንዱ ሰው ለመቅደሱ ሥራ የሚሆን ግማሽ ሰቄል እንዲከፍል ለማድረግ የእስራኤል ሰዎች ተቆጥረው ነበር።
  • ኢየሱስ ሕፃን በነበረ ጊዜ መንግሥታቸው ውስጥ የሚኖረውን ሕዝብ ለማወቅና ግብር እንዲከፍሉ ለማድረግ የሮም መንግሥት የሕዝብ ቆጠራ አድርጎ ነበር።

በለስ

በለስ የበለስ ዛፍ ላይ የሚበቅል ትንሽና ጣፋጭ ፍሬ ነው። ሰዎች ትኩሱን፣ ቀቅለው ወይም አድርቀው በለስ መብላት ይችላሉ፣ ወይም ይከትፏቸውና እንደቂጣ አድርገው ይበሏቸዋል።

  • የበለስ ዛፎች ቁመት 6 ሜትር ድረስ ያድጋል፤ ሰፋፊ ቅጠሎቻቸው ጥሩ ጥላ ይሆናል።
  • እስራኤላውያን እዚያ ከመምጣታቸው በፊት ያበለስ ዛፍ ምድረ ከነዓን ውስጥ በጣም ጠቃሚ መብል ነበር።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በለስ ለምግብና ሌላም ገቢ ለማግኘት ዋና ምንጭ ነበር።
  • መጽሐፍ ቅዱስ የእስራኤልን መበልጸግ ወይም አለመበልጸግ ምልክት እንዲሆን በለስን በምሳሌያዊ መልኩ ይጠቀማል (1 ነገሥት 4፣25፤ ኤርምያስ 5፣17)

በረሐ፣ ምድረ በዳ

በረሐ ወይም ምድረ በዳ በጣም ጥቂት ተክሎችና ዛፎች ብቻ የሚያድጉበት ደረቅና ጠፍ ቦታ ነው።

  • በረሐ ጥቂት ተክሎች ወይም እንስሳት ያሉት ደረቅ የአየር ፀባይ ያለው አካባቢ ነው።
  • እንዲህ ያለው ቦታ በጣም አስቸጋሪ በመሆኑ በረሐ ውስጥ የሚኖሩ በጣም ጥቂት ሰዎች ናቸው። ይህ ቦታ፣ “ምድረ በዳ” ተብሎም ይጠራል።
  • “ምድረ በዳ” ሲባል በጣም ሩቅ፣ የተተወና ከሰዎች መኖሪያ የተገለለ የሚል ዐሳብ አለው።
  • ይህ ቃል፣ “ሰው የማይኖርበት” ወይም፣ “ሩቅ ቦታ” ወይም “የተተወ ቦታ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

በረዶ

“በረዶ” ተራሮችን በመሳሰሉ ከፍታ ቦታዎች ወይም የዓለማችን ሰሜን ወይም ደቡብ ጫፍ ላይ የሚወርድ ውሃ አዘል ጠጣር ነገር ነው

  • በክረምት ኢየሩሳሌም ላይ በረዶ ይጥላል ሆኖም፣ ብዙ ጊዜ ሲጠራቀም አይታይም
  • ነጭ ነገርን ለማመልከት በረዶ እንደምሳሌ ይቀርባል
  • የበረዶ ንጣት የንፅሕና ሕይወት ተምሳሌት ነው
  • መጽሐፍ ቅዱስ፣ ኅጢአታችን እንደ በረዶ እንደሚነጣ ሲናገር እግዚአብሔር ሕዝቡን ፈጽሞ ከኅጢአታቸው ያነጻቸዋል ማለት ነው
  • የዮሐንስ ራዕይ የከበረው ክርስቶስን ሲያመለክትት፣ ጠጉሩ፣ “እንደበረዶ ነጭ” ነበር ይላል
  • አንዳንድ ቋንቋዎች በረዶን ለማመልከት የተለያዩ ቃሎች ይጠቀሙ ይሆናል

በሬ፣ በሬዎች

በሬ በተለይ ለእርሻ ስራ የተገራ የከብት ዓይነት ነው። ብዙ ቁጥስ ሲሆን፣ “በሬዎች” ይባላል። በሬ የሚያገለግለው ለተባዕቱ ብዙውን ጊዜ እንዲኮላሹ ይደረጋል።

  • ከመጽሐፍ ቅዱስ የምንመለከተው የበሬዎች ምሳሌ ሰረገላ ወይም ሞፈር እንዲስቡ ቀንበር የተሸከሙ እንስሶች መሆናቸው ነው።
  • ቀንበር የተሸከሙ በሬዎች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በጣም የተለመደ ከመሆኑ የተነሳ፣ “ቀንበር መሸከም” የከባድ ሥራ ወይም ልፋት ተለዋጭ ዘይቤ ሆኗል።
  • ወይፈን ያልተኮላሸ ተባዕት እንስሳ ሲሆን፣ ለእርሻ ሥራ ገና ያልተገራ ነው።

በሮች፣ የበር ሳንቃ

“በር” ቤት ወይም ከተማ አጥር ወይም ግድግዳ ላይ ያለ ወደ ቤት የሚገባበት ላይ የተያያዘ ከለላ ነው። “የበር ሳንቃ” በርን ለመዝጋት መንቀሳቀስ የሚችል ከእንጨት ወይም ከብረት የተሠራ ጣውላ ነው።

  • ሰዎች፣ እንስሳት፣ ጭነት ወደ ከተማ እንዲወጡና እንዲገቡ የከተማ በር ይከፈታል።
  • ለከተማዋ መከላከያ እንዲሆን ግድግዳውና በሩ ወፍራምና ጠንካራ ይሆናል። የጠላት ወታደሮች ወደ ከተማው እንዳይገቡ በሮቹ በብረት ወይም በእንጨት ጣውላ ይዘጉና ይቆለፋሉ።
  • የከተማ ግንቦች ወይም አጥሮች በጣም ወፍራምና መተላለፊያም ያላቸው ስለ ነበሩ ከፀሐይ ሙቀት የሚከላከል ቀዝቀዝ ያለ ጥላ ነራቸው፤ ስለዚህም ሰዎች ተሰብስበው ለመነጋገር፣ ንግድ ለመለዋወጥና ዳኝነትን ለመሳሰሉ ጉዳዮች እዚያ ይገናኙ ነበር።

በስኬት መደሰት

?


በትረ መንግሥት

“በትረ መንግሥት” አንድ ንጉሥ ወይም የአገር አስተዳዳሪ የሚይዘው ጌጠኛ በትር ወይም ዱላ ነው

  • መጀመሪያ ላይ በተረ መንግሥት የሚሠራው ጌጣ ጌጦች ከተቀረጹበት የዛፍ ቅርንጫፍ ነበር። በኋላ ግን ወርቅን ከመሳሰሉ የከበሩ ድንጋዮችም ይሠራ ጀመር
  • በትረ መንግሥት ከንጉሡ ጋር የተያያዘውን ክብርና ታላቅነት የሚያሳይ የንጉሣዊነትና የሥልጣን ምልክት ነው
  • ብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር የጽድቅ በትር እንዳለው ይናገራል
  • የብሉይ ኪዳን ትንቢት መንግሥታትን ለመግዛት ክርስቶስ ከእስራኤል እንደበትረ መንግሥት እንደሚወጣ ያመለክታል

በትር

በትር ቀጭን፣ ጠንካራና በተለያየ መንገድ ጥቅም ላይ የሚውል ከዘራ መሰል ነገር ነው። ምናልባትም በትንሹ አንድ ሜትር ያህል ሊረዝም ይችላል።

  • የእንጨት በትር እረኛው በጎችን ከአውሬዎች ለመጠበቅ ይጠቀምበታል። ርቆ የሄደን በግ ወደ መንገድም ለመመለስ ያገለግላል።
  • መዝሙር 23 ላይ ንጉሥ ዳዊት የእግዚአብሔርን ምሪትን ለመግለጥ፣ እንደ ተለዋጭ ዘይቤ፣ “በትር” እና፣ “ምርኩዝ” በተሰኙ ቃሎች ይጠቀማል።
  • የእረኛው በትር በበታቹ እንዲያልፉ በማድረግ በጎቹን ለመቁጠር ይጠቅማል። “በበትር ሥር ማለፍ” የሚለው ምሳሌያዊ አነጋገር በሥልጣን ሥር መሆንን ያመለክታል።
  • “የብረት በትር” የሚለው ሌላው ተለዋጭ ዘይቤ በእርሱ ላይ የሚያምጹትንና ክፉ የሚያደርጉትን እግዚአብሔር እንደሚቀጣ ያመለክታል።
  • በጥንት ዘመን ከብረት፣ ከእንጨት ወይም ከሌላ ነገር የተሠራ መለኪያ በትር ሕንፃንና የተለያየ ነገርን ለመለካት ጥቅም ላይ ይውል ነበር።
  • በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት፣ የእንጨት በትር ልጅን ሥርዓት ለማስያዝ ጥቅም ላይ ይውል ነበር።

በኣል

አጠቃላይ በሆነ መልኩ በኣል የማኅበረሰቡ ሰዎች በአንድነት የሚያከብሩት ሁኔታ ነው።

  • በብሉይ ኪዳን መሠረት፣ “በዓል” ቃል በቃል፣ “የተወሰነ ወይም የተመደበ ቀን” ማለት ነው።
  • እስራኤላውያን የሚያከብሯቸው በዓሎች እግዚአብሔር እንዲጠብቁት ባዘዛቸው መሠረት በተለየ ሁኔታ የተመደበ ጊዜ ወይም ወቅት ናቸው።
  • እስራኤላውያን በየዓመቱ የሚያከብሯቸው ዋና ዋና በዓሎች አሉ፤
  • የፋሲካ በዓል
  • የቂጣ በዓል
  • የመከር በዓል
  • በዓለ-ሃምሳ
  • የመለከት በዓል
  • የስርየት በዓል
  • የዳስ በዓል
  • የእነዚህ በዓሎች ዓላማ እግዚአብሔርን ለማመስገንና ሕዝቡን ለመታደግ፣ ለመጠበቅና የሚያስፈልገውን በመስጠት ያደረጋቸውን ድንቅ ነገሮች ለማስታወስ ነው።

በኩራት

“በኩራት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው በእያንዳንዱ መከር ወቅት ከሚሰበሰበው እህል ሆነ አትክልት የመጀመሪያውን ፍሬ ነው።

  • የስጦታ መሥዋዕት እንደሆነ እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር በኩራት ያቀርቡ ነበር።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቃሉ ቤተሰቡ ውስጥ የሚወለደውን የመጀመሪያ ወንድ ልጅ ለማመልከት ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል። ያም ማለት የቤተሰቡ የመጀመሪያ ልጅ እንደመሆኑ መጠን፣ የቤተሰቡ ስም እና ክብር የሚጠራው በእርሱ ነው ማለት ነው።
  • ኢየሱስ ከሞት በመነሣቱ ለሞቱትና አንድ ቀን ከሞት ለሚነሡት አማኞች ሁሉ፣ “በኩራት” ነው ብሎአል።
  • በኢየሱስ የሚያምኑ አማኞችም፣ የፍጥረታቱ በኩራት ተብለዋል፤ ይህ የሚያመለክተው ኢየሱስ ያዳናቸው ሕዝቡ እንዲሆኑ የጠራቸው ያላቸውን መብትና ቦታ ነው።

በኩር

“በኩር” የሚለው ቃል መጀመሪያ የሚወለደውን የሰውም ሆነ የእንስሳትን የመጀመሪያ ልጅ ነው።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙውን ጊዜ “በኩር” የሚያመለክተው መጀመሪያ የሚወለድ ወንድ ልጅን ነው።
  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን የበኩር ልጅ ሌሎች ልጆች የሚያገኙትን የቤተሰብ ዕጥፍ የመውረስ መብት ነበረው።
  • ብዙውን ጊዜ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት የሚቀርበው መጀመሪያ የተወለደው እንስሳ ነበር።
  • ይህ ቃል ምሳሌያዊ በሆነ መልኩም ጥቅም ላይ ይውላል። ለምሳሌ ከሌሎች ሕዝቦች የተለየ መብት ስለሰጣቸው የእስራኤል ሕዝብ የእግዚአብሔር በኩር ተብለው ተጠርተው ነበር።
  • በሌሎች ሁሉ ላይ ባለው ሥልጣንና የበላይነት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስም “በኩር” ተብሏል።

በዓል

በዓል ሰዎች በአንድነት ተሰብስበው በመመገብ የሚይሳልፉት ሁኔታ ሲሆን፣ እንዲህ የሚደረገው አንድን ሁኔታ አብሮ ለማክበር ሊሆን ይችላል። “በዓል ማድረግ” በልዩ አይነት ሁኔታ የተዘጋጀ ምግብ በብዛት መመገብን ያሳያል።

  • አይሁዳውያን እንዲያከብሩ እግዚአብሔር ያዘዛቸው በዓሎች ብዙውን ጊዜ አብሮ ደስተኛ ጊዜ ማሳለፍንም ያካትታል።
  • ነገሥታትና ሌሎች ሀብታሞችና ታዋቂ ሰዎች ብዙውን ጊዜ መብልና መጠጥ ለሰዎች የሚያቀርቡበት ግብዣ (በዓል) ያደርጋሉ።
  • ስለጠፋው ልጅ በተነገረው ታሪክ ልጁ ወደቤቱ በተመለሰ ጊዜ አባትዮው የተለየ ግብዣ (በዓል) አድርጎ እንደነበረ እናያለን።
  • አንዳንዴ ግብዣው ለጥቂት ቀኖች ወይም ከዚያም በላይ ሊቆይ ይችላል።

በደል፣ መበደል፣ መጉዳት

በደል፣ በመደልና መጉዳት ሌላው ሰው ላይ አካላዊ፣ ስሜታዊና ሕግን ተገን በማድረግ ጉዳት ማድረስ ማለት ነው።

  • ሌላው ላይ ጉዳት ማድረስ ትክክል ባልሆነ ፍትሕ በተጓደለበት ሁኔታ ሰውን መጉዳት ማለት ነው።
  • አንድን ሰው መበደል የሚባለው ያ ሰው ላይ መጥፎ ወይም ጭካኔ ያለበት ነገር ሲፈጸም ነው።
  • ይህ ቃል አንድን ሰው ብቻ ሳይሆን ብዙዎች ላይ ጉዳት ማድረስን በተመለከተም ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።

በገና

በገና ባለ ገመድ የሙዚቃ መሣሪያ ሲሆን፣ ቀጥ ያሉ ክሮች ወይም ገመዶች ይኖሩታል።

  • የጥድ እንጨት በገናና ሌሎች የሙዚቃ መሣሪያዎች ለመሥራት ያገለግላል።
  • በጥንት ዘመን በገና ብዙውን ጊዜ በእጅ ተይዞ መንገድ ሲሄዱ የሚጫወቱት ነበር።
  • ብዙውን ጊዜ በገና ጥቅም ላይ የሚውለው እግዚአብሔርን ለማመስገን ነበር።
  • ዳዊት በገና ሲደረድር ንጉሥ ሳኦል ከጭንቀት መንፈስ ፋታ ያገኝ ነበር። በበገና የተዜሙ በርካታ መዝሙሮችንም ጽፎአል።

በግ፣ አውራ፣ እንስት በግ

በግ አካሉ ላይ የሱፍ መሥሪያ ጠጉር ያለው መጠነኛ ቁመት ያለው ባለአራት እግር እንስሳ ነው። ወንዱ በግ አውራ ሲባል ሴቷ እንስት በግ ትባላለች

  • እስራኤላውያን አብዛኛውን ጊዜ መሥዋዕት የሚያቀርቡት በግ በተለይም ወንዱንና ከግልገል ከፍ ያለውን በግ ነበር
  • ሰዎች የበጎችን ሥጋ ይመገባሉ፤ ጠጉራቸውን ሱፍና ሌሎች ነገሮችን ለመሥራት ይጠቀሙበታል
  • በግ ሌሎችን የሚያምኑ፣ ደካማና ድንጉጦች ናቸው። በቀላሉ ከቦታቸው የሚኮበልሉ ናቸው። በትክክለኛው አቅጣጫ የሚመራቸው፣ የሚከለከልላቸውና ምግብ፣ ውሃና መጠለያ የሚያዘጋጅላቸው እረኛ ያስፈልጋቸዋል
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰዎች የእግዚአብሔር እረኝነት በሚያስፈልጋቸው በጎች ተመስለዋል

ባለሟል

“ባለሟል” የተመረጠና ከፍ ያለ ደረጃ ያለውን ሰው፣ በፖለቲካና በማኅበረ ሰቡ ውስጥ ሁነኛ ቦታ ያለውን ሰው ያመለክታል።

  • “ባለሟል” የመንግሥት ባለ ሥልጣንና የንጉሥ የቅርብ አገልጋይ ሰው ነው።
  • “ባለሟል” የሚለውን፣ “የንጉሥ ባለ ሥልጣን” ወይም፣ “የመንግሥት ሥልጣን” ወይም፣ “ከትልቅ ሰው የተወለደ”ብሎ መተርጎም ይቻላል።

ባልንጀራ

“ባልንፈራ” እንደ ጓደኛ ወይም እንደ የትዳር አጋር ከአንድ ሰው ጋር አብሮ መሆንን ወይም ኅብረት ማድረግን ያመለክታል።

  • ጓደኛሞች ብዙ ነገሮችን ይጋራሉ፤ አብረው ይበላሉ፤ እርስ በርስ ይረዳዳሉ ይደጋገፋሉ።
  • በምንባቡ መሠረት ይህ ቃል፣ “ጓደኛ” ወይም “አብሮ ተጓዥ” ወይም “ረዳት” ተብሎ መተሮም ይችላል።

ባሕል

ባሕል የሚያመለክተው ለረጅም ዘመን የተያዘና ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረ ወግ ወይም ልማድ ነው።

  • እስራኤላውያን ይዘዋቸው የነበሩ ብዙ ባሕሎች በጊዜ ሂደት በኋላ የሃይማኖት መሪዎቹ የጨምሩት እንጂ በብሉይ ኪዳን የታዘዙ አልነበሩም።
  • አንዳንድ ጥቅሶች “የሰዎችን ባሕሎች” ይዘዋል፤ ይህም አይሁድ ይለማመዷቸው የነበሩ በኋላ የተጨመሩ እንጂ፣ የእግዚአብሔር ትእዛዞች እንዳልሆኑ ግልጽ ያደርጋል።
  • አንዳንድ፣ “ባሕሎች”እግዚአብሔር የሰጠው ትእዛዞችንና እንዲሁም የሰዎች ሃይማኖታዊ ባሕልን ያካተቱ በመሆናቸው አጠቃላይ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ ይውላሉ።
  • በዚህ ዘመን ቤተ ክርስቲያኖች የሚለማመዷቸው ብዙ ባሕሎች የቅዱሳት መጻሕፍት ድጋፍ የላቸውም፤ ይሁን እንጂ፣ በታሪክ ውስጥ ተቀባይነት እያገኙ የመጡ ልማድና አሠራሮች ናቸው።

ባርያ ማድረግ፣ ባርነት

አንድን ሰው ባርያ ማድረግ ያ ሰው ለጌታ እንዲገዛ ማስገደድ ወይም አንድን መግዛት ማለት ነው። ባርነት በሰዎች ወይም በነገሮችና በሁኔታዎች ቁጥጥር ሥር መሆን ማለት ነው።

  • ባርያ የሆነ ወይም በባርነት ያለ ሰው ያለ ምንም ክፍያ ሌላውን ማገልገል አለበት፣ የፈለገውን ማድረግ አይችልም።
  • ባርያ ማድረግ የሰውን ነጻነት መንጠቅ ማለት ነው።
  • ከርእሱ ቁጥጥርና ኃይል ኢየሱስ ነጻ እስኪያወጣቸው ድረስ ምሳሌያዊ በሆነ አነጋገር የሰው ልጆች የኃጢአት ባርያዎች ናቸው።
  • አንድ ሰው በክርስቶስ አዲስ ሕይወት ሲቀበል የኃጢአት ባርያ መሆኑ ይቀርና የጽድቅ ባርይ ይሆናል።

ባርያ፣ ባርነት

አገልጋይ በውዴታ ወይም በግዴታ ለሌላው የሚሠራ ሰው ነው። “ባርያ” የሚለው ቃል “አገልጋይ” ማለትም ይሆናል። ከዐውዱ ጋር ይበልጥ የሚስማማው የትኛው ቃል እንደሆነ ብዙ ጊዜ ምንባቡ ግልጽ ያደርጋል

  • “አገልጋይ” ማለትም ይሆናል። ከዐውዱ ጋር ይበልጥ የሚስማማው የትኛው ቃል እንደሆነ ብዙ ጊዜ ምንባቡ ግልጽ ያደርጋል
  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን አገልጋዮች ወይም ባሪያዎች በጌታቸው ቤተሰብ ውስጥ ሁነኛ ድርሻ ነበራቸው፤ ብዙዎቹም ከቤተሰቡ አባሎች ባልተለየ ሁኔታ ነበር የሚያዙት። በብሉይ ኪዳን ዘመን አንድ ሰው የሌላው ሰው የዕድሜ ልክ አገልጋይ ለመሆን ምርጫ ያደርግ ነበር።
  • ባርያ ለሚያገለግለው ጌታ እንደንብረት የሚቆጠር ሰው ነበር። ጌቶች ባርያዎቻቸውን በጥሩ ሁኔታ ሲይዙ ሌሎች ግን ይበድሏቸው ነበር።
  • በጥንት ዘመን ያለባቸውን ዕዳ ለመክፈል አንዳንድ ሰዎች በፈቃደኝነት የአበዳሪዎቻቸው ባርያዎች ይሆኑ ነበር
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልፎ አልፎ የምናገኘው፣ “እኔ ባርያህ ነኝ” የሚለው ሐረግ የአክብሮትና የታዛዥነት ምልክት ነበር
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ የእግዚአብሔር ነቢያትና እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ሌሎች ሰዎች ብዙውን ጊዜ፣ የእርሱ፣ “ባርያ” ተብለው ይጠራሉ
  • አዲስ ኪዳን ውስጥ በክርስቶስ በማመን ለእግዚአብሔር የሚታዘዙ ብዙውን ጊዜ የእርሱ፣ “አገልጋዮች” ተብለዋል። ክርስቲያኖች፣ “የጽድቅ ባርያዎች” ተብለውም ተጠርተዋል፤ ይህም አንድ አገልጋይ ለጌታው የሚሰጠውን አገልግሎት ለእግዚአብሔር ለመታዘዝ መስጠት ጋር በንጽጽር የቀረበ ተለዋጭ ዘይቤ ነው

ባዕድ፣ መጻተኛ

“ባዕድ” ወይም “መጻተኛ” የሚለው ከራሱ አገር ውጪ የሚኖርን ሰው ያመለክታል። በተለይም ብሉይ ኪዳን ውስጥ ከራሱ ሕዝብ መካከል ወጥቶ ሌላ ሕዝብ ጋር የሚኖር ሰው ማለት ነው።

  • መጻተኛ በቋንቋም ሆነ በባሕሉ የተለየ ሰው ነው።
  • ክርስቶስን ከማወቃቸው በፊት ለእግዚአብሔር ኪዳን፣ “መጻተኞች” እንደ ነበሩ ሐዋርያው ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች ይጽፋል።
  • “መጻተኛ” የሚለውን ቃል፣ “ከሌላ አገር የመጣ” ብሎ መተርጎም ይቻላል፤ እንዲህ ሲባል ግን እናንተ የማታውቁት ሰው ሁሉ ማለት እንዳልሆነ መረዳት ይኖርባችኋል።

ባድማ፣ ወና ማድረግ

“ባድማ” ወይም “ወና ማድረግ” መኖሪያ የነበረውን ከእንግዲህ መኖሪያ እስከማይሆን ድረስ አንድ ቦታ ማጥፋት መደምሰስ ማለት ነው።

  • ሰውን አስመልክቶ ጥቅም ላይ ከዋለ፣ “ባድማ” ጥፋትን፣ ብቸኝነትንና ሐዘንን ያመለክታል።
  • “ወና ማድረግ” የሚለው ሐረግ መተው ወይም መረሳት ማለት ነው።
  • እህል ሲያበቅል የነበረ ቦታ ባድማ ከሆነ ተባይችን ወይም ወራሪ ሠራዊትን የመሳስሉ እህሉን የሚያጠፉ ነገሮች አሉ ማለት ነው።
  • “ባድማ አካባቢ” ጥቂት እህል ወይም አትክልት ብቻ የሚያድጉበት በመሆኑ ብዙ ሰዎች የማይኖሩበት ቦታ ማለት ነው።
  • ማኅበረ ሰቡ ያገለላቸው የቆዳ በሽታ ያለባቸው ሰዎችና የመሳሰሉትና አደገኛ አራዊት የሚኖሩበት “ባድማ ምድር” ወይም “ጠፍ መሬት” ይባላል።
  • አንድ ከተማ “ወና ሆኖአል” ከተባለ ሕንፃዎች ፈራርሰዋል ወይም ተሰርቀዋል፤ ሕዝቡም በምርዶ ተወስደዋል ማለት ነው። ከተማው ባዶ ሆኖአል፤ ሁሉም ነገር ወድሞአል ማለት ነው። ይህ ማውደም፣ ማጥፋት ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ትርጕም ቢኖረውም፣ የበለጠ አጽንዖት የሚሰጠው ባዶ መሆኑን ነው።
  • እንደ ዐውዱ ሁኔታ፣ “ጥፋት” ወይም፣ “ውድመት” ወይም፣ “መደምሰስ” ወይም፣ “የተተወና ፈላጊ የሌለው” ተብሎ መተርጎም ይችላል።

ቤተ መቅደስ

ቤተ መቅደስ እስራኤል ለጸሎትና ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ለማቅረብ የሚሰበሰቡበት ዙሪያውን በተከበበ አደባባይ ውስጥ ያለ ሕንፃ ነው። ቤተ መቅደስ የነበረው ኢየሩሳሌም ከተማ ውስጥ ባለው የሞሪያ ተራራ ነበር።

  • አብዛኛውን ጊዜ፣ “ቤተ መቅደስ” የሚለው ቃል ዋናውን ሕንፃ የሚከብባትን አደባባዮች ጨምሮ መላውን ሕንፃ ያመለክታል። አንዳንዴ የሚያመለክተው ውስጡ የሚፈጸመውን አምልኮ ሳይሆን ሕንፃውን ብቻ ነው።
  • የቤተ መቅደስ ሕንፃ ቅድስትና ቅድስተ ቅዱሳን የሚባሉ ሁለት ክፍሎች ነበሩት።
  • ቤተ መቅደሱ የእርሱ ማደሪያ እንደ ሆነ እግዚአብሔር ተናግሯል።
  • መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው ከመኖሩ የተነሣ በክርስቶስ ያመኑ ሰዎች “የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ” ተብለው ተጠርተዋል።

ቤተ መንግሥት

“ቤተ መንግሥት” ከቤተሰቡና ከአገልጋዮቹ ጋር ንጉሥ የሚኖርበት ሕንፃ ወይም ቤት ማለት ነው።

  • አዲስ ኪዳን እንደሚነግረን ሊቀካህናቱም የሚኖረው በቤተ መንግሥት ነበር።
  • ቤተ መንግሥቶች በጣም ያጌጡ፣ ሕንፃዎቻቸው ያማሩና ውስጣቸው ያለው ዕቃም የተሟላ ነበር።
  • የቤተመንግሥት ሕንፃዎችና ዕቃዎቻቸው ከድንጋይ ወይም ከእንጨት የተሠሩ ቢሆንም አብዛኛውን ጊዜ በጣም ውድ በሆኑ እንጨቶች፣ ወርቅ ወይም የዝሆን ጥርስ ይለበጡ ነበር።
  • አብዛኛውን ጊዜ በርካታ ሕንፃዎችና አደባባዮች በሚኖሩት ቤተ መንግሥት ውስጥ ሌሎች ብዙ ሰዎችም ይኖራሉ፤ እዚያም ይሠራሉ።

ቤተሰብ

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቤተሰብ በዚህ ዘመን፣ “የሩቅ” ቤተሰብ የምንለውን ጨምሮ በጋብቻ ወይም በመወለድ የተዛመዱ ሰዎች መኅበረሰብ ነው።

  • የአይሁድ ቤተሰብ በአምልኮና በአስተምህሮ አማካይነት ከአንዱ ወደሌላው የሚተላለፍ ባሕል ያለው ሃይማኖታዊ ማኅበረሰብ ነው።
  • ብዙውን ጊዜ የቤተሰቡ ዋና ባለሥልጣን የሚሆነው አባት ነው።
  • ቤተሰብ ሲባል፣ አገልጋዮችን፣ የሩቅ ዘመዶችን ሌላው ቀርቶ ቤት ውስጥ ያሉ ባዕድ ሰዎችንም ያካትታል።
  • አንዳንድ ቋንቋዎች “ነገድ” ወይም፣ “ጎሳ” የተሰኘ ሰፋ ያለ ቃል ይጠቀሙ ይሆናል፤ እየተናገረ ያለው ከወላጆችና ከልጆች ውጪ ስላሉት ከሆነ በዐውዱ መሠረት በእነዚህ ቃሎች መጠቀም ተገቢ ነው።

ቤተሰብ

“ቤተ ሰብ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የቤተ ሰብ አባሎችንና ያሉዋቸውን አገልጋዮች ጨምሮ አንድ ቤት ውስጥ አብረው የሚኖሩ ሰዎችን ሁሉ ነው።

  • አንድ ሰው ቤተ ሰብ የሚያስተዳድር ከሆነ በንብረት ላይ ኀላፊ እንደ መሆን ሁሉ እዚያ ያሉ አገልጋዮች መምራትንም ይመለክታል።
  • አንዳንዴ፣ “ቤተ ሰብ” ቀዳሚ አባቶችንና ዘሮችን ጨምሮ የቤተ ሰቡን ሁሉ የዘር ሐረግ ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ማመልከት ይችላል።

ቤት

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙውን ጊዜ፣ “ቤት” ጥቅም ላይ የዋለው በምሳሌያዊ መልኩ ነው።

  • አንዳንዴ፣ አንድ ቤት ውስጥ አብሮ የሚኖሩ ሰዎችን የምያመለልክት፣ “ቤተ ሰብ” እንደ ማለት ይሆናል።
  • ብዙ ጊዜ፣ “ቤት” የአንድን ሰው ቅድመ አባቶች፣ ዘሮች ወይም ዘመዶች ያመለክታል፤ ለምሳሌ፣ “የዳዊት ቤት” እንደሚለው።
  • “የእግዚአብሔር ቤት” እና፣ “የያህዌ ቤት” የተሰኘው ሐረግ መገናኛውን ድንኳን ወይም ቤተ መቅደስን ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላል። በጠቅላላው እግዚአብሔር ያለበትን ወይም የሚኖርበትን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።
  • ዕብራውያን 3 ላይ፣ “የእግዚአብሔር ቤት” ሲል እንደ ተለዋጭ ዘይቤ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ወይም የበለጠ ጠቅለል ባለ መልኩ መላውን የእስራኤልን ሕዝብ ወይም በሰሜናዊው የእስራኤል መንግሥት ያሉ ነገዶችን ለይቶ ማመልከቱ ነው።

ብልሹ፣ ብልሽት

“ብልሹ” እና፣ “ብልሽት” የሰዎችን ክፋትና ግብረ ገባዊ ዝቅጠት ያመለክታል።

  • ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “ብልሹ” ማለት፣ “የተጣመመ” ወይም በግብረ ገባዊ ይዞታው “የወደቀ” ማለት ነው።
  • ብልሹ ሰው ከእውነት ወደ ኋላ የተመለሰና ወራሳ ወይም ጸያፍ ነገሮችን የሚያደርግ ሰው ነው።
  • አንድን ሰው ማበላሸት ወራዳና ጸያፍ ነገሮች እንዲያደርግ በዚያ ሰው ላይ ተጽዕኖ ማድረግ ማለት ነው።

ብልት፣ ክፍል

ብልት ወይም ክፍል የአንድ ሕንፃ፣ አካል ወይም ቡድን አንድን ክፍል ያመለክታል።

  • አዲስ ኪዳን ክርስቲያኖችን የክርስቶስ አካል፣ “ብልቶች” ይላቸዋል። በክርስቶስ የሚያምኑ ከተለያዩ ብዙ ብልቶች የተሠራው አካል ወገን ናቸው።
  • ኢየሱስ ክርስቶስ የአካሉ፣ “ራስ” ሲሆን እያንዳንዱ አማኝ እንደ አካሉ ብልቶች ይሠራሉ። መላው አካል በሚገባ መሥራት እንዲችል መንፈስ ቅዱስ ለእያንዳንዱ የአካሉ ብልት ትክክለኛ ቦታውን ይሰጠዋል።
  • የአይሁድ ሸንጎና የፈሪሳውያንን በመሳሰሉ ቡድኖች ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው ግለ ሰቦች የእነዚያ ቡድኖች “ብልቶች” ተብለዋል።

ብልጥ

“ብልጥ” በተለይ ተግባራዊ በሆኑ ነገሮች በጣም ብልህና አስተዋይ ሰው ነው

  • ብዙ ጊዜ፣ ብልጥ ሰው ከሌሎች ይልቅ ራሱን መጥቀም ላይ ያተኩራል
  • ብዙውን ጊዜ ራስ ወዳድነትንም የሚያመለክት በመሆኑ፣ “ብልጥ” የሚለው ቃል በከፊልም ቢሆን አሉታዊ ትርጉም አለው
  • ይህን ቃል ለመተርጎም፣ “ብልህ” ወይም፣ “አስተዋይ” ወይም፣ “ዘዴኛ” ማለት ይቻላል

ብሔር፣ ሕዝብ

“ብሔር” አብዛኛውን ጊዜ የሚያመለክተው ከአንድ ቅድመ አባት የተገኙትን ትውልዶችንና ተመሳሳይ ቋንቋና ባሕል ያላቸው ሰዎች ነው።

  • የብሔር አባሎች አብዛኛውን ጊዜ በአንድ ምድር ወይም አገር በአንድነት ይኖራሉ።
  • የሕዝብ ስብስብ ከአንድ ወይም ከብዙ ነገዶች የተገኙ ሊሆኑ ይችላሉ።
  • “ብሔር” አንዳንዴ፣ “ሕዝብ” ተብሎ ቢተረጎምም ሁለቱም ሁሌም አንድ ትርጕም የላቸው። “ብሔር” ግን የሚያመለክተው ሕዝብንና ባሕላቸውን ጭምር ነው።
  • አንዳንዴ፣ “ሕዝብ” – “ብሔር” ለማለትም ጥቅም ላይ ይውላል። ለምሳሌ፣ “ሕዝብህ” ሲባል፣ “ብሔርህ” ወይም፣ “ቤተ ሰብህ” ማለት ሊሆንም ይችላል።

ብር

ብር ሳንቲሞችን፣ ጌጣጌጦችን፣ ዕቃዎችንና ማስዋቢያዎችን ለመሥራት የሚያገለግል አንጸባራቂ ነጭ/ግራጫ መልክ ያለው የከበረ ድንጋይ ነው

  • በኢየሩሳሌም የነበረው ቤተ መቅደስ ከብር የተሠሩ ዕቃዎች ነበሩት። ባቢሎናውያን ኢየሩሳሌምን ሲወርሩና በ586 ዓቅክ አብዛኛውን እስራኤላዊ ሲይዙ እነዚህ ሁሉ በእነርሱ ተወስደዋል
  • እነዚህ ከብር የተሠሩ ዕቃዎች መካከል መጠጫዎች፣ ሳህኖችና ድስቶች እንዲሁም ሌሎች ነገሮችም ነበሩ
  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ሰቅል የሚባሉ የብር ሳንቲሞች ጥቅም ላይ ውለው ነበር
  • ኢየሱስን አሳልፎ በመስጠቱ ይሁዳ 30 ጥሬ ብር ተከፍሎት ነበር

ብርሃን

መጽሐፍ ቅዱስ “ብርሃን” የሚለውን ቃል በተለያዩ ምሳሌያዊ ገለጻዎች ይጠቀምበታል። ብዙውን ጊዜ ጻድቃን፣ ቅድስናንና እውነትን ለማመልከት እንደ ተለዋጭ ዘይቤ ያገለግላል።

  • የእግዚአብሔርን እውነተኛ መልእክት ወደ ዓለም ማምጣቱንና ሕዝቡንም ከጨለማና ከኀጢአት እንደሚያድን ለማመልከት ኢየሱስ፣ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ” አለ።
  • ክርስቲያኖች “በብርሃን እንዲመላለሱ” ታዝዘዋል፤ ያም ማለት እግዚአብሔር በሚፈልገው መንገድ መኖርና ክፋትን ማስወገድ አለባቸው ማለት ነው።
  • ሐዋርያው ዮሐንስ፣ “እግዚአብሔር ብርሃኝ” እንደ ሆነና በእርሱ ጨለማ እንደሌለ ጽፏል።
  • ብርሃንና ጨለማ ፍጹም ተቃራኒ ናቸው። ጨለማ ምንም ዐይነት ብርሃን ያለ መኖር ማለት ነው።
  • እርሱ፣ “የዓለም ብርሃን” እንደ ሆነና ተከታዮቹም እግዚአብሔር ምንኛ ታላቅ መሆኑን በሚያሳይ መንገድ እየኖሩ በዓለም ውስጥ እንደ ብርሃን ማንጸባረቅ እንደሌለባቸው ኢየሱስ ተናግሮአል።
  • “በብርሃን መመላለስ” መልካምና ትክክል የሆነውን በማድረግ እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ መንገድ መኖርን ይወክላል። በጨለማ መመላለስ በእግዚአብሔር ላይ እያመፁ መኖርንና ክፉ ነገሮችን ማድረግን ይወክላል።

