“ሁሉን ቻይ” የሚለው ቃል በቃል “ኃይል ሁሉ የእርሱ የሆነ” ማለት ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁሉም የሚያመልክተው እግዚኣብሔርን ነው።
ይህ አገላለጽ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሰጠውን ተስፋ ለመፈጸም ታማኝ መሆኑን ነው።
“ሊቀ ካህን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የተቀሩት እስራኤላውያን ካህናት መሪ በመሆን ለአንድ ዓመት እንዲያገለግል የተሾመ የተለየ ካህንን ያመለክታል።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ልብ የሰውን ሐሳብ፣ ስሜት፣ ፍላጎት ወም ፈቃድ ለማመልከት ብዙውን ጊዜ በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።
“ልዑል እግዚአብሔር” ከእግዚአብሔር መጠሪያዎች አንዱ ሲሆን፣ የእርሱን ታላቅነትና ሥልጣን ያመለክታል።
“ልጅ” የሚለው ቃል ከወላጆቹ ጋር ካለው ግንኙነት አንፃር ትንሽ ልጅን ወይም ሰውን ያመለክታል። የአንድ ሰው ወንድ ወይም ሴት ልጅ ወይም እንደ ልጅ የተቀበለውን ሰው ያመለክታል
“ልጅነት” የተሰኘው ቃል አንድን ሰው በተፈጥሮ ወላጆቹ ያልሆኑ ሰዎች ሕጋዊ ልጅ የማድረግ ሂደት ያመለክታል።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ልጅ” የሚለው ቃል ሕፃንን ጨምሮ በአጠቃላይ በዕድሜ ወጣት የሆነውን ያመለክታል። “ልጆች” የብዙ ቊጥር ሲሆን፣ ጥቂት ምሳሌያዊ ጠቀሜታዎችም አሉት።
ይህ አባባል መንፈሳዊ ልጆች የሆኑ ሰዎችንም ያመለክታል። ለምሳሌ፣ “የእግዚአብሔር ልጆች” ሲባል በኢየሱስ በማመን የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎችን ያመለክታል።
ሐሰተኛ አምላክ በአንዱ እውነተኛ አምላክ ቦታ ሰዎች የሚያመልኩት ነገር ነው። ወንድ ጣዖት እንዳለ ሁሉ ሴት ጥዖትም አለች።
ሐዋርያት ስለ እግዚአበሔር ስለ መንግሥቱ ለሰዎች እንዲሰበኩ እየሱስ የላካቸው ሰዎች ነበሩ፤ሐዋርያነት የሚለው ቃል ሐዋርያነት ለመሆን የተመረጡ ሰወች የነበራቸውን ቦታና ስልጣን ያመለክታል።
ሞትንና ሰዎች ሲሞቱ የሚሄዱበትን ቦታ ለማመልከትት “ሐዴስ” እና “ሲኦል” የተሰኙት ቃሎች ጥቅም ላይ ውለዋል። የሁለቱም ትርጕም ተመሳሳይ ነው።
እነዚህ ቃሎች ሁሉ የሚመለከቱት በሕይወት መሆንን፣ አለመሞትን ነው። መንፈሳዊ ሕያውነትን ለማመልከትም ጥቅም ላይ ይውላሉ። “ሥጋዊ ሕይወት” እና፣ “መንፈሳዊ ሕይወት” ሁለቱም ሕይወት ቢሆኑም፣ አንዱ ጊዜያዊ ሌላው ግን ዘላለማዊ ነው።
እነዚህ ቃሎች ሁሉ እስራኤላውያን እንደታዘዟቸው እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ትእዝዞችና ትምህሮች የሚያመልክቱ ናቸው። “ሕጉ” እና፣ “የእግዚአብሔር ሕግ” የተሰኙት በአጠቃላይ እግዚአብሔር ሕዝቡ እንዲታዘዙ የሚፈልጋቸው ማንኛውንም ነገር ያመለክታሉ።