ብርቱ፣ ብርታት

  • “ብርቱ” እና፣ “ብርታት” የሚያመለክቱት ታላቅ ኀይል ወይም ጥንካሬን ነው።
  • “ኀያላን ሰዎች” ብዙውን ጊዜ የሚያመለክተው ደፋሮችና በጦርነት አሸናፊ የሆኑትን ነው። እግዚአብሔር ራሱም፣ “ብርቱ” ተብሏል።
  • “ብርቱ (ታላላቅ) ሥራዎች” የሚለው ሐረግ አብዛኛውን ጊዜ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ያደረጋቸው ድንቅ ነገሮችን በተለይም ተአምራትን ነው።
  • ከዚሁ ጋር “ሁሉን ቻይ” የሚል መያያዙ የተለመደ የእግዚአብሔር መገለጫ ሲሆን የእርሱን ፍጹም ኀይል ያመለክታል።

ብርታት፣ ማበርታት

“ብርታት” የሚለው ቃል አካላዊ፣ ስሜታዊ ወይም መንፈሳዊ ጥንካሬን ነው። ማበርታት አንድን ሰው ወይም ነገር ጠንካራ ማድረግ ማለት ነው

  • “ብርታት” በተቃውሞ ውስጥ ጸንቶ መቆምን ሊያመለክት ይችላል
  • አንድ ሰው ለፈተና ካልተሸነፈ ያ ሰው ብርቱ ነው ይባላል
  • አንድ የመዝሙሮች ጸሐፊ ያህዌ ብርታቱ እንደሆነ ተናግሯል፤ ይህም ብርቱ እንዲሆን ያህዌ ይረዳዋል ማለት ነው
  • አጥርን ወይም ቤትን የመሳሰሉ ሕንፃዎች እንዲበረቱ ከተደረገ ማንኛውንም ጥቃት መቋቋም እንዲችሉ በብዙ ድንጋዮችና ሸክላዎች ተጠናክረዋል ማለት ነው

ብቁ፣ ብቁ መሆን

“ብቁ” የሚለው ቃል የተወሰኑ ጥቅሞችን ለመቀበል ወይም የተለያዩ ሙያዎች ባለቤት የመሆንን ዕውቅትና ማግኘት ማለት ነው።

  • አንድ ዐይነት ሥራ ለመሥራት፣ “ብቁ” የሆነ ሰው ያንን ለማድረግ የሚያስችለው ሙያ ወይም ሥልጠና አለው ማለት ነው።
  • ለቆላስይስ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ እግዚአብሔር አማኞችን የብርሃን መንግሥቱ ተካፋዮች እንዲሆኑ እንዳደረጋቸው ጽፏል።
  • አንድ አማኝ በራሱ የእግዚአብሔር መንግሥት አካል የመሆንን መብት አያገኝም። ብቁ የሚሆነው በክርስቶስ ደም እግዚአብሔር የዋጀው በመሆኑ ብቻ ነው።

ተመስጦ

ተመስጦ የሚባለው ሰውየው እንቅልፍ ላይ ባይሆንም፣ አንድ ሌላ ነገር እየተመለከተ ወይም እየተለማመደ ከመሆኑ የተነሣ በዙሪያው ስላለው ነገር ግንዛቤ የሚያጣባት የአእምሮ ዝንባሌ ነው።

  • አዲስ ኪዳን ውስጥ ይህ ቃል እግዚአብሔር በራእይ በተናገራቸው ጊዜ ጴጥሮስና ጳውሎስ የነበራቸውን ልዕለ ተፈጥሮአዊ የአእምሮ ሁኔታ ያመለክታል።
  • ጴጥሮስና ጳውሎስ ተመስጦ ውስጥ የሆኑት እየጸለዩ እያለ ነበር።
  • ተመስጦ ውስጥ እንዲሆኑ ያደረገው እግዚአብሔር ነበር።
  • “ተመስጦ” – “ራእይ” ከሚለው ቃል የተለየ በመሆኑ፣ ትርጕሙም የተለየ መሆን አለበት።
  • “ተመስጦ ወደቀበት” ማለት ሳይተኛ ወይም ሳያንቀላፋ፣ “በድንገት እንደ እንቅልፍ ያለ ሰመመን ውስጥ ሆነ” ማለት ነው።

ተኩላ

ተኩላ አደገኛ ሥጋ በል አውሬ ሲሆን፣ ከቀበሮ ጋር ይመሳሰላል።

  • ብዙውን ጊዜ ተኩላዎች የሚያድኑት በመንጋ ሆነው ነው።
  • የሚያጠቁትን እንስሳ ለመያዝ ተኩላዎች በጣም ፈጣንና ሸማቂ ናቸው።
  • የሐሰት መምህራን ለአማኞች አደገኛ ናቸው፤ በጎችን በሚያጠቁ ተኩላዎች የተመሰሉት በዚህ ምክንያት ነው።
  • በተለይ፣ ጥሩ ጠባቂ የሌላቸው በጎች ለተኩላ ጥቂት ይጋለጣሉ።

ተዋጊ፣ ወታደር

ሁለቱም ሰራዊት ውስጥ ሆኖ መዋጋትን የሚያመለክቱ በመሆናቸው፣ “ተዋጊ” እና፣ “ወታደር” ትርጕማቸው ተመሳሳይ ነው። ያም ሆኖ ግን፣ መጠነኛ ልዩነትም አላቸው።

  • ብዙ ጊዜ፣ “ተዋጊ” የሚለው በጦር ሜዳ ልምድና ድፍረት ያለውን ሰው የሚያመለክት አጠቃላይና ሰፋ ያለ ቃል ነው።
  • በምሳሌያዊ አነጋገር ያህዌ ራሱ፣ “ተዋጊ” እንደ ሆነ ተነግሯል።
  • “ወታደር” በጣም ግልጽ በሆነ ሁኔታ በአንድ ሰራዊት ውስጥ ወይም ዐውደ ውጊያ ውስጥ የሚዋጋ ሰው ነው።
  • በትርጕምና በአጠቃቀም የተለየ ትርጕም ያላቸው ሁለት ቃላት ሊኖር መቻላቸውን ተርጓሚው ልብ ማድረግ አለበት።

ተገዢ፣ የተገዛ፣ መገዛት

“ተገዢ” የሚለው በሌላው ሰው ሥልጣን ሥር መሆንን ያመለክታል፥ “መገዛት” – “ለሌላው ሰው ሥልጣን” ታዛዥ መሆን ማለት ነው

  • “ማስገዛት” ሰዎች በመሪ ወይም በገዢ ሥልጣን ሥር እንዲሆኑ ማድረግን ያመለክታል
  • “አንድን ሰው ማስገዛት” በዚያ ሰው ላይ ቅጣትን የመሰለ አሉታዊ ነገር እንዲደርስ ማድረግ ማለት ነው
  • “መገዛት” – “መታዘዝ” ወይም፣ “እሺ ማለት” ወይም፣ “እጅ መስጠት” ማለትም ይሆናል

ታማኝነት

ይህ ቃል የሚያመለክተው ቅንነትን ሲሆን፣ ሰው ባያይ እንኳ በጠንካራ ግብረ ገባዊ መርሕና ፀባይ በመነሣሣት ታማኝ ሆኖ መገኘትን ነው።

  • ዮሴፍንና ዳንኤልን የመሳሰሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ገጸ ባሕርያት ክፉ ነገርን ባለማድርግና ይልቁንም ለእግዚአብሔር መታዘዝን በመምረጥ ታማኝነትን አሳይተዋል።
  • ታማኝ ሆኖ መደኽየት፣ ብልሹ ሆኖ ሀብታም ከምሆን እንደሚሻል መጽሐፈ መሳሌ ያመለክታል።

ታጋሽ፣ ትዕግሥት

“ታጋሽ” እና፣ “ትዕግሥት” የሚለው ቃል አስቸጋሪ የሆነ ሁኔታ መቋቋምን ወይም በዚያ ውስጥ በጽናት መኖርን ያመለክታል። አብዛኛውን ጊዜ ትዕግሥት መጠበቅንም ይጨምራል።

  • አንድን ሰው መታገሥ ያ ሰው የቱንም ያህል በደል ቢፈጽም እርሱን መውደድና ይቅር ማለት ማለት ነው።
  • ችግር ሲገጥማቸው የእግዚአብሔር ሕዝብ መታገሥና እርስ በርሳቸውም ትዕግሥተኞች መሆን እንደሚገባቸው መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል።
  • ከምሕረቱ የተነሣ ቅጣት የሚገባቸው ኀጢአተኞች ቢሆኑም እግዚአብሔር ሕዝቡን ይታገሣል።

ትልቅ ማድረግ፣ ማጉላት

ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “ትልቅ ማድረግ” ታዋቂነት እንዲያገኝ በማሰብ ወደ አንድ ሰው ወይም አንድ ነገር የሌሎችን ትኵረት መሳብ ማለት ነው።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ትልቅ ማድረግ” ሲባል ሁሌም ጥቅም ላይ የሚውለው ንጉሥን ወይም ራሱ እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ ለማድረግ ነው።
  • አንድ ሰው ራሱን ትልቅ ካደረገ ያ ሰው ትዕቢተኛ ነው፤ በጣም አስፈላጊ ሰው ሆኖ ለመታየት እየሞከረ ነው ማለት ነው። በመጨረሻው ዘመን ሰዎች እንዲያመልኩት ራሱን በጣም ትልቅ የሚያደርግ ንጉሥ እንደሚመጣ ነቢዩ ዳንኤል ይናገራል።

ትውልድ

ትውልድ የሚባለው በአንድ ዘመን የተወለደና በአንድ ዘመን የነበረ የሰዎች ስብስብ ነው።

  • ብዙውን ጊዜ ከወላጆች እስከ ልጆች ያሉ ሰዎች ናቸው።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙውን ጊዜ አንድ ትውልድ የ40 ዓመታት ዕድሜ እንዳለው ይታሰብ ነበር።

ችጋር

ችጋር በመላው አገር ወይም አካባቢ የምግብ እጥረትን የሚጨምር ጥፋት ሲስፋፋ ማለት ነው።

  • የዝናብ አለመኖርን፣ ጥሩ ያልሆነ የአየር ሁኔታን፣ የሰብል መቀጨጭ ወይም ተባዮችን በመሳሰሉ ተፈጥሮአዊ ምክንያቶች የተነሳ የምግብ እጥረት ይከሰታል።
  • ከጦርነት ወይም መልካም ካልሆነ አስተደድር የተነሣም የምግብ እጥረት ሊኖር ይችላል።
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንመለከተው በእርሱ ላይ ኀጢአት ያደረገ ሕዝብን ለመቅጣት እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ ራብ እንዲኖር ያደርግ ነበር።
  • አሞጽ 8፣11 ላይ “ራብ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው ለእነርሱ ባለመናገር ሕዝቡን ይሚቀጣበት ጊዜ እንደሚመጣ በሚያመለክት ምሳሌያዊ አነጋገር ነው።

ችግር፣ መከራ፣ ሁከት

“ችግር” የሚለው ቃል የሚያመለክተው በጣም አዳጋችና አስጨናቂ የሕይወት ልምምድን ነው። “ሁከት” ከአንዳች ንገር የተነሣ መረበሽ ወይም መጨነቅ ማለት ነው።

  • ችግር ሲባል ሰውን የሚጎዳ ማንኛውም አካላዊ፣ ስሜታዊ ወይም መንፈሳዊ ሁከት ሊሆን ይችላል።
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንመለከተው የተለያዩ ችግሮች በእምነታቸው እንዲያድጉና እንዲጠነክሩ ለመርዳት እግዚአብሔር የሚጠቀምባቸው የመከራና የፈተና ጊዜዎች ናቸው።
  • ዐመፀኛ በሆኑትና እግዚአብሔርን ችላ በሚሉ ሕዝቦች ላይ የሚመጣውን ፍርድ ለማመልከት ብሉይ ኪዳን፣ “መከራ” በሚለው ቃል ይጠቀማል።

ኀላፊ፣ ባለ ዐደራ

መጽሐፍ ቅዱስ፣ “ኀላፊ” ወይም “ባለ ዐደራ” የሚለው የጌታውን ንብረትና የሥራ እንቅስቃሴን በተመለከተ ሙሉ ኀላፊነት የተሰጠውን አገልጋይ ለማመልከት ነው።

  • ባለ አደራ በጣም ትልቅ ኀላፊነት የተሰጠው ሰው ሲሆን፣ ሌሎች አገልጋዮችን የመቆጣጠርንም ሥራ ይጨምራል።
  • ባለ አደራ ከሚለው ይልቅ፣ “ኀላፊ” የሚለው ይበልጥ በዘመኑ የተለመደ ቃል ነው፤ ሁለቱም የሚያመለክቱት የሌላው ሰው ተግባራዊ ጉዳዮችን ማስተዳደርን ነው።

ነቀፋ

ነቀፋ የአንድን ሰው ፀባይና አኗኗር መብቶች ወይም ይሁንታ መንፈግ ማለት ነው። ብዙውን ጊዜ ነቀፋ ሰውየውን በተመለከተ አሉታዊ ቃል መሰንዘር ነው።

  • አንድ ሰው፣ “ከነቀፋ በላይ” ነው ከተባለ፣ ያ ሰው እግዚአብሔርን በሚያስከብር ሁኔታ እየኖረ ነው። ስለዚህም የሚነቀፍበት ወይም የሚተችበት ነገር የለም፣ ቢኖር እንኳ በጣም ጥቂት ነው ማለት ነው።
  • “ነቀፋ” – “እፍረት” ወይም፣ “ውርደት” ተብሎ መተርጎምም ይችላል። ስለዚህም አንድን ሰው መንቀፍ እርሱን ማሳፈር ወይም ማዋረድ ነው።

ነብር

ነብር ጥቁርና ነጭ ዝንጉርጉር መልክ ያለው ትልቅ ድመት መሰል የዱር አውሬ ነው።

  • ነብር ሌሎች እንስሳትን በማደን ይበላል።
  • ቁጡና አስደንጋጭ ባሕርይ ያለው ከመሆኑ የተነሣ በድንገት የሚመጣ ጥፋት በነብር ተመስሎአል።
  • ዳንኤልና ዮሐንስ ባዩት ራእይ ውስጥ ነብር ከአውሬዎቹ አንዱ ነብር ይመስል እንደ ነበር ተነግሯል።

ነገድ

ነገድ ብዙውን ጊዜ ከአንድ ቀዳሚ አባት የተገኙ ሰዎች ስብስብ ማለት ነው።

  • ከአንድ ነገድ የወጡ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ተመሳሳይ ቋንቋና ባሕል ይኖራቸዋል።
  • ከብሉይ ኪዳን እንደምንመለከተው የእስራኤል ሕዝብ በአሥራ ሁለት ነገዶች የተከፈሉ ነበር። እያንዳንዱ ነገድ የተገኘው ከያዕቆብ ልጅ ወይም የልጅ ልጅ ነበር።
  • ነገድ ከሕዝብ ያንሳል፣ ከጎሳ ግን ከፍ ይላል።

ነጻ ማድረግ

“ነጻ ማድረግ” አንድ ሰው ከተከሰሰበት በደል ወይም ርኩሰት ነጻ መሆኑን በግልጽ መናገር ወይም ማወጅ ማለት ነው።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኃጢአተኛን ይቅር ማለትን አስመልክቶ ለመናገር ይህ ቃል ጥቅም ላይ ይውላል።
  • ብዙውን ግዜ ዐውዱ በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ያደረጉና በእርሱ ላይ ያመፁ ሰዎችን አለ አግባብ ነጻ ማድረግን ይመለከታል።
  • “ንጽህናን ማወጅ”ወይም “ከበደል ነጻ ማድረግ” ተብሎ መተርጎም ይችላል

ናስ (ነሐስ)

“ናስ” - መዳብናን ቆሮቆሮን አብሮ በማንጠር የሚሠራ አንድ ዐይነት ብረት መሳይ ነገር ነው። ጥቁር ቡኒ መልክ ቢኖረውም በመጠኑ ወደ ቀይም ወሰድ ያደርገዋል።

  • ናስ በውሃ መሸርሸርን ይከላከላል፤ ጥሩ የሙቀት አስተላላፊም ነው።
  • በጥንት ዘመን ናስ መገልገያ መሣሪያዎችን፣ የጦር ዕቃዎችን፣ የቅርጽ ሥራዎችን፣ መሠዊያዎችን፣ ድስቶችን፣ የወታደር ትጥቆችን የመሳውሰሉ ነገሮችን ለመሥራት ያገለግል ነበር።
  • የሐሰተኛ አማልክት ምስሎችም ከናስ ይሠሩ ነበር።
  • የናስ ዕቃዎች የሚሠሩት በመጀመሪያ ናሱን በማቅለጥና ፈሳሹን ቅርጽ ማውጫ ላይ በማፍሰስ ነው። ይህ ሂደት፣ “ቅርጽ ማውጣት” ይባላል።

ንስር

ንስር እንደ ዓሣ፣ አይጥ፣ እባብና ጫጩት የመሳሰሉ ትንንሽ እንስሳትን የሚመገብ በጣም ግዙፍና ብርቱ ወፍ ነው።

  • መጽሐፍ ቅዱስ የሰራዊትን ፍጥነትና ብርታት ንስር የሚመገበውን እንስሳ በፍጥነትና በድንገት ነጥቆ ከሚወስድበት ሁኔታ ጋር ያመሳስላል።
  • በእግዚአብሔር የሚተማመኑ እንደ ንስር ወደ ላይ እንደሚመጥቁ ኢሳይያስ ይናገራል። ይህ በእግዚአብሔር በመተማመንና ለእርሱም በመታዘዝ የሚገኘውን ነጻነትና ብርታት የሚያመለክት ምሳሌያዊ አነጋገር አንው።
  • ከትንቢተ ዳንኤል እንደምንመለከተው የንጉሥ ናቡከደነፆር ጸጉር ርዝመት ከንስር ላባዎች ጋር ተነጻጽሮአል፤ ይህም ከ50 ሳንቲ ሜትር የበለጠ ይረዝም ነበር ማለት ነው።

ንቀት፣ የተናቀ

“ንቀት” አንድ ሰው ለሌላው ሰው ወይም ለሌላው ነገር ክብር መንፈጉን የሚያሳይበት መንገድ ነው። ክብር የተነፈገው፣ “የተናቀ” ይባላል።

  • አንድ ሰው በግልጽ እግዚአብሔርን አለማክበሩን የሚያሳይበት መንገድ ንቀት ሲሆን፣ “ማቃለል” ወይም፣ “ማዋረድ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
  • “መናቅ” የአንድን ሰው ዋጋ ማሳነስ ወይም፣ ከራስ ይልቅ ሌላው ሰው ለምንም ነገር ተገቢ እንዳልሆነ መቍጠር ማለት ነው።
  • ንጉሥ ዳዊት ዝሙት በማድረግና ሰውን በመግደል ኃጢአት የፈጸመ ጊዜ ዳዊት እኔን ንቆአል በማለት እግዚአብሔር ተናግሮአል። እንዲህ በማድረጉ ለእግዚአብሔር ይገባ የነበረውንክብር ነፍጎአል።

ንብረት ማድረግ፣ ንብረት

“ንብረት ማድረግ” እና፣ “ንብረት” ብዙውን ጊዜ የሚያመለክቱት የአንዳች ነገር ባለቤት መሆንን ነው። አንድን ነገር ወይም አካባቢን መቆጣጠርንም ያመለክታል። አብዛኛውን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉት በዚህ መልክ ነው።

  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ ይህ ቃል ብዙውን ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው፣ የተወሰነ ቦታን፣ “መያዝ” ወይም፣ “መውሰድን” በሚያመለክት ዐውድ ውስጥ ነው።
  • ምድረ ከነዓንን፣ “ንብረት” እንዲያደርጉ ያህዌ ለእስራኤላውያን ሲናገር ወደዚያ ሄደው በምድሩ መኖር አለባቸው ማለት ነው። ይህም በመጀመሪያ እዚያ ይኖሩ የነበሩ ከነዓናውያንን ድል ማድረግን ይጨምራል።
  • ምድረ ከነዓን፣ “ንብረታቸው” እንዲሆን እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ተናግሯል፤ ይህም ማለት ከነዓናውያንን ድል በማድረግ ምድሪቱን እንዲይዙ እርሱ ይረዳቸዋል ማለት ነው፥
  • የእስራኤል ሕዝብ የያህዌ፣ “የተለዩ ንብረት ወይም ርስት” ተብለዋል። ይህም ማለት እርሱን እንዲያመልኩና በእርሱ እንዲገዙ እንደ ሕዝብ የእርሱ ሆነዋል ማለት ነው።

ንዴት

ንዴት ከቁጥጥር የወጣ ቁጣ ነው። አንድ ሰው ከተናደደ፣ አጥፊ በሆነ ሁኔታ ቁጣውን እየገለጸ ነው ማለት ነው።

  • ንዴት የሚመጣው የቁጣ ስሜት ራስን መግዛትን ሲያሸንፍ ነው።
  • ሰዎች ሲናደዱ ሌሎችን የሚጎዳ ነገር ያደርጋሉ፤ ሌሎችን የሚጎዳ ቃል ይናገራሉ።
  • “ንዴት” የሚለው፣ ኀይለኛ የባሕር ሞገድን ወይም ወጀብን ለማመልከትም ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።

ንጉሣዊ

“ንጉሣዊ” የሚለው ቃል ከንጉሥ ወይም ከልዕልት ጋር የተያያዙ ሰዎችንና ነገሮችን ማለትም ዙፋናቸውን፣ ቤተ መንግሥታቸውን፣ ልብሶቻቸውንና ልጆቻቸውን ይመለክታል።

  • “ንጉሣዊ” ተብሎ ለሚጠሉ ነገሮች ምሳሌ የሚሆኑን ነገሮች የንጉሥ ልጆችን፣ ልብሶችን፣ ቤተ መንግሥቶችን፣ ዙፋኖችንና አክሊሎችንም ያካትታል።
  • ቤተ መንግሥት ንጉሥ ወይም ንግሥት የሚኖሩበት በጣም የሚያምር ልዩ መኖሪያ ነው።
  • ንጉሡ፣ አንዳንዴ “ንጉሣዊ” ልብስ ተብሎ የሚጠራ ልዩ ልብስ ይለብሳል። ብዙ ጊዜ ንጉሥ በጣም ውድ የሆነውንና በቅ አላሉ የማይገኘውን ሐምራዊ ቀለም የተነከረ ልብስ ይለብሳል።

ንጉሥ

ንጉሥ የአንድ ነጻ ከተማ፣ መንግሥት ወይም አገር መሪ ነው።

  • አንዳንዴ አንድ ሰው ንጉሥ የሚሆነው ንጉሣቸው እንዲሆን የተወሰኑ ሰዎች ቡድን ሲመርጠው ነው።
  • አንዳንዴ በእርሱ ቦታ ንጉሥ ለመሆን በማሰብ ሰዎች ንጉሥን ይገድላሉ።

ንጹሕ ያልሆነ

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ንሑሕ ያልሆነ” የሚለው ምሳሌያዊ አነጋገር የሚያመለክተው ሕዝቡ ሊነካው፣ ሊበላው ወይም መሥዋዕት ሊያቀርበው እንደማይገባው እግዚአብሔር የተናገረለት ነገርን ነው።

  • እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን የትኛው እንስሳ ንጹሕ፣ የትኛው እንስሳ ንጹሕ እንዳልሆነ መመሪያ ሰጥቷል። ንጹሕ ያልሆኑ እንስሳት እንዲበሉ ወይም መሥዋዕት እንዲቀርቡ አልተፈቀደም።
  • አንዳንድ ዐይነት የቆዳ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ከዚያ እስኪፈወሱ ድረስ ንጹሕ እንዳልሆኑ ይቆጠሩ ነበር።
  • እስራኤላውያን ንጹሕ ያልሆነ ነገር ከነኩ ለተወሰነ ወቅት እነርሱ ራሳቸው ንጹሕ እንዳልሆኑ ይቆጠሩ ነበር።
  • ንጹሕ ያልሆነ ነገርን ባለመንካትና ባለመብላት ለእግዚአብሔር መታዘዝ እስራኤላውያንን ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለዩ ያደርጋቸው ነበር።
  • ይህ አካላዊና ሥርዓታዊ ንጹሕ አለመሆን፣ የግብረ ገባዊ ርኩሰት ምሳሌ ነበር።
  • በሌላ ምሳሌያዊ አነጋገር፣ “ንጹሕ ያልሆነ/ርኩስ” መንፈስ ክፉ መንፈስን ያመለክታል።

አህያ፣ በቅሎ

አህያ ከፈረስ የሚያንስና ትላልቅ ጆሮዎች ያሉ ፈረስን የሚመስል ባለ አራት እግር አገልጋይ እንስሳ ነው።

  • በቅሎ ከወንድ አህያና ከሴት ፈረስ የምትወለድ መሐን እንስሳ ናት።
  • በቅሎዎች ብርቱ እንስሳት በመሆናቸው ለተለያየ አገልግሎት ከፍ ያለ ጥቅም አላቸው።
  • አህዮችና በቅሎዎች ዕቃዎችንና ሰዎን ለመሸከም ያገልግላሉ።
  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን በሰላም ጊዜ ንጉሦች ያሚጓዙት በአህያ ሲሆን፣ በጦርነት ጊዜ የሚጓዙት በፈረስ ነበር።
  • ከመስቃሉ አንድ ሳምንት በፊት ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም የገባው በአህያ ውርንጭላ ተቀምጦ ነበር።

አለመታዘዝ፣ የማይታዘዝ

“አለመታዘዝ” ሥልጣን ላይ ያለ ሰው ትእዛዝን ወይም መመሪያን አለመቀበል ማለት ነው። ይህን የሚያደርግ ሰው የማይታዘዝ ይባላል።

  • ማድረግ የሌለበትን የሚያደርግ ሰው ታዛዥ አይደለም።
  • የታዘዙትን አለማድረግ አለመታዘዝ ነው።
  • ሆን ብሎ የታዘዘውን የማያደርግ ዐመፀኛ ሰው፣ “የማይታዘዝ” ይባላል።
  • “የማይታዘዙ ሰዎች” የሚለውን፣ “ዐመፀኞች” ወይም፣ “እግዚአብሔር ያዘዘውን የማያደርጉ” ብሎ መተርጎም ይቻላል።

አለቃ፣ ዋና

“አለቃ” የሚለው ቃል በተወሰኑ አካል ላይ ከፍ ያለ ሥልጣን ያለውን ወይም በጣም አስፈላጊ መሪን ያመለክታል።

  • ለዚህ ምሳሌ የሚሆኑ፣ “የሙዚቀኞች፣ የመዘምራን አለቃ” “የካህናት አለቃ” እና፣ “የግብር ሰብሳቢዎች አለቃ” እና “መሪ አለቃ” የተሰኙትንም ይጨምራል።
  • ዘፍጥረት 36 ላይ አንዳንድ ሰዎች የቤተ ሰባቸው ወይም የጎሳቸው፣ “አለቃ” ተብለው እንደ ተጠሩ የአንድ የተወሰነ ቤተ ሰብን ራስ ወይም መሪ ያመለክታል። እንዲህ ሲሆን፣ “መሪዎች” ወይም፣ “ራሶች” ተብሎ መተርጎም ይችላል ወይም፣
  • ስምን ለማመልከት ጥቅም ላይ ከዋለ፣ “ሙዚቀኞችን፣ መዘምራንን የሚመራ” ወይም፣ “ካህናትን የሚያስተዳድር” እንደሚለው፣ “የሚመራ” ወይም፣ “የሚገዛ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፥

አለአግባብ፣ አግባብ ያልሆነ፣ ፍትሕ ማጉደል

“አለ አግባብ” እና፣ “አግባብ ያልሆነ” የተሰኙት ቃሎች ሰዎችን መግፋት፣ ማሳዘን፣ ብዙውን ጊዜ በጣም በሚጎዳ ሁኔት መበደል ማለት ነው።

  • “ፍትሕ ማጉደል” ለሰዎች ከሚገባው ውጪ እነርሱ ላይ መጥፎ ነገር ማድረግ ማለት ነው። አለአግባብ ሰዎችን መጉዳትን ያመለክታል።
  • አንዳንዶች በአግባቡ ሲስተናገዱ ሌሎችን አለአግባብ ማስተናገድም፣ “ፍትሕ ማጉደል” ነው።
  • አግባብ ባልሆነ መንገድ የሚንቀሳቀስ ሰው፣ “አድልዎ” ያደርጋል፤ ሰዎችን ዕኩል ባለ ማስተናገድም፣ “መጥፎ ተፅዕኖ” ይፈጽማል።

አማኝ

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “አማኝ” ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ መሆኑን የሚያምንና የሚደግፍ ማለት ነው

  • አማኝ ቃል በቃል፥ “የሚያምን ሰው” ማለት ነው
  • በክርስቶስ የሚያምኑና ለቃሉ የሚታዘዙ በመሆናቸው የኋላ ኋላ “ክርስቲያን” የሚለው ቃል የአማኞች ዋና መጠሪያ ሆን

አሥረኛ፣ አሥራት

“አሥረኛ” ወይም፣ “አሥራት” የተሰኙት ቃሎች የአንድን ሰው ገንዘብ፣ እህል፣ የቤት እንስሳት ወይም ሌሎች ንብረቶች አንድ አሥረኛ ክፍል ያመለክታል።

  • በብሉይ ኪዳን ዘመን ለእርሱ ምስጋና እንዲሆን ካላቸው ነገር ሁሉ አንድ አሥረኛውን እንዲሰጡ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ተናግሮአል።
  • ይህ ስጦታ በካህንነትና መገናኛ ድንኳኑን ወይም ቤተ መቅደሱን በመጠበቅ እስራኤላውያንን ያገለግሉ ለነበሩ ሌዋውያን መደጎሚያ ይውላል።
  • አዲስ ኪዳን ለእግዚአብሔር አሥራት እንዲሰጥ አያዝም፤ ይሁን እንጂ ክርስቲያናዊ አገልግሎትንና ድኾችን መርጃ እንዲሆን በልግስናና በቸርነት መስጠትን አጽንዖት ይሰጣል።
  • ይህ፣ “አንድ አሥረኛ” ወይም፣ “ከአሥር አንድ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

አሥሩ ትእዛዞች

እግዚአብሔር ለሙሴ እስራኤል ሊታዘዟቸው የሚገባ ብዙ ትእዛዞች ሰጥቶታል። ከእነዚህ ትእዛዞች አሥሩን በሁለት የድንጋይ ጽላቶች ላይ ጽፏቸዋል።

  • አሥሩ ትእዛዞች እስራኤላውያን እግዚአብሔርን እንዲወዱና እንዲያመልኩት፣ ሌሎች ሰዎችንም እንዲወዱ ለመርዳት የታሰቡ ልዩ ትእዛዞች ናቸው።
  • እነዚህ ትእዛዞች እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያደረገው ኪዳን አካል ናቸው። እግዚአብሔር እንዲያደርጉ ለሰጣቸው ትእዛዝ ከታዘዙ እግዚአብሔርን መውደዳቸውንና የእርሱ መሆናቸውን ያሳያሉ።

አሥራ ሁለት የእስራኤል ነገዶች

አሥራ ሁለት የእስራኤል ነገዶች የተባሉት የያዕቆብ ልጆችና የእነርሱ ዘሮች ናቸው።

  • ያዕቆብ የአብርሃም የልጅ ልጅ ነበር፤ በኋላ እግዚአብሔር ስሙን እስራኤል አለው።
  • የነገዶቹ ስም፣ ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ዳን፣ ንፍታሌም፣ ጋድ፣ አሴር፣ ይሳኮር፣ ዛብሎን፣ ዮሴፍና ብንያም ናቸው።
  • እግዚአብሔርንና ሕዝቡን ለማገልገል የተለዩ የካህናት ነገድ በመሆናቸው፣ የሌዊ ነገድ ከነዓን ውስጥ ምንም ርስት አልተሰጣቸውም ነበር።
  • ዮሴፍ በሁለት ልጆቹ ማለት በኤፍሬምና በምናሴ በኩል ዕጥፍ የርስት ድርሻ ተቀብሏል።
  • የነገዶቹ ዝርዝር መጠነኛ ልዩነት የተደረገላቸው ክፍሎች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሉ። ለምሳሌ አንዳንድ ጊዜ ሌዊ፣ ዮሴፍ ወይም ዳን ዝርዝሩ ውስጥ አይገኙም፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሁለቱ የዮሴፍ ልጆች ኤፍሬምና ምናሴ ዝርዝሩ ውስጥ ይካተታሉ።

አረማዊ

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “አረማዊ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው ያህዌን ሳይሆን ሐሰተኛ አምላኮችን የሚያመልኩ ሰዎች ለማመልከት ነበር።

  • ከእነዚያ ሰዎች ጋር የተያያዘ ማንኛውም ነገር ማለትም የሚያመልኩበት መሠዊያ፣ የሚፈጽሙት ሃይማኖታዊ ሥርዓትና እምነታቸው ጭምር፣ “አረማዊ” ይባላል።
  • የአረማውያን እምነት ተፈጥሮን ወይም ከአንዱ እውነተኛ አምላክ ከያህዌ ውጪ ብዙ አምላኮች ማምለክንም ይጨምራል።
  • አንዳንድ የአረማውያን ሃይማኖቶች የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚደረግበት አምልኮን ወይም እንደ አንድ የአምልኳቸው ክፍል ሰዎችን መሥዋዕት ማቅረብንም ያካትታል።

አሳልፎ መስጠት (መካድ)፣ አሳልፎ ሰጪ (ካጂ)

“አልፎ መስጠት” (መካድ) ሌላውን ሰው የሚያሳስትና የሚጎዳ ተግባር ነው። “አሳልፎ ሰጪ” (ካጂ) የተማመነበትን ወድጁን አሳልፎ የሚሰጥ ወይም የሚክድ ሰው ነው።

  • ኢየሱስን እንዴት አድርጎ እንደሚያስይዘው ለአይሁድ መሪዎች ተናግሮ ስለ ነበር ይሁዳ፣ “አሳልፎ ሰጪ” (ካጂ) ነው።
  • በተለይ ይሁዳ ኢየሱስን አሳልፎ መስጠቱ በጣም የከፋ ወንጀል ነበር፤ ምክንያቱም ምንም እንኳ እርሱ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ቢሆንም የኋላ ኋላ ትክክል ላልሆነው የኢየሱስ መገደል ምክንያት የሆነውን መረጃ ለአይሁድ መሪዎች ይሰጥ ነበር፤ ለዚህ ተግባሩም ገንዘብ ይቀበል ነበር።

አስማት፣ አስማተኛ

“አስማት” ከእግዚአብሔር ከሚመጣው ውጪ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ኀይል መለማመድ ወይም መጠቀም ነው። አስማት የሚለማመድ ሰው አስማተኛ ይባላል።

  • እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በግብፅ ተአምራዊ ነገሮችን ባደረገ ጊዜ፣ የፈርዖን አስማተኞችም አንዳንድ ተመሳሳይ ነገሮች አድረገው ነበር፤ ይሁን እንጂ ያንን ያደረጉበት ኀይል ከእግዚአብሔር የመጣ አልነበረም። በሙሴ በኩል እግዚአብሔር ያደረጋቸው ተአምራዊ ነገሮችን በማድረግ አልዘለቁም።
  • ብዙውን ጊዜ አስማት አንድ ዐይነት ልዕለ ተፈጥሮአዊ ነገር እንዲሆን መድገምን ወይም ማነብነብንም ይጨምራል።
  • ከመንፈሳዊው ዓለም መረጃ ለማግኘት አረማውያን አስማተኞች የእንስሳት ሆድ ዕቃ ማንበብን፣ የእንስሳትን አጥንት መሬት ላይ በመጣል ሁኔታዎችን መገምገምን የመሳሰሉ የተለያዩ ነገሮች ያደርጋሉ።
  • አስማተኞቹ እነዚህ ሁኔታዎች ከሐሰተኛ አምላካቸው ያገኙዋቸው ምልክቶች እንደ ሆኑ በማሰብ ይተረጕሟቸዋል።
  • ከእነዚህ አስማታዊ ነገሮች አንዱንም እንኳ እንዳያደርጉ እግዚአብሔር ሕዝቡን አዝዟል።

አስቀድሞ ማወቅ

ቃሉ የሚያማለክተው ገና ከመሆኑ በፊት አንድን ነገር ማወቅን ነው።

  • እግዚአብሔር በጊዜ አይወሰንም። ባለፈው ጊዜ፣ አሁንና ወደ ፊት የሚሆነውን ሁሉ ያውቃል።
  • በተለይ ቃሉ ጥቅም ላይ የዋለው ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝ አድርጎ በመቀበል የሚድኑ ሰዎችን እግዚአብሔር አስቀድም የሚያውቅ መሆኑን ከማመልከት አንጻር ነው።

አስተማሪ

አስተማሪ ለሌሎች ሰዎች አዲስ መረጃ የሚሰጥ ሰው ነው። አስተማሪዎች ሰዎች ዕውቀትና ሙያ እንዲያገኙ ይረዳሉ

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “መምህር” ስለ እግዚአብሔር የሚያስተምርን ሰው በሚያመለክት የተለየ መልኩ ጥቅም ላይ ውሏል
  • ከመምህር ዕውቀት የሚገበዩ ሰዎች “ተማሪዎች” ወይም፣ “ደቀመዛሙርት” ይባላሉ

አስተምህሮ

ቃል በቃል ሲወሰድ አስተምህሮ ትምህርት በተለይም ሃይማኖታዊ ትምህርት ማለት ነው።

  • ከክርስቲያናዊ ትምህርት አንጻር አስተምህሮ፣ ስለ እግዚአብሔር አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ማለትም የእርሱን ባሕርይና እርሱ ያደረገውን ሁሉ የሚያካትት ትምህርት ነው።
  • ክርስቲያኖች እርሱን የማያስከብር የተቀደሰ ሕይወት እንዴት መኖር እንደሚችሉ እግዚአብሔር ያስተማረው ማንኛውም ትምህርት ነው።
  • አስተምህሮ የሚለው ቃል አንዳንዴ ከሰዎች የሚመጣ ሐሰተኛ የዓለም ሃይማኖቶችን ትምህርት ለማመልከትም ጥቅም ላይ ይውላል። ቃሉ ጥቅም ላይ የዋለበት ዐውድ ትርጕሙን ግልጽ ያደርገዋል።
  • በቀላል አነጋገር አስተምህሮ ትምህርት ማለት ነው።

አስተዳደር፣አስተዳዳሪ

“አስተዳደር” እና “አስተዳዳሪ” የተሰኙት ቃሎች የአንድ አገር ሰዎች ሥርዓት ባለው መንገድ እንዲኖሩ መምራትን ወይም ማስተዳደርን ያመለክታል።

  • ዳንኤልና ሌሎች ሦስት አይሁዳውያን ወጣቶች በተወሰኑ የባቢሎን ክልሎች አስተዳዳሪዎች ፥ወይም የመንግሥት ባለ ሥልጣናት፣ እንዲሆኑ ተሹመው ነበር
  • አዲስ ኪዳን ውስጥ “አስተዳደር” የተሰኘው ቃል ከመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አንዱን ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል ሕንፃዎችና ሌሎች ንብረቶች እንደ መቆጣጠርና መጠበቅ ሁሉ ሰዎችን መምራትና ማስተዳደርም ይችላል።

አባት፣ ጥንተ አባት

ቃል በቃል ከተወሰደ፣ “አባት” የአንድ ሰው ወንዱ ወላጅ ማለት ነው። ይህን ቃል በተመለከተ በርካታ ምሳሌያዊ አነጋገሮች አሉት።

  • ብዙውን ጊዜ፣ “አባት” ወይም “ጥንተ አባት” የተሰኙ ቃሎች ጥቅም ላይ የሚውሉት በቀድሞ ዘመን የነበሩ ጥንታውያን ወላጆችን ለማማልከት ነው።
  • “የ…አባት” የሚለው አገላለጽ የአንድ አገር መሪ ወይም መሥራችን የሚያመለክት ምሳሌያዊ አነጋገር ነው። ለምሳሌ ዘፍጥረት 4 ላይ፣ “እርሱም በድንኳን ውስጥ ለሚቀመጡ ሁሉ አባት ነበር” ሲል፣ “ድንኳን ውስጥ ለመኖር የመጀመሪያ ለሆኑት ሕዝቦች ጎሳ መሪ” ማለት ሊሆን ይችላል።
  • ሐዋርያው ጳውሎስ ወንጌልን በማካፈል ክርስቲያን እንዲሆኑ የረዳቸው ሰዎች “አባት” በማለት በምሳሌያዊ መልኩ ራሱን ይጠራል።

አባቶች (ርዕሳነ አበው)

ብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ “አባቶች” ለሚለው ቃል የሚያመለክተው የአይሁድ ሕዝቡ መሥራች የሆኑትን አባቶች (ርዕሳነ አበው) በተለይም አብርሃም፣ ይስሐቅንና ያዕቆብን ነው።

  • 12ቱ የእስራኤል ነገዶች የሆኑትን 12ቱን የያዕቆብ ልጆችንም ያመለክታል።
  • “አባቶች” የሚለው ቃል፣ “የቀደሙ አባቶች” ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ትርጕም ቢኖረውም፣ ይበልጥ የሚያመለክተው ግን በጣም የታወቁ የነገድ የሕዝብ ስብስብ መሪዎችን ነው።

አንበሳ

አንበሳ እጁ የገባውን የሚገድልበትና የሚግነጣጥልበት ጥርሶችና ጥፍሮች ያሉት ባለ አራት እግር ትልቅ የዱር አውሬ ነው።

  • አንበሶች የሚያድኑትን እንስሳ ለመያዝ የሚያስችላቸው ብርቱ አካልና ታላቅ ፍጥነት አላቸው።
  • ወንዶቹ አንበሶች ራሳቸው ዙሪያ ጎፈር አላቸው።
  • አንበሶች ለምግብ ሌሎች እንስሳትን ይገድላሉ፤ ለሰዎችም ቢሆን አደገኛ ሊሆኑይችላሉ።
  • ንጉሥ ዳዊት ወጣት በነበረ ጊዜ ይጠብቃቸው የነበሩ በጎች ለመታደግ አንበሶች ገድሎ ነበር።

አንበጣ

“አንበጣ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው አንዳንዴ እጅግ በብዛት የሚመጡ፣ ያገኙትን ሁሉ የሚበሉ በጣም አጥፊ ትልቅ በራሪ ፌንጣዎች ናቸው።

  • አንበጦችና ሌሎች ፌንጣዎች ትል፣ ቀጥ ያል ክንፎችና በረጅሙ መወርወር የሚያስችሏቸው ወደ ኋላ የታጠፉ እግሮች ያሏቸው ፍጥረቶች ናቸው።
  • መላው ብሉይ ኪዳን አንበጦችን የሚያቀርበው ሰብልንና እንስሳትን ለማጥፋት በብዛት እንደሚመጣ ወራሪ ነው።
  • እግዚአብሔር ግብፅ ላይ ካመጣቸው አሥር መቅሠፍቶች አንዱ አንበጦች ነበር።
  • መጥምቁ ዮሐንስ አንበጦችን ይመገብ እንደ ነበር አዲስ ኪዳን ያመለክታል።

አንገተ ደንዳና፣ ግርት

“አንገተ ደንዳና” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ለእግዚአብሔር ባለ መታዘዝ የዳኑትንና ተግሣጹን የማይቀበሉ ሰዎችን ያመለክታል። እነዚህ ትዕቢተኞች ናቸው።

  • የመሲሑን መምጣት የነገሯቸውን ነቢያትን በተመለከተ ባሳዩት ዝንባሌ እስራኤላውያን አንገተ ደንዳና ሆነዋል
  • ሐሰተኛ አማልክትን በማምለክ በመቀጠላቸው እስራኤላውያን አንገተ ደንዳኖች መሆናቸው ታይቷል
  • ይህ ቃል፣ “በግትርነት የጸና” ወይም፣ “እብሪተኛና መመለስ የማይፈልግ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል
  • አንገተ ደንዳና ሰው ለእግዚአብሔር ሥልጣን አይገዛም
  • ሌሎች ቋንቋዎች ተመሳሳይ ትርጉም ያለው ፈሊጣዊ አነጋገር ሊኖራቸው ይችላል

አእምሮ (ልብ)

አእምሮ የሚያስብና ውሳኔ የሚያደርግ የሰው ተፈጥሮ ክፍል ነው።

  • የሰው አንጎል ቁሳዊ የማሰቢያ አካል ነው።
  • የእያንዳንዱ ሰው አእምሮ የእርሱ ወይም የእርሷ ሐሳብና አመክንዮ ሁለንተና ነው።
  • “የክርስቶስ አእምሮ (ልብ)” ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚያስበውና እንደሚያደርገው ማሰብና ማድረግ ማለት ነው። ይህንንም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ለክርስቶስ ትምህርት በመገዛት ለእግዚአብሔር አብ መታዘዝ ማለት ነው።

አክሊል፣ አክሊል መድፋት (መጫን)

አክሊል ንጉሦችና ልዕልታትን የመሳሰሉ መሪዎች ራሳቸው ላይ የሚያደርጉት ክብ ቅርጽ ያለው ጌጥ ነበር። አክሊል መድፋት አንድ ሰው ራስ ላይ አክሊል ማኖር ማለት ሲሆን፣ በምሳሌያዊ ትርጕሙ፣ “ማክበርን” ያመለክታል።

  • ብዙውን ጊዜ አክሊል የሚሠራው ከወርቅ ወይም ከብር ሲሆን የተለያዩ የከበሩ ድንጋዮች ፈርጥ ይኖሩታል።
  • አክሊል የነገሥታትን ሥልጣንና ሀብት ያመለክታል።
  • በንጽጽር ሮማውያን ኢየሱስ ራስ ላይ ያኖሩት ከእሾክ ቅርንጫፎች የተሠራ አክሊል እርሱን ለመጉዳትና በእርሱ ለማፌዝ ታስቦ የተደረገ ነበር።
  • በጥንት ዘመን በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች ያሸነፉ ሰዎች ከወይራ ዛፍ ቅርንጫፎች የተሠራ አክሊል ይሸለሙ ነበር። በሁለተኛው የጢሞቴዎስ መልእክቱ ሐዋርያው ጳውሎስ የጠቀሰው እንዲህ አይነቱን አክሊል ነበር።
  • በምሳሌያዊ አነጋገር ጥቅም ላይ ከዋለ፣ “አክሊል መድፋት (መጫን)” ያንን ሰው ማክበር ማለት ነው። ለእርሱ ስንታዘዝና እርሱን ስናመሰግን እግዚአብሔርን እናከብራለን። ይህ እርሱ ላይ አክሊል የማኖርና ንጉሥነቱን የመቀበል ያህል ነው።
  • ጳውሎስ አማኝ ወገኖችን፣ “የደስታዬ አክሊል”ይላቸዋል። እዚህ ላይ “አክሊል” የሚለውን ቃል የተጠቀመው እነዚያ አማኞች በታማኝነት እግዚአብሔርን ከማገልገላቸው የተነሣ በእነርሱ ምን ያህል ደስ እንደ ተሰኘና ክብር እንደ ተሰማው በሚያመልክት ምሳሌያዊ መልኩ ነው።
  • ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ ሲውል፣ “አክሊል” – “ዋጋ” ወይም፣ “ክብር” ወይም፣ “ሽልማት” ተብሎ መተርጎም ይችላል።
  • ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ ሲውል፣ “አክሊል መድፋት (መጫን)” ማክበር ወይም መሸለም ተብሎ መተርጎም ይችላል።
  • አንድ ሰው አክሊል ካገኘ፣ “ራሱ ላይ አክሊል ተደረገ” ተብሎ መተርጎም ይችላል።
  • “ክብርና ግርማ ተቀዳጀ” የተሰኘው አገላለጽ፣ “ክብርና ግርማ ተሰጠው” ወይም፣ “ክብርና ግርማ ተቀበለ”፣ “ክብርና ግርማ ለበሰ” ተብሎ መተርጎም ይችላል።

አክብሮት

“አክብሮት” ለአንድ ሰው ወይም አንዳች ነገር ጥልቅ ስሜትና ክብር ያመለክታል።

  • የአክብሮት ስሜት ክብርን በሚገልጥ ተግባር ይታያል።
  • እግዚአብሔርን መፍራት ውስጣዊ አክብሮት ቢሆንም፣ ለእግዚአብሔር ትእዛዝ በመገዛት ሕይወት ይገለጻል።
  • ይህ ቃል “ፍርሃትና ክብር” ወይ፣ “እውነተኛ አክብሮት” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

አውራጃ

አውራጃ አንድ ወረዳ ወይም የአገር ክፍል ነው።

  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ አውራጃዎች በንጉሥ አክዓብና በአስቴር ዘመን የእስራኤል ክፍሎች ነበሩ።
  • አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን የሮም መንግሥት በተለያዩ አውራጃዎች የተከፋፈለ ነበር፤ ከእነርሱም መካከል መቄዶንያ፣ ቆጵሮስ፣ እስያ፣ ሶርያ፣ ግብፅና ገላትያ ይገኙ ነበር።
  • እያንዳንዱ አውራጃ የራሱ ገዢ የነበሩት ሲሆን፣ እርሱም ለንጉሡ ወይም ለአገሩ አስተዳደር ይገዛ ነበር።
  • ይህ ቃል፣ “አካባቢ” ወይም፣ “ክልል” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

አውሬ

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙውን ጊዜ ስለሌላ “እንስሳ” ለመናገርም ጥቅም ላይ ይውል ነበር

  • የዱር አውሬ በነጻነት ጫካ ውስጥ ወይም ገላጣ ሜዳዎች ላይ የሚኖርና ሰዎች ለማዳ ያላደረጉት የእንስሳ ዓይነት ነው
  • ለማዳ አውሬ ሰዎች ጋር የሚኖርና ምግብ ለመሆን የሚጠበቅ ወይም እርሻን ለመሳሰሉ ሥራዎች የሚያገለግል እንስሳ ነው። “የቤት እንስሳ” የሚለው ቃል እንዲህ ያሉትን እንስሳት ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላሉ
  • የብሉይ ኪዳኑ ትንቢተ ዳንኤልና የአዲስ ኪዳኑ የዮሐንስ ራእይ ክፉ ኅይሎችንና እግዚአብሔርን የሚቃወሙ ባለሥልጣኖችን የሚወክሉ አራዊት ያሉባቸው ራእዮችን ይዘዋል።
  • ከእነዚህ አራዊት አንዳንዶቹ ከአንድ በላይ ራሶችና ብዙ ቀንዶች ያሏቸው ያልተለመዱ ዓይነት ፍጥረቶች ነበሩ። ብዙውን ጊዜ ትልቅ ሥልጣንና ኅይል ያላቸው ሲሆኑ፥ አገሮችን፥ ሕዝቦችንና ሌሎች የፖለቲካ ኅይሎችን ይወክሉ ነበር
  • እነዚህን ቃሎች ለመተርጎም እንደ ዐውዱ አገባብ “ፍጡራን” ወይም፥ “ፍጡር ነገሮች” ወይም፥ “እንስሳት” ወይም፥ “የዱር እንስሳት” ማለት ይቻላል

አዛዥ፣ እዝ

“አዛዥ” የተወሰኑ ወታደሮችን የመምራትና የማዘዝ ኃላፊነት ያለውን የሰራዊት መሪ ያመለክታል።

  • ሰራዊት፣ “ማዘዝ” ያንን ሰራዊት መምራት፣ በዚያ ሰራዊት ላይ ባለ ሥልጣን መሆን ማለት ነው።
  • አንድ አዛዥ በቁጥር ጥቂት ወይም ብዙ (ለምሳሌ በሺህ የሚቆጠሩ) ወታደሮች ላይ ኃላፊነት ሊኖረው ይችላል።
  • እርሱ የመላእክት ሰራዊት አዛዥ እንደ መሆኑ መጠን ይህ ቃል ያህዌንም ይመለከታል።
  • “አዛዥ” የተሰኘውን ቃል ለመተርጎም፣ “መሪ” ወይም “ባለ ሥልጣን” ማለት ይቻላል።
  • ሰራዊት፣ “ማዘዝ”፣ ሰራዊት፣ “መምራት” ወይም ሰራዊቱ ላይ፣ “ባለ ሥልጣን” መሆን ተብሎ መተርጎም ይችላል።

አደባባይ፣ ችሎት

“አደባባይ” ዙሪያውን የተከበበና ከላይ በኩል ክፍት የሆነ ገላጣ አካባቢ ነው።

  • “ችሎት” ዳኞች ፍትሕ ብሔርና ወንጀል ነክ ነገሮችን የሚዳኙበት ቦታ ማለት ነው።
  • መገናኛው ድንኳን በወፍራም የጨርቅ መጋረጃዎች ግድግዳነት በታጠረ አንድ አደባባይ ተከብቦ ነበር።
  • የቤተ መቅደሱ ሕንፃ ሦስት የውስጥ አደባባዮች ነበሩት፤ አንዱ ለካህናት፣ አንዱ ለአይሁዳውያን ወንዶችና ሌላው ደግሞ ለአይሁዳውያን ሴቶች።
  • አነዚህ የውስጥ አደባባይች አሕዛብ እንዲያመልኩ ከተፈቀደበት ውጫዊ አደባባይ የሚለያቸው በቁመት ዝቅ ያሉ የድንጋይ ግድግዳ ነበራቸው።
  • የአንድ ቤት አደባባይ ቤቱ መካከል ላይ ያለ ግልጥ ቦታ ነው።
  • “የንጉሥ ችሎት” የሚለው ሐረግ ቤተ መንግሥቱን ወይም ፍርድ የሚሰጥበትን ቦታ ሊያመለክት ይችላል።
  • “ይያህዌ አደባባይ” ይያህዌ መኖሪያን ወይም ሰዎች ያህዌን ለማምለክ የሚሰጡበት ቦታን የሚያመለክት ምሳሌያዊ አንጋገር ነው።

አዲስ ኪዳን

“አዲስ ኪዳን” የሚለው አገላለጽ የሚያመለክተው በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ መሥዋዕት በኩል እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያደረገውን ስምምነት ወይም ውል ነው።

  • እግዚአብሔር የገባው፣ “አዲስ ኪዳን” – “አዲስ ኪዳን” በመባል በሚታወቀው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ተብራርቶአል።
  • ይህ አዲስ ኪዳን በብሉይ ኪዳን ዘመን እግዚአብሔር ከእስራኤላውያን ጋር ካደረገው፣ “አሮጌ” ወይም፣ “የቀድሞ” ኪዳን ጋር ይነጻጸራል።
  • ለሕዝቡ ኀጢአት ለዘላለም ፍጹም ቤዛ በሆነው በኢየሱስ መሥዋዕት ላይ የተመሠረተ በመሆኑ አዲሱ ኪዳን ከአሮጌው ይበልጣል። በአሮጌው ኪዳን ሲቀርቡ የነበሩ መሥዋዕቶች ይህን ማድረግ አልቻሉም።
  • አዲሱን ኪዳን በኢየሱስ በሚያምኑት ሰዎች ልብ ውስጥእግዚአብሔር ይጽፈዋል። ይህም ለእግዚአብሔር መታዘዝ እንዲፈልጉና የተቀደሰ አኗኗር ምኖር እንዲጀምሩ ያደርጋቸዋል።
  • በመጨረሻው ዘመን እግዚአብሔር መንግሥቱን በዚህ ምድር ሲመሠርት አዲሱ ኪዳን ሙሉ በሙሉ ይፈጸማል። በመጀመሪያ እግዚአብሔር ዓለምን ሲፈጥር እንደ ነበረው ማንኛውም ነገር እንደ ገና መልካም ይሆናል።

አዲስ ጨረቃ

“አዲስ ጨረቃ” የሚባለው ጨረቃ በመሬት ምሕዋር ዙሪያ ስትጓዝ የሚኖራት የመጀመሪያው ገጽታዋ ነው። በዚህ ጊዜ ጨረቃ ፍጹም ጨለማ መስላ ትታያለች ወይም ጫፏ ላይ ትንሽ ማጭድ መሰል ቅርጽ ያለው ብርማ ብርሃን ይኖራታል።

  • በመሐፍ ቅዱስ መሠረት፣ “አዲስ ጨረቃ” የሚለው አገላለጽ የሚያመለክተው ጨረቃ ፍጹም ጨለማ የምትሆንበትን ሳይሆን ትንሽ ብርማ የጨረቃ ብርሃን የሚታይበት ጊዜ እንደ ሆነ ግልጽ ነው።
  • አዲስ ጨረቃ የተለያዩ ወቅቶች ጅማሬ ተደርጎ ይታሰባል።
  • እስራኤላውያን ቀንደ መለኮት የሚነፋበት አዲስ ጨረቃ በዓል ያከብሩ ነበር።

አጋዘን

አጋዘን ጫካዎች ውስጥ ወይም ተራሮች ላይ የሚኖር ግዙፍና የሚያምር ባለ አራት እግሮች እንስሳ ነው። ወንዱ አጋዘን በጣም ትላልቅ ቀንዶች አሉት።

  • አጋዘን ከፍ ብሎ ለመዝለልና በፍጥነት ለመኖጥ የሚያስችሉት ቀጫጭንና ጠንካራ እግሮች አሉት።
  • የእግሮቻቸው ሸኾና ስንጥቅ መሆኑ በማንኛውም ቦታ እንዲራመዱና ማንኛውንም ከፍታ ለመወጣት ይረዳቸዋል።

አጥፊ

ቃል በቃል ሲወስድ፣ “አጥፊ” የሚለው ቃል፣ “የሚያጠፋ ሰው” ማለት ነው።

  • ይህ ቃል ብሉይ ኪዳን ውስጥ ብዙውን ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው ወራሪ ሠራዊት እንደሚያደርገው ሌላውን ሕዝብ የሚያጠፋ ለማለት ነው።
  • የግብፃውያንን በኩር ወንዶች እንዲገድል እግዚአብሔር የላከው መልአክ፣ “የበኩር ልጆችን የሚያጠፋ” ተብሎ ተጠርቷል።
  • ከዮሐንስ ራእይ እንደምንመለከተው በመጨረሻው ዘመን ሰይጣን ወይም ርኩሳን መናፍስት፣ “አጥፊ” ተብለዋል። “አጥፊው” እርሱ ራሱ ነው፤ ምክንያቱም የእርሱ ዓላማ እግዚአብሔር የፈጠረውን ሁሉ ማጥፋትና ማበላሸት ነው።

እህል

ብዙውን ጊዜ፣ “እህል” የሚያመለክተው እንደ ስንዴ፣ ገብስ፣ በቆሎ፣ ማሽላ ወይም ሩዝን የመሳሰሉ ለምግብ የሚሆኑ እህል ዘሮችን ነው። አንዳንዴ ዘሩ ራሱን ያመለክታል።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዋናነት የተጠቀሱ እህሎች ስንዴና ገብስ ናቸው።
  • የእህል ራስ እህሉ ያለበት የተክሉ አካል ነው።

እምነት የሌለው፣ የማያምን

“እምነት የሌለው” የማያምን ወይም ማመን የማይፈልግ ማለት ነው።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “አለማመን” ኢየሱስ አዳኙ መሆኑን የማያምን ወይም በእርሱ የማይተማመን ሰውን ያመለክታል።
  • በኢየርሱ “እምነት የሌለው” ሰው፣ “የማያምን” ይባላል።

እምነት፣ መተማመን

“እምነት” እኛ “መተማመን” አንድ ነገር እውነት መሆኑንና ያም ነገር በእርግጥ የሚፈጸም መሆኑን እርግጠኛ መሆንን ያመለክታሉ። በድፍረትና በልበ ሙሉነት መንቀሳቀስንም ያመለክታሉ።

  • እርሱ እንደማይዋሽና ምንጊዜም ቃሉን እንደሚጠብቅ በማወቃቸው እግዚአብሔርን በሰጣቸው የተስፋ ቃሎች አማኞች እርግጠኞች ናቸው።
  • እርግጠኝነት መሠረት የሚያደርገው አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢኖሩ እንኳ በእግዚአብሔር መተማመን ላይ ነው።
  • ሌሎች የመጸሐፍ ቅዱስ ትርጕሞች፣ “ተስፋ” በማለት የተረጎመበትን አንዳንድ ትርጕሞች፣ “እርግጠኝነት” ብለውታል፤ ይህም ያ ነገር እንደሚፈጸም በሚገባ ማወቅን ግምት ውስጥ በማስገባት ነው።
  • ብዙውን ጊዜ፣ “እምነት” የሚያመለክተው በተለይ የእግዚአብሔርን ተስፋ ቃል እውነተኛነትን፣ አንድ ቀን አማኞች ሁሉ ለዘላለም በሰማይ ከእግዚአብሔር ጋር እንደሚሆኑ እርግጠኛ መሆንን ያመለክታል።
  • “በእግዚአብሔር ማመን” እርሱ ቃል የገባውን ለመቀበልና ለመለማመድ በፍጹም ልብ መጠበቅ ማለት ነው።

እረኛ

እረኛ በጎችንና እነርሱን የመሳሰሉ እንስሳትን የሚጠብቅ ሰው ነው

  • እረኛ ለበጎቹ ይጠነቀቃል፤ መልካም ምግብና ውሃ ወዳለበት ቦታ ይመራቸዋል። እረኛ በጎቹ እንዳይጠፉም ይጠብቃል፤ ከዱር አውሬ ይጠብቃቸዋል
  • ይህ ቃል ለሰዎች መንፈሳዊ ጉዳይ ማሰብን ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ጊዜ እንደ ተለዋጭ ዘይቤ ቀርቧል። ይህም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር ለእነርሱ የተናገረውን ማስተማርን መሄድ በሚገባቸው መንገድ መምራትንም ይጨምራል
  • ለእነርሱ የሚያስብና የሚጠነቀቅ በመሆኑ ብሉይ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር የሕዝቡ፣ “እረኛ” ተብሏል። እርሱ ይመራቸዋል፤ ደግሞም ይከላከልላቸዋል
  • ያህዌን እንዲይያመልኩ በመንፈሳዊ ደረጃ እነርሱን በመምራቱና ወደ ምድረ ከነዓን በሚያደርጉትም ጉዞ ይመራቸው ስለነበር ሙሴ የእስራኤላውያን እረኛ ነበር
  • አዲስ ኪዳን ውስጥ ኢየሱስ፣ “መልካም እረኛ” በማለት ራሱን ጠርቷል።
  • አዲስ ኪዳን ውስጥ “እረኛ” የሚለው ቃል የአማኞች መንፈሳዊ መሪ የሆን ሰውን ያመለክታል። የቤተክርስቲያን ሽማግሌዎችና መጋቢዎችም እረኛ ተብለዋል

እርሾ፣ የቦካ

እርሾ ሊጥ ኩፍ እንዲል የሚያደርግ ነገር ነው። እርሾ የገባበት ሊጥ የቦካ ይባላል።

  • በጥንት ዘመን ሊጥ እንዲቦካ ወይም ኩፍ እንዲል ከተፈለገ ለጥቂት ቀኖች መቀመጥ ነበረበት። የሚቀጥለው ሊጥ እንዲቦካ ለማድረግ በፊት ከነበረው ሊጥ ጥቂት ተወስዶ እንዲቀላቀል ይደረጋል።
  • እስራኤላውያን ከግብፅ ሲወጡ ሊጡ እስኪቦካ ድረስ ለመጠበቅ ጊዜ አልነበራቸውም፤ ስለዚህ ካልቦካ ሊጥ የተጋገረ እንፈራ ይዘው ነበር ጉዞ የጀመሩት። ለዚህ መታሰቢያ እንዲሆን በየዓመቱ አይሁድ የፋሲካን በዓል ሲያከብሩ ያልቦካ እንጀራ ይበላሉ።
  • ኀጢአት በሰው ሕይወት እንደሚስፋፋና ሌሎች ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ፣ “እርሾ” በሚለው ቃል ይጠቀማል። ይህ ሐሰተኛ ትምህርትንም ይመለከታል።
  • “እርሾ” የእግዚአብሔር መንግሥት ከአንዱ ሰው ወደ ሌላው እንዴት እንደሚተላለፍ ለማመልከት አዎንታዊ በሆነ መልኩም ጥቅም ላይ ውሏል።

እርድ

ብዙውን ጊዜ “ጭፍጨፋ” በአንድ ጊዜ ብዙ እንስሳት ወይም ሰዎችን መግደል ወይም በአሰቃቂ ሁኔታ መግደል ነው። ማረድ በሚለው ቃል ከተጠቀምን ደግሞ ለመብል እንዲሆኑ ጥቂት እንስሳትን መግደልም ይሆናል

  • አብርሃም ምድረ በዳ ውስጥ በነበረ ድንኳኑ ሦስት እንግዶች ተቀብሎ ነበር፤ ያማረውን ወይፈን አርደው ለእንግዶቹ መልካም ምግብ እንዲያዘጋጁ አገልጋዮቹን አዘዘ
  • ቃሉን የማይከተሉትን ሁሉ እንዲገድሉ (እንዲጨፈጭፉ) እግዚአብሔር መልአኩን እንደላከ ነቢዩ ሕዝቅኤል አመልክቷል
  • 1ሳሙኤል እግዚአብሔር ላይ በማመፃቸው 30,000 የሚሆኑ እስራኤላውያን በጠላቶቻቸው ስለተገደሉበት ጭፍጨፋ ይናገራል
  • ይህ ቃል፣ “መግደል” ወይም፣ “ማረድ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል

እሳት

እሳት አንድ ነገር ሲቃጠል የሚገኝ ሙቀት፣ ብርሃንና ነበልባል ነው።

  • እንጨት ሲቃጠል ከሰልና ዐመድ ይሆናል።
  • ቅዱሳት መጽሐፍት ውስጥ እሳት የሚታየውና የሚዳሰሰው ነገር ብቻ ሳይሆን ኃይልንም ይወክላል።
  • የማያምኑ ሰዎች የመጨረሻ ፍርድ በገሃነም እሳት ውስጥ መጣል ነው።
  • እሳት ወርቅን ያጠራል፣ ቅዱሳት መጻሕፍት ይህን እውነት መከራና ፈተና የሰውን ሕይወት የማጥራት ችሎታ እንዳላቸው ለማመልከት ይጠቀሙበታል።

እስር ቤት፣ እስረኛ

እስር ቤት የሚያመለክተው በጥፋታቸው እንዲቀቱ ወንጀለኞች የሚጠበቁበትን ቦታ ነው። እስረኛ እስር ቤት ውስጥ የሚጠበቅ ሰው ነው።

  • አንድ ሰው ፍርድ እስኪያገኝ እስር ቤት ውስጥ ሊቆይ ይችላል።
  • ምንም እንኳ አንዳች የፈጸሙት ወንጀል ባይኖርም ብዙ ነቢያትና ሌሎች የእግዚአብሔር አገልጋዮች እስር ቤት ገብተዋል።

እስትንፋስ

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “እስትንፋስ” የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ ሕይወትን ለመስጠት ወይም በሕይወት መሆንን ለማመልከት በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ውሏል።

  • እግዚአብሔር አዳም ውስጥ የሕይወትን እስትንፋስ፣ “እፍ” እንዳለበት መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። አዳም ሕያው ነፍስ የሆነው ያኔ ነበር።
  • ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ላይ እፍ በማለት፣ “መንፈስን ተቀበሉ” ሲላቸው ምናልባትም መንፈስ ቅዱስ ወደ እነርሱ መምጣቱን በምሳሌ ለማመልከት ቃል በቃል ከእርሱ የወጣ እስትንፋስ እፍ ብሎባቸው ይሆናል።
  • “መተንፈስ” እና፣ “እፍ ማለት” የተሰኙት ቃሎች መናገርን ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላሉ።
  • “የእግዚአብሔር እስትንፋስ” ወይም፣ “የያህዌ እስትንፋስ” የተሰኘው ምሳሌያዊ ሐረግ ብዙውን ጊዜ ዐመፀኞችና ክፉ ሕዝቦ ላይ ያወረደውን የእግዚአብሔር ቊጣ ያመለክታል። እስትንፋሱ የኃይሉ መተላለፊያ ነው።

እበት፣ ማዳበሪያ

እበት የእንስሳ እዳሪ ሲሆን፣ መሬትን ለማለስለስ ወይም ለማዳበር በሚውልበት ጊዜ ማዳበሪያ ይባላል።

  • ምንም ጥቅም የሌለው ወይም የማያስፈልግ ነገርን ለማመልከት በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።
  • የደረቀ እበት ለማገዶ ያገለግላል።
  • ከኢየሩሳሌም ቅጥር በስተ ደቡብ የነበረው ቆሻሻ መጣያ፣ ምናልባት የከተማው ቆሻሻ የሚጠራቀምበት ቦታ ሊሆን ይችላል።

እባብ

እባብ የዘንዶ ሌላ ስም ነው። በኤደን አትክልት ቦት ከሔውን ጋር በተናገረ ጊዜ ሰይጣን በዚህ ስም ነበር የተጠራው

  • እባቡ ኅጢአት እንድታደርግ ሔዋንን ካሳተ በኋላ በመሬት እየተሳበ እንዲሄድ እግዚአብሔር ረገመው፤ ያም ማለት ከዚያ በፊት እግሮች ነበሩት ማለት ሊሆን ይችላል
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መርዛማ እባብን ለማመልከት፣ “እፉኝት” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ውሏል

እብሪት

  • “እብሪት” የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ በውጫዊ ሁኔታ በግልጽ የሚታይ ትዕቢት ማለት ነው።
  • እብሪተኛ ሰው ብዙውን ጊዜ በራሱ ይመካል
  • ብዙውን ጊዜ እብሪት ሌሎች ሰዎች የእኔን ያህል አስፈላጊ አይደሉም ውይም የእኔ ዐይነት ስጦት የላቸውም በማለት ማሰብን የጨምራል
  • እግዚአብሔርን የማያከብሩና በእርሱ ላይ ያመፁ ሰዎች እግዚአብሔር እጅግ ታልቅ መሆኑን ስለማይቀበሉ እብሪተኞች ናቸው

እኅት

እኅት የምትባለው ቢያንስ በአንዱ ወላጅ ከሌላው ጋር የምትጋራ እንስት ናት

  • አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን፣ በክርስቶስ የምታምን ሴትን ለማመልከት፣ “እኅት” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ይውል ነበር
  • ወንዶችም ሆኑ ሴቶች በክርስቶስ የሚያምኑ ወገኖችን ለማመልከት እንዳንዴ፣ “ወንድሞችና እኅቶች” የተሰኘው ሐረግ ጥቅም ላይ ውሏል
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ ባለው መሐልየ መኃልይ፣ “እኅት” የሚያመለክተው ፍቅረኛን ወይም የትዳር ጓደኛን ነው

እኔ፣ ያህዌ

ብዙውን ጊዜ ብሉይ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር ስለ ራሱ ሲናገር በተውላጠ ስም ከመጠቀም ይልቅ፣ በራሱ መጠሪያ ስም ይጠቀማል።

  • ለምሳሌ፣ “እኔን አክብሩ” ከማለት ይልቅ፣ “እግዚአብሔርኝ አክብሩ” ይላል።

እንከን፣ ነውር

“እንከን” ወይም ነውር አንድ እንስሳ ወይም ሰው ላይ ያለ ጉድለትን ወይም ሙሉ ያለመሆንን ያመለክታል። ሰዎች ላይ ያለ በደልን ወይም መንፈሳዊ ጉድለትንም ያመለክታል።

  • አንዳንድ መሥዋዕቶችን በተመለከተ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ሲናገር እንከን ወይም ነውር የሌለበትን እንስሳ እንዲያቀርቡ መመሪያ ሰጥቷል።
  • ይህ ሥዕል ኢየሱስ ክርስቶስ ምንም ኃጢአት የሌለው ፍጹም መሥዋዕት መሆኑን ያመለክታል።
  • በክርስቶስ የሚያምኑ አማኞች በእርሱ ደም ከኃጢአታቸው ነጸተዋል፤ ስለዚህም እንከን ወይም ነውር የሌለባቸው ተብለዋል።
  • እንደ ዐውደ ምንባቡ ይህን፣ “ጉድለት” ወይም፣ “ነቀፋ” ወይም፣ “ኃጢአት” በማለት መተርጎም ይቻላል።

እንደራሴ(አምባሳደር)፣ተወካይ

እንደ ራሴ(አምባሳደር)ሀገሩን በይፋ በመወከል ለውጪ አገሮች ጋር ግንኙነት እንዲያደርግ የሚመረጥ ሰው ነው፥ ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን አንዳንዴ ጠቅለል ባለ ሁኔታ፣ “ተወካይ” ተብሎም ይተረጎማል።

  • እንድ እንደ ራሴ ወይም ተወካይ ከላከው ሰው ወይም መንግስት ለሰዎች መልእክት ይሰጣል።
  • “ተወካይ” የተሰኘው ይበልጥ አጠቃላይ የሆነውን ቃል በሚወክለው ሰው ቦታ ሆኖ እንዲሠራ እንዲናገር ሥልጣን የተሰጠውን ሰው ያመለክታል።
  • በዚህ ዓለም ክርስቶስ የሚወክልና የእርሱን መልዕክት ለሌሎች የሚያስተምሩ በመሆናቸው ክርስቲያኖች የክርስቶስ፣ “እንደራሴዎች” ወይም “ተወካዮች” መሆናቸውን ሐዋርያው ጳውሎስ አስተምርሯል።
  • ጥቅም ላይ በዋለበት ዐውድ መሠረት ይህ ቃል፣ መንግሥታዊ ተወካይ ወይም፣የተሾመ መልእክተኛ ወይም “የመረጠ” ተወካይ ወይም፣በእግዚዘብሔር ተወካይ ተብሎ መተርጎም ይችላል።
  • “የእንደራሴዎች ቡድን” የሚለው፣ “ጥቂት መንግስታዊ መልዕክተኞች” ወይም፣ “የተመረጡ ተወካዮች ቡድን” ወይም ሰዎችን ሁሉ በመወከል ለሰዎች እንዲናገር ሥልጣን ያለው ቡድን ተብሎ መተርጎም ይቻላል።

እንጀራ፣ ዳቦ

እንጀራ ውሃና ዘይት ተቀላቅሎ ከተቦካ ዱቄት ሊጥ ይሠራል። ከዚያ ሊጡ የእንጀራውን ወይም የዳቦውን ቅርጽ እንዲይዝ ተደርጎ ይጋገራል።