መለኮት የሚለው ቃል ከእግዚአብሔር የሆነ ማንኛውንም ነገር ይመለከታል። ይህ ቃል ጥቅም ላይ ከሚውልባቸው መንገዶች ጥቂቶቹ “መለኮታዊ ሥልጣን”፣ “መለኮታዊ ፍርድ”፣ “መለኮታዊ ባሕርይ”፣ “መለኮታዊ ኃይል” እና፣ “መለኮታዊ ክብር የተሰኙት ናቸው።
መለየት አንድን ነገር ወይም ሰው እግዚአብሔርን እንዲያገለግል መመደብ ማለት ነው። በዚህ መልኩ የተለየ ሰው ወይም እቃ ለእግዚአብሔር እንደ ተቀደሰና እንደ ተለየ ይቆጠራል።
“መለየት” የሚለው ቃል አንድ ዓላማን ለመፈጸም ከአንድ ነገር ተለይቶ መውጣትን ያመለክታል
መልአክ በእግዚአብሔር የተፈጠረ ሃያል መንፈዊ ፍጡር ነው፤መላአኮች የተፈጥጠሩት እርሱ የሚነግራቸውን በማድረግ እግዚአብሔርን እንድያገለግሉ ነው፤የመላክት አለቃ ሌሎች መላአኮችን ሁሉ የሚያዝዝ ወይም የ መልአክን ያመለክታል።
ለሰወች ሲናገር በመልአክ ተመስሎ የመጣ ራሱ እግዚአብሔር ሊያመለክት ይችላል፤አንድ መልአክ ያህዌ ራሱ የተናገረ ያህል’’እኔ’’እያለ የተናገረው ለምን እንደ ነበር ከእነዚህ ትርጉሞች አንዱ በቂ ገለጻ ይሰጠን ይሆናል።
“መልካም” የሚለው ቃል እንደ ምንባቡ ዐውድ ሁኔታ የተለያዩ ትርጕሞች ይኖሩታል። እነዚህን የተለያዩ ቃሎች ለመተርጎም የተለያዩ ቋንቋዎች የተለያዩ ትርጕሞች ያቀርባሉ።
“መመለስ” እና፣ “መታደስ” አንድን ነገር ቀድሞ ወደ ነበረበት ቦታ፣ ወደ ተሻለ ሁኔታ መመለስ ማለት ነው።
መመስከር አንድ ነገር እውነት መሆኑን መቀበል ወይም መናገር ማለት ነው። “ምስክርነት” አንድ ነገር እውነት መሆኑን በቃል ወይም በጽሑፍ በዚያም መስማማት ማለት ነው።
“መመካት” በሰዎች ወይም በነገሮች በመመካት በትዕቢት መናገር ማለት ነው። ብዙውን ጊዜ ስለ አራስ በእብሪት መናገር ማለት ነው።
“መማለጃ” እና፣ “ምልጃ” በሌሎች ስፍራ ሆኖ ስለ እነርሱ መለመን ወይም መጸለይን ያመለክታል። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይህ ቃል ጥቅም ላይ የዋለው ስለሌሎች ከመጸለይ ጋር ነው።
መሠዊያ ለእግዚአብሔር መባ(ስጦታ)እንዲሆን እስራኤላውያን እንስሳትና የእህል ዓይነቶችን የሚያቃጥልበት ከፍ ብሎ የሚሠራ ነገር ነው።
“መርሳት” አንድን ሰው ወይም አንድን ነገር ጨርሶ መተው ማለት ነው። “የተረሳ” በሌላው ወገን ጨርሶ የተተወ ግምት ውስጥ የማይገባ ሰው ነው።
“መርገም” አንድ ሰው ወይም አንድ ነገር ላይ መጥፎ ነገር እንዲደርስበት ማድረግ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን መስቀል አንድ ቀጥ ብሎ የወጣ እንጨት ሲሆን ጫፉ አካባቢ አንድ ሌላ ግንድ ይጋደምበት ነበር።
“መስቀል” ማለት አንድን ሰው መስቀል ላይ ማሰርና በታላቅ ሕመምና ስቃይ እስኪሞት ድረስ እዚያው መተው ማለት ነው።
መሾም እና የተሾመ የተሰኙት ቃላት አንድ የተለየ ተግባርን ወይም ተልኮን እንዲሁም አንድን ሰው መምረጥን ያመለክታል።
እንዲቀበሉ ተመርጠዋል ማለት ነው።