  • ብዙውን ጊዜ የእንጀራ ወይም የዳቦ ሊጥ ኩፍ እንዲል እርሾን የመሰለ ነገር ይገባበታል።
  • ኩፍ እንዳይል ከተፈለገ እንጀራን ወይም ዳቦን ያለ እርሾ ሊጋገር ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲህ ያለው፣ “ያልቦካ እንጀራ” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን፣ በፋሲካ ሰሞን አይሁድ የሚበሉት እንዲህ ያለውን እንጀራ ነው።
  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን እንጀራ ወይም ዳቦ የብዙ ሰዎች ዋና ምግብ ሲሆን፣ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቃሉ ማንኛውንም ምግብ ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላል።
  • “ገጸ ኅብስት” የሚለው ቃል መገናኛው ድንኳን ወይም ቤተ መቅደስ ውስጥ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንዲሆኑ አሥራ ሁለት ኅብስቶች ወይም እንጀራዎች ወይም ዳቦዎች የወርቁ መሠዊያ ላይ ይቀመጡ ነበር። እነዚህ ኅብስቶች አሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶችን የሚወክሉ ሲሆን፣ የሚበሏቸው ካህናቱ ብቻ ነበሩ። ይህ ቃል፣ “እግዚአብሔር በመካከላቸው መሆኑን የሚያመለክቱ ኅብስቶች” ተብሎ መተርጎም ይችላል።
  • “ከሰማይ እንጀራ” የተሰኘው ምሳሌያዊ አነጋገር በምድረ በዳ በነበሩ ጊዜ እግዚአብሔር ለእስራኤል የሰጠውን፣ “መና” የሚባለውን የተለየ ነጭ ምግብ ያመለክታል።
  • ኢየሱስም፣ “ከሰማይ የወረደ እንጀራ” እና፣ “የሕይወት እንጀራ” በማለት ራሱን ጠርቷል።
  • ከመሞቱ በፊት ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ የፋሲካውን ምግብ አብረው እየበሉ በነበረ ጊዜ ያልቦካውን የፋሲካ እንጀራ መስቀል ላይ ከሚቆስለውና ከሚገደለው የራሱ አካል ጋር አመሳስሎት ነበር።

እጅ፣ ቀኝ እጅ

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “እጅ” የሚለው ቃል በምሳሌያዊ አነጋገር በበርካታ ቦታዎች ጥቅም ላይ ውሏል።

  • ብዙውን ጊዜ “እጅ” የእግዚአብሔርን ኀይልና ሥራ ለማመልከት ተጠቅሷል፤ “እጁ ይህን ሁሉ አላደረገችምን?” እንደሚለው።
  • “በእጅ ተላልፎ መሰጠት” የሚለው አገላለጽ አንድ ሰው በሌላው ሰው ቁጥጥር ሥልጣን ሥር እንዲሆን አሳልፎ መስጠትን ያመለክታል።
  • “እጆችን መጫን” አንድን ሰው ለእግዚአብሔር አገልግሎት ለመለየት ወይም እንዲፈወስ ለመጸለይ እጆችን እርሱ ላይ ማድረግን ያመለክታል።
  • “እጅ” የሚለው ቃል በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ሲውል፣ “እጆችህን አትጫን” ማለትም ማንንም አትጉዳ የሚለውን ይጨምራል።
  • “ከ . . . እጅ ማዳን” አንድ ሰው ሌላውን እንዳይጎዳ ማስቆም ማለት ነው።
  • “በቀኝ እጅ” በቀኝ በኩል ወይም በቀኝ ወገን ቦታ መያዝ ማለት ነው።
  • በ . . . እጅ” የሚለው ሐረግ በዚያ ሰው እጆች የተከናወነ ወይም የተደረገ ተግባር ያመለክታል፤ ለምሳሌ፣ “በጌታ እጅ” ማለት ያንን ያደረገ እግዚአብሔር ነው ማለት ነው።
  • ጳውሎስ፣ “ይህን በእጄ የጻፍኩ እኔ ነኝ” ሲል ያ መልእክት የተጻፈው እርሱ በቃል በሚነግረው በሌላው ሰው እጅ ሳይሆን በእርሱ ራሱ እጅ የተጻፈ መሆኑን ያመለክታል።

ከንቱ፣ ከንቱነት

“ከንቱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ምንም ጥቅም ወይም ዓላማ የሌለውን ነገር ነው። ከንቱ ነገሮች ባዶና እርባነ ቢስ ናቸው።

  • “ከንቱ” እርባና ቢስ ወይም ባዶ ማለት ነው። ትዕቢትና እብሪትን ለማመልከትም ጥቅም ላይ ይውላል።
  • በእውነት መጸለይ እንጂ፣ “ከንቱ ቃላት መደጋገም” እንደሌለባቸው ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ነግሮአቸዋል፤ እንዲህ ያለው ቃላትን መደጋገም ብቻውን ትርጕም የሌለው መሆኑን ለማመልከት ነ።ው
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ ጣዖቶች ማዳን መታደግ የማይችሉ ከንቱዎች ተብለዋል። ጥቅመ ቢስና እርባና ቢስ ናቸው።
  • አንድ ነገር “ከንቱ” ሆኖ ከተሠራ ከእርሱ መልካም ውጤት ሊገኝ አይችልም። ጥረት ወይም ተግባር ምንም ማከናወን አይችልም።

ከፍታ ቦታዎች

“ከፍታ ቦታዎች” የሚለው ሐረግ የጣዖት አምልኮ መሠዊያና ማምለኪያ ቤት የሚሠራባቸው ኮረብቶች ወይም ተራሮች ላይ ያሉ ቦታዎችን ያመለክታል።

  • በእነዚህ ከፍታ ቦታዎች ለሐሰተኛ አማልክት መሠዊያዎች በመሥራት ብዙዎቹ የእስራኤል ንጉሦች እግዚአብሔርን በድለው ነበር። ይህም ሕዝቡ በከፍተኛ ደረጃ ጣዖት እንዲያመልኩ አደረገ።
  • እግዚአብሔርን የሚፈራ ንጉሥ በእስራኤል በነገሠ ጊዜ ሁሉ ከፍታ ቦታዎችን ያስወግድና ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ነበር።
  • ይሁን እንጂ፣ ከእነዚህ መልካም ንጉሦች አንዳንዶቹ ቸልተኛ ነበሩ፤ መላው የእስራኤል ሕዝብ ጣዖት ማምለኩን እንዲቀጥል ምክንያት የሆኑትን ከፍታ ቦታዎች አላስወገዱም።

ከፍታ፣ በከፍታ

“ከፍታ” እና “በከፍታ” የተሰኙ ቃሎች ሰማይን የሚያመለክቱ ፈሊጣዊ አነጋገር ናቸው።

  • “በከፍታ” የተሰኘው ፈሊጣዊ አነጋገር ሌላው ትርጉም፣ “በጣም የተከበረ” የሚለው ነው።
  • “ከፍታ” ከፍ ብለው በሰማይ እንደሚበሩ ወፎች ወደሰማይ ከፍ ማለትንም ያመለክታል። ዐውዱ እንደዚያ ከሆነ፣ “ ወደሰማይ ከፍ ብሎ” ወይም፣ “ከረጃጅም ዛፎች በላይ” በማለት መተርጎም ይቻላል።
  • “ከፍ ያለ” የሚለው ሐረግ ላቅ ያለ ቦታን ወይም የሰውን ወይም የነገርን ላቅ ያለ ጠቀሜታ ያመለክታል።
  • “ከከፍታ” የሚለው፣ “ከሰማይ” ተብሎ መተርጎም ይችላል።

ኪሩቤል፣ ኪሩብ

“ኪሩብ” እና “ኪሩቤል” በመባል በብዙ ቊጥር የሚጠሩት እግዚአብሔር የፈጠራቸው የተለዩ ዓይነት ሰማያዊ አካሎች ናቸው። ኪሩቤል ክንፎችና የእሳት ነበልባል እንዳላቸው መጽሐፍ ቅዱስ ያመለክታል።

  • ኪሩቤል የእግዚአብሔርን ክብርና ኃይል ይገልጣሉ፤ የተቀደሱ ነገሮች ጠባቂዎችም ይመስላሉ።
  • አዳምና ሔዋን ኃጢአት ካደረጉ በኋላ፣ ሰዎች ወደ ሕይወት ዛፍ እንዳይደርሱ የእሳት ነበልባል የሆነ ሰይፍ ያላቸው ኪሩቤልን ከገነት አትክልት ቦታ አኖረ።
  • ፊት ለፊት የቆሙና የኪዳኑ ታቦት፣ የስርየት መክደኛ ላይ ክንፎቻቸውን ያጋጠሙ ሁለት ኪሩቤል እንዲሠሩ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አዘዘ።
  • መገናኛው ድንኳን ውስጥ የነበሩ መጋረጃዎችም ላይ የኪሩቤልን ምስል በጥልፍ እንዲሠሩም ነግሮአችዋል።
  • አንዳንድ ምንባቦች ውስጥ እነዚህ ፍጥረቶች አራት ፊቶች ማለትም የሰው፣ የአንበሳ፣ የበሬ እና የንስር ፌት እንዳላቸው ተገልጿል።
  • አንዳንዴ ኪሩቤል መላእክት እንደ ሆነ ይታሰባል፤ መጽሐፍ ቅዱስ ግን ያንን በግልጽ አይናገርም።

ካባ

ካባ ወንዶችም ሆነ ሴቶች የሚለብሱት እጅጌ ረጃጅም ከውጭ የሚደረብ ልብስ ነው። ከኮት ጋር ይመሳሰላል።

  • ካባ ከፊት ለፊቱ ክፍት ሲሆን፣ በመታጠቂያ ወይም በቀበቶ ታስሮ ይገጠማል።
  • ቁመታቸው ረጅም ወይም አጭር ሊሆን ይችላል።
  • ሐምራዊ ካባ የንጉሣዊነት፣ የሀብትና የታዋቂነት መገለጫ እንዲሆን የሚለብሱት ንጉሦች ነበር።

ክራር፣ መሰንቆ

ክራርና መሰንቆ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ለማምለክት የሚጠቀሙባቸው ትናንሽ ባለ ገመድ የሙዚቃ መሣሪያዎች ናቸው።

  • መሰንቆ ክሮቹ የሚወጠሩበት ቀዳዳ ያሉት በመሆኑ በጣም በገናን ይመስላል።
  • ክራር የድምፅ እንጨት ሳጥንና ክሮቹ የሚወጠሩበት ረዘም ያለ አንገት ስላለው በብዙ መልኩ የዘመኑን ጊታር ይመስላል።
  • ክራር ወይም መሰንቆ ለመጫወት ሲፈለግ አንዳንድ ክሮች ጫን ተደርገው በጣቶች ሲያዙ፣ ሌሎች ደግም በሌላ እጅ ይመታሉ።
  • የክሮቹ ቁጥር የተለያየ ቢሆንም፣ ብሉይ ኪዳን በተለይ አሥር ክሮች (አውታር) ስላሉት መሣሪያዎች ይናገራል።

ክብር

“ክብር” የሚለው ቃል ብዙ ጊዜ ከሀብትና መልክ ጋር የሚያያዝ የላቀ ውበትና ግርማ ያመለክታል

  • ብዙ ጊዜ፣ “ክብር” ጥቅም ላይ የሚውለው የሚያመለክተው አንድ ንጉሥ ያለውን ሀብት ወይም፣ የሚለብሳቸው ውድ ልብሶችና ውብ ቁመና ነው
  • ክብር የዛፎችና የተራሮችንና ሌሎች እግዚአብሔር የፈጠራቸው ነገሮችን ውበት ለማመልከትም ጥቅም ላይ ይውላል
  • አንዳንድ ከተሞች ያላቸው የተፈጥሮ ሃብት፣ ያማሩ ሕንፃዎች፣ መንገዶች፣ ውድ ልብሶችን፣ ወርቅና ብር ጨምሮ የሕዝቡን ሀብት ለማመልከት ክብር ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል
  • እንደ ዐውዱ አገባብ ይህ ቃል፣ “የላቀ ውበት” ወይም፣ “አስደናቂ ግርማ” ወይም፣ “ንጉሣዊ ታላቅነት” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል

ክፉ አድራጊ

“ክፉ አድራጊ” ኀጢአትና ዐመጻን የሚያደርጉ ሰዎች አጠቃላይ መገለጫ ነው።

  • ለእግዚአብሔር የማይገዙ ሰዎችን የሚያመለክት አጠቃላይ ቃልም ይሆናል።
  • ይህን ቃል ክፉ ወይም ዐመጸኛ በማለት መተርጎም ይቻላል።

ወራሽ

ወራሽ የሚባለው የአንድ የሞተ ሰው ንብረት ወይም ገንዘብ የመቀበል ሕጋዊ ዕውቅና የተሰጠው ሰው ነው።

  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ዋናው ወራሽ የመጀመሪያው ወንድ ልጅ ነበር፤ አብዛኛውን የአባቱን ንብረትና ገንዘብ የሚቀበል እርሱ ነበር።
  • እርሱ መንፈሳዊ አባታቸው በምሆኑ ክርስቲያን የሚወርሱትን መንፈሳዊ ጥቅም አስመክቶ መጽሐፍ ቅዱስ፣ “ወራሽ” የሚለውን ቃል ይጠቀምበታል።
  • እንደ የእግዚአብሔር ልጆች ክርስቲያኖች ከክርስቶስ ጋር አብረው ወራሾች መሆናቸው ተነግሯል።

ወሬ

“ወሬ” አንድን ሁኔታ አስመልክቶ በቃል ወይም በጽሑፍ አንዱ ለሌላው የሚናገረው ነው።


ወርቅ

ወርቅ ቢጫ መልክ ያለው በጣም ውድ ነገር ነው። በጥንት ዘመን ወርቅ ከማንኛውም የበለጠ ውድ ነገር ነበር።

  • ወርቅ በተፈጥሮው ጥራት ባለው ደረጃ የሚገኝ ሲሆን፣ ለዘመናት የሚዘልቅ ዕድሜ እንዳለው ይታወቃል።

መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ጣዖቶች፣ ጌጣጌጦች፣ መሠዊያዎች፣ የቃል ኪዳኑ ታቦት የተወሰነ ክፍልና መገናኛው ድንኳን ወይም ቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበሩ ሌሎች ነገሮች የሚሠሩት ከወርቅ ነበር። አንዳንዴ፣ “ወርቅ” የሚባለው ወርቅ የተለበጠ እንጂ እውነተኛ ወርቅ ላይሆን ይችላል። በዚህ ጊዜ፣ “ወርቃማ” ወይም፣ “ወርቅ የተለበጠ” በተሰኙ ሐረጎች እንጠቀማለን።

  • ወርቅ በመግዛትና በመሸጥ ተግባር ውስጥ ወርቅ ሁነኛ ቦታ አለው። የዋጋውን ልክ ለመወሰን በሚዛን ይመዘናል።
  • በሁለተኛው ቤተ መቅደስ ከተገነባ በኋላ ወርቅ ሳንቲሞችንም ለመሥራት ጥቅም ላይ መዋል ጀመረ።

ወርካ

ወርካ ረጅም፣ ትልቅ ግንድና ጥላ የሚሆኑ ሰፋፊ ቅርንጫፎች ያሉት ዛፍ ነው።

  • የወርካ ዛፎች መርከቦችንና የእርሻ ሞፈሮችን፣ የበሬ ቀንበሮችንና ለሽማግሌዎች የሚሆኑ ምርኩዞችን ለመሥራት የሚያገለግሉ ጠንካራ እንጨቶች ያሉዋቸው ዛፎች ናቸው።
  • የወርካ ዛፍ ዘር፣ “ፍሬ” ይባላል።
  • የአንዳንድ ወርካ ዛፍ ቅርንጫፎች 6 ሜትር ገደማ ያህል ስፋት አሏቸው።
  • ወርካ የረጅም ዕድሜ ምሳሌ ሲሆን፣ ሌሎች መንፈሳዊ ትርጕሞችም አሉት። አብዛኛውን ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ቅዱስ ከሚባሉ ቦታዎች ጋር ይያያዛል።

ወሲባዊ እርኩሰት

ወሲባዊ እርኩሰት የሚለው ኃረግ በአንድ ወንድ እና ሴት መካከል የከጋብቻ ውጪ የሚፈጸም ወሲብን ያመለክታል። ይህ ከእግዚአብሔር ሕግ ጋር ይቃረናል።


ወንጀል፣ ወንጀለኛ

“ወንጀል” ብዙውን ጊዜ የሚያመለክተው የአንድ አገርን ወይም መንግሥትን ሕግ የማፍረስ ኃጢአትን ነው። እንዲህ ያለውን በደል የፈጸመ ሰው ወንጀለኛ ይባላል።

  • ሰውን መግደል ወይም የሌላውን ንብረት መስረቅ ወንጀል ከሚባሉት ጥቂቶቹ ናቸው።
  • ብዙውን ጊዜ ወንጀለኛ እስር ቤት ወይም ወህኒ ቤት ውስጥ ተጠብቆ ይቀመጣል።
  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ከፈጸሙት በደል የተነሣ ሊበቀሏቸው ከሚፈልጉ ሰዎች ለመሸሽ ወንጀለኞች ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላው ይቅበዘበዙ ነበር።

ወይን መርገጫ

በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ወይን መርገጫ የወይን ጠጅ ለመሥራት የወይኑ ፍሬ የሚረገጥበት ቦታ ነው።

  • የእስራኤል ወይን መርገጫ መሬት ላይ የተቆፈረ ትልቅ፣ ሰፊ ጉድጓድ ነበር። የወይኑ ዘለላዎች ታችኛው የጉድጓዱ ጠፍጣፋ ቦታ ላይ ይደረጉና የወይኑ ጭማቂ እንዲወጣ ሰዎች በእግራቸው ይረግጡት ነበር።
  • ወይን መርገጫ የእግዚአብሔር ቁጣ ሕዝቡ ላይ መፍሰሱን ለማሳየት በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።

ወይን ጠጅ

ወይን ጠጅ ከወይን ፍሬ ጭማቂ የሚሠራ የተብላላ መጠጥ ነው። ያልተብላላው የወይን ፍሬ ጭማቂም በዚሁ ስም ይጠራል።

  • ወይን ጠጅ ለመሥራት ውስጡ ያለው ፈሳሽ እንዲወጣ ወይን ፍሬው ይጨፈለቃል። በጊዜ ሂደት ጭማቂው ይብላላና አልኮል ይፈጠራል።
  • በጥንት ዘመን ወይን ጠጅ ከምግብ ጋር የተለመደ መጠጥ ነበር። እንደ እሁኑ ዘመን ወይን ጠጅ ብዙ አልኮል አልነበረውም።
  • ወይን ጠጅ ከመጠጣቱ በፊት ብዙውን ጊዜ ውሃ ይገባበት ነበር።
  • አንተ ባለህበት አካባቢ የወይን ጠጅ የማይታወቅ ከሆነ፣ “ውሎ ያደረ የወይን ፍሬ ጭማቂ” ወይም፣ “ከወይን ፍሬ የሚሠራ የተብላላ መጠጥ” ወይም፣ “የተብላላ መጠጥ” በማለት መተርጎም ይችላል።

ወይን ጠጅ ኀላፊ

በብሉይ ኪዳን ዘመን፣ “ወይን ጠጅ ኀላፊ” ለንጉሡ ወይን በጽዋ የሚያቀርብ ሰው ሲሆን፣ ወይኑ ያልተመረዘ መሆኑን ለማረጋገጥ ብዙውን ጊዜ ኀላፊው መጀመሪያ እንዲቀምስ ይደረግ ነበር።

  • ቃል በቃል ትርጕሙ፣ “ጽዋ አቅራቢ” ወይም፣ “ጽዋውን የሚያቀርብ ሰው” ማለት ነው።
  • ወይን ጠጅ ኀላፊ በንጉሡ ዘንድ የተወደደና እምነት የሚጣልበት ነበር።
  • ታማኝና ከመሆኑ የተነሣ ወይን ጠጅ ኀላፊው መሪው በሚያደርገው ውሳኔ ተጽዕኖ የማሳደር ዐቅም ነበረው።
  • ነህምያ እስራኤላውያን በባቢሎን ምርኮ ውስጥ በነበሩ ዘመን የፋርስ ንጉሥ የአርጤክስስ ወይን ጠጅ አሳላፊ ነበር።

ወዳጅ (አፍቃሪ)

“ወዳጅ” የሚለው ቃል፣ “የሚወድ ሰው” ማለት ሲሆን ብዙውን ጊዜ የሚያመለክተው ግብረ ሥጋዊ ግንኙነት ያላቸው ሰዎችን ነው።

  • የግብረ ሥጋ ግንኙነት በባልና በሚስት መካከል ብቻ መደረግ እንዳለበት የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ወዳጅ” የሚል ቃል ጥቅም ላይ ከዋለ ብዙውን ጊዜ ከሌሎች ያላገቡ ሰዎች ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት እያደረጉ ያሉ ያላገቡ ሰዎች ያመለክታል።
  • የዚህ ዐይነቱ ተገቢ ያልሆነ የግብረ ሥጋ ግንኙነት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጣዖቶችን በማምለክ እስራኤል እግዚአብሔር ላይ ማመፅዋን ለማመልከትም ጥቅም ላይ ውሏል። ስለዚህም፣ “ወዳጅ” የሚለው ቃል የእስራኤል ሕዝብ ያመለኳቸው ጣዖቶችን ለማመልከት በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ውሏል ማለት ነው። በእንዲህ ያሉ ዐውዶች ይህ ቃል፣ “የረከሰ ግንኙነት” ወይም፣ “የዝሙት ጓደኛሞች” ወይም፣ “ጣዖቶች” ተብሎ መተርጎምም ይችላል።
  • የገንዘብ፣ “ወዳጅ” ገንዘብ ለማግኘትና ሀብታም ለመሆን በጣም የጋለ ፍላጎት ያለው ማለት ነው።
  • ማሕልየ መሐልይ በተባለው የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ፣ “ወዳጅ” የተሰኘው ቃል ቀና ወይም አዎንታዊ በሆነ መልኩ ቀርቧል።

ወገብ

ወገብ በታችኛው ጎድንና በዳሌ አጥንት መካከል የሚገኝ የሰው ወይም የእንስሳ አካል ክፍል ነው፣ አንዳንዴ ታችኛው የሆድ ዕቃም ይባላል።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምሳሌያዊ ወይም ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ የወንድን የመራቢያ አካል ያመለክታል፤ ምክንያቱም የወደ ፊት ዘሮቹ መገኛ ቦታ በመሆኑ ነው።
  • “ወገብን መታጠቅ” የሚለው ፈሊጣዊ ገለጻ ለከባድ ሥራ መዘጋጀትን ነው የሚያመለክተው። ይህ አባባል የመጣው አንድ ሰው ያለ ምንም ችግር መሄድ ሲፈልግ ታችኛውን የቀሚሱን ጫፍ ወገቡ ላይ ወዳለው ቀበቶ ሥር ሸጥ ያደርግ ከነበረበት ሁኔታ ነው።
  • ወገብ የብርታት ምንጭ መሆኑ ተነግሯል።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥብዙ ጊዜ “ወገብ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ለመሥዋዕት የቀረበውን እንስሳ ታችኛውን የጀርባውን ክፍል ነው።
  • “ከወገብህ የሚገኘው” የሚለው ሐረግ፣ “ዘርህ ይሆናል” ወይም፣ “ከዘርህ ይወለዳል” ወይም፣ “እግዚአብሔር ከአንተ እንዲገኝ ያደርጋል” ተብሎ መተርጎም ይችላል።

ወጥመድ፣ አሽከላ

“ወጥመድ” እና፣ “አሽከላ” የተሰኙት ቃሎች እንስሶችን ለመያዝና ከዚያ እንዳያመልጡ ለመድረግ ጥቅም ላይ የሚውሉ ነገሮች ናቸው። የሚጠመደውን እንስሳ በድንገት እንደያዘው ብዙውን ጊዜ ወጥመዱ ወይም አሽክላው ድብቅ ቦታ ላይ ይቀመጣል

  • በመንፈሳዊ መልኩ አንድን ሰው ማጥመድን አስመልክቶ እነዚህ ቃሎች በምሳሌነት ጥቅም ላይ ይውላሉ
  • ብዙውን ጊዜ ወጥመድ እንስሳው ሲረግጠው እግሩን ለመያዝ በድንገት የሚጠብቅ የገመድ ወይም የሽቦ ሸምቀቆ ይኖረዋል
  • ብዙውን ጊዜ ወጥመድ የሚሰራው ከብረት ወይም ከእንጨት ሲሆን የእንስሳውን አንድ አንድ አካል ክፍል በፍጥነትና በኅይል ለመያዝ እርስ በርስ የሚገጣጠሙ ሁለት ክፍሎች አሉት’
  • ኅጢአትና ፈተና ሰዎችን እንደሚያጠምድ ወጥመድ መሆናቸውን ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ በእነዚህ ቃሎች ይጠቅማል
  • ሰዎች ኅጥአትን እንዲፈጽሙ ለማነሳሳት ሰይጣንና ክፉ ሰዎች ወጥመድ እንደሚዘረጉ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል
  • “ወጥመድ መዘርጋት” ሌላውን ለመያዝ በፍጥነት እንዲዘጋ ወጥመድ ማዘጋጀት ማለት ነው
  • “ወጥመድ ውስጥ መውደቅ” እንድ ሰው ውስጥ እንዲወድቅ ታስቦ የተቆፈረ ጉድጓድ ወይም ጉድባ ውስጥ መውደቅን ያመለክታል
  • በኅጢአት ወጥመድ መያዝ ወይም መጠመድ አደገኛ ውጤት ያስከትላል

ዋሽንት

መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ዋሽንት ከአጥንትና ከእንጨት የሚሠራ የሙዚቃ መሣሪያ ሲሆን ድምፅ እንዲያወጣ መተላለፊያዎች ይሠሩለትም ነበር።

  • ብዙውን ጊዜ እረኞች ራሳቸውን ዘና ለማድረግና እንስሶቻቸውንም ለማረጋጋት ዋሽንት ይጫወቱ ነበር።
  • በጥንቱ ቤተ መቅደስ በዝማሬ አገልግሎት ዋሽንት ጥቅም ላይ ይውል ነበር።
  • ንጉሥ ናቡከደነፆር ለጣኦቶቹ ክብር ሰዎች እንዲጫወቱ ካዘዛቸው የሙዚቃ መሣሪያዎች አንዱ ዋሽንት ነበር።

ዋጋ፣ ሽልማት

ይህ ቃል የሚያመለክተው መልካምም ሆነ ክፉ አንድ ሰው ላደረገው የሚቀበለውን ነገር ነው። “ዋጋ መስጠት” የሚያመለክተው የሚገባውን ነገር ለሰው መስጠትን ነው።

  • ሽልማት አንድ ሰው መልካም በማድረግ ወይም ለእግዚአብሔር በምታዘዙ የሚቀበለውን መልካም ወይም አዎንታዊ ነገር ሊሆን ይችላል።
  • አንዳንዴ “ዋጋ” የሚለው ቃል ከመጥፎ ፀባይ የተነሣ የሚመጣውን አሉታዊ ውጤት ያመለክታል፤ ለምሳሌ፣ “ለክፉ ሥራው የሚገባውን ዋጋ” እንደሚለው በዚህ ዐውድ፣ “ዋጋ” የሚያመለክተው ቅጣትን ወይም ለክፉ ሥራ የሚገባውን አሉታዊ ውጤት ነው።

ውሃ፣ ውሆች

ከመጀመሪያው ትርጕሙ በተጨማሪ፣ “ውሃ” - እንደ ውቅያኖስ፣ ባሕር፣ ሐይቅ ወይም ወንዝን የመሳሰሉ የውሃ አካል ይጨምራል።

  • “ወሆች” የሚለው የሚያመለክተው የውሃ አካላትን ወይም ብዙ የውህ ኣመገኛዎችን ነው። በጣም ስፋት ያለው ውሃን የሚያመለክት አጠቃላይ ቃል ሊሆንም ይችላል።
  • ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ፣ “ውሆች” ከባድ ችግርን፣ መከራንና አዳጋች ሁኔታን ያመለክታል። ለምሳሌ እግዚአብሔር በውሆች ውስጥ ብናልፍ እንኳ እንደሚጠብቀን ቃል ገብቷል።
  • “ብዙ ውሆች” የሚለው ሐረግ ችግሩ ምን ያህል ብዙ መሆኑን ያሳያል።
  • የቤት እንስሳትን፣ “ማጠጣት” ለእነርሱ ውሃ ማቅረብ ማለት ነው። መጥንት ዘመን ብዙውን ጊዜ እንዲህ የሚደረገው በመቅጃ ውሃ ከጉድጓድ በምቅዳትና እንስሶቹ እንዲጠቱ ገንዳ ላይ በማፍሰስ ነበር።
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር ለሕዝቡ፣ “የሕያው ውሃ ምንጭ” እንደሆነ ተነግሯል። ይህም ማለት እርሱ የመንፈሳዊ ኀይልና ርካታ ሁሉ ምንጭ ነው ማለት ነው።
  • አዲስ ኪዳን ውስጥ ኢየሱስ፣ “ሕያው ውሃ” የሚለውን ቃል የተጠቀመበት ለመለወጥና አዲስ ሕይወት ለማምጣት ሰው ውስጥ የሚሠራውን መንፈስ ቅዱስን ለማመልከት ነበር።

ውድ፣ የተወደደ፣ ክቡር

“ውድ” የሚለው ቃል በጣም የተወደዱ፣ በጥቂቱ የሚገኙ ወይም ከፍ ያለ ዋጋ ያላቸውን ሰዎች ወይም ነገሮችን ያመለክታል።

  • “ክቡ ድንጋይ” ወይም፣ “የከበረ ዕንቁ” የተለያየ መልክ ያላቸውን ወይም ውብ የሚያደርጋቸው ባሕርያት ያላቸው ድንጋዮችና ማዕድኖችን ያመለክታል።
  • ዕንቁ፣ አልማዝና ኤመራልድ የከበሩ ድንጋዮች ዐይነት ናቸው።
  • ወርቅና ብርም፣ “የከበሩ ድንጋዮች” ይባላሉ።
  • ሕዝቡ በእርሱ ፊት የከበሩ (ብርቅ) መሆናቸውን ያህዌ ይናገራል (ኢሳይያስ 43፡4)
  • ገርና ጭምት መንፈስ በእግዚአብሔር ፊት ክብሩ ዋጋ እንዳለው ጴጥሮስ ጽፏል (1ጴጥሮስ 3፡4)።
  • ይህ ቃል፣ “ክቡር” ወይም፣ “በጣም ውድ” ወይም፣ “ብርቅ” ወይም፣ “ከፍ ያለ ዋጋ (ግምት) ያለው” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

ዐመድ

“ዐመድ” የሚለው የሚያመለክተው እንጨት ከተቃጠለ በኋላ የሚቀረውን ግራጫ ዱቄት መሳይ ነገርን ነው። ዋጋ ቢስ ውይም ጥቅም የሌለውን ነገር ለማመልከት ምሳሌያዊ በሆን መልኩ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጥቅም ላይ ውሏል።

  • የ “ዐመድ ክምር” የዐመዶች ቁልል ማለት ነው።
  • በጥንት ዘመን ዐመድ ላይ መቀመጥ የሐዘን ወይም የለቅሶ ምልክት ነበር።
  • ሐዘን ሲያጋጥም ማቅ መልበስና ዐመድ ላይ መቀመጥ ወይም ርስ ላይ ዐመድ መነስነስ የዘመኑ ባሕል ነበር።
  • አንድ ሰው ጥቅም የሌለውን ነገር የሚይያሳድድ ከሆነ ተግባሩ፥ “ዐመድ እንደመብላት” ነው ይባል ነበር
  • አንዳንዴ መጽሐፍ ቅዱስ ስለዐመድ ሲናገር፥ “አፈር” በሚለው ቃል ይጠቀማል። ደረቅ መሬት ላይ የሚገኘውን በጣም የላመ ደቃቅ አቧራን ያመለክታል።
  • “ዐመድ” የሚለውን ቃል ሲተረጉሙ፥ እንጨት ከተቃጠለ በኋላ የሚቀረውን ለማመልከት ነው

የትርጉም ሥራው ፕሮጀክት በሚጠቀምበት ቃል ተጠቀሙ


ዐምድ፣ ምሰሶ

“ዐምድ” ጣራ ወይም ሌላውን የሕንጻ ክፍል ደግፎ ለመያዝ የሚያገለግል ቀጥ ብሎ የሚቆም ነገር ነው። “ምሰሶ” የዐምድ ሌላ ስም ነው።

  • ከብሉይ ኪዳን እንደምንመለከተው ሳምሶን በፍልስጥኤማውያን በተያዘ ጊዜ ሕንጻውን ደግፈው የነበሩ ዐምዶች በመነቅነቅ ቤተ መቅደሳቸው እንዲፈርስ አድርጓል።
  • አንዳንዴ ዐምዱ የመቃብር ምልክት ወይም ይአንዳች ታሪካዊ ሁነት መታሰቢያ በመሆን ያገለግላል።
  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ሕንጻዎችን የሚደግፉ ዐምዶች የሚሠሩት አብዛኛውን ጊዜ ቀጥ ብሎ ከወጣ አንድ ግንድ ወይም ድንጋይ ነበር።
  • ብዙውን ጊዜ የመታሰቢያ ዐምድ የሚሆነው አንድ ትልቅ ድንጋይ ወይም የተለያዩ ነገሮች ክምር ነበ።ር
  • አንዳንዴ፣ “ዐምድ” የሚለው ቃል ሐሰተኛ አምላክን ለማምለክ የሚያገለግል ምስል ማለትም ይሆናል። ሌላው መጠሪያው፣ “የተቀረጸ ምስል” ሲሆን፣ “ሐውልት” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
  • “ዐምድ” ቀጥ ብሎ የወጣ ነገር መጠሪያም ይሆናል፤ ለምሳሌ እስራኤል በምድረ በዳ ይጓዙ በነበረ ጊዜ በሌሊት ይመራቸው የነበረው፣ “የእሳት ዐምድ” ወይም የሎጥ ሚስት ዘወር ብላ ከተማዪቱን በመመልከትዋ፣ “የጨው ዐምድ” መሆንዋን የሚያመለክተውን ማየት ይቻላል።
  • እንደ ዐውዱ ሁኔታ ይህ ቃል፣ “ሐውልት” ወይም፣ “ደጋፊ ድንጋይ” ወይም፣ “መታሰቢያ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

ዐዋጅ

ዐዋጅ የሚባለው ሕግን ወይም መምሪያን ለሰዎች በአደባባይ በግልጽ መናገር ነው።

  • የእግዚአብሔር ሕጎችም ዐዋጅ፣ መመሪያ ወይም ትእዛዞች ተብለዋል።
  • እንደ ሕግና ትእዛዝ ሁሉ ሰዎች ለዐዋጅም መታዘዝ አለባቸው።
  • አንድ ሰብዓዊ መሪ ላደረገው ዐዋጅ ምሳሌ የሚሆነን በሮም የሚኖር ሰው ሁሉ ወደ ተወለደበት አካባቢ ሄዶ እንዲቆጠር ያዘዘው የአውጉስጦስ ቄሳር ዐዋጅ ነው።
  • አንድ ነገር ማወጅ ልንታዘዘው የሚገባ ትእዛዝ መስጠት ማለት ነው። ይህም፣ “ማዘዝ” ወይም፣ “መናገር” ወይም፣ “መመሪያ መስጠት” ተብሎ መተርጎም ይችላል።
  • “ዐዋጅ” ተነገረ ማለት ያ ነገር፣ “በእርግጥ ይሆናል” ወይም፣ “ያ ነገር በፍጹም አይለወጥም” ወይም፣ “ያ ነገር እንዲደረግ ተወስኖአል” ማለት ነው።

ዐይነት፣ ዐይነቶች

“ዐይነት” እና “ዐይነቶች” የሚባሉት ባሕርያትን በመጋራት የተያያዙ ነገሮች ቡድን ወይም ምድብ ናቸው።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይህ ቃል የሚያመለክተው እግዚአብሔር ዓለምን ሲፈጥር የፈጠራቸው የተለያዩ ዕፅዋትና እንስሳትን ምድብ የማመልከት ነው።
  • ብዙውን ጊዜ በእያንዳንዱ “ዐይነት” ውስጥ የተለያዩ ዘሮችና ልዩ ልዩ ነገሮች ይኖራሉ። ለምሳሌ ፈረሶች፣ በቅሎዎችና አህዮች፣ አንድ፣ “ዐይነት” ቤተ ሰብ ቢሆኑም፣ የተለያዩ፣ ዝርያዎች ናቸው።
  • እያንዳንዱ፣ “ዐይነት” ከሌሎች ልዩ የሚያደርገው፣ የዚያ ምድብ ወገኖች፣ የእነርሱን፣ “ዐይነት” የሚያፈሩ መሆኑ ነው።

ዓሣ አጥማጆች

ዓሣ አጥማጆች ለመግብ የሚሆናቸውንና ሸጠው ገንዘብ የሚያገኙበትን ዓሣ ከባሕር የሚያጠምዱ ሰዎች ናቸው። አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን ዓሣ አጥማጆች ዓሣ የሚያጠምዱት በመረብ አማካይነት ነበር።

  • በኢየሱስ ከመጠራታቸው በፊት ጴጥሮስና ሌሎቹ ሐዋርያት ዓሣ ያጠምዱ ነበር።
  • የእስራኤል ምድር የተለያዩ ባሕሮች ባሉበት ቦታ በመሆኑ ስለዓሣ እና ዓሣ አጥማጆች ብዙ ማጣቀሻዎች አሉት።
  • ይህ ቃል፣ “ዓሣ የሚይዙ ሰዎች” ወይም፣ “ዓሣ በመያዝ ገንዘብ የሚያገኙ” ተብሎ መተርጎም ይችላል።