መቀደስ፣ ቅዱስ ይሆን ዘንድ አንድን ነገር መለየት ማለት ነው። ቅድስና ቅዱስ የመሆን ሂደት ነው
“መቀባት” የሚለው ቃል ሰውን ወይም አንድን ነገር በ ማሰብ ወይም ላይ ላይ ዘይት ማፍሰስ ማለት ነው፤አንዳንዴ ዘይቱ ከተለዩ ቅመሞች ጋር ስለሚቀላቀል በጣም ጣፋጭ መዕዛ ያለው ሽቶ ይሆናል፤ቃሉ ምሳሌያዊ በሆነ መንገድ መንፈስ ቅዱስ ሰው መምረጡንና ሃይል ማስታጠቁን ያመለክታል።
አንድ ሰው ወይም አንድ ነገር፣ “መባረክ” በዚያ ሰው ወይም ነገር ላይ መልካምና ጠቃሚ ነገር እንዲሆን ማድረግ ማለት ነው።
“መተላለፍ” ትእዛዝን፣ ደንብን ወይም ሕግን ማፍረስ ማለት ነው።
“መታመን” አንድ ሰው ወይም አንድ ነገር እውነት ወይም እምነት ሊጣልበት የሚገባ መሆኑን ያመለክታል። “ታማኝ” ሰው ትክክልና እውነት የሆነ ነገር እንደሚያደርግና እንደሚናገር እምነት ይጣልበታል።
መቶ አለቃ ከእርሱ ሥር 100 ወታደሮች የነበሩት የሮም ሰራዊት ባለ ሥልጣን ነበር።
መና ከግብፅ ከወቱ በኋላ እስራኤል በምድረ በዳ ይንከራተቱ በነበሩ ጊዜ እግዚአብሔር የሰጣቸው እንጀራ የመሰለ ስስ ምግብ ነበር።
እነዚህ ሦስት ቃሎች የሚያመለክቱት እርሱ ራሱ እግዚአብሔር የሆነው መንፈስ ቅዱስን ነው። እውነተኛው አንድ አምላክ አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ የሚባሉ አካላት አሉት።
“መንፈስ” የሚለው ቃል የሰዎችን ቁሳዊ ያልሆነና የማይታይ ክፍል ያመለክታል። ሰው ሲሞት መንፈሱ ከአካሉ ይለያያል
“መኮነን” እና “ኵነኔ” አንዳች በደል ከመፈጸሙ የተነሣ ሌላው ላይ መፍረድን ያመለክታል።
“መወሰን” እና፣ “የተወሰነ” የተሰኙት ቃሎች አንድ ነገር ከመሆኑ በፊት እንደዚያ እንዲሆን መቁረጥን ወይም ማቀድን ያመለክታሉ።
መንጠቅ፣ ንጥቂያ “መንጠቅ” የሚያመለክተው አንድን ነገር፣ ብዙውን ጊዜ ደግሞ ለምግብ የሚሆን እንስሳን ማደንን ነው።
“መዋጀት” የሚለው ቃል በሌሎች ተወስዶ የነበረ ነገርን በመግዛት የራስ ማድረግ ማለት ነው።
“መውረስ” እና፣ “ውርስ” ከእነርሱ ጋር ካለ የተለየ መቀራረብ የተነሣ ከወላጆቹ ወይም ከሌሎች ጠቃሚ ነገር መቀበል ማለት ነው። ያንን ውርስ የሚቀበል ወራሽ ይባላል።
መዓት ለረጅም ጊዜ የሚቆይ በጣም ከባድ ቁጣ ነው። ብዙውን ጊዜ ኀጢአት ላይ የሚመጣውን የእግዚአብሔር ጻድቅ ፍርድና በእርሱ ላይ የሚያምፁ ሰዎችን ቅጣት ያመለክታል።
ቅዱስ ዝማሬ፣ ብዙ ጊዜ በሙዚቃ የታጀበ ግጥም ወይም ቅኔ ማለት ነው። ብሉይ ኪዳን ውስጥ ያለው መጽሐፈ መዝሙር በእስራኤላውያን የተጻፉ የመዝሙሮች ስብስብ ይዟል።
“መግረዝ” ከወንድ ወይም ወንድ ከሆነ ትንሽ ልጅ ብልት ትርፍ የሆነውን ቆዳ መቊረጥ ማለት ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ የግርዘት ሥርዓት ሊኖርም ይችላል።
መገናኛ ድንኳን እስራኤላውያን 40 ዓመት በምድረ በዳ በነበሩ ጊዜ እግዚአብሔር የሚያመልኩበት ድንኳን መሰል ነገር ነበር
“መግለጽ” አንድ ነገር እንዲታወቅ ማድረግ ማለት ነው “መገለጽ” እንዲታወቅ የተደረገ ነገር ነው።