ዓሣማ፣ እሪያ

ዓሣማ ሰዎች ለምግብነት የሚያረቡት ባለ አራት እግርና ሸኾና ያለው እንስሳ ነበር። ሥጋው የዓሣማ ሥጋ ይባላል።

  • የዓሣማ ሥጋ እንዳይበሉና እንደ ርኵስ እንዲቆጠር እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ተናግሮአል። ዛሬም ቢሆን እስራኤላውያን እንደ ርኵስ ስለሚቆጥሩት ሥጋውን አይበሉም።
  • ሌሎች ሰዎች ለምግብነት እንዲገዟቸው ዓሣሞች በእርሻ ቦታ እንዲረቡና እንዲያድጉ ይደረግ ነበር።
  • እርሻ ቦታ ሳይሆን ዱር ውስጥ የሚኖሩ ዓሣሞችም አሉ፤ እነዚህ የዱር ዓሣዎች የሚባሉት ናቸው። ሹል ጥርሶች ስላሉዋቸው እንደ አደገኛ አውሬ ይቆጠራሉ።

ዕረፍት

“ዕረፍት” የሚለው ቃል ዘና ለማለትና ኀይልን ለማደስ የሚሠሩትን ማቆም ማለት ነው።

  • አንድ ነገር፣ “ዐርፏል” ከተባለ፣ እዚያ ቦታ ቆሟል ወይም ተቀምጧል ማነት ነው።
  • “ያረፈች” ጀልባ ቀዘፋ ላይ ያልሆነች፣ ይልቁን ወደቡ ላይ አርፋ የቆመች ማለት ነው።
  • ሰዎች ወይም እንስሳት አርፈዋል ከተባለ ራሳቸውን ዘና ለማድረግ ተቀምጠዋል ወይም ተጋድመዋል ማለት ነው።
  • በሳምንቱ ሰባተኛ ቀን እንዲያርፉ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አዟል። ያ ምንም ሥራ የማይሠራበት ቀን፣ “ሰንበት” ይባላል።

ዕቁባት

ዕቁባት ቀድሞውኑ ሚስት ያለችው ወንድ ሁለተኛ ሚስት ናት። ብዙውን ጊዜ ዕቁባት የሰውየው ሕጋዊ ሚስት አትሆን።

  • በብሉይ ኪዳን ዘመን ዕቁባት የሚሆኑት እንስት ባሪያዎች ነበሩ።
  • በግዢ፣ በጦር ጊዜ ድል በማድረግ ወይም ለዕዳ በሚደረግ ክፍያ ዕቁባት ማግኘት ይቻላል።
  • አንድ ንጉሕ ብዙ ዕቁባቶች ካሉት ብዙውን ጊዜ የኃይሉና የሥልጣኑ ምልክት ተደርጎ ይወሰድ ነበር።
  • ዕቁባት የመያዝ ልምምድ ከእግዚአብሔር ፈቃድ የሚጻረር መሆኑን አዲስ ኪዳን ያስተምራል።

ዕቡይ

ዕቡይ ሰው ከሚገባው በላይ ስለ ራሱ ከፍ ያለ ግምት አለው።

  • “ዕቡይ” የእብሪተኝነት ዝንባሌ ያለው፣ “ትዕቢተኛ” ሰው ነው።
  • ስለ ራሱ በትዕቢት የሚያስብ ሰውን ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ “ዕቡይ ዐይን” ወይም፣ “ዕቡይ አንገት” የተሰኙ አገላለጾች አሉት።

ከ . . . ጋር ግንኙነት፣ ከ . . . ጋር መተኛት፣ አብሮ ተኛ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እነዚህ ቃሎች በተዘዋዋሪ ግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸምን የሚያመለክቱ ናቸው።

  • ከአንድ ሰው ጋር መተኛት ከዚያ ሰው ጋር ግብረ ሥጋ መፈጸምን የሚመልከት የተለመደ አነጋገር ነው። የዚህ ኀላፊ ጊዜ፣ “አብሮ ተኛ” የሚለው ነው።
  • “መሐልዩ መሓልይ ዘሰሎሞን” በተሰኘው የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ULB የተሰኘው ትርጕም፣ “ፍቅር መሥራት” ብሎታል፤ በዚያ ዐውድ ውስጥ፣ “ፍቅር” ግብረ ሥጋ ግንኙነትን ያመለክታል። ይህ፣ “ከ . . . ጋር ፍቅር መሥራት” ከሚለው አገላለጽ ጋር ይገናኛል።

ዕቡይ/ትዕቢተኛ፣ ትዕቢት፣ ኩራት፣ ኩሩ

“ትዕቢተኛ” እና፣ “ትዕቢት” ስለ ራሱ ከፍ ያለ ሐሳብ ያለውንና ከሌሎች የበለጠ እንደ ሆነ የሚያስብን ሰው ያመለክታል።

  • ብዙውን ጊዜ ትዕቢተኛ ሰው ስሕተቱን አይቀበልም። ትሑት አይደለም።
  • ትዕቢት በሌሎች መንገዶችም ለእግዚአብሔር ወዳለመታዘዝ ያደርሳል።
  • አንዳንዴ ትዕቢት ኩራት የሚል ትርጕምም አለው፤ እንዲህ ከሆነ አንድ ሰው በፈጸመው ነገር “መኩራት” ወይም ልጆቻችን ባከናወኑት ነገር “መኩራት” የሚል ቀና ትርጕም ይኖረዋል። “በሥራዬ እኮራለሁ” ከተባለ ሥራህን በሚገባ በማከናወንህ ደስ ብሎሃል ማለት ነው።
  • አንድ ሰው ትዕቢተኛ ሳይሆን በሠራው ሥራ ሊኮራ ይችላል።
  • “ትዕቢተኛ” የሚለው ቃል ሁሌም አሉታዊ ሲሆን፣ “እብሪተኛ” ወይም፣ “እምቢተኛ” ወይም “ራስን ማግዘፍ” ማለት ነው።
  • “ትዕቢት” የሚለው ስም፣ እብሪት” ወይም፣ “ኩሩ” ወይም፣ “ራሱን የሚያገዝፍ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

ዕጣ፣ ዕጣ መጣል (ማውጣት)

“ዕጣ” አድልዎ የሌለበት ምርጫ ወይም ውሳኔ ለማድረግ ሲታሰብ ሰዎች ምልክት የተደረገባቸው ተመሳሳይ ነገሮችን ይጥላሉ ወይም ከሌሎች ተመሳሳይ ነገሮች መካከል አንዱን ማንሣት ማለት ነው። እግዚአብሔር ምን እንዲያድረርጉ እንደሚፈልግ ማወቅ የሚፈልጉ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ዕጣ በመጣል ዕጣ በማውጣት ይጠቀሙ ነበር።

  • ቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበሩ የተለዩ ተግባሮችን በተገቢው ጊዜ መፈጸም ያለበትን ካህን ለመምረጥ ዕጣ ይጣል ነበር።
  • ኢየሱስን የሰቀሉ ወታደሮች ልብሱን ማን መውሰድ እንዳለበት ዕጣ ተጣጣሉ።
  • ዕጣ መጣል የተወሰኑ ተመሳሳይነት ያላቸው ነገሮችን ወደ ላይ መበተንን ወይም ምልክት የተደረገባቸው ድንጋዮች ወይም የሸክላ ዕቃ ስብርባሪዎችን ማንከባለልንም ይጨምራል።
  • ለዚሁ ተብሎ ምልክት የተደረገበትን ነገር ያንከባለለ ሰው ለተፈለገው ጉዳይ ይመረጣል።
  • በአንዳንድ ባሕሎች ሰዎች ዕጣ ሲያወቱ የተወሰኑ ሣሮች ይጠቀማሉ። የሣሮቹን ርዝመት ማንም ማየት እንዳይቻል አንድ ሰው ሥራሮቹን ይይዛል። እያንዳንዱ ሰው ከሣሮቹ አንዱን ይመዝዛል፤ በውላቸው መሠረት ረጅሙን ወይም አጭሩን የመዘዘ ሰው ለተፈለገው ነገር ይመረጣል።
  • “ዕጣ መጣል” የሚለው ቃል፣ “ዕጣ ማውጣት” ተብሎ መተርጎም ይችላል። ዕጣ መጣል ሲባል ለዕጣው የሚያገለግሉ ነገሮችን ራቅ አድርጎ መጣል የሚል ትርጕም እንዳይኖረው አረጋገጡ።

ዕጣን

ዕጣን ከዛፍ ሙጫ የሚገኝ ጣፋጭ ሽታ ያለው ቅመም ነው። ሽቱኑ ሌላም ጣፋጭ መዓዛ ያለው ነገር ለመሥራት ያገለግላል።

  • የሞተ ሰው አካልን ለመቃብር ለማዘጋጀት የሚያገለግል ጠቃሚ ቅመም ነው። ተፈጥሮአዊ ፈስውና መረጋጋት ያስገኛል።
  • ሕፃኑ ኢየሱስን በኢየሩሳሌም ለማየት ከምሥራቅ የመጡት ጠቢባን ይዘውይ ከነበረ ሦስት ስጦታ አንዱ ዕጣን ነበር።

ነጻ መሆን፣ ነጻነት፣ አርነት “ነጻ መሆን” ወይም፣ “ነጻነት” ባርያ አለመሆንን በምንም ዓይነት ቀንበር ሥር አለመሆንን ያመለክታል።

  • “አርነት” የሚለውም ቃል፣ “ነጻነት” ከሚለው ጋር አንድ ትርጕም አለው።
  • “ነጻ ማድረግ” ወይም፣ “ነጻ ማውጣት” የተሰኘው አገላለጽ ከእንግዲህ ከባርነት ወይም ቀንበር ሥር እንዳይሆን ማድረግ ማለት ነው።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እነዚህ ቃሎች ብዙውን ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውሉት በኢየሱስ የሚያምኑ ሰዎች ከእንግዲህ ከኃጢአት ኀይል በታች አለመሆናቸውን በሚያመለክት ምሳሌያዊ አነጋገር ነው።
  • “አርነት መውጣት” ወይም በመንፈስ ቅዱስ ትምህርትና ምሪት ነጻ ሆኖ መኖር እንጂ፣ “ነጻነት” ከእንግዲህ የሙሴን ሕግ ከመጠበቅ ግዴታ ነሣ መሆንንም ሊያመለክት ይችላል።

ዕጣን

ዕጣን እሳት ላይ በሚደረግበት ጊዜ ደስ የሚል ሽታ የሚሰጥ ጣፋጭ መዓዛ ያላቸው ቅመሞድ ድብልቅ ነው። እነዚህ ቅመሞች ከዕፅዋት ክፍሎች የተገኙ ሲሆኑ፣ በጣም ጥቃቅን እስኪሆኑ ድረስ ይደቅቃሉ።

  • ለእርሱ መሥዋዕት የሚሆን ዕጣን እንዲያጨሱ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ተናግሮአል። ዕጣኑ የሚቀመመው እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ሁሉም እኩል መጠን ካላቸው አምስት ቅመሞች ነበር። የተቀደሰ ዕጣን በመሆኑ፣ ለሌላ ዓይነት ዓላማ እንዲውል አይፈቀድም ነበር።
  • ለዕጣን ማጨሻ ብቻ የተመደበ የወርቅ መሠዊያ ነበር።
  • በእያንዳንዱ የጸሎት ጊዜ ቢያንስ በቀን አራት ጊዜ ዕጣኑ መጨስ ነበረበት።
  • በተጨማሪም የሚቃጠል ሥጋ መሥዋዕት በሚቀርብበት ጊዜ ሁሉ ዕጣን መጨስ ነበረበት።
  • የዕጣን መጨስ ጸሎትንና ከሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር የሚወጣ አምልኮን ይወክላል።
  • ዕጣን የሚለውን ቃል ለመተርጎም ሌሎች መንገዶች፣ “ጣፋጭ ሽታ ያለው ቅመም” ወይም፣ “ጥሩ ሽታ ያላቸው ተክሎች” የተሰኙ ናቸው።

ዕፍረት፣ አሳፋሪ፣ አፈረ

ዕፍረት አንድ ሰው ወይም ሌላው ካደረገው መጥፎ ወይም ተገቢ ያልሆነ ነገር የተነሣ የሚደርስ ውርደት ወይም ጥሩ ስሜት እንዳይኖር የሚያደርግ ሕመም ነው

  • “አሳፋሪ” ነገር ተገቢ ያልሆነ ወይም፣ የሚያዋርድ ነገር ነው
  • “አፈረ” የሚለው አንድ ሰው መጥፎ ወይም ተገቢ ያልሆነ ነገር ሲያደርግ የሚሰማውን ስሜት ያመለክታል
  • “ማሳፈር” – ማሸነፍ ወይም ውርደት እንዲሰማቸው ኅጢአታቸውን መግለጥ ማለት ነው
  • ነቢዩ ኢሳይያስ ጣዖት የሚሠሩና የሚያመልኩ እንደሚያፍሩ ይናገራል
  • አንድ ሰው ከኅጢአቱ በንስሐ ካልተመለሰ ኅጢአቱን በመግለጥና እርሱን በማዋረድ ያንን ሰው እግዚአብሔር ያሳፍረዋል

ዘላለም

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ዘላለም” የሚያመለክተው ፍጻሜ የሌለውን ጊዜ ነው። አንዳንዴ፣ በታም ረጅም ጊዜን ለማመልከትም ጥቅም ላይ ይውላል።

  • “ከዘላለም እስከ ዘላለም” አንድ ነገር ሁሌም እንደሚኖር አጽንዖት የሚሰጥ ቃል ነው።
  • “ከዘላለም እስከ ዘላለም” የሚለው ሐረግ ዘላለም ወይም የዘላለም ሕይወት ምን ማለት መሆልኑን የሚያሳይ አገላለጽ መንገድ ነው። ማለቂያ ወይም ማብቂያ የሌለውን ጊዜ ያመለክታል።
  • የዳዊት ዙፋን፣ “ለዘላለም” እንደሚጸና እግዚአብሔር ይናገራል። ይህ የሚያመለክተው የዳዊት ዘር የሆነው ኢየሱስ ለዘላለም እንደሚነግሥ ነው።

ዘመን/ዕድሜ

“ዘመን/ዕድሜ” አንድ ሰው የኖረበት ዓመት ቁጥር ያመለክታል አጠቃላይ በሆነ መልኩ ጊዜን ወይም ወቅትን ያመለክታል።

  • የተወሰነ የጊዜ ገደብን የሚያመለክቱ ሌሎች ቃሎች “ዘመን” እና “ወቅት” የተሰኙት ናቸው።
  • እየሱስ ፣ይህን ዘመን፣ ክፋት፣ ኅጢአትና ዐመፃ ምድርን ሞልቶ ያለበት አሁን ያለው ጊዜ ብሎታል።
  • በአዲስ ሰማይና በአዲስ ምድር ጽድቅ የሚገዛበት ወደ ፊት የሚመጣ ጊዜም ይኖራል።

ዘመድ

“ዘመድ” በሥጋና በደም የቅርብ ግንኙነት ያለው ሰው ነው።

  • “ዘመድ” ወላጆችን፣ አያቶችን፣ እኅት ወንድሞችን ወይም ጥቂት ራቅ የሚሉ አክስቶችን፣ አጎቶችን ወይም የእኅት የወንድም ልጆችን የመሳሰሉ ለአንድ ሰው ቀረቤታ ያላቸው ሰዎች ናቸው።
  • በጥንቱ እስራኤል አንድ ወንድ ከሞተ ለእርሱ ቅርበት ያለው ወንድ ዘመዱ የሟቹን ሚስት እንዲያገባ፣ ንብረቱን እንዲያስተዳድርና የቤተ ሰቡ ዘር እንዳይጠፋ ማስቀጠል ይጠበቅበት ነበር። እንዲህ ያለው፣ ሂደት፣ “መቤዠት” ይባል ነበር።

ዘራ፣ ዘሪ

መዝራት ተክል ለማግኘት ዘሮችን ምድር ውስጥ ማኖር ማለት ነው። ይህን የሚያደርግ ሰው፣ “ዘሪ” ይባላል

  • ዘር የመዝራትና ተክል የመትከል ዘዴ ሊለያይ ይችላል፤ በጣም የተለመደው ግን እፍኝ ዘር በእጅ ይዞ የታረሰው መሬት ላይ መበተን ነው
  • መዝራት ለሚለው ሌላ ቃል፣ “መትከል” ነው

ዘር

ዘር እርሱን የመሳሰሉ ብዙ ዘሮች እንዲገኙ መሬት ላይ የሚዘራ ወይም የሚተከል የአትክልት ክፍል ነው። በርካታ ምሳሌያዊ ትርጉሞችም አሉት

  • “ዘር” የሚለው ቃል ሕፃን ሴት ማሕፀን ውስጥ እንዲፈጠር ወንድ ወይም ሴት ውስጥ ያለውን ፍሬ ለማመልከት ጥቅም ላይ የሚውል ምሳሌያዊ ቃል ነው
  • ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ “ዘር” የአንድን ሰው ልጆች ወይም ዘሮች ሊያመለክትም ይችላል
  • ይህ ቃል ከአንድ የበለጠ ዘር ወይም ከአንድ የበለጠ ትውልድ ለማመልከት ብዙ ጊዜ ሁለት ትርጉሞች ይኖሩታል
  • ኢየሱስ ስለ ዘሪው በተናገረው ምሳሌ ዘር መልካም መንፈሳዊ ፍሬ እንዲያፈራ ሰውልብ ውስጥ ከሚተከል የእግዚአብሔር ቃል ጋር ተመሳስሎአል
  • ሐዋርያው ጳውሎስም የእግዚአብሔርን ቃል ለማመልከት፣ “ዘር” በተሰኘው ቃል ተጠቅሟል

ዘር (ልጅ)

ዘር (ልጅ) ቀጥተኛ የደምና ሥጋ ዝምድና ያለው ወይም የሩቅ ዘመድ የሆነ ሰው ነው።

  • ለምሳሌ አብርሃም የኖኅ ዘር ነው።
  • የአንድ ሰው ልጆች፣ የልጅ ልጆች፣ የልጅ ልጅ ልጆች፣ ወዘተ የእርሱ ዘሮች ናቸው።

ዘንባባ

“ዘንባባ” ረጃጅም፣ በቀላሉ የሚተጣጠፍ፣ ከጫፉ ጀምሮ እንደማራገቢያ ዓይነት ቅጠል ያበዛባቸው ቅርንጫፎች ያሉት ረጅም የዛፍ ዘር ነው።

  • አብዛኛውን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገርለት “ቴምር” የሚባል ፍሬ ስለሚያፈራው የዘንባባ ዛፍ ነው።
  • ኢየሱስ በአህያ ተቀምጦ ኢየሩሳሌም ሲገባ ሰዎቹ እርሱ ፊት መሬቱ ላይ የዘንባባ ዝንጣፊ አንጥፈው ነበር።
  • የዘንባባ ቅርንጫፎች(ዝንጣፊዎች) ሰላምንና የድል መታሰቢያን ያመለክታትሉ።

ዘይት

ዘይት ከአንዳንድ ተክሎች ወይም ፍሬዎች ሊገኝ የሚችል ወፈር ያለ ፈሳሽ ነገር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን አብዛኛውን ጊዜ ዘይት የሚገኘው ከወይራ ፍሬዎች ነው።

  • የወይራ ዛፍ ለምግብ ማጣፈጫ፣ ለቅባት፣ ለመሥዋዕት፣ ለመብራትና ለመድኃኒትነት ጥቅም ላይ ይውል ነበር።
  • በጥንት ዘመን የወይራ ዛፍ ትልቅ ዋጋ ነበረው፤ የዘይት ባለቤት መሆን የሀብታምነት መገለጫ ተደርጎ ይታሰብ ነበር።
  • በዚህ ቃል ስንጠቀም ለምግብ የሚሆነው ዘይት እንጂ፣ ለሞተር የሚሆን ዘይትን የሚያመለክት እንዳይሆን መጠንቀቅ አለብን። አንዳንድ ቋንቋዎች ለተለያዩ የዘይት ዓይነቶች የተለያዩ ቃሎች አሏቸው።

ዙፋን

ዙፋን አብዛኛውን ጊዜ ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ፍርድ ለመስጠት ንጉሥ የሚቀመጥበት የተለየ ወንበር ነው።

  • ንጉሡን፣ ግዛቱንና ሥልጣኑን ለማመልከት ብዙውን ጊዜ በምሳልያዊ አነጋገር፣ “ዙፋን” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ይውላል።
  • መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔርን በዙፋኑ ላይ እንደ ተቀመጠ ንጉሥ ያቀርበዋል።

ዙፋን

ዙፋን አብዛኛውን ጊዜ ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ፍርድ ለመስጠት ንጉሥ የሚቀመጥበት የተለየ ወንበር ነው።

  • ንጉሡን፣ ግዛቱንና ሥልጣኑን ለማመልከት ብዙውን ጊዜ በምሳልያዊ አነጋገር፣ “ዙፋን” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ይውላል።
  • መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔርን በዙፋኑ ላይ እንደ ተቀመጠ ንጉሥ ያቀርበዋል።

ዜና መዋዕል

“ዜና መዋዕል” የሚለው ቃል በዘመናት ውስጥ በጽሑፍ የሰፈረ ሰነድን ነው።

  • ሁለት የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት፣ “1ዜና መዋዕል” እና “2ዜና መዋዕል” ተብለው ተጠርተዋል።
  • “ዜና መዋዕሎች” የተባሉት መጻሕፍት ከአዳም አንሥቶ የሰዎችን ስም በመዘርዘር የእስራኤልን ሕዝብ ታሪክ በከፊል አስፍረዋል።
  • “1ዜና መዋዕል” የንጉሥ ሳኦልን ፍጻሜና በንጉሥ ዳዊት አገዛዝ ዘመን የተከናወኑ ሁኔታዎች አስፍሮአል።
  • “2ዜና መዋዕል” የቤተ መቅደሱ መሠራትንና የሰሜኑ የእስራኤል መንግሥት ከደቡብ የይሁዳ መንግሥት መከፈሉን ጨምሮ የንጉሥ ሰሎሞንንና የበርካታ ሌሎች ነገሥታት አገዛዝ አስፍሮአል።
  • 2ዜና መዋዕል የሚያበቃው የባቢሎን ምርኮ መጀመሩን በመግለጽ ነው።

ዜጋ

አንድ ዜጋ በአንድ የተወሰነ አገር ወይም መንግሥት ውስጥ የሚኖር ሰው ነው። በተለይም የዚያ አገር ነዋሪ መሆኑን በልጽ ዕውቅና የተሰጠው ሰውን ያመለክታል።

  • እንደ ዐውዱ ሁኔታ ይህ፣ “ነዋሪ” ወይም፣ “ሕጋዊ ኗሪ” ተብሎ መተርጎም ይችላል።
  • አንድ ዜጋ የአንድ ትልቅ አገር ክፍል በሆነ አገር በንጉሥ፣ በፕሬዚደንት ወይም ጠቅላይ ሚኒስትር የሚተዳደር አገር ውስጥ መኖር ይችላል። ለምሳሌ ጳውሎስ ብዙ የተለያዩ አውራጃዎች በውስጡ የያዘው የሮም መንግሥት ዜጋ ነበር፤ ጳውሎስ ከእነዚህ አውራጃዎች በአንዱ ይኖር ነበር።
  • በምሳሌያዊ አነጋገር በኢየሱስ የሚያምኑ ሰዎች የመንግሥተ ሰማይ፣ “ዜጋ” ተብለዋል፤ ይህ የሚያሳየው አንድ ቀን እዚያ የሚኖሩ መሆኑን ነው። እንደ አንድ አገር ዜጋ ሁሉ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር መንግሥት ዜጎች ናቸው።

ዝሙርት አዳሪነት፣ ግልሙትና

“ዝሙት አዳሪነት” ወይም፣ “ግልሙትና” ገንዘብ ለማግኘት ወይም፣ ለሃይማኖታዊ ሥርዓት የግብረ ሥጋ ግንኙነትን የሚፈጽም ሰው ያመለክታል። ብዙውን ጊዜ ዝሙት አዳሪዎችና ጋለሞቶች ሴቶች ቢሆኑም፣ አንዳንዴ ወንዶችም ሊሆኑ ይችላሉ።

  • “እንደ ጋለሞታ” የሚለው ፈሊጣዊ አንጋገር፣ የግብረ ሥጋ ግንኙነት በመፈጸም እንደ ጋለሞታ መኖር ማለት ነው።
  • ሐሰተኛ አማልክት የሚያመልክ ወይም ጥንቆላን የሚለማመድን ሰው ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር አንዳንዴ፣ “ጋለሞታ” በሚለው ቃል ይጠቀማል።
  • ለአንድ ነገር፣ “ራስን ጋለሞታ ማድረግ” ግብረ ሥጋ መፈጠም ማለት ሲሆን፣ በምሳሌያዊ አንጋገር ጥቅም ላይ ከዋለ ሐሰተኛ አማልክትን በማምለክት ለእግዚአብሔር ታማኝ አለምሆን ማለት ነው።
  • በጥንት ዘመን አንዳንድ የአረማውያን መቅደሶች የሃይማኖት ሥርዐትን ለመፈጸም በሴቶችና በወንዶች ጋለሞታዎች ይጠቀሙ ነበር።
  • ይህ ቃል፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጕም የሚሠራለት ቋንቋ እንዲህ ያለውን ሰው ለማመልከት በሚጠቀምበት ቃል ወይም ሐረግ መተርጎም ይችላል። አንዳድን ቋንቋዎች ይህን ለማመልከት ቀጥተኛ ያልሆነ ቃል ይጠቀሙ ይሆናል።

ዝቅተኛ፣ ዝቅተኝነት

“ዝቅተኛ” እና፣ “ዝቅተኝነት” የተሰኙት ቃሎች ድህነትን ወይም ዝቅ ያሉ ማንነትና ደረጃን ያመለክታሉ።

  • ኢየሱስ ሰው ወደ መሆንና ባርያ ወደ መሆን ደረጃ ድረስ ራሱን ዝቅ አደረገ።
  • እርሱ የተወለደው ቤተ መንግሥት ሳይሆን የከብቶች ማደሪያ በረት ውስጥ ስለ ነበር ልደቱም በጣም ዝቅተኛ ነበር።
  • ዝቅተኛ ለሚለው ሌላው ቃል፣ “ትሑት” የሚለው ሊሆን ይችላል።
  • ዝቅተኛ ዝንባሌ የትዕቢተኝነት ተቃራኒ ነው።

ዝግባ

“ዝግባ” የሚለው ቃል ቀይ ቡናማ እንጨት ያለው ሾጣጣ ጫፍ ያለውን ግዙፍ ዛፍ ያመለክታል። እንደ ሌሎች ሾጣጣ ዛፎች ሁሉ እንደ መርፌ የሾሉ ቅጠሎች አሉት።

  • ብሉይ ኪዳን ይህ ዛፍ በብዛት ይበቅልበት ከነበረው ከሊባኖስ ጋር አያይዞ ስለ ዝግባ ዛፍ ብዙ ይናገራል።
  • የዝግባ ዛፍ የኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ሲሠራ ጥቅም ላይ ውሏል።
  • መሥዋዕት ለማቅረብና ሰዎችን በማንጻት ሥርዓትም ጥቅም ላይ ይውል ነበር።

የሐሰት ምስክር፣ ጠማማ ምስክር፣ ሐሰተኛ ወሬ

“ሐሰተኛ ምስክር” እና “ጠማማ ምስክር” ሰዎችን ወይም ሁኔታዎችን በተመለከተ እውነቱን የማይናገር ሰው ሲሆን፣ ብዙውን ጊዜ እንዲህ ሲደረግ የሚታየው በመደበኛ ፍርድ ቦታ ነው።

  • ሐሰተኛ ወሬ የሚባለው ሐሰተኛ ምስክር የተናገረው ነው።
  • “በሐሰት መመስከር” ሰዎችን ወይ ሁኔታዎችን በተመለከተ እውነት ያልሆነውን መናገር ነው።
  • አንድ ሰው እንዲቀጣ ወይም እንዲገደል ለማድረግ ሰዎች ሐሰተኛ ምስክሮችን ቀጥረው ስለነበረበት ሁኔታ መጽሐፍ ቅዱስ በርካታ ታሪኮች አሉት።

የሕይወት መጽሐፍ

“የሕይወት መጽሐፍ” የሚለው ቃል እርሱ ያዳናቸውንና የዘላለም ሕይወት ያሰጣቸውን ሰዎች ስም የጻፈበትን መዝገብ ያመለክታል።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ይህን፣ “የበጉ የሕይወት መጽሐፍ” ይለዋል። “የኢየሱ የበጉ የሆኑ ሰዎች የተጻፈበት የሕይወት መጽሐፍ” ተብሎ መተርጎምም ይችላል። የእርሱ በማመን የዘላለም ሕይወት እንዲኖራቸው የኢየሱስ መስቀል ላይ መሞት የሰዎችን ኃጢአት ዕዳ ከፍሏል።
  • መጽሐፍ፣ “ጥቅልል ጽሑፍ” ወይም፣ “ደብዳቤ፣ መልእክት” ወይም፣ “ጽሑፍ” ወይም፣ “ሕጋዊ ሰነድ” ማለትም ይሆናል። ቃል በቃል ወይም ምሳሌያዊ ሊሆን ይችላል።

የመጠጥ ቍርባን

የመጠጥ ቍርባን ወይን ጠጅ መሠዊያ ላይ ማፍሰስን የሚያካትት ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት ነው። ብዙውን ጊዜ የሚቀርበው ከሚቃጠል መሥዋዕትና ከእህል መሥዋዕት ጋር በአንድነት ነው።

  • የእርሱ ሕይወት እንድ መጠጥ መሥዋዕት እንደሚፈስ ጳውሎስ ተናግሮአል። ይህም ማለት መከራ ቢደርስበትም ምናልባት ከዚያ የተነሣ ሊገደል ቢችልም እግዚአብሔርን ለማገልገልና ለሰዎችም ስለ ኢየሱስ ለመናገር ሙሉ በሙሉ ሕይወቱን ሰጥቷል ማለት ነው።
  • የኢየሱስ መስቀል ላይ ሞት የመጨረሻው የመጠጥ ቍርባን ነበር፤ ምክንያቱም የእርሱ ደም ለእኛ ኃጢአት መስቀል ላይ ፈስሶአል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን፣ ቀን

“ቀን” ቃል በቃል 24 ሰዓት ውስጥ ያለው ጊዜ ነው። ምሳሌያዊ ሆነ መንገድም ጥቅም ላይ ይውላል።

  • የእስራኤላውያንና የአይሁዳውያን ቀን የሚጀምረው ፀሐይ ከምትወጣበት ቀን አንስቶ ፀሐይ የምትጠልቅበት ሁለተኛው ቀን ድረስ ያለው ነው።
  • አንዳንዴ “ቀን” የሚለው ቃል፣ “የያህዌ ቀን” ወይም፣ “የመጨረሻው ቀን” እንደሚባሉት፣ ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ረዘም ያለ ወቅት ወይም ዘመንን ያመለክታል።
  • አንዳንድ ቋንቋዎች እነዚህ ምሳሌያዊ አጠቃቀሞች ለመግለጽ የተለያዩ ፈሊጣዊ ቋንቋዎች ይጠቀሙ ይህናል ወይም “ቀን” የሚለውን ቃል የሚተረጕሙት ቃል በቃል ብቻ (ምሳሌያዊ ሳይሆኝ) ይሆናል።
  • “ቀን” ለሚለው ቃል ሌሎች ትርጕሞች እንደ ዐውዱ አገባብ፣ “ጊዜ”” ወይም፣ “ወቅት” ወይም፣ “ሁኔታ” ወይ፣ “ኹነት” የተሰኙትን ይጨምራል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጊዜ ወር

“ወር” ሲባል አራት ሳምንት ገደማ ያለው ወቅ ነው። እንደምንጠቀምበት የጊዜ አቆጣጠር (በጨረቃ ወይም በፀሐይ) መሠረት አንድ ወር ውስጥ ያሉ ቀኖች ሊለያዩ ይችላሉ።

  • በጨረቃ ቀን አቆጣጠር የእያንዳንዱ ወር ርዝማኔ ጨረቃ በመሬት ዙሪያ ለመዞር እንደሚወስድበት ጊዜ መጠን (ማለት 29 ቀን) ይወሰናል። በዚህ አቆጣጠር በዓመት ውስጥ 12 ወይም 13 ወሮች ይኖራሉ።
  • “አዲስ ጨረቃ” ወይም ብርማ ብርሃን ያለበት የጨረቃዋ ገጽታ ጅማሬ በጨረቃ አቆጣጠር የምንጠቀም ከሆነ የእያንዳንዱ ወር ጅማሬ ይሆናል።
  • እስራኤላውያን ይጠቀሙ የነበሩት በጨረቃ አቆጣጠር ስለ ነበር መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ወሮች ስም በሙሉ የጨረቃ አቆጣጠርን መሠረት ያደረጉ ናቸው።
  • በዚህ ዘመን ጥቅም ላይ የዋለው የፀሐይ አቆጣጠር መሬት በፀሐይ ዙሪያ ለመዞር የሚወስድባት ጊዜ ላይ (365 ቀን ገደማ) የተመሠረተ ነው። በዚህ አቆጣጠር መሠረት ዓመቱ ሁሌም በአሥራ ሁለት ወሮች ይከፈላል፤ የየወሮቹ ርዝመት ከ28 እስከ 31 ቀኖች ገደብ ይወሰናል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጊዜ፣ ሰዓት

ብዙውን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰዓቱ የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውለው አንድ ነገር የተፈጸመበትን ጊዜ ለይቶ ለመናገር ነው።

  • አይሁድ ብርሃን ያለበትን ቀን መቊጠር የሚጀምሩት ፀሐይ ከወጣችበት ጊዜ (ከጠዋቱ 12 አካባቢ) አንሥቶ ነው። ለምሳሌ፣ “የሌሊቱ ሦስተኛ ሰዓት” ከተባለ፣ በዚህ ዘመን አቆጣጠር፣ “ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ” ማለት ነው።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጊዜን የሚያመለክቱ ማጣቀሻዎች፣ በትክክል ከዘመናችን አቆጣጠር ዘዴ ጋር ስልማይስማሙ፣ “ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ” ወይም፣ “ስድስት ሰዓት ገደማ” የተሰኙ ሐረጎችን መጠቀም ይቻላል።
  • እየተነገረ ያለው ስለ የትኛው የቀኑ ክፍል እንደ ሆነ ግልጽ ለማድረግ፣ “ምሽት ላይ” ወይም፣ “ጠዋት ላይ” ወይም፣ “ከሰዓት በኋላ” የሚሉ ሐረጎች ይጨምራሉ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጊዜ፤ ሳምንት

ሳምንት ሰባት ቀኖች ያሉት ጊዜ ነው።

  • በአይሁድ አቆጣጠር ስልት መሠረት ሳምንት የሚጀምረው ፀሐይ ቅዳሜ ከጠለቀችበት ጊዜ ይጀምርና በሚቀጥለው ቅዳሜ ፀሐይ እስከጠለቀችበት ጊዜ ይጀምርና በሚቀጥለው ቅዳሜ ፀሐይ እስከምትጠልቅበት ድረስ ያለው ጊዜ ነው፥
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንዳንዴ፣ “ሳምንት” የሚለው ቃል ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ሰባት የጊዜ ክፍሎችን ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላል፤ ለምሳሌ ሰባት ዓመት።
  • “የሳምንቶች በዓል” ከፋሲካ ሰባት ሳምንት በኋላ የሚመጣ የመከር ጊዜ በዓል ነው። በዓለ ሃምሳ ተብሎም ይጠራል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጊዜ፤ ትጋት

መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን፣ “ትጋት” ይባል የነበረው አንድ የከተማ ጠባቂ ወይም ዘበኛ ጠላት ከሚሰነዝረው የትኛውም ጥቃት ለመጠበቅ ግዳጅ ላይ የሚሆንበት የሌሊቱ ጊዜ ነው።

  • በብሉይ ኪዳን ዘመን እስራኤላውያን፣ “ጅማሬ” (ከፀሐይ መጥለቅ እስከ ሌሊቱ 4 ሰዓት)፣ “መካከለኛ” (ክሌሊቱ 4 እስከ 8 ሰዓት) እና “ጠዋት” (ከ8 ሰዓት እስከ ፀሐይ መውጣት) በመባል የሚጠሩ ሦስት ትጋቶች ነበሩዋቸው።
  • በአዲስ ኪዳን ዘመን፣ አይሁድ የሮማውያንን ሥርዐት ስለ ተከተሉ “መጀመሪያ” (ከፀሐይ መጥለቅ እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት)፣ “ሁለተኛ” (ከ3 ሰዓት እስከ 12 ሰዓት እኩለ ሌሊት)፣ “ሦስተኛ” (ከ6 እስከ 9) እና፣ “አራተኛ” (9 ሰዓት እስከ ፀሐይ መውጣት ድረስ) አራት ትጋቶች ነበሯቸው።
  • እየተነገረ ባለው ትጋት መሠረት እነዚህም፣ “በጣም ሲመሽ” ወይም፣ “ዕኩለ ሌሊት” ወይም፣ “ጠዋት ማለዳ” በተሰኘ አጠቃላይ ቃሎች መተርጎም ይችላሉ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጊዜ፤ ዓመት

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቃል በቃል ጥቅም ላይ ከዋለ፣ “ዓመት” 354 ቀኖች የያዙ ጊዜን ያመለክታል። ይህ ጨረቃ በምድር ዙሪያ ለመዞር የሚወስድባትን ጊዜ መጸት እንደማይደርገው እንደ ጨረቃ አቆጣጠር ነው።

  • በዚህ ዘመን ጥቅም ላይ የዋለው የፀሐይ ዑደትን መሠረት ያደረገው አቆጣጠር እያንዳንዳቸው 12 ወሮች ያሉት 365 ቀኖች አሉት፤ ይህም ምድር በፀሐይ ዙሪያ ለመዞር የሚወስድባት ጊዜ ማለት ነው።
  • በሁለቱም ቀን አቆጣጠር አንድ ዓመት 12 ወሮች አሉት። ይሁን እንጂ የጨረቃ አቆጣጠር ከፀሐይ አቆጣጠር ከዓመት 11 ቀኖች ስለሚቀንስ የጨረቃ ቀን አቆጣጠር ላይ አንድ ተጨማሪ ወር ይኖረዋል። ይህም ሁለቱም የቀን አቆጣጠሮች እርስ በርስ የሚመጣጠን ጊዜ እንዲኖራቸው ይረዳል።
  • አንድ ልዩ ሁኔታ የተፈጸመበትን ጊዜ እንዲሁ በደፈናው ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ዓመት” የሚለው ቃል ምሳሌያዊ በሆነ መንገድም ጥቅም ላይ ይውላል። ይህን የሚመለከቱ ምሳሌዎች፣ “የያህዌ ዓመት” ወይም፣ በረሐብ ዘመን” ወይም፣ “የተወደደችው የጌታ ዓመት” የተሰኙትም ያካትታሉ። በዚህ ዐውድ መሠረት፣ “ዓመት” – “ጊዜ” ወይም፣ “ወቅት” ወይም፣ “ዘመን” ተብሎ መተርጎም ይችላል።

የሚቃጠል መሥዋዕት፣ በእሳት መሠዋት

“የሚቃጠል መሥዋዕት” የሚባለው መሠዊያው ላይ በእሳት ተቃጥሎ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት ዐይነት ነው። የሚቃጠለው ለሕዝቡ ኀጢአት ስርየት ለመሆን ነው። “በእሳት መሠዋት” ተብሎም ይጠራል።

  • ለዚህ መሥዋዕት የሚቀርብ እንስሳት ብዙውን ጊዜ በጎችና ፍየሎች ቢሆኑም፣ በሬዎችና ወፎችም መሥዋዕት ይሆናሉ።
  • የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት ጊዜ ከቆዳው ውጪ የእንስሳው አካል በሙሉ ይቃጠላል። ቆዳው ወይም ሌጦው ለካህኑ ይሰጠዋል።
  • በዓመት ሁለት ጊዜ የሚቃጠል መሥዋዕት እንዲያቀርቡ እግዚአብሔር የአይሁድን ሕዝብ አዝዞ ነበር።

የሚያሰክር መጠጥ

“የሚያሰክር መጠጥ” የሚለው ቃል፣ የተብላሉ መጠጦችን ያመለክታል፣ “አልኮል” መጠጥም ይባላል

  • የአልኮል መጠጦች እንዲብላላ ከተደረገ እህል ወይም ፍራፍሬ ይሥራል። ጠንካራ መጠጦች ሲባል ጠላን፣ ቦርዴን፣ አረቄን፣ ወይን ጠጅን(ከወይን ፍሬ)፣ ከቴምር ፍሬ የሚሠራ ጠጅንና ሰውን የሚያሰክሩ ሌሎች መጠጦችን ሁሉ ያካትታል

የሚያስደስት

«የሚያስደስ ነገር» ማለት ሰውን በእጅጉ የሚያስደት ወይንም በዙ ሐሴትን የሚያመጣ ነገር ማለት ነው በ አንድ ነገር መደሰት ማለት


የማኅፀን ፍሬ

የማኅፀን ፍሬ በሥጋና በደም ከሰዎች ወይም ከእንስሳት ለሚወዱ ሁሉ የሚሰጥ አጠቃላይ ቃል ነው።

  • በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት፣ “የማኅፀን ፍሬ” የሚለው ሐረግ፣ “ልጅ” ወይም፣ “ዘር” የተሰኘ ትርጕም አለው።

የማይጠቅም

“የማይጠቅም” አንዳች ጠቀሜታ የሌለው ማለት ነው።

  • ይህ ቃል፣ “ጥቅም ያለው” ወይም፣ “የማይገባ” ወይም፣ “እርባና ቢስ” ወይም፣ “ከንቱ” ወይም፣ “ረብ የለሽ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

የምግብ ቁርባን

“የምግብ ቁርባን” የሚባለው ለእግዚአብሔር መሥዋዕት የሚቀርብ እህል ወይም እንጀራ ነው።

  • የዚህ ሌላው ስም፣ “የእህል ቁርባን” ነው።
  • ብዙውን ጊዜ የምግብ ቁርባን የሚቀርበው ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር ነው።

የምጥ ጣር

“ምጥ” ላይ ያለች ሴት ልጅ ከመውለዷ በፊት ሕመም ይደርስባታል፤ ይህም “የምጥ ጣር” ይባላል።

  • የክርስቶስ ባሕርይ አማኞች ውስጥ የሚሳልበትን ወይም የሚወለድበትን ሂደት ለማመልከት ጳውሎስ ይህን ቃል በምሳሌያዊ መልኩ ተጠቅሞበታል።
  • በመጨረሻው ዘምን እየጨመረና እያደገ የሚሄደውን መከራና ጭንቀት ለማመልከት የምጥ ጣር እንደ ምሳሌ ቀርቧል።

የራስ ቅል

የራስ ቅል የአንድ ሰው ራስ አጥንት የሆነው ክፍል ነው

  • እንስሳትም የራስ ቅል አላቸው
  • “የራስ ቅል ቦታ” ኢየሱስ የተሰቀለበት የጎልጎታ ሌላው ስም ነው

የስብሰባ ድንኳን

እግዚአብሔር በሲና ተራራ ሕጉን በሰጠ ጊዜ የስብሰባ ድንኳን እንዲሠሩ ለእስራኤላውያን ተናግሮ ነበር። ይህ ከእነርሱ ጋር የሚገናኝበት የተቀደሰ ቦታ ነበር። በምድረ በዳ በሚጓዙበት ጊዜ ይዘውት ይሄዱ ነበር፤ እግዚአብሔር ሲነግራቸው መልሰው ይተክሉት ነበር። * የስብሰባው ድንኳን የእንጨት ማዕቀፎች ላይ በተዘረጋ ጨርቅ የተሠራ ቤት ነበር።

  • የስብሰባውን ድንኳን ከጨርቅና ከእንጨት በተሠራ ግድግዳ በተከበበው ትልቅ አደባባይ መካከል እንዲተክሉ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ተናገረ።
  • መሠዊያውን አደባባዩ መካከል የስብስባው ድንኳን ፊት ለፊት እንዲያኖሩ እግዚአብሔር ነገራቸው። ሰዎች ወደ አደባባዩ በመሄድ ስቶታዎችንና መሥዋዕቶችን ለእግዚአብሔር ማቅረብ ይችላሉ። አገልግሎት ላይ ያሉ ካህናት ሰዎች ያመጡትን ይቀበሉና ሕጉ በሚጠይቀው መሠረት የመሥዋዕቱ መሠዊያ ላይ ያቀርቡታል።
  • የስብሰባው ድንኳን መካከሉ ላይ የተሰቀለ ወፍራም መጋረጃ ነበረው፤ ይህ መጋረጃ ድንኳኑን ለሁለት ይከፍለዋል። መጋረጃው ሰዎች በሌላው ወገን ያለውን ክፍል እንዳያዩና ወደዚያ እንዳይገቡ ይከልል ነበር። የመጀመሪያው ክፍል ቅድስት ይባላል፤ ወድዚያ የሚገቡ ካህናት ብቻ ነበር። ሁለተኛው ክፍል ቅድስተ ቅዱሳን ይባላል፤ ወደዚያ የሚገባው ሊቀ ካህናቱ ብቻ ነበር።

የበላይ ተመልካች

የበላይ ተማልካች የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው የሌሎች ሰዎች መብትና ጥቅም መከበሩን የመቆጣጠር ሥራ በኅላፊነት የሚከታተል ሰው ነው።

  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ ተመልካች የሚባለው በእርሱ ኅላፊነት ስር ያሉ ሠራተኞች ሥራቸውን በአግባቡ እየፈጸሙ መሆኑን የሚከታተል ሰው ነበር።
  • አዲስ ኪዳን ውስጥ ይህ ቃል፣ የጥንት ቤተክርስቲያን መሪዎችን ለመመልከት ጥቅም ላይ ውሏል። የእነርሱ ተግባር ትክክለኛ መጽሐፍ ቅዱሲ ትምህርት ማግኘታቸውን ጨምሮ የአናኞችን መንፈሳዊ ጉዳይ በበላይነት መምራት ነበር።
  • የበላይ ተመልካች የእርሱ፣ “መንጋ” የሆኑትን አጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ አማኞች እንደሚጠብቅ እረኛ እንደሆነ ጳውሎስ ያመለክታል።
  • እንደ እረኛ ሁሉ የበላይ ተመልካችም መንጋውን ይጠብቃል። አማኞችን ይመራል፣ መንፈሳዊ ትምህርትና ክፉ ተፅዕኖ ካላቸው ነገሮች ይጠብቃል።
  • ኢየሱስም ዋናው የቤተክርስቲያን የበላይ ተመልካች ተብሏል።
  • “የበላይ ተመልካች” – “ሽማግሌ” እና፣ “እረኛ/ፓስተር” የተሰኙት ቃሎች ተመሳሳይ መንፈሳዊ መሪዎችን የሚያመለክቱ የተለያዩ አገላልጾች እንደሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ያመለክታል።

የበደል መሥዋዕት

“በደል” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ኀጢአት ማድረግን ወይም ወንጀል መፈጸምን ነው።

  • “መበደል” ግብረ ገባዊ ያልሆነ ነገር ማድረግ ማለትም በእግዚአብሔር ላይ ማመፅ ማለት ነው።
  • “የበደል” ተቃራኒ፣ “ንጹሕነት” ነው።

የበጎ ፈቃድ ስጦታ

የበጎ ፈቃድ ስጦታ ማለት የአይሁድ ሕግ ከሚጠይቀው መሥዋዕት የበለጠ ወይም ያለፈ መሥዋዕት ማለት ነው።

  • በበጎ ፈቃድ የሚቀርበው መሥዋዕት እንስሳ ከሆነ፣ ነጻ ስጦታ በመሆኑ መጠነኛ ጉድለት ቢኖረው እንኳ ይፈቀዳል።
  • የበዓሉ አንድ አካል በመሆኑ እስራኤላውያን ሁሉ በበጎ ፈቃድ መሥዋዕት የቀረበውን እንስሳ ይበላሉ።
  • መጽሐፍ ዕዝራ እንደ ገና ቤተ መቅደሱን እንደ ገና ለመሥራት መሰጠት የተጀመረ የተለየ ዓይነት የበጎ ፈቃድ ስጦታ ይናገራል። ይህም የወርቅና የብር ሳንቲሞችንና የካህናት ልብሶችንም ይጨምራል።
  • የበጎ ፈቃድ ስጦታ መትረፍረፍንና የተዋጣ መከር የማግኘት ጊዜን ስለሚያመለክት ለእስራኤላውያን የደስታ ጊዜ ነበር።

የበጎ ፈቃድ ስጦታ

የፈቃደኝነት መሥዋዕት ማለትበሙሴ ሕግ ያልተጠየቀ የመሥዋዕት አይነት ነው። የበጎ ፈቃድ ስጦታ ማለት የአይሁድ ሕግ ከሚጠይቀው መሥዋዕት የበለጠ ወይም ያለፈ መሥዋዕት ማለት ነው።

  • በበጎ ፈቃድ የሚቀርበው መሥዋዕት እንስሳ ከሆነ፣ ነጻ ስጦታ በመሆኑ መጠነኛ ጉድለት ቢኖረው እንኳ ይፈቀዳል።
  • የበዓሉ አንድ አካል በመሆኑ እስራኤላውያን ሁሉ በበጎ ፈቃድ መሥዋዕት የቀረበውን እንስሳ ይበላሉ።
  • መጽሐፍ ዕዝራ እንደ ገና ቤተ መቅደሱን እንደ ገና ለመሥራት መሰጠት የተጀመረ የተለየ ዓይነት የበጎ ፈቃድ ስጦታ ይናገራል። ይህም የወርቅና የብር ሳንቲሞችንና የካህናት ልብሶችንም ይጨምራል።
  • የበጎ ፈቃድ ስጦታ መትረፍረፍንና የተዋጣ መከር የማግኘት ጊዜን ስለሚያመለክት ለእስራኤላውያን የደስታ ጊዜ ነበር።

የባሕር አውሬ

“የባሕር አውሬ” ውቅያኖስ ወለል ላይ ያሉትን የባሕር ሣሮችንና ተክሎችን የሚበላ ግዙፍ የባሕር እንስሳ ነው

  • ይህ ግራጫና ጠንካራ ቆዳ አለው። እንደ እጅና እግር በሚጠቀምባቸው የአካል ክፍሎቹ ባሕር ውስጥ ይንቀሳቀሳል
  • በጥንት ዘመን ሰዎች የባሕር አውሬን ቆዳና ሌጦ ድንኳን ለመሥሪያ ይጠቀሙበት ነበር። ይህ ቆዳ የመገናኛውን ድንኳን የላይኛውን ክፍል ለመሸፈኛነትም ይጠቅም ነበር
  • እንደ ላም ሣር ስለሚበላ አንዳንድ ሰዎች፣ “የባሕር ላም” በማለት ይጠሩታል፤ በሌሎች ብዙ ነገሮች ግን አይመሳሰሉም

የቤት እንስሶች

“የቤት እንስሶች” የሚባሉት ምግብና ሌሎችም ጠቃሚ ነገሮች ለማግኘት ሰፈር ውስጥ የሚያድጉ እንስሳት ናቸው።

  • የቤት እንስሳት በጎችን፣ ላምና በሬዎችን፣ ፍየሎችን፣ ፈረሶችንና አይሆችንም ያካትታሉ።
  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን የአንድ ሰው ሀብት የሚለካው ባሉት የቤት እንስሳት መጠን ነበር።
  • የቤት እንስሳት እንደ ሥጋ፣ ሱፍ፣ ወተት፣ እርጎ፣ አይብና ልብስ የመሳሰሉ ነገሮችን ይሰጣሉ።

የተማሩ ሰዎች፣ ኮኮብ ቆጣሪዎች

ማቴዎስ በሚያቀርበው የክርስቶስ ልደት ታሪክ መሠረት እነዚህ፣ “የተማሩ” ወይም፣ “ያወቁ” ሰዎች ኢየሱስ በቤተ ልሔም በተወለደ ጊዜ እዚያ ድረስ ስጦታዎች ያመጡለት “ጠቢብባን ሰዎች” ነበር። ምናልባትም ከዋክብትን የሚያጠኑ ኮከብ ቆጣሪዎች ለሆኑ ይችላሉ።

  • እነዚህ ሰዎች ከእስራኤል በስተ ምሥራቅ በጣም ርቆ ካለ አገር ነበር የመጡት። ከየት እንደ መጡና እነርሱም እነማን እነደ ሆኑ በትክክል አይታወቅም። ይሁን እንጂ፣ ከዋክብትን ያጠኑ ምሁራን መሆናቸው ግልጽ ነው።
  • ምናልባትም ከዋክብትንና ማጥናትና ሕልምን መተርጎምን ጨምሮ ብዙ ሥልጠና የነበራቸው በዳንኤል ዘመን የባቢሎን ንጉሦችን ያገለግሉ የነበሩ ጠቢባን ዘሮች ሊሆኑ ይችላሉ።
  • ለኢየሱስ የመጡት ስጦታዎች ሦስት ከመሆናቸው የተነሣ እነዚያ ጠቢባን ሦስት ሰዎች እንደ ሆኑ ይታሰባል። ይሁን እንጂ፣ ከዚያ በላይ ሊሆኑ እንደሚችሉም በጣም ግልጽነው።

የተቀደሰ

“የተቀደሰ” የሚለው ቃል ቅዱስ የሆነና ለእግዚአብሔር ክብር የተለየ ነገርን ያመለክታል

  • መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ የተቀደሰ ነው
  • የእግዚአብሔር የዕረፍት ቀን ስለሆነ ሰንበት የተቀደሰ ነው
  • ለእግዚአብሔር አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውሉ በመሆኑ፣ “የተቀደሰ” ተብለው የሚታሰቡ ነገሮች ዋጋ አላቸው
  • ይህ ቃል ሐሰተኛ አመልክትን ለማምለክ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሃይማኖታዊ ነገሮችንም ሊያመለክት ይችላል

የተጠላ፣ መጥላት

“የተጠላ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የማይወደድና የተናቀ ነገር ነው። አንድን ነገር “መጥላት” ያንን ነገር አጥብቆ አለመውደድ ማለት ነው።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ክፉን ስለ መጥላት ደጋግሞ ይናገራል። ይህም ክፉን አለመውደድና ክፉን መጽሐፍ ማለት ነው።
  • ሐሰተኛ አማልክትን የሚያመልኩ ሰዎች የሚያደርጉትን ክፉ ሥራ አስመልክቶ ሲናገር እግዚአብሔር፣ “የተጠላ” በሚለው ቃል ተጠቅሟል።
  • ጎረቤቶቻቸው የነበሩ አገሮች ያደርጉ የነበረውን ኃጢአትና ርኵሰት እንዲጠሉ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አዝዞአል።
  • ቅጥ ያጣ የግብረ ሥጋ ግንኙነትን እግዚአብሔር፣ “የተጠላ” ብሎታል።
  • ጥንቆላ፣ መተትና ሕፃናትን መሥዋዕት ማድረግ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠሉ ናቸው።
  • “መጥላት” የሚለውን ቃል፣ “አለመውደድ” ወይም፣ “መጸየፍ” ወይም፣ “መናቅ” ብሎ መተርጎም ይቻላል።
  • እርሱ ራሱ፣ “ርኵስ” ያላቸውንና ለምግብነት መዋል እንደሌለባቸው የተናገረላቸው አንዳንድ እንስሳት፣ እንዲጠሉ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ተናግሮአል። ይህ፣ “በጣም መጸለይ” ወይም፣ “ማስወገድ” ወይም፣ “ተቀባይነት እንደሌለው ነገር መቁጠር” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

የተጻፈ

“እንደ ተጻፈ” ወይም፣ “የተጻፈው” የተሰኙት ቃሎች አዲስ ኪዳን ውስጥ ተደጋግመው ጥቅም ላይ ውለዋል፣ ብዙውን ጊዜ የሚያመለክቱት በዕብራውያን ቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፉ ትእዛዞች ወይም ትንቢቶች ነው።

  • አንዳንዴ፣ “እንደ ተጻፈ” የሚለው የሚያመለክተው በሙሴ ሕግ ውስጥ የተጻፉ ነገሮችን ነው።
  • ሌላ ጊዜ ደግሞ፣ ከብሉይ ኪዳን ነቢያት አንዱን ለመጥቀስ ነው።
  • ይህም፣ “በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈ” ወይም፣ “ከብዙ ዘመን በፊት ነቢያት እንደ ጻፉት” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
  • ሌላ ጊዜ ደግሞ፣ “እንደ ተጻፈ” የሚለውን መተርጎምና ያ ምን ማለት እንደ ሆነ በግርጌ ማስታወሻ ማመልከት ሌላው አማራጭ ሊሆን ይችላል።

የኅብረት መሥዋዕት

“የኅብረት መሥዋዕት” እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር እንዲያቀርቡ ከታዘዙት በርካታ የመሥዋዕት ስጦታዎች አንዱ ነበር። “የምስጋና መሥዋዕት” ወይም፣ “የሰላም መሥዋዕት” ተብሎም ይጠራል።

  • ይህ መሥዋዕት ምንም ጉድለት የሌለበት እንስሳ መሥዋዕት ማቅረብን፣ ደሙን መሠዊያው ላይ መርጨትንና በተለያየ ሁኔታ የተቀረውን የእንስሳውን አካልና ስቡን ማቃጠልንም ይጨምራል።
  • ከዚህ በተጨማሪ በሚቃጠለው መሥዋዕት ላይ የሚቃጠለውን እርሾ ያለበትና የሌለበት እንጀራም መሥዋዕት ይቀርባል።
  • ካህኑና መሥዋዕቱን የሚያቀርበው ሰው የቀረበውን መሥዋዕት እንዲበሉ ይፈቀድላቸዋል።

የኅብረት መሥዋዕት፣ የሰላም መሥዋዕት

የኅብረት መሥዋዕት ብሉይ ኪዳን ውስጥ የሰላም መሥዋዕት ተብሎ ይጠራል። ተባዕት ወይም እንስት እንስሳ መሥዋዕት የሚቀርብበት ነው።

  • ይህ መሥዋዕት ከሚቀርብበት ምክንያቶች ጥቂቶቹ፣ ስእለትን ለመፈጸም፣ ለእግዚአብሔር ምስጋናና ውዳሴ ለማቅረብ፤
  • የመሥዋዕቱ የተወሰነው ክፍል ለእግዚአብሔር ከቀረበ በኋላ የኅብረቱን መሥዋዕት ካህናቱ፣ መሥዋዕቱን ያመጣው ሰው እና ሌሎች እስራኤላውያን ይከፋፈሉታል።
  • ከዚህ መሥዋዕት ጋር ያልቦካ እንጀራንም የሚያካትት አብሮ መብላትም ይኖራል።

የኅጢአት መሥዋዕት

የኅጢአት መሥዋዕት ለተፈጸመው ኅጢአት ይቅርታ ለማግኘት ይቀርብ የነበረ መሥዋዕት ነበር

  • ዕብራውያን 9፥22 ኅጢአት እንዲነጻ ከተፈለገ ለተፈጸመው ኅጢአት ዋጋ የሚሆን ደም መፍሰስ እንዳለበት ይናገራል
  • በብሉይ ኪዳን ዘመን የኅጢአት መሥዋዕት የሚሆኑ እንስሳት ይቀርቡ ነበር፤ ይሁን እንጂ፣ እነዚህ መሥዋዕቶች ለዘለቄታው የኅጢአት ይቅርታን ማስገኘት ስለማይችሉ በየጊዜው መቅረብ ነበረባቸው
  • አዲስ ኪዳን እንደሚያስታውቀው ኢየሱስ የኅጢአት ፍጹም መሥዋዕት ሆነ። የእርሱ መስቀል ላይ ሞት ለአንዴና ለሁልጊዜ የኅጢአት ዋጋ ከፈለ።

የአይሁድ መሪዎች፤ የአይሁድ ባለ ሥልጣኖች፣ የሃይማኖት መሪዎች

የአይሁድ መሪዎች ካህናትንና የሕግ ምሑራንን የመሳሰሉ የሃይማኖት መሪዎች ነበሩ።

  • ብዙዎቹ የሃይማኖት መሪዎች ኢየሱስ መሲሕ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አላመኑበትም። በኢየሱስ ላይ ቅናት ስላደረባቸው ሌሎችም ቢሆኑ በእርሱ እንዲያምኑ አልፈለጉም።
  • አንዳንድ የሃይማኖት መሪዎች መሞት ከተነሣ በኋላ እንኳ በኢየሱስ አላመኑም።
  • ብዙዎቹ የሃይማኖት መሪዎች ከሌሎች ይልቅ እነርሱ ጻድቃን እንደሆኑ ያስቡ ነበር፤ ኀጢአተኛ መሆናቸውን እንዳይቀበሉም ትዕቢት ነበራቸው። ኢየሱስን አስመልክቶ ለሮማውያን ሐሰት ተናግረው እርሱ እንዲገደል ጠየቁ።
  • ኢየሱስ የአይሁድ መሪዎችን ግብዝነት አወገዘ። እግዚአብሔርን እንደሚያውቁ ይናገራሉ፤ ግን ለእርሱ አይታዘዙም።

የእህል ቍርባን

የእህል ቍርባን የሚባለው ብዙውን ጊዜ ከሚቃጠል መሥዋዕት በኋላ ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን የስንዴ ወይም የገብስ ዱቄት ነው።

  • ለእህል መሥዋዕት የሚቀርበው እህል ድቅቅ ተደርጎ የተፈጨ እህል ሲሆን አንዳንዴ መሥዋዕት ከመሆኑ በፊት ለበሰለ ወይም ላይበስል ይችላል።
  • የእህሉ ዱቄት ውስጥ ዘይትና ጨው ቢገባም፣ እርሾና ማር ግን እንዲገቡበት አይፈለግም።

የእውነት ቃል

“የእውነት ቃል” የእግዚአብሔር ቃል ወይም ትምህርት ሌላ መጠሪያ ነው።

  • የእግዚአብሔር የእውነት ቃል እግዚአብሔር ስለ ራሱ፣ ስለ ፍጥረትና በኢየርሱ በኩል ስላለው የማዳን ዕቅድ ለሰዎች ያስተማረውን ማንኛውንም ነገር ይጨምራል።
  • ይህ ቃል እግዚአብሔር የነገረን እውነት፣ የታመነና እውን መሆኑን አጽንዖት ይሰጣል።

የእግር መረገጫ

“የእግር መረገጫ” አንድ ሰው እግሮቹን በተለይም በሚቀመጥ ጊዜ እግሮቹን የሚያሳርፍበት ነገር ነው። መገዛትንና ዝቅ ያለ ማንነትን የሚያመለክት ትርጕም ያለው ምሳሌያው ቃልም ነው።

  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ሰዎች እግሮች ዝቅ ያለ ክብር ያላቸው የሰውነት ክፍሎች እንድ አሆልኑ ያስቡ ነበር። ስለሆነም፣ “የእግር መረገጫ” እግር የሚያርፍበት ከመሆኑ የተነሣ፣ “የእግር መረገጫ” ከዚያ የባሰ ዝቅ ያለ ነገር ተደርጎ ነበር የሚቆጠረው።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር፣ “ጠላቶቼን የእግሮቼ መረገጫ አደርጋለሁ” ሲል በእርሱ በሚያምፁ ሰዎች ላይ ሥልታን እንዳለው፣ እንደሚቆጣጠራቸውና ጨርሶ እንደሚያሸንፋቸው ማመልከቱ ነው። ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ፈቃድ እስኪገዙ ድረስ በጣም ዝቅ ይላሉ ይዋረዳሉ።
  • “በእግዚአብሔር እርግ መረገጫ መስገድ” እርሱ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ እያለ ለእርሱ ለመስገድ ዝቅ ማለት ወይም መንበርከክ ማለት ነው። ይህም በድጋሚ በእግዚአብሔር ፊት ዝቅ ማለትንና ለእርሱ መገዛትን ነው የሚያመለክተው።
  • የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ዳዊት፣ “የእግሩ መረገጫ” ይለዋል። ይህም እርሱ በሕዝቡ ላይ ያለውን ፍጡም ሥልጣንና የበላይነት ያመለክታል። ይህ እግዚአብሔር ዙፋኑ ላይ ያለ፣ እግሮቹን መረገጫ ላይ ያደረገንጉሥ ሥዕል የሚያመልክት ሲሆን ማንኛውም ነገር ለእርሱ መገዛቱን ነው የሚያሳየው።

የካህናት አለቆች

ኢየሱስ በዚህ ምድር በነበረ ጊዜ የካህናት አለቆች ከፍ ያለ ሥልጣን የነበራቸው የአይሁድ ሃይማኖት መሪዎች ነበሩ።

  • የካህናት አለቆች ቤተ መቅደስ ውስጥ በሚደረገው የአምልኮ አገልግሎት ማንኛውም ነገር ላይ ኃላፊነት ነበራቸው፤ ለቤተ መቅደስ የሚሰጠውን ገንዘብ የሚቆጣጠሩትም እነርሱ ነበሩ።
  • ከተራዎቹ ካህናት የበለጠ ደረጃና ሥልጣን ነበራቸው። ከእነርሱ የሚበልጥ ሥልጣን የነበረው ሊቀ ካህኑ ብቻ ነበር።
  • የካህናት አለቆች ከኢየሱስ ዋነኛ ጠላቶች ጥቂቶቹ ሲሆኑ፣ እርሱን እንዲይዙና እንዲገድሉት ሮማውያን መሪዎች ላይ ከባድ ተጽዕኖ ያደረጉ እነርሱ ነበሩ።

የወይራ ፍሬ

የወይራ ፍሬ ከወይራ ዛፍ የሚገኝ ትንሽ ሾጣጣ ቅርጽ ያለው ፍሬ ሲሆን፣ አብዛኛውን ጊዜ የሚገኘው በሜድትራኒያን ባሕር አካባቢዎች ነው።

  • የወይራ ዛፍ ሁልጊዜ ለምልሞ የሚታይና ነጫጭ አበቦች ያሉት ቁጥቋጦ ነው። ጥሩ ሆኖ የሚያድገው ሞቃት የአየር ጸባይ ባለበት ቦታ ሲሆን፣ ጥቂት ውሃ ካገኘ እንደለመለመ የመዝለቅ ባሕርይ አለው።
  • የወይራ ፍሬ መልኩ አረንጓዴ ቢሆንም፣ እየበሰለ ሲሄድ ይጠቁራል። የወይራ ፍሬ ለመብል ይሆናል፤ ዘይትም ይወጣዋል።
  • የወይራ ዘይት ለምግብ ብቻ ሳይሆን፣ በሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት መብራት በመሆንም ያገለግላል።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የወይራ ዛፍ ምሳሌያዊ በሆነ አነጋገር ሰዎችንም ያመለክታል።

የወይን እርሻ

የወይን እርሻ ወይም ልማት ወይን የሚበቅልበት ወይን፣ በእንክብካቤ የሚያድግበት ቦታ ነው።

  • ወይን መትከልና ማልማት በጣም አድካሚ ሥራ ነው።
  • ፍሬዎቹን ከሌቦችና ከእንስሳት ለመጠበቅ ሲባል የወይን እርሻ ዙሪያ ግንብ ይሠራል።
  • እግዚአብሔር እስራኤልን እንክብካቤ ቢደረግለትም መልካም ፍሬ ማፍራት ካልቻለ ወይን እርሻ ጋር አመሳስሏቸዋል።

የወይን ዛፍ

“የወይን ዛፍ” ወይን የሚያፈራ የዛፍ ዓይነት ነው።

  • ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንመለከተው ፍሬ ለማግኘት ሰዎች ወይን ይተክሉ ነበር።
  • ወይኑ ግንድ ላይ ቅርንጫፎች ያድጋሉ፤ ብርታትንም ሆነ የሚያስፈልጓቸውን ምግብ የሚያገኙት ከግንዱ ነው።
  • ኢየሱስ ራሱን የወይን ግንድ፣ ሰዎችንም ቅርንጫፎች በማለት ጠርቷል።

የወይን ፍሬ

ወይን ፍሬ የወይን ሐረጉ እዚህና እዚያ ተበታትነው የሚያድጉ ትናንሽ ክብ ፍሬዎች ናቸው። ወይን ጠጅ የሚሆነው እነዚህ ፍሬዎች ተጨምቀው ነው።

  • ሰዎች የወይን እርሻቸው ውስጥ ወይን ይተክላሉ። ብዙውን ጊዜ ይህ የሚሆነው የወይን ግንዶችን መደዳውን በመትከል ነው።
  • የወይን ፍሬዎች ብዙ ጊዜ ስለማይቆዩ ከበሰሉ በኋላ ለመብላት ሰዎች ያደርቋቸዋል። እነዚህ የደረቁት ወይኖች ዘቢብ ይባላሉ። ብሉይ ኪዳን ስለ ዘቢብ ጥፍጥፍ የሚለው አለው።

የዋህ፣ የዋህነት

“የዋህ” የሚለው ቃል ጨዋ፣ እሺ ባይና መከራን በትዕግሥት የሚቀበልን ሰው ያመለክታል። መናደድ ኀይል መጠቀም ተገቢ መስሎ ቢታይ እንኳ ጨዋ ሆኖ ለመገኘት የዋህነት ታላቅ ችሎታ ነው።

  • ብዙ ጊዜ የዋህነት ከትሕትና ጋር ይያያዛል።
  • እርሱ የዋህና በልቡም ትሑት እንደ ሆነ ኢየሱስ ተናግሮአል።
  • ይህ ቃል፣ “ጨዋ” ወይም፣ “ረጋ ያለ” ወይም፣ “ገር” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
  • “የዋህነት” የሚለውም ቃል፣ “ጨዋነት” ወይም፣ “ትሕትና” ተብሎ መተርጎም ይችላል።

የዕጣን መሠዊያ

  • የዕጣን መሠዊያ ከእንጨት ይሠራና ላዩና ጎኖቹ በወርቅ ይለበጣል። ግማሽ ሜትር ርዝመት ግማሽ ሜትር ስፋትና አንድ ሜትር ያህል ቁመት ነበረው።
  • መጀመሪያ ላይ መገናኛው ድንኳን ውስጥ ነበር የሚቀመጠው በኋላም ቤተ መቅደሱን ውስጥ ይቀመጥ ነበር።
  • በየጠዋቱና በየምሽቱ ካህን ላዩ ላይ ዕጣን ያቃጥላል።
  • “ዕጣን ማቃጠያ መሠዊያ” ወይም “የወርቅ መሠዊያ” ወይም፣ “ዕጣን ማቃጠያ” ወይም “የዕጣን ገበታ”ተብሎ መርጎምም ይቻላል።

የደም መፍሰስ

“የደም መፍሰስ” በግድያ፣ በጦርነት ወይም በሌላ አደጋ የሰዎችን ሞት ያመለክታል።

  • ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “ደም መፍሰስ” ሰውየው አካል ላይ ካለ ቁስል ደም መውጣቱን ነው የሚያመለክተው።
  • “ደም መፍሰስ” ብዙውን ጊዜ ሰዎች በብዛት መገደላቸውን ለማሳየት ጥቅም ላይ ይውላል።
  • አጠቃላይ በሆነ መልኩ የግድያ ኃጢአት መፈጸምን ያሳያል።

የገሊላ ባሕር

የገሊላ ባሕር ምሥራቃዊ እስራኤል ያለ ሐይቅ ነው። የገሊላ ባሕር በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ ወደ ደቡብ ከዚያም ወደ ሙት ባሕር ይፈስሳል።

  • የቅፍርናሆምና የቤተሳይዳ ከተሞች ገሊላ ባሕር አጠገብ ነበሩ
  • የገሊላ ባሕር ሌሎች ስሞች፣ የጥብርያዶስ ባሕር፣ ጌንሳሬጥ ባሕርና የጌንሳሬጥ ሐይቅ የተሰኙ ናቸው

የግብረ ሥጋ ኅጢአት

“የግብረ ሥጋ ኅጢአት” የሚባለው በወንድና በሴት መካከል ካለው ጋብቻ ውጪ የሚደረግ ማንኛውም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ነው። እንዲህ ያለው ከእግዚአብሔር ዕቅድ ውጪ ነው።

  • ይህ ቃል ግብረ ሰዶማዊነትንና ወሲብ ነክ ስዕሎችን ጨምሮ ከእግዚአብሔር ፈቃድ የሚጋጭ ማንኛውንም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ያመለክታል። አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች፣ “ሴሰኝነት” ይሉታል
  • አንዱ የግብረ ሥጋ ኅጢአት ዝሙት ሲሆን፣ ይህ የሚያመለክተው ከባልና ከሚስት ግንኙነትና የትዳር ጓደኛ ውጪ የሚደረግ ማንኛውም የግብረ ሥጋ ግንኙነትን ነው
  • ሌላው የግብረ ሥጋ ኅጢአት፣ “ዝሙት አዳሪነት” ሲሆ፣ አስከፍለው የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚያደርግ ሰውን ይመለከታል
  • ይህ ቃል ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ሐሰተኛ አማልክትን በማምለክ እስራኤል ለእግዚአብሔር ታማኝ እንዳልነበሩ ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል

ያልተገረዘ፣ አለመገረዝ

“ያልተገረዘ” እና “አለመገረዝ” አካላዊ ግርዘት ያላደረገ ወንድን ያመለክታል። ይህ ቃል በምሳሌያዊ አንጋገርም ጥቅም ላይ ይውላል።

  • ግብፅም ግርዘት እንድትረጽም የተነገራት ሕዝብ ናት። ስለዚህ ግብፅ “ባልተገረዙ” ወገኖች እንደ ተሸነፈች እግዚአብሔር ሲናገር ግብፃውያን ያልተገረዙ በማለት የናቋቸው ወገኖችን ማመልከቱ ነው።
  • መጽሐፍ ቅዱስ፣ “ያልተገረዘ ልብ” ስላላቸው ወይም፣ “የልብ ግርዛት” ስላላደረጉ ሕዝብ ይናገራል። ይህ ምሳሌያዊ አነጋገር የእግዚአብሔር ሕዝብ እንዳይደሉና ግትር ሆነው በእርሱ ላይ እያመጹ መሆናቸውን ያመለክታል።

ያልተፈቀደ

“ያልተፈቀደ” ነገር የሚያደርግ ሰው ሕግ ያፈርሳል።

  • አዲስ ኪዳን ውስጥ፣ “ያልተፈቀደ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው፣ የእግዚአብሔርን ሕግ ማፍረስን ብቻ ሳይሆን ሰው ሠራሽ የአይሁድ ሕግንም ለማፍረስ ጭምር ነው።
  • በጊዜ ውስጥ አይሁድ እግዚአብሔር በሰጣቸው ሕግ ላይ የራሳቸውንም ጨምረዋል። ከእነርሱ ሰው ሠራሽ ሕግ ጋር የማይስማማውን አይሁድ፣ “ያልተፈቀደ” ይሉታል።
  • ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ በሰንበት ቀን እሸት ቀጥፈው በመብላታቸው፣ በዚያ ቀን ምንም ነገር እንዳይደረግ የደነገገውን የአይሁድ ሕግ ማፍረስ በመሆኑ፣ “ያልተፈቀደ” ብለውታል።
  • ንጹሕ ያልሆነ ምግብ መብላት ለእርሱ፣ “ያልተፈቀደ” እንደ ነበር ጴጥሮስ ሲናገር ይህን ምግብ ከበላ አንዳንድ ምግቦችን እንዳይበሉ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን የሰጠውን ሕግ ማፍረስ መሆኑን ማመልከቱ ነበር።

ያልታመነ፣ አለመታመን

“ያልታመነ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው እንዲያደርግ እግዚአብሔር ያዘዘውን ነገር የማያደርገውን ሰው ነው። እንዲህ ማድረግ አለመታመን ነው።

  • ጣዖትን በማምለካቸውና በሌሎች መንገዶችም ለእግዚአብሔር ባልታዘዙ ጊዜ እስራኤላውያን፣ “ያልታመኑ” ተብለዋል።
  • ከትዳር ጓደኛው ውጪ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚያደርግ ሰው፣ “ያልታመነ” ይባላል።
  • “ያልታመነ” በሚለው ቃል እግዚአብሔር የተጠቀመው የእስራኤልን ዐመፀኝነት ለማመልከት ነበር። ለእርሱ እየታዘዙ ወይም እርሱን እያከበሩ አልነበረም።
  • መንፈሳዊ ያልሆነ፣ እግዚአብሔርን የማይፈራ፣ እግዚአብሔርን አለመፍራት፣ መንፈሳዊ አለመሆን “መንፈሳዊ ያልሆነ” እና፣ “እግዚአብሔርን የማይፈራ” የተሰኙት ቃሎች እግዚአብሔር ላይ እያመፁ ያለ ሰውን ያመለክታሉ። እግዚአብሔርን ባለማሰብ በክፉ መንገድ መኖር ወይም “እግዚአብሔርን አለመፍራት” መንፈሳዊ አለምሆን ማለት ነው።
  • የእነዚህ ሁሉ ቃሎች ትርጕም በጣም ተመሳሳይ ነው። ይሁን እንጂ፣ “እግዚአብሔርን አለመፍራት” እና፣ “እግዚአብሔርን የማይፈራ” የተባሉት ቃሎች በጣም በባሰበት ሁኔታ እግዚአብሔርን ወይም በእነርሱ ላይ ያለውን ሥልጣን የማይቀበሉ ሰዎችን ያመለክታል።
  • እግዚአብሔርን በማይፈሩ፣ እርሱንና የእርሱን መንገድ ችላ በሚሉት ላይ እግዚአብሔር ይፈርዳል።

ይሁዳ፣ የይሁዳ ሃይማኖት

የአይሁድ ሕዝብ የሚለማመደውን ሃይማኖት ማለትም የአይሁድ ሃይማኖትን ለማመልከት አዲስ ኪዳን ከተጻፈበት ዘመን አንስቶ እስከዚህ ዘመን ድረስ፣ “ይሁዲ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ውሏል።

  • በብሉይ ኪዳን ዘመን፣ “ይሁዲ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ አልዋለም ነበር። በዚያ ዘመን የእስራኤል ሃይማኖቶች፣ “ የአይሁድ ሃይማኖት” ነበር የሚባለው።
  • የአይሁድ ሃይማኖት(ይሁዲ) እንዲታዘዙት እግዚአብሔር ለእስራኤል የሰጠውን የብሉይ ኪዳን ሕጎችንና መመሪያዎች ሁሉ ያጠቃልላል። በዘመናት ውስጥ የአይሁድ ሃይማኖት ውስጥ የተጨመሩ ባህሎችና ወጎችንም ሁሉ ያካትታል። ከዚያ በፊት ቃሉ ጨርሶ ስላለነበር፣ “ይሁዲ” የሚለውን ቃል ጥቅም ላይ መዋል ያለበት አዲስ ኪዳን ውስጥ ብቻ ነው።

ደስታ፣ ደስተኛ

ደስታ የደስታ ስሜት ወይም ከእግዚአብሔር የሚመጣ ጥልቅ ርካታ ነው። ከዚሁ ጋር ታያያዥ የሆነው፣ “ደስተኛ” የሚለው ቃል በጣም ደስ የተሰኘ ሰውን ያመለክታል።

  • እያለፈበት ያለው መልካም መሆኑን በተመለከተ ጥልቅ ግንዛቤ ሲኖረው አንድ ሰው ደስታ ይሰማዋል።
  • ለሰዎች እውነተኛ ደስታ የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው።
  • ደስ ለመሰኘት የግድ ደስ የሚል አካባቢ ወይም ሁኔታ ውስጥ መሆን የለብንም በሕይወታቸው በጣም አስቸጋሪ ነገሮች እየተፈፀሙ እንኳ እግዚአብሔር ለሰዎች ደስታ መስጠት ይችላል።
  • አንዳንዴ ቤቶችን ወይም ከተሞችን የመሳሰሉ ነገሮች ደስ የሚያሰኙ ተብለዋል። እንዲህም ማለት እዚያ የሚኖሩ ሰዎች ደስተኞች ናቸው ማለት ነው።

ደብዳቤ፣ መልእክት

ደብዳቤ ብዙ ጊዜ ከጸሐፊው ርቀው ላሉ ወገኖች ወይም ሰዎች የሚላክ መልእክት ነው። መልእክት የተለየ ዐይነት ደብዳቤ ሲሆን፣ ብዙውን ጊዜ የሚጻፈው ማስተማርን ለመሰሉ የተለዩ ዓላማ ነው።

  • አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን መልእክቶችና ሌሎች ደብዳቤዎች ይጻፉ የነበረው ከእንስሳት ቆዳ ከሚሠራ ብራና ወይም ፓፒረስ በሚባል ተክል ልጥ ላይ ነበር።
  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ጳውሎስ፣ ዮሐንስ፣ ያዕቆብ፣ ይሁዳና ጴጥሮስ በመላው የሮም መንግሥት የተለያዩ ከተሞች ውስጥ የነበሩ የጥንት ክርስቲያኖችን ለማበረታታትና ለማጽናናት መልእክቶች ጽፈው ነበር።

ደጃፍ

“ደጃፍ” የሚባለው የበር ታችኛው ክፍል ነው። ወደ አንድ ቤት ሲገባ ደጃፉን መርገጥ ይገባል።

  • አንዳንዴ ደጃፍ ከበሩ ውስጥ ያለውን የቤቱን ክፍል ይጨምራል።
  • መግቢያም ደጃፍ ይባላል።

ደጋንና ቀስት

ይህ ከደጋን ገመድ ቀስትን ማስፈንጠርን የሚያካትት መሣሪያ ዐይነት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ጠላትን ለማጥቃት ወይም ለምግብ የሚሆን እንስሳን ለመግደል ያገለግል ነበር።

  • ደጋን ከእንጨት፣ ክአጥንት፣ ከብረት፣ ወይም የሚዳቋ ቀንድን ከመሳሰሉ ሌሎች ጠንካራ ነገሮች ይሠራል። የጎበጠ ቅርጽ አለው፤ በሲባጎ፣ በገመድ ወይም በጅማት በጥብቅ ይወጠራል።
  • ቀስት ጫፉ ላይ ሹል የሆነ ስለታም ዘንግ መሳይ ነገር ነው። በጥንት ዘመን እንጨትን፣ አጥንትን፣ ድንጋይን ወይም ብረትን ከመሳሰሉ የተለያዩ ነገሮች ቀስት ይሠራ ነበር።
  • አዳኞችና ጦረኞች ሁሉ በደጋንና በቀስት ይጠቀሙ ነበር።
  • “ቀስት” የተሰኘው ቃል አንዳንድ የጠላትን ጥቃት ወይም መለኮታዊ ፍርድን ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምሳሌያዊ በሆነ አነጋገር ጥቅም ላይ ይውል ነበር።

ደፋር፣ በድፍረት፣ ድፍረት

እነዚህ ቃሎች አስቸጋሪና አደገኛ ቢሆን እንኳ እውነትን ለመናገርና ትክክለኛውን ለማድረግ ደፋርና ጎበዝ መሆንን ነው የሚያመለክቱት።

  • ደፋር ሰው ለተበደሉ መከራከርን ጨምሮ መልካምና ትክክል የሆነ ነገርን ለመናገር አይፈራም። ይህ፣ “ጎበዝ” ወይም “ፍርሃት የለሽ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
  • ከአዲስ ኪዳን እንደምንመለክተው ለታሰሩ ወይም ሊገደሉ እንደሚችሉ ቢያውቁ እንኳ ደቀ መዛሙርት በአደባባይ ስለ ኢየሱስ፣ “በድፍረት” እውነቱን መናገራቸውን እንደ ቀጠለ እንመለከታለን። ይህ፣ “በልበ ሙሉነት” ወይም፣ “በጽናት” ወይም፣ “ያለ አንዳች ፍርሃት” ተብሎ መተርጎም ይችላል።
  • እነዚህን የጥንት ደቀ መዛሙርት የክርስቶስን መስቀል ላይ ሞት ቤዛነት የምሥራች “በድፍረት” ከመናገራቸው የተነሣ በእስራኤልና በአጎራባች አገሮች በመጨረሻም ወደ ተቀረው ዓለም ሁሉ ወንጌል ተስፋፋ። “ድፍረት” የሚለው ቃል፣ “የማያወላውል ጽናት” ተብሎ መተርጎም ይችላል።

ዳኛ፣ ፈራጅ

አስተዳደራዊ፣ ሕጋዊ ወይም መንፈሳዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ትክክልና ስሕተት የሆኑ ነገሮችን የሚወስን ሰው ዳኛ ወይም ፈራጅ ይባላል።

  • ትክክል ወይም ስሕተት የሆኑ ነገሮችን በተመለከተ ፍጹም ዳኛ ወይ ፈራጅ እርሱ በመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙውን ጊዜ ዳኛ የሚባለው እግዚአብሔር ነው።
  • የእስራኤል ሕዝብ ወደ ተስፋው ምድር ከገቡ በኋላና በንጉሦች ከመተዳደራቸው በፊት በችግር ጊዜ የሚመሯቸው ዳኞች እግዚአብሔር ሾሞላቸው ነበር። ብዙ ጊዜ እነዚህ ዳኞች ከጠላቶቻቸው አድነዋቸዋል።

ድምፅ

አንድ ሰው ሲናገር ድምፅ ይጠቀማል፤ ስለዚህም ብዙ ጊዜ “ድምፅ” ንግግርን ወይም ሐሳብ ማስተላለፍን ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላል።

  • ምንም እንኳ እርሱ የሰው ዓይነት ድምፅ ባይኖረውም፣ እግዚአብሔር በድምፅ መጠቀሙ ተነግሯል።
  • ድምፅ ሰውን በመወከልም ጥቅም ላይ ውሏል፤ ለምሳሌ፣ “የጌታን መንገድ አዘጋጁ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ድምፅ” እንደሚለው ይህንንም፣ “አንድ ሰው ምድረ በዳ ውስጥ ሲጮኽ ተሰማ” በማለት መተርጎም ይቻላል።
  • አንዳንዴ መናገር የማይችሉ ነገሮችን አስመልክቶም “ድምፅ” ጥቅም ላይ የዋለበት ሁኔታ አለ፤ ለምሳሌ እግዚአብሔር የሠራቸው አስደናቂ ፍጥረታት እርሱ ምን ያህል ታላቅ መሆኑን፣ “ድምፅ” አውጥተው እንደሚናገሩ ዳዊት አመልክቷል። ይህም፣ “የፍጥረታቱ ውበት የእግዚአብሔርን ታላቅነት ያሳያል” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

ድብ

ድብ ጥቁር ቡናማ ጠጉርና ጠንካራ ጥርሶችና ጥፍሮች ያሉት ባለአራት እግር ግዙፍ እንስሳ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ድብ በእስራኤል በብዛት ይገኝ ነበር

  • እነዚህ አራዊት የሚገኙት ጫካዎች ውስጥና ተራራማ አካባቢዎች ነበር፤ ዓሶችን፥ ጥቃቅን ነፍሳትንና ተክሎችን ይመገባሉ
  • በብሉይ ኪዳን ድብ የብርታትና ጥንካሬ ምሳሌ ተደርጎ ይቀርባል
  • በጎች ይጠብቅ በነበረ ጊዜ እረኛው ዳዊት ከድብ ጋር ታግሎ አሸንፎ ነበር
  • ሁለት ድቦች ከጫካ መጥተው ኤልሳዕ ላይ ያላገጡ በርካታ ልጆችን ገደሉ

ድነት

“ድነት” የሚለው ቃል ከክፉና ከአደጋ መዳንና ማምለጥን ያመለክታል

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ድነት” አብዛኛውን ጊዜ ኅጢአታቸውን በመናዘዝ፣ በኢየሱስ ለማያምኑ ሰዎች እግዚአብሔር የሚሰጠውን መንፈሳዊና ዘላለማዊ መዳን የመለክታል
  • መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከጠላቶቻቸው እንደሚያድናቸው ወይም እንደሚታደጋቸው ይናገራል

ድንኳን

ድንኳን ተንቀሳቃሽ መጠለያ ሲሆን፣ የሚሠራው ምሰሶዎች ላይ በማንጠልጠሉና ከእንርሱ ጋር በተያያዙ ጠንካራ ጨርቅ ነበር።

  • ድንኳኖች የብዙ ሰዎች መኖሪያ ነበር። ለምሳሌ አብርሃምና ቤተ ሰቡ ለዓመታት ትልቅ ድንኳን ውስጥ ኖረው ነበር።
  • እስራኤል በሲና ምድረ በዳ በነበሩ ጊዜ የሚኖሩት ድንኳኖች ውስጥ ነበር።
  • መገናኛው ድንኳን በጣም ትልቅ ድንኳን ሲሆን ከጨርቅ የተሠሩ በጣም ትልልቅ መጋረጃዎች እንደ ድንኳን ያገለግሉ ነበር።
  • ወንጌልን ለማዳረስ ከአንዱ ከተማ ወደ ሌላው በሚጓጓዝበት ጊዜ ራሱን የሚረዳበት ገንዘብ ለማግኘት ሐዋርያው ጳውሎስ ድንኳን ይሰፋ ነበር።
  • አንዳንዴ በአጠቃላይ ሰዎች የሚኖሩበትን ለማመልከት፣

ድንጋይ

ይህ ቃል የሚያመለክተው ከሰማይ የሚወርድ ጠጣር ነገርን ነው።

  • ጢስ ወይም ጠጠር መልክ ከሰማይ የሚወርድ ድንጋይ “የበረዶ ድንጋይ” ይባላል። እነዚህ የበረዶ ድንጋዮች ብዙውን ጊዜ ትንንሾች ቢሆኑም (ጥቂት ሳንቲ ሜትር ስፋት ያላቸው) እስከ 20 ሳንቲ ሜትር ስፋት ያላቸውና ከአንድ ኪሎ በላይ የሚመዝኑ ትልልቅ የበረዶ ድንጋዮችም አሉ።
  • አዲስ ኪዳን ውስጥ የምናገኘው የዮሐንስ ራእይ ሰዎች ላይ ስለሚወርድ ፍርድ ይናገራል፤ ይህ ፍርድ 50 ኪሎ ግራም የሚመዝን የበረዶ ድንጋይንም ይጨምራል።

ድንግል

ድንግል የግብረ ሥጋ ግንኙነት ያላደረገች ሴት ናት።

  • ነቢዩ ኢሳይያስ መሲሕ ከድንግል እንደሚወለድ ተናግሯል።
  • ማርያም ኢየሱስን የፀነሰችው ድንግል እያለች ነበር፤ ኢየሱስ የሥጋ አባት የለውም።

ድኝ

“ደኝ” ቢጫ መልክ ያለው ንጥረ ነገር ሲሆን፣ እሳትን በማቀጣጠልም ይረዳል

  • ድኝ የበሰበሰ እንቁላል የመሰለ ኅይለኛ ሽታ አለው
  • በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ድኝ ያለበት እሳት እግዚአብሔርን በማይፈሩ ዐመፀኞች ላይ የሚወርደውን የእርሱን ፍርድ ያመለክታል
  • እግዚአብሔር በክፉዎቹ ከተሞች ሰዶምና ገሞራ ላይ እሳትና ድኝ አወረደ

ድፍረት፣ ደፋር

“ድፍረት” አስቸጋሪ፣ አስፈሪ ወይም አደገኛ ነገሮችን በጉብዝና መጋፈጥ ወይም አንድ ነገር ማድረግ ማለት ነው።

  • “ደፋር” ፍርሃት ወይም ተስፋ መቁረት ሊያሳድርበት በሚችል ሁኔታ ውስጥ እንኳ ቢሆን በጉብዝና የሚንቀሳቀስ ሰው ያመለክታል።
  • አንድ ሰው ደፋርነቱን የሚያሳየው ስሜታዊና አካላዊ ሕመምን በጽናትና በትዕግሥት መቋቋም ሲችል ነው።
  • “አይዞህ” የተሰኘው የተለመደ ቃል፣ “ጎበዝ ሁን” ወይም፣ “አትፍራ” ወይም፣ “ነገሮችን እንደሚለወጡ እርግጠኛ ሁን” ማለት ነው።
  • ኢያሱ ወደ አደገኛው የከነዓን ምድር ለመሄድ በተዘጋጀ ጊዜ ሙሴ፣ “አይዞህ” በማለት አበረታታው።
  • “ደፋር” – “ልበ ሙሉ” ወይም፣ “ፍርሃት የለሽ” ወይም፣ “ጀግና” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
  • እንደ ዐውዱ ሁኔታ፣ “አይዞህ” የሚለው፣ “ልብህ ይበርታ” ወይም፣ “ተረጋጋ” ወይም፣ “አትናወጥ” ተብሎ መተርጎም ይችላል።
  • “በድፍረት መናገር” – “ያለ ፍርሃት መናገር” ወይም “በልበ ሙሉነት መናገር” ወይም “በእርግጠኝነት መናገር” ማለት ነው።

ገለባ

ደረቅ የእህል ዘር መከላከያ ሽፋን ነው። ገለባ ለምግብነት አይጠቅምም፤ ስለዚህም ከእህሉ እንዲለያይ ይደረግና በኋላ ይጣላል።

  • ብዙውን ጊዜ ገለባው ከእህሉ የሚለየው እህሉን ወደ አየር በመበተን ነበር፤ ነፋስ ገለባውን ይወስደዋል፣ እህሉ ግን መሬት ላይ ይወድቃል። ይህ ሂደት “ማበራየት” ይባላል።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይህ ቃል ክፉ ሰዎችንና ጥቅም የሌለው ነገርን ለማመልከት በምሳሌያዊ አነጋገር ጥቅም ላይ ይውላል።

ገብስ

“ገብስ” እንጀራ ወይም ዳቦ ለማዘጋጀት የሚጠቅም የእህል አይነት ነው

  • ገብስ ረዘም ያል አገዳ ያለው ተክል ሲሆን፥ ዘሮቹ ወይም እህሉ የሚያድገው ጫፍ ያለው ራሱ ላይ ነው።
  • ገብስ ሞቃት የአየር ፀባይ ባለው አካባቢ ጥሩ ሆኖ ያድጋል፤ ስለዚህም በፀደይ ወይም በጋ ወሮች የታጨዳል
  • ገብስ ሲወቃ ለምግብ የሚውለው ዘር ጥቅም ከሌለው ገለባ ይለያል
  • የገብስ እህል ፍሬው ዱቄት እንዲሆን ይፈጫል፤ ከዚያም በውሃ ወይም በዘይት ይለወስና እንጀራ ወይም ዳቦ ይዘጋጃል
  • ገብስ በማይታወቅበት አካባቢ፥ “ገብስ የሚባል እህል” ወይም፥ “ የገብስ እህል” ብሎ መተርጎም ይቻላል

ገዢ፣ መግዛት

ገዢ፣ አገርን፣ አካባቢን ወይም ክልልን የሚገዛ ሰው ነው። “መግዛት” ሰዎችን ወይም ነገሮችን መምራት ወይም ማስተዳደር ማለት ነው።

  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ገዢ በንጉሥ ወይም በንጉሠ ነገሥት ነበር የሚሾሙት።
  • ገዦች ከንጉሥ ወይም ከንጉሠ ነገሥት ሥልጣን ሥር ነበሩ።

ገዢ፣ ገዦች፣ ግዛት

ገዢ እንደ አገር መሪ፣ መንግሥት ወይም ሃይማኖታዊ ድርጅት ላይ ሥልጣን ያለውን ሰው የሚያመለክት አጠቃላይ ቃል ነው

  • በብሉይ ኪዳን ዘመን አብዛኛውን ጊዜ “ገዢ” የሚባለው ንጉሥ ነበር፤ “እስራኤልን ገዛ” እንደሚባለው
  • እግዚአብሔር ሌሎች ገዦችን ሁሉ የሚገዛ የሁሉም የበላይ ገዢ ነው
  • አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን የምኩራብ መሪ፣ “ገዢ” ይባል ነበር
  • አገር አስተዳዳሪም፣ “ገዢ” ይባላል
  • እንደ ዐውዱ ሁኔታ፣ “ገዢ” “መሪ” ወይም፣ “ሥልጣን ያለው ሰው” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል

ጉቦ፣ መማለጃ

“ጉቦ” ወይም መማለጃ፣ ትክክል ወይም ተገቢ ያልሆነ ነገር እንዲያደርግ እዚያ ሰው ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ገንዘብን የመሰለ አንዳች ዋጋ ያለው ነገር መስጠት ማለት ነው።

  • የኢየሱስን ባዶ መቃብር ይጠብቁ የነበሩ ወታደሮች በእርግጥ የሆነውን ነገር እንዳይናገሩ የገንዘብ ጉቦ ተቀብለው ነበር።
  • አንዳንዴ ወንጀልን አይቶ እንዳላየ እንዲያልፍ ወይም አንድ ውሳኔ እንዲያደርግ ለመግንሥት ባለ ሥልጣንም ጉቦ ይሰጣል።
  • ጉቦ መስጠትንም ሆነ መቀበልን መጽሐፍ ቅዱስ ይከለክላል።
  • “ጉቦ” የሚለው ቃል፣ “ተገቢ ያልሆነ ክፍያ” ወይም፣ “ለውሸት የሚደረግ ገንዘብ” ወይም፣ “ሕግን ወይም ደንብን ለመተላለፍ የሚሰጥ ገንዘብ” ተብሎ ሊተርጎም ይችላል።
  • “ጉቦ መስጠት” – “አንድ ሰው ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር የሚደረግ ክፍያ” ወይም፣ “ተገቢ ያልሆነ ነገር እንዲደረግ የሚሰጥ ገንዘብ” ወይም፣ “ተወዳጅ ለመሆን ገንዘብ መስጠት” በተሰኘ ቃል ወይም ሐረግ መተርጎም ይችላል።

ጉድጓድ

ጉድጓድ ወደ መሬት በጣም ዝቅ ብሎ የተቆፈረ ድንጋይ ነው።

  • ጉድጓድ እንስሳ ለማጥመድ ወይም ውሃ ለመፈለግ ሊቆፈር ይችላል። አንዳንዴ እስረኞችን ለማኖሪያ ጊዜያዊ ቦታ ሆኖም ያገለግላል።
  • በአይሁድ ሕግ ርስቱ ላይ ያለው ያልተሸፈነ ጉድጓድ ውስጥ ሰው ወይም እንስሳ ወድቆ ቢጎዳ ላደረሰው ጉዳት ባለቤቱ ተጠያቂ ይሆን ነበር።
  • በጣም ጥልቅ ጉድጓድ፣ “ጥልቁ” ተብሎም ይጠራል።

ጉድጓድ፣ ውሃ ማጠራቀሚያ

መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን፣ “ጉድጓድ” እና “ውሃ መያዣ” ሁለት የተለያዩ የውሃ መገኛ ቦታዎችን ነበር የሚያመለክተው።

  • ጉድጓድ መሬት ውስጥ ያለው ውሃ ወጥቶ እንዲጠራቀምበት ጠለቅ ተደርጎ የሚቆፈር ጉድጓድ ነው።
  • ውሃ መያዣም ጠላት ተደርጎ የተቆፈረ ጉድጓድ ሲሆን የዝናብ ውሃ ለማጠራቀም ያገልግላል።
  • ብዙውን ጊዜ ውሃ መያዣ ከዐለት ተፈልፍሎ የተሠራ ሲሆን፣ ውሃው እንዳይባክን በመክደኛ ይከደን ነበር። “ውሃ መያዝ የማይችል” የሚባለው መክደኛው ተሰንጥቆ ውሃ የሚያሰርግ ሲሆን ነው።
  • ውሃ መያዣዎች 6 ሜትር ጥልቀትና 1 ሜትር ስፋት ይኖራቸዋል።
  • ለሰዎችም ሆነ ለእንስሳት ውሃ በጣም አስፈላጊ በመሆኑ የውሃ ጉድጓድ አጠቃቀምን አስመልክቶ ብዙ ፀብና ግጭት ይፈጠራል።
  • እነርሱ ውስጥ ምንም ያልተፈለገ ነገር እንዳይገባ ጉድጓድም ሆነ የውሃ መያዣ በትልቅ ድንጋይ ይገጠማሉ። ብዙውን ጊዜ ውሃ ቀድቶ ለማውጣት ባልዲ የታሰረበት ገመድ ይኖራል።
  • ዮሴፍና ኤርምያስ ላይ ከሆነው እንደሚታየው አንዳንድ ጊዜ የደረቁ የውሃ መያዣዎች እንደ እስር ቤት ያገለግሉ ነበር።

ጊዜ

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ጊዜ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው የተወሰኑ ነገሮች የተፈጸሙበትን ወቅት ወይም ዘመን ለማመልከት ነው። “ዕድም” ወይም፣ “ዘመን” ወይም “ወቅት” ጋር የሚመሳሰል ትርጕም አለው።

  • ይህ ደቂቃዎች፣ ሰዓቶች፣ ቀኖች ወይም ወሮች ከሚለካበት መለኪያ የተለየ ትርጕም አለው።
  • ትንቢተ ዳንኤልና የዮሐንስ ራእይ በምድር ላይ ታላቅ መከራ የሚመጣበት፣ “ጊዜ” መኖሩን አመልከተዋል።
  • “ዘመን (ጊዜ)፣ ዘመናትና የዘመን እኩሌታ” የሚለው ሐረግ ውስጥ “ዘመን፣ ጊዜ” የሚያመለክተው አንድ፣ “ዓመትን” ነው። ይህ ሐረግ በዘመን ፍጻሜ ላይ ለሦስት ዓመት ተኩል የሚሆነውን ታላቅ መከራ ያመለክታል።
  • “ሁለተኛ ጊዜ” ወይም፣ “ብዙ ጊዜ” የተሰኙት ሐረጎች አንድ ነገር የሆነበትን ድርጊት ቁጥር ያመለክታሉ።
  • “በጊዜው” ማለት ሳይዘገዩ በሚጠበቀው ጊዜ መድረስ ማለት ነው።

ጊደር

ጊደር ገና ያልወለደች ወጣት ላም ናት። ወራሽ ወራዕ የሚባለው የአንድ የሞተ ሰው ንብረት ወይም ገንዘብ የመቀበል ሕጋዊ ዕውቅና የተሰጠው ሰው ነው።

  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ዋናው ወራሽ የመጀመሪያው ወንድ ልጅ ነበር፤ አብዛኛውን የአባቱን ንብረትና ገንዘብ የሚቀበል እርሱ ነበር።
  • እርሱ መንፈሳዊ አባታቸው በምሆኑ ክርስቲያን የሚወርሱትን መንፈሳዊ ጥቅም አስመክቶ መጽሐፍ ቅዱስ፣ “ወራሽ” የሚለውን ቃል ይጠቀምበታል።
  • እንደ የእግዚአብሔር ልጆች ክርስቲያኖች ከክርስቶስ ጋር አብረው ወራሾች መሆናቸው ተነግሯል።

ጋሻ

ጋሻ ከሚወረወር ፍላጻና ከሌሎችም ጠላት ከሚሰነዝራቸው ጥቃቶች ራሱን ለመከላከል አንድ ወታደር በጦርነት ይይዘው የነበረ ነገር ነበር ለአንድ ሰው ጋሻ መሆን እርሱን ከአደጋ መከለከል ማለት ነው

  • ጋሻዎች የተለያየ ቅርጽ ሊኖራቸው ቢችልም፤ አብዛኛውን ጊዜ ግን ክብ ወይም ሞላላ ናቸው
  • ጋሻዎች የሚሠሩት ቆዳን፣ እንጨትን ወይም ሰይፍ፣ ጦርና ፍላጻን መቋቋም በሚችል ብረት ነው
  • ይህን ቃል እንደተለዋጭ ዘይቤ በመጠቀም፣ እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደሚከልል ጋሻ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ያመለክታል
  • ጳውሎስም፣ አማኞችን ከመንፈሳዊ ጥቃትና ከሰይጣን ስለሚከልል፣ “የእምነት ጋሻ” ተናግሮአል

ጌታ

ጌታ የሚለው ቃል ሰዎች ላይ ባለቤትነት ወይም ሥልጣን ያለውን ሰው ያመለክታል።

  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ ይህ ቃል፣ “ሁሉን ቻይ ጌታ እግዚአብሔር” ወይም፣ “ጌታ ያህዌ” ወይም፣ “ያህዌ የእኛ ጌታ” በተሰኙት አገላለጾች ጥቅም ላይ ይውል ነበር።
  • አዲስ ኪዳን ውስጥ ሐዋርያቱ፣ “ጌታ ኢየሱስ” እና፣ “ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ” ለማለት በዚህ ቃል ተጠቅመዋል፤ ይህም የሚያመለክተው ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን ነው።
  • አዲስ ኪዳን ውስጥ፣ “ጌታ” የሚለው ቃል በተለይ ከብሉይ ኪዳን በተወሰዱ ጥቅሶች በቀጥታ እግዚአብሔርን ብቻ ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል። ለምሳሌ ያህል፣ የብሉይ ኪዳን “በያህዌ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው” ሲል፣ አዲስ ኪዳን ደግሞ “በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው” ይላል።
  • ULB እና UDB ውስጥ፣ “ጌታ” የሚለው መጠሪያ ጥቅም ላይ የዋለው የዕብራይስጥም ሆነ የግሪኩ ቃል፣ “ጌታ” ለማለት በተጠቀመበት መልኩ ለመተርጎም ነው። በብዙ የተለያዩ ቦታዎች እንደ ተደረገው እንደ የእግዚአብሔር ስም (ያህዌ) ትርጕም አይደለም ጥቅም ላይ የዋለው።

ግመል

ግመል ጀርባው ላይ አንድ ወይም ሁለት ሻኛ ያለው ግዙፍ ባለ አራት እግር እንስሳ ነው።

  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ግመል በእስራኤልና በአካባቢው አገሮች የሚገኝ ትልቁ እንስሳ ነበር።
  • ግመል ሰዎችና ሌሎች ነገሮችን ለመሸከም በዋነኛነት ደረጃ ጥቅም ላይ ይውል ነበር።
  • አንዳንድ ሕዝቦች ግመልን ለምግብነትም ይጠቀሙበት የነበረ ቢሆንም፣ ግመል ንጹሕ ያልሆነ እንስሳ መሆኑንና መበላትም እንደሌለበት እግዚአብሔር በመናገሩ እስራኤላውያን ግን አይበሉትም ነበር።
  • በአሸዋ ላይ በፍጥነት መጓዝና ያለ ምግብ ውሃ ለበርካታ ሳምንቶች መኖር ይችል ስለ ነበር ግመል በጣም ጠቃሚ እንስሳ ነው።

ግራር

“ግራር” የተሰኘው ቃል በጥንት ዘመን በከነዓን ምድር ይበቅል የነበረው በብዛት ይገኝ የነበረው ቁጥቋጦ ወይም ዛፍ ስም ነው። ዛሬም ቢሆን በዚያ አካባቢ በብዛት ይገኛል።

  • ብርቱካናማ፣ ቡኒ መልክ ያለው የግራር እንጨት በጣም ጠንካራና ረጅም ዘመን መኖር የሚችል በመሆኑ አንዳንድ ነገሮችን ለመሥራት ያገለግላል።
  • ይህ እንጨት ውስጡ ውሃ የማይዝ ጥቅጥቅ ያለ በመሆኑ ለረዥም ዘመን አይበላሽም፤ምስጦችን የሚከላከል ተፈጥሮአዊ መከላከያ አለው።
  • በመጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን የግራር እንጨት የቃል ኪዳኑን ታቦ ለመሥራት ጥቅም ላይ ውሏል።

ግብር

ግብር ከለላ ለማግኘትና በሕዝቦቻቸው መካከል መልካም ግንኙነት እንዲኖር አንድ መንግሥት ወይም ገዢ ለሌላው የሚያቀርበው ስጦታ ነው።

  • ግብር አንድ ገዢ ወይም መንግሥት ከሕዝቡ የሚሰበስበው ገንዘብ ወይም ዋጋ ያለው ሌላ ነገር ሊሆን ይችላል።
  • በጥንት ዘመን ጕዞ ላይ ያሉ ንጉሦች ወይም ገዦች ጥበቃና ከለላ እንዲደረግላቸው ለሚያልፉበት አካባቢ ንጉሥ ወይም ገዢ ግብር ይከፍሉ ነበር።
  • ብዙውን ጊዜ ከገንዘብ ሌላ ምግብ፣ ቅመማ ቅመም፣ ውድ ልብሶች፣ እና ወርቅን የመሳሰሉ የከበሩ ድንጋዮችን ግብር ማቅረብ የተለመደ ነበር።

ግብዣ

ብዙውን ጊዜ ግብዣ የተለያዩ የምግብ ዓይነቶች የሚቀርቡበት ታዋቂ ሰፊ ድግስ ነው

  • በጥንት ዘመን የፖለቲካ መሪዎችንና ታዋቂ እንግዶችን ለማዝናናት ነገሥታት የተለያዩ ግብዣዎች ያደርጉ ነበር
  • ይህ “የጣፈጠ ምግብ” ወይም፥ “ሁነኛ ድግስ” ወይም ፥ “ብዙ ምግቦች ያሉበት ድግስ” ተብሎ መተርጎም ይችላል

ግዙፍ

ግዙፍ የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ የሚያመለክተው ያልተለመደ ቁመትና ጉልበት ያለውን ሰው ነው።

  • ዳዊትን ውጊያ የገጠመው ፍልስጥኤማዊው ወታደር ጎልያድ በጣም ረጅም. ትልቅና ጠንካራ ስለ ነበር ግዙፍ ተብሏል።
  • ምድረ ከነዓንን የሰለሉ እስራኤላይውና ሰላዮች እዚያ የሚኖሩ ሰዎች በጣም ግዙፍ እንደ ሆኑ ተናገሩ።

ጎረቤት

አብዛኛውን ጊዜ ጎረቤት የሚባለው በአካባቢው የሚኖር ሰው ነው። ይበልጥ አጠቃላይ በሆነ መልኩ፣ በምትኖሩበት ማኅበረ ሰብ ወይም የሰዎች ስብስብ ውስጥ የሚኖር ሰውን ያመለክታል።

  • “ጎረቤት” የሚለው አንዱ ትርጕም፣ እናንተ በምትኖሩበት ማኅበረ ሰብ ውስጥ የሚኖር በመሆኑ ከለላ የምትሆኑትና ደግ የምትሆኑለት ሰው ማለት ነው።
  • ስለ መልካሙ ሳምራዊ አዲስ ኪዳን ውስጥ ኢየሱስ በተናገረው ምሳሌ ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ፣ “ጎረቤት” የሚለውን ቃል የተጠቀመበት ሌላው ቀርቶ ጠላት የሚባለው እንኳ ሳይቀር የሰው ልጅን ሁሉ በሚያካትት ሰፋ ባለ ሁኔታ ነው።
  • የአሥሩ ትእዛዞች የመጨረሻዎቹ ስድስቱ ሌሎች ሰዎችን ማለትም ጎረቤቶችን መውደድ ላይ ያተኵራሉ።
  • የሚቻል ከሆነ ይህን ቃል በቃል ለመረርጎም “አጠገብህ የሚኖር ሰው” የሚል ትርጕም ባለው ቃል ወይም ሐረግ መጠቀሙ የተሻለ ነው።

ጎርፍ

ብዙውን ጊዜ ጎርፍ የሚባለው ምድሩን ሁሉ የሚሸፍን ብዛት ያለው ውሃ ነው። የአንድን ነገር ብዛት ወይም በድንገት ነገር ለማመልከትም ምሳሌያው በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።

  • በኖኅ ዘመን የነበሩ ሰዎች በጣም ክፉዎች ከመሆናቸው የተነሣ እግዚአብሔርን ምድርን ሁሉ ሌላው ቀርቶ የተራሮችን ጫፍ እንኳየሚሸፍን ጎርፍ አመጣ። ሌሎች ጎርፎች የተወሰነ የምድርን ክፍል ብቻ ነው የሚሸፍኑት።
  • ይህ ቃል. “እንባዬ እንደ ጎርፍ ፈሰሰ” ለማለትም ጥቅም ላይ ይውላል።

ጎሳ

“ጎሳ” ከአንድ አባት የተገኙ ረጅም ሐረግ ያለው ቤተ ሰብ አካሎች ናቸው።

  • በብሉይ ኪዳን ዘመን እስራኤል በጎሳቸው ወይም በቤተ ሰብ ወገናቸው ይቆጠሩ ነበር።
  • አንዳንዴ ግለ ሰቦችም በጎሳቸው ስም ይጠሩ ነበር። ለምሳሌ የሙሴ ሚስት አባት ዮቶር ራጉኤል በተሰኘው የጎሳው ስም ተጠርቷል።
  • ጎሳ፣ “የቤተ ሰብ ስብስብ” ወይም፣ “ረጅም የቤተ ሰብ ዝርዝር” ወይም፣ “ዘመዶች” ተብሎ መተርጎም ይችላል።

ጎተራ

“ጎተራ” ምግብ ወይም ሌሎች ነገሮችን ለማከማቸት የሚያገለግል ማስቀመጫ ነው

  • መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈበት አመን አብዛኛውን ጊዜ፣ “ጎተራ” ጥቅም ላይ የሚውለው ከረሃብ የተነሣ የምግብ እጥረት ሲኖር ለመጠቀም ትርፍ እህልንና ሌሎች ምግቦችን ለማከማቸት ነበር
  • አንዳንድ ጊዜ የቤተሰቡን ሀብት ለማጠራቅም ጎተራ ጥቅም ላይ ይውላል
  • ይህ ቃል ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ፣ እግዚአብሔር ለሕዝቡ መስጠት የሚፈልገውን መልካም ነገር ሁሉ ያመልክታል
  • ከተሸነፉ ጠላቶች የተወሰዱና ለያህዌ የተቀደሱ ዋጋ ያላቸው ነገሮች ሁሉ የሚጠበቁት ያህዌ ቤት ውስጥ ባለው ጎተራ ነበር። ይህ ሀብት ቤተመቅደስን ማደሻ እንዲሆን ይከማቻል። አንዳንዴም፣ “ግምጃ ቤት” ይባላል
  • “ጎተራ” የሚለውን ቃል ለመተርጎም ጥቅም ላይ መዋል የሚችሉ ቃሎች፣ “እህል ማጠራቀሚያ” ወይም፣ “ምግብ ማከማቻ” ወይም፣ “ዋጋ ያላቸው ነገሮች የሚቀመጡበት” የተሰኙት ናቸው

ጠላት/ባለጋራ

“ጠላት/ባለጋራ” አንዳንድ ሰው ወይም አንድን ነገር የሚቃወም ሰው ወይም ሰዎች ማለት ነው።

  • ጠላት የሚባለው ሊቃወማችሁ ወይም ሊጎዳችሁ የሚሞክር ሰው ሊሆን ይችላል።
  • አንድ አገር ሌላውን አገር የሚወጋ ከሆነ ፣”ጠላት” ሊባል ይችላል
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ዲያቢሎስ፣ “ጠላት” እና “ባላጋራ” ተብሎ ተጠርቷል።
  • ጠላት “ተዳራሪ” ወይም “ባለጋራ” ተብሎ ሊተረጎም ቢችልም የሚያመለክተው ጽኑ ዐይነት ተቃውሞን ነው።

ጠማማ፣ የተጣመመ

“ጠማማ” ግብረ ገባዊ ወልጋዳነት ወይም ገዳዳነት ያለውን ሰው ወይም ተግባር ለሚመለከት ጥቅም ላይ የሚውል ቃል ነው። “የተጣመመ” - ወልጋዳ ማለት ነው።

  • ጠማማ የሆነ ሰው ወይም ነገር መልካምና ትክክል ከሆነው የወጣ ማለት ነው።
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንመለከተው ለእግዚአብሔር ባለ መታዘዝ እስራኤል የተጣመመ ሕይወት ኖረዋል። አብዛኛውን ጊዜ እንዲህ የሆነው ሐሰተኛ አማልክትን በማምለካቸው ነበር።
  • ከእግዚአብሔር መለኪያ ወይም ባሕርይ የማይስማማ ማንኛውም ነገር ጠማማ ተብሎ ይጠራል።
  • እንደ ዐውዱ ሁኔታ “ጠማማ” የሚለውን ቃል ለመተርጎም የሚጠቅሙ መንገዶች፣ “ግብረ ገባዊ ገዳዳ የሆነ” ወይም፣ “የተበላሸ” ወይም፣ “ቀጥተኛ ከሆነው የእግዚአብሔር መንገድ የወጣ” የተሰኙት ሊሆኑ ይችላሉ።
  • “ጠማማ ንግግር” የሚለውን ቃል፣ “ክፉ መናገር” ወይም፣ “አሳሳች ንግግር” ወይም፣ “የማይረባ አነጋገር” በማለት መተርጎም ይቻላል።
  • ጠማማ ሕዝብ” የሚለውን ሐረግ፣ “ገዳዳ ሕዝብ” ወይም፣ “ከግብረ ገብ ውጪ የሆነ ሕዝብ” ወይም፣ “ዘወትር ለእግዚአብሔር የማይታዘዝ ሕዝብ” በማለት መተርጎም ይቻላል።
  • “የተጣመመ ተግባር” የሚለውን ሐረግ፣ “ክፉ ሥራ” ወይም፣ “ከእግዚአብሔር ትምህርት በወጣ መንገድ መኖር” በማለት መተርጎም ይቻላል።

ጠባቂ

“ጠባቂ” አንድ ነገር በጥንቃቄ የሚመለከት፣ ረጋ ብሎና ቀረብ ብሎ በማስተዋል የሚመረምር ማለት ነው። ቃሉ በርካታ ምሳሌያዊ ትርጕሞችም አሉት።

  • “ለሕይወትህና ለትምህርት ተጠንቀቅ” ማለት ምንጊዜም ንቁ ሁን፣ ኀጢአትና ክፉ ነገርን ለማድረግ አትዘናጋ ማለት ነው። “ዝግጁ ሁን” ማለትም ይሆናል።
  • “በጥንቃቄ መጠበቅ” ወይም፣ “በቅርብ ሆኖ መከታተል” ከተባለ አንድ ሰው ወይም አንድን ነገር፣ ከለላ መሆን ክፉ እንዳያገኘው መከላከል ማለት ነው።

ጠብ

ጠብ በሰዎች መካከል ያለ አካላዊ ወይም ስሜታዊ ግጭት ማለት ነው

  • ጠብ ፈጣሪ ሰው በሰዎች መካከል ስምምነት እንዳይኖር የሚያደርጉ ነገሮችን ያደርጋል
  • ጠብ አንዳንዴ ቁጣን ወይም መራራነትን የመሳሰሉ መጥፎ ስሜቶች ያመለክታል
  • ይህን ቃል ለመተርጎም፣ “አለመስማማት” ወይም፣ “ጭቅጭቅ” ወይም፣ “ግጭት” የተሰኙ ቃሎች ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ

ጠንቃቃ

“ጠንቃቃ” የሚለው ቃል ስለሚሠራው ነገር ረጋ ብሎ የሚያስብና ትክክለኛ ውሳኔ የሚያደርግ ሰውን ይገልጣል።

  • አንዳንዴ ጠንቃቃ የሚለው ቃል ገንዘብና ንብረትን የመሳሰሉ ቁሳዊ ነገሮችን በአግባቡ ከመያዝ አስተዋይነት ጋር ይያያዛል።
  • በገንዘብ ወይም በንብረት አያያዙ የሰው ጠንቃቃነት ይታያል።
  • ምንም እንኳ፣ “አስተዋይ” ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ትርጕም ቢኖረውም፣ “ጥበብ” በአጠቃላይ መንፈሳዊና ግብረ ገባዊ ነገሮች ላይ ያተኩራል።
  • እንደ ዐውዱ ሁኔታ ይህ “ብልኅ” ወይም፣ “ልባም” ወይም፣ “አስተዋይ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

ጠንካራ፣ ጥንካሬ

“ጠንካራ” የሚለው ቃል እንደ ዐውዱ ሁኔታ የተለያዩ ትርጕሞች ይኖሩታል። ብዙዎን ጊዜ የሚያመለክተው አስቸጋሪ፣ አዳጋች ወይም የማይበገር ነገርን ነው።

  • “ልበ ጠንካራ” የተሰኘው ፈሊጣዊ አነጋገር ግትርና ንስሐ የማይገቡ ሰዎችን ያመለክታል። ይህ አነጋገር ከክፉ ሥራቸው የተነሣ ከባድ መከራ ቢደርስባቸው እንኳ በእግዚአብሔር ላይ ማመፃቸውን የሚቀጥሉ ሰዎች መገለጫ ነው።
  • “የልብ ጥንካሬ” እና “የልባቸው ጥንካሬ” የሚለው ምሳሌያዊ ገለጻም እንዲሁ ግትር አለመታዘዝን ያመለክታል።
  • “ጠንክሮ መሥራት” ወይም፣ “ጠንክሮ መሞከር” ማለት በጽናትና በትጋት አንድን ነገር ማድረግ፣ አንድን ነገር ጥሩ አድርጎ ለመሥራት ከባድ ጥረት ማድረግን ያመለክታል።

ጢቢብ፣ ጥበብ

“ጠቢብ” የሚለው ቃል መልካምና ግብረ ገባዊ ነገሮችን የሚረዳና በተረዳው መሠረት የሚኖር ሰው ነው። እውነትና ግብረ ገባዊ የሆኑ ነገሮችን መረዳት፣ “ጥበብ” ይባላል።

  • ጥበበኛ መሆን መልካም ውሳኔ የማድረግ ችሎታን በተለይም፣ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኙ ነገሮችን መምረጥንም ያካትታል።
  • በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት፣ “የዓለም ጥበብ” የዚህ ዓለም ሰዎች ጥበብ የሚሉት በመሠረቱ ግን ሞኝነት የሆነ ነገርን የሚያመለክት ምሳሌያዊ አነጋገር ነው።
  • ጥበበኛ ሰው እንደ ደስታ፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ ቸርነትና ትዕግሥትን የመሳሰሉ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች በሕይወቱ ያሳያል።

ጣዖት፣ ጣዖት አምላኪ

ጣዖት እርሱን ለማምለክ ሰዎች የሚያበጁት ነገር ነው። ከአንዱ እውነተኛ አምላክ ይልቅ ለአንዳች ሌላ ነገር ክብር ሲሰጥ ያ ጣዖት አምልኮ ይባላል።

  • ሰዎች የሚያመልኳቸውን አማልክት የሚወክሉ ጣዖቶች ያበጃሉ።
  • እነዚህ ሐሰተኛ አማልክት ሕልውና የላቸውም፤ ከያህዌ ሌላ አምላክ የለም።
  • አንዳንዴ ኀይል ያለው መስሎ እንዲታይ አጋንንት በጣዖቱ ይሠራሉ።
  • ብዙውን ጊዜ ጣዖቶች ወርቅ፣ ብር፣ ናስ ወይም ውድ ዋጋ ያለውን እንጨት በመሳሰሉ ዋጋ ባላቸው ነገሮች ይሠራሉ።
  • “ጣዖት አምላኪ መንግሥት” – “ጣዖት የሚያመልኩ ሰዎች መንግሥት” ወይም፣ “ ምድራዊ ነገሮችን የሚያመልክ መንግሥት” ማለት ነው።
  • “የጣዖት ቅርጽ” የሚለው፣ “የጣዖት ምስል” ወይም፣ “ጣዖት” የማለት ሌላ ቃል ነው።

ጥላ

ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “ጥላ” ብርሃን ሲጋረድ የሚፈጠረውን ጨለማ ያመለክታል። በርካታ ምሳሌያዊ ጠቀሜታዎችም አሉት

  • “የሞት ጥላ” ማለት ጥላ ለአንድ ነገር ቅርብ የሆነውን ያህል በዙሪያው ሞት አለ፤ ሞት ቅርብ ነው፤ አጠገብ ነው ማለት ነው
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሰው ሕይወት ብዙ ከማይቆይና እውን ካልሆነ ጥላ ጋር ብዙ ጊዜ ተመሳስሏል
  • አንዳንዴ፣ “ጥላ” – “ጨለማ” ለማለት ሌላ ቃል ነው
  • መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር ክንፎች ወይም እጆች ጥላ ውስጥ ስለመሸሸግ ይናገራል። ይህም ከአደጋ መከለልንና መደበቅን ያመለክታል። እንዲህ ባለው ዐውድ ውስጥ፣ “ጥላ” የሚለውን፣ “ከለላ” ወይም፣ “መደበቂያ ቦታ” በማለት መተርጎም ይቻላል
  • “ጥላ” የሚለውን የአካባቢው ቋንቋ በሚጠቀምበት ሁኔታ ቃል በቃል መተርጎሙ ይመረጣል

ጥልቆ/ጥልቁ

“ጥልቅ/ጥልቁ”የሚለው ቃል በጣም ሰፊና ጥልቅ ጉድጓድን ወይም ማለቂያ የሌለው ሸለቆን ያመለክታል

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ጥልቅ/ጥልቁ” የቅጣት ቦታ ነው።
  • ለምሳሌ ከሰውየው እንዲወጡ እየሱስ አጋንንቱን ባዘዛቸው ጊዜ ወደ ጥልቁ እንዳይሰዳቸው ለምነውት ነበር።
  • “ጥልቅ/ጥልቁ” የሚለው ቃል፣ማለቂያ የሌለው ጥልቅ ጉድጓድ ወይም በጣም የጠለቀ፣ሸለቆ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።ሆኖም ፣ቃሉ ከ፣“ሐዲስ” “ሲዖል”ወይም ከገሃነም የተለየ መሆኑ መታወቅ አለበት።

ጥሩር

ጥሩር የሚባለው በጦርነት ጊዜ ወታደሩን ለመከለል ደረትን የሚሸፍን መሥራሪያ ነው። እስራኤላዊው ሊቀ ካህን ይለብስ የነበረው ልዩ ዐይነት ልብስ ክፍል ጥሩር ይባል ነበር።

  • ወታደሮች የሚጠቀሙበት ጥሩር ከእንጨት፣ ከብረት ወይም ከቆዳ ነበር የሚሠራው። ዓላማው ቀስት፣ ጦር ወይም ሰይፍ የወታደሩን ደረት እንዳይወጋው መከላከል ነበር።
  • እስራኤላዊ ሊቀ ካህን የሚለብሰው ጥሩት ከጨርቅ የተሠራ ሲሆን፣ የከበሩ ጌጣጌጦች ይያያዙበት ነበር። ቤተ መቅደሱ ውስጥ እግዚአብሔርን የማገልገል ሥራውን ሲያከናውን ካሁኑ ይህን ይለብስ ነበር። የሊቀ ካህኑ ጥሩር፣ “ደረት መሸፈኛ” ይባልም ነበር።

ጥርስ ማፋጨት

ጥርስ ማፋጨት ማለት ጥርሶችን በማያያዝ ወደ ፊት ወደ ኋላ በማድረግ ወይም ግራና ቀኝ በማድረግ እርስ በርሳቸው እንዲፋጩ ማድረግ ማለት ነው። ይህ ብዙውን ጊዜ የሚያሳየው ከባድ ስቃይን (ሕመምን) ወይም ቊጣን ነው።

  • ገሃነም ውስጥ የሚኖሩ ከሚደርስባቸው ከባድ ስቃይ የተነሣ ጥርሳቸውን እንደሚያፏጩ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
  • የአገርህ ባሕል አንድ ሰው ሲቆጣ ጥርሱን የማያፋጭ ከሆነ ይህ ሐረግ፣ “በቍጣ ጥርስን ማፋጨት” ብሎ መተርጎም ይቻላል። ወይም በአንተ ባሕል ሰዎች ሲቆጡ የሚያደርጉትን እንደ እግርን አንስቶ መሬቱን በኀይል መርገጥን የላይ የታች ጥርሶችን ግጥም አድርጎ መያዝን ወይም መጮኽን የመሳሰሉ ቃሎች መጠቀም ይቻላል።

ጥቅልል መጽሐፍ

በጥንት ዘመን ጥቅልል ከአንድ ረጅም የፓፒረስ ገጽ ወይም ከቆዳ የሚሠራ የመጽሐፍ ዓይነት ነበር። ጥቅልሉ ላይ ከተጻፈ ወይም ከተነበበ በኋላ ሰዎች ጫፉ ላይ ትንሽ በትር መሳይ ነገር በማኖር ይጠቀልሉት ነበር

  • ጥቅልሎች ሕጋዊ ሰነዶችንና ቅዱሳት መጻሕፍትን ለመጻፍ ያገለግላሉ
  • አንድ ሰው ለሌላው መልእክተኛ ጥቅልል ጽሑፍ እንዲያደርስለት ከፈለገ በሰም ያሽገው ነበር። ይህም መልእክተኛው ወይም ሌላ ሰው ውስጥ ሌላ ነገር እንዳይጽፍ ወይም እንዳያነብ ለማድረግ ነበር። ጥቅልል ጽሑፉን የሚቀበለው ሰው ስሙ ወይም ማኅተሙ አለመልቀቁን በማየት ማንም እንዳልከፈተው እርግጠኛ ይሆን ነበር።

ጥቅም፣ ጠቃሚ

በአጠቃላይ “ጠቃሚ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሚገኝ መልካም ነገርን ነው። ለራሱ መልካምነገር የሚያስገኝ ወይም ለሌሎች መልካም ነገር የሚያስገኝ ከሆነ አንድ ነገር ጠቃሚ ነው ይባላል።

  • የበለጠ ግልጽ በሆነ መልኩ፣ ብዙውን ጊዜ፣ “ጠቃሚ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው አንድን ሥራ ሠርቶ የሚገኝ ገንዘብን ነው። ከወጪው የበለጠ ገንዘብ የሚያስገኝ ሥራ “ጠቃሚ” ነው።
  • ከሚያስፈልገው በላይ ገንዘብ በመጠየቅ የሚገኝ ጥቅምን መጽሐፍ ቅዱስ ይቃወማል።
  • የምጽሐፍ ቃል ሰዎችን በጽድቅ ለመምከርና ለማስተማር “ጠቃሚ” መሆኑን 2ጢሞቴዎስ 3፡16 ይናገራል። ይህም ማለት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ሰዎች እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንዲኖሩ ለማስተማር ይረዳሉ፣ ይጠቅማሉ ማለት ነው።
  • 1ቆሮንቶስ 10፡23 ለክርስቲያኖች ሁሉም የተፈቀደ ቢሆንም፣ ሁሉም፣ “ጠቃሚ” እንዳልሆነ ይናገራል። ይህም ማለት አንድ ነገር የተፈቀደ ቢሆን እንኳ፣ ክርስቲያን እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ ሁኔታ እንዲኖር በመርዳት ረገድ የሚሰጠው ጥቅም የለም ማለት ነው።

ጥድ

ጥድ ዓመቱን ሙሉ አረንጓዴ የሆነ፣ ዘሩን የሚይዝበት ሾጣጣ መያዣዎች ያሉት የዛፍ ዓይነት ነው።

  • የጥድ ዛፍ ሁሌም አረንጓዴ ሆኖ የሚገኝ ዛፍ በመሆን ይታወቃል።
  • በጥንት ዘመን የጥድ ዛፍ እንጨት የሙዚቃ መሣሪያ ለመሥራት፣ ጀልባዎችን፣ ቤቶችንና ቤተመቅደሶችን ለመሥራት ጥቅም ላይ ይውል ነበር።

ጥፋት

ጥፋት የሚለው ቃል ምንም ይግባኝ ወይም ማምለጫ የሌለው ፍርድና ኩነኔን ያመለክታል።

  • የእስራኤል ሕዝብ በምርኮ ወደ ባቢሎን ሲወሰዱ እነርሱ ላይ ጥፋት መምጣቱን ነቢዩ ሕዝቅኤል አመልክቷል።
  • በዐውዱ መሠረት ይህ ቃል፣ “ቅጣት” ወይም፣ “ተስፋ የሌለው ጥፋት” ተብሎ መተርጎም ይችላል።

ጦር

ጦር በአንድ በኩል ሹል ብረት ያለው ሆኖ ጠላት ላይ የሚወረወር ረጅም እጀታ ያለው መሣሪያ ነው

  • በጥንት ዘመን ጦር በጦርነት ጊዜ የተለመደ መሣሪያ ነበር። በአሁኑ ጊዜም ቢሆን የተለያዩ ወገኖች ይጠቀሙበታል
  • ኢየሱስ መስቀል ላይ በነበረ ጊዜ ወታደሩ ጎኑን የወጋው በጦር ነበር
  • አንዳንዴ ሰዎች ዓሣ ለመያዝ ወይም የሚበላ ሌላ እንስሳ ለመግደል ጦር ይወረውራሉ

ጨለማ

ቃል በቃል፣ “ጨለማ” የብርሃን አለመኖር ማለት ነው። ይህ ቃል የተለያዩ ምሳሌያዊ ትርጕሞችም አሉት።

  • እንደ ተዋጭ ዘይቤ፣ “ጨለማ” – “ርኵሰት” ወይም፣ “ክፉ” ወይም፣ “መንፈሳዊ ዕውርነት” ማለት ነው።
  • ማንኛውም ኀጢአትና ግብረ ገባዊ ብልሽትንም ሊያመለክት ይችላል።
  • “የጨለማ ግዛት” የሚለው አገላለጽ ክፉ የሆነውንና በሰይጣን የተገዛውን ሁሉ ያመለክታል።
  • “ጨለማ” የሞት ተለዋጭ ዘይቤ በምሆንም ያገለግላል።
  • እግዚአብሔርን የማያውቁ ሰዎች፣ “ጨለማ ውስጥ እየኖሩ ነው” ይባላል፤ ይህም የጽድቅ አኗኗርን መረዳት አይችሉም ማለት ነው።
  • እግዚአብሔር ብርሃን ነው (ጽድቅ) ጨለማም (ክፉ) በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም።
  • እግዚአብሔርን የሚንቁ ሰዎች የሚቀጡበት ቦታ አንዳንድ፣ “በውጭ ያለው ጨለማ” ይባላል።

ጽድቅ የሌለበት፣ ኀጥእ

“ጽድቅ የሌለበት” ኀጢአተኛና ምግባረ ምልሹ ማለት ሲሆን፣ “ኀጥእ” ኀጢአት ማድረግን ወይም፣ ኀጢአተኛ መሆንን ያመለክታል።

  • እነዚህ ቃሎች በተለይ የሚያመለክት በእግዚአብሔር ትምህርትና ሕጎች ላይ እያመፁ መኖርን ነው።
  • ጽድቅ የሌላቸው ሰዎች በሐሳባቸውም ሆነ በተግባራቸው ዐመፀኞች ናቸው።
  • አንዳንዴ፣ “ኀጥእ” የሚለው ቃል በተለይ የሚያመለክተው በኢየሱስ የማያምኑ ሰዎችን ነው።

ጽድቅ የሌለበት፣ ኀጥእ

“ጽድቅ የሌለበት” ኀጢአተኛና ምግባረ ምልሹ ማለት ሲሆን፣ “ኀጥእ” ኀጢአት ማድረግን ወይም፣ ኀጢአተኛ መሆንን ያመለክታል።

  • እነዚህ ቃሎች በተለይ የሚያመለክት በእግዚአብሔር ትምህርትና ሕጎች ላይ እያመፁ መኖርን ነው።
  • ጽድቅ የሌላቸው ሰዎች በሐሳባቸውም ሆነ በተግባራቸው ዐመፀኞች ናቸው።
  • አንዳንዴ፣ “ኀጥእ” የሚለው ቃል በተለይ የሚያመለክተው በኢየሱስ የማያምኑ ሰዎችን ነው።

ጽድቅ የሌለበት፣ ኀጥእ

“ጽድቅ የሌለበት” ኀጢአተኛና ምግባረ ምልሹ ማለት ሲሆን፣ “ኀጥእ” ኀጢአት ማድረግን ወይም፣ ኀጢአተኛ መሆንን ያመለክታል።

  • እነዚህ ቃሎች በተለይ የሚያመለክት በእግዚአብሔር ትምህርትና ሕጎች ላይ እያመፁ መኖርን ነው።
  • ጽድቅ የሌላቸው ሰዎች በሐሳባቸውም ሆነ በተግባራቸው ዐመፀኞች ናቸው።
  • አንዳንዴ፣ “ኀጥእ” የሚለው ቃል በተለይ የሚያመለክተው በኢየሱስ የማያምኑ ሰዎችን ነው።

ጾም

መጾም ምግብን ወይም አንዳንድ የምግብ ዐይነቶችንና መጠጦችን ለተወሰነ ጊዜ ማቆም ነው።

  • ጾም ሰዎች ትኩረታቸውን እግዚአብሔር ላይ እንዲያደርጉና በምግብ አስተሳሰባቸው ሳይበታተን መጸለይ እንዲችሉ ይረዳል።
  • የተሳሳተ ዓላማ ይዞ በመጾም ኢየሱስ የአይሁድ ሃይማኖት መሪዎችን ተቃውሞ ነበር። ይጾሙ የነበረው ምን ያህል ሃይማኖተኞች መሆናቸውን ሌሎች እንዲያዩላቸው ነበር።
  • አንዳንዴ ሰዎች የሚጾሙት በአንድ ነገር ምክንያት በጣም ማዘናቸውንና መተከዛቸውን ለማሳየት ነው።
  • ይህ ቃል፣ “መመገብን መተው” ተብሎ መተርጎም ይችላል።

ፈረሰኛ

መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን “ፈረሰኛ” የሚባለው ብዙውን ጊዜ ፈረስ ላይ ሆኖ ወደ ጦርነት የሚሄድ ሰው ነበር።

  • ፈረሶች ሰረገለና ጋሪ ለመሳብ ይረዳሉ።
  • ይሁን እንጂ እስራኤላውያን ብዛት ያላቸው ፍረሰኞች አልነበሯቸውም።
  • ድል ለማድረግ በያህዌ ከሙታን ይልቅ፣ በጦርነት ጊዜ በፈረሰኞች ብዛት መተማመን የአረማውያን ባሕል እንደ ሆነ ያምኑ ነበር።

ፈረስ

ፈረስ ግዙፍ ባለ አራት እግር እንስሳ ሲሆን፣ መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን በአብዛኛው ለእርሻ ሥራና ለሰዎች መጓጓዣ ያገለግል ነበር።

  • አንዳንድ ፈረሶች ሰረገላና ጋሪ ለመጎተት ሲያገለግሉ፣ ሌሎች ሰዎችን በመሸከም ያገለግሉ ነበር።
  • ወደ ተፈለገው አቅጣጫ ፈረሶችን መምራት እንዲቻል አፋቸው ውስጥ ልጓም ይገባል።
  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን በአመዛኙ በጦርነት ጊዜ ካላቸው ጠቀሜታ የተነሣ ፈረሶች እንደ ትልቅ ሀብት የባለጠጋነት መለኪያ ይቆጠሩ ነበር። ለምሳሌ ንጉሥ ሰሎሞን አንድ ሺህ ፈረሶች ነበሩት።
  • ፈረስ የሚመስሉ እንስሳት አህያና በቅሎ ናቸው።

ፈራጅ፣ ፈራጆች

ፈራጅ ሕግን በሚመለከቱ ጉዳዮች የመዳኘትና የመወሰን ሥልጣን እንዲኖረው የተሾመ ባለ ሥልጣን ነው።

  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን አንድ ፈራጅ በሰዎች መካከል ባለው ጉዳይ መፍትሔ ይሰጥ ነበር።
  • ቃሉ፣ “ዳኛ” ወይም፣ “ዐቃቤ ሕግ” ወይም፣ “የሕግ ባለ ሥልጣን” ወይም ፣ “ባለ ሥልጣን” ወይም፣ “ገዢ” ተብሎ መተርጎም ይችላል።

ፊት

“ፊት” የሚለው ቃል የአንድ ሰው ራሱ ከፊት በኩል ያለውን ክፍል ነው፤ ቃሉ አያሌ ምሳሌያዊ ትርጉሞች አሉት።

  • “ፊትህ” ማለት፣ “አንተ” ማለት ሲሆን፣ በተመሳሳይ፣ “ፊቴ” ማለት፣ “እኔ” ወይም፣ “የእኔ” ማለት ነው።
  • አንድ ሰው ወይም አንድን ነገር፤ “ፊት ለፊት” መግጠም ማለት በቀጥታ ያን ሰው ወይም ነገር ወዳለበት አቅጣጫ መመልከት ማለት ነው።
  • “ፊት ለፊት መገናኘት” ማለት፣ “ፊት ለፊት መተያየት” ማለት ነው።
  • “ፊት ለፊት መሆን” ሁለት ሰዎች በቅርብ ርቀት እርስበርስ ሲተያዩ ማለት ነው።
  • ኢየሱስ፣ “ወደኢየሩሳሌም ለመሄድ ፊቱን አቀና” ማለት ወደዚያ ለመሄድ ወሰነ ማለት ነው።
  • አንድ ሰው ወይም አገር ላይ፣ “ፊትን ማክበድ” ላለመርዳት መወሰን ወይም ያን ሰው ወይ አገር ችላ ማለት ማለት ነው።
  • “የምድሪቱ ፊት” የሚለው ሐረግ የምድሪቱን ውጫዊ ገጽታ የሚያመለክት ሲሆን ብዙውን ጊዜ፣ ምድርን ሁሉ የሚያመለክት አጠቃላይ ቃል ነው። ለምሳሌ፣ “የምድርን ፊት የሚሸፍን ራብ” ሲባል፣ ብዙ ሰዎችን ጉዳት ላይ የጣለ ራብ መስፋፋቱን ነው የሚያመለክተው።
  • “ከሕዝብህ ፊትህን አትሰውር” የሚለው ምሳሌያዊ አገላለጽ፣ “ሕዝብህን ችላ አትበል” ወይም፣ “ሕዝብህን አትተው” ወይም፣ “ለሕዝብህ ማሰብን አትተው” ማለት ነው።

ፍሬ፣ ፍሬያማ

ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “ፍሬ” የሚበላ የተክል ክፍል ነው። “ፍሬያማ” ብዙ ፍሬ ያለው ማለት ነው። እነዚህ ቃሎች ምሳሌያዊ በሆነ ንግግር ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላሉ።

  • መጽሐፍ ቅዱስ፣ የሰውን ተግባርና ዐሳብ ለማመልከት፣ “ፍሬ” በሚለው ቃል ብዙ ጊዜ ይጠቀማል። ዛፍ ላይ ያለው ፍሬ ዛፉ ምን ዓይነት መሆኑን እንደሚያሳይ ሁሉ፣ የአንድ ሰው ቃልና ተግባርም የእርሱን ማንነት ያሳያሉ።
  • አንድ ሰው መልካም ወይም መጥፎ መንፈሳዊ ፍሬ ማፍራት ይችላል፤ ይሁን እንጂ፣ “ፍሬያማ” የሚለው ቃል ሁሌም የሚያመለክተው ብዙ መልካም ፍሬ መገኘቱን የሚያመለክተው አዎንታዊ ጎኑን ነው።
  • “ፍሬያማ” የሚለው ቃል በምሳሌያዊ መልኩ፣ “ባለጸጋ” ማለትም ይሆናል። ይህም ባለ ብዙ ሀብት ወይም ምግብ እንደ መሆን ሁሉ. ብዙ ልጆችና የልጅ ልጆች ያሉት መሆንን ይጨምራል።
  • አጠቃላይ በሆነ አነጋገር፣ “የ. . .ፍሬ” ከአንድ ሰው የሚመጣ ወይም ከእርሱ የሚገኝ ነገርን ያመለክታል። ለምሳሌ፣ “የጥበብ ፍሬ” ሲባል ጠቢብ በመሆን የተገኘ መልካም ነገርን ያመለክታል።
  • “የምድሪቱ ፍሬ” የሚለው ሐረግ ምድሪቱ የምታስገኘውን ሰዎች የሚመገቡትን በአጠቃላይ ያመለክታሉ። ይህም እንኳ እንደ ብርቱካን ወይም ማንጎ የመሳሰልቱን ፍሬዎች ብቻ ሳይሆን አትክልቶችን፣ ለውዝንና የእህል ዐይነቶችን ሁሉ ይጨምራል።
  • “የመንፈስ ፍሬ” የተሰኘው ምሳሌያዊ አነጋገር በሚታዘዙት ሰዎች ሕይወት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ የሚያስገኘው መንፈሳዊ ባሕርያት ያመለክታል።
  • “የማኅፀን ፍሬ” የሚለው ፈሊጣዊ ንግግር፣ “ከምኅፀን የሚገኘውን” ማለትም ልጆችን ያመለክታል።

ፍትወት

ፍትወት በጣም የጋለ ምኞት ሲሆን፣ ብዙውን ጊዜ ኀጢአት ወይም ግብረ ገባዊ ካልሆነ ነገር ፍላጎት ጋር ይያያዛል።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ፍትወት” ብዙውን ጊዜ የሚያመለክተው ከትዳር ጓደኛ ውጪ ግብረ ሥጋ ግንኙነት የማድረግ ፍላጎትን ነው።
  • አንዳንዴ ከጣዖት አምልኮ ጋር በተያያዘ ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።
  • እንዲህ ያለው፣ “ትክክል ያልሆነ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፍላጎት” ወይም፣ “ኀጢአት የማድረግ ጽኑ ፍላጎት” ተብሎ መተርጎም ይችላል።

ፍየል

ፍየል መጠነኛ ቁመት ያለው፣ ከበግ ጋር የሚመሳሰልና በዋነኛነት ደረጃ ወተትና ሥጋ ለማግኘት ሰዎች የሚያረቡት ባለ አራት እግር እንስሳ ነው። የፍየል ግልገል “ወጠጤ” ይባላል።

  • እንደ ብጎች ሁሉ ፍየሎችም መሥዋዕት ይቀርቡ ነበር፤ በተለይም ለመሥዋዕት የሚፍለጉት በፋሲካ በዓል ነበር።
  • ምንም እንኳ ፍየሎች ከበጎች ጋር ቢመሳሰሉም በግልጽ የሚታዩ ጥቂት ልዩነቶችም አሏቸው።
  • ፍየሎች ጥቁርና ሻካራ ጠጉር አላቸው፤ የበጎች ጠጉር ግን ሱፍ ልብስ ይሠራበታል።
  • የፍየል ጭራ ወደ ላይ የቆመ ሲሆን የበግ ጭራ ግን የተንጠለጠለ ነው።
  • ፍየሎች ጉጉ ስለሆኑ፣ ሌሎች ፍየሎች ባሉበት ቦታ አይሆኑም ወይም ሌሎች በሚሄዱበት አይሄዱም፤ በጎች ግን ከሌሎች በጎች ጋር አብረው መሆን ምቾት ይሰጣቸዋል፤ እረኛውን የመከተል ባሕርይም አላቸው።
  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ፍየሎች በእስራኤል በዋናነት ደረጃ ወተት የሚገኘው ከፍየሎች ነበር።
  • የፍየሎች ቆዳ ድንኳን የወይን ጠጅ የሚያዝበት ስልቻ መመሥሪያ ያገለግል ነበር።
  • በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ፍየሎች የኀጢአተኞች ምሳሌ ተደርገው ይቀርቡ ነበር፤ ምናልባትም ለዚህ ምክንያቱ ፍየሎች ከሚጠቃቸው ሰው የመኮብለል ብርቱ ዝንባሌ ስላላቸው ሊሆን ይችላል።
  • እስራኤላውያን ፍየሎችን እንደ የኀጢአት ተሸካሚ ምሳሌ ያደርጓቸው ነበር።

ፍጡር

“ፍጡር” ሰዎችንና እንስሳትን ጨምሮ እግዚአብሔር የፈጠረውን ሕያው ነገር ሁሉ ያመለክታል።

  • ነቢዩ ሕዝቅኤል በራእይ የእግዚአብሔርን ክብር ሲያይ አራት፣ “ሕያዋን ፍጡራን” ማየቱን ይናገራል። በትክክል ምንነታቸውን መረዳት ባለ መቻሉ ነበር ይህን ስም የሰጣቸው።
  • ሕይወት ያላቸውንና ሕይወት የሌላቸውን ነገሮች (መሬትን፣ ባሕርንና ከዋክብትን) ጨምሮ እግዚአብሔር የፈጠራቸው የተለያዩ ነገሮችን ስለሚያካትት፣ “ፍጥረት” የሚለው ቃል የተለየ ትርጕም ሊኖረው እንደሚችል ልብ ማድረግ ይኖርብናል። “ፍጡር” ሕይወት ያላቸው ነገሮችን ብቻ ነው የሚያመለክተው።

ፍጹም

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ፍጹም” የሚለው ቃል በክርስትና ሕይወታችን አስተዋዮችን በሳሎች ሆኖ መገኘትን ነው። አንዳንዴ “ፍጹም” የሚለው ቃል የተሟላና እንከን የሌለበት እስኪሆን ድረስ በክርስትና ሕይወት ማደግ ማለትም ይሆናል።

  • አንድ ክርስቲያን ፍጹምና በሳል ሆነ ሲባል ታዛዥ፣ ኀጢአት የሌለው ሆነ ማለት ነው።
  • “ፍጹም” – “የተሟላ” ወይም፣ “ሙሉ” መሆን ማለትም ይሆናል።
  • በመከራ መጽናት፣ አማኙ ውስጥ ሙሉነትንና ብስለትን እንደሚያስገኝ አዲስ ኪዳን ውስጥ ያለው የያዕቆብ መልእክት ይናገራል።
  • ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን ሲያጠኑና ለቃሉ ሲታዘዙ በባሕርያቸው ውስጥ ክርስቶስን እየመሰሉ ስለሚሄዱ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ሙሉና በሳሎች ይሆናሉ።