“መጣስ” ሕግ ማፍረስ ወይም የሌሎችን መብት መንካት ማለት ነው።
“መጥራት” እና “መጣራት” የተሰኙ ቃሎች ቅርብ ላልነበረ ሰው ጮኽ ብሎ አንዳች ነገር መናገር ማለት ነው። ሌሎች ምሳሌያዊ ትርጕሞችም አሏቸው።
“መጥፋት” የሚለው ቃል አብዛኛውን ጊዜ በአንድ ዓይነት ጥቃት ወይም አደጋ የተነሣ መሞት ወይም መደምሰስ ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተለይ ለዘላለም በገሃነም መቀጣት የሚል ትርጕም አለው።
መጸለይ ለእግዚአብሔር መናገር ነው።
መፈተን አንድ ሰው ተገቢ ያልሆነ ነገር እንዲያደርግ መሞከር ማለት ነው።
“መፈጸም” አንዳች የሚጠበቅ ነገርን ፈጽሞ ወይም አከናውኖ መገኘት ማለት ነው።
“ማመን” እና “አመነ” በጣም የተያያዙ ቢሆንም በመጠኑ የሚለያይ ትርጉም አላቸው
“ማምለክ፣ መስገድ” እግዚአብሔርን ማክበር፣ ማመስገንና ለእርሱ መታዘዝ ማለት ነው።
“ማሰር” አንድን ነገር ጥብቅ አድርጎ ማሰር ወይም እንዳይበታተን አድርጎ መቋጠር ማለት ነው። አንድ ነገር የሚያስር ወይም እርስ በርስ የሚያያይዝ፣ “ማሰሪያ” ይባላል።
“ማስተሰረያ” የሚለው ቃል የእግዚአብሔርን ፍትሕ ለማርካት ወይም ለመፈጸምና ቁጣውን ለማስታገሥ የሚቀርብ መሥዋዕት ነው።
“ማስታረቅ” እና፣ “ዕርቅ” ቀድሞ እርስ በርስ ይጠላሉ በነበሩ ሰዎች መካከል፣ “ሰላም ማድረግ” ማለት ነው።
“ማበረታታት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሰዎች ትክክልና እውነት የሆነውን ነገር እንዲያደርጉ ማደፋፈርን ነው።
ማዘዝ ማለት አንዳች ነገርን እንዲያደርጉ ወይም እንዳያደርጉ ለሰዎች መናገር ማለት ነው። ትእዛዝ የሚባለው እንዲያደርጉ ወይም እንዳያደርጉ ለሰዎች የተሰጠው መመሪያ ነው።
“ማዳን” አንድን ሰው ከአንዳች መጥፎ ወይም ጎጂ ነገር መጠበቅ ማለት ነው “ደኅንነት” ከጉዳት ወይም ከአደጋ የተጠበቀ ማለት ነው
አዲስ ኪዳን ውስጥ “ማጥመቅ” እና፥ “ጥምቀት” የተሰኙ ቃሎች ብዙውን ጊዜ ከኃጢአት መንጻቱንና ከክርስቶስ ጋር መተባበሩን ለማሳየት ክርስቲያኑን ውሃ ውስጥ የመንከር ስርዓትን ያመለክታል
ምልክት የተለየ ትርጉም ያለው መልእክት የሚያስተላልፍ ዕቃ፣ ሁኔታ ወይም ድርጊት ሊሆን ይችላል
“ምሕረት” እና፣ “መሐሪ” የተሰኙት ቃሎች ችግር ውስጥ በተለይም እጅግ በተዋረደ ዝቅረኛ ደረጃ ያሉ ሰዎችን መርዳትን ያመለክታሉ።
ምሳሌ ግብረ ገባዊ ወይም ሃይማኖታዊ ትምህርት ለማስተማር የሚቀርብ አጭር ታሪክ ነው።
“ምስክር” እና፣ “መመስከር” አንድን ነገር በተመለከተ የሚያውቁትን እውነት በግልጽና በሰው ሁሉ ፊት መናገር ማለት ነው።
ምኩራብ አይሁድ እግዚአብሔርን ለማምለክ የሚሰበሰቡበት ቦታ ነው። ከጥንት ዘመን ጀምሮ ምኩራቦች ለጸሎት፣ ቅዱሳት መጽሐፍትን ለማንበብና ለመማር አገልግሎት ላይ ውለው ነበር
“ሞኝ” የሚባለው ብዙውን ጊዜ የተሳሳተ ምርጫ የሚያደርግ በተለይም አለመታዘዝን የሚመርጥ ሰው ነው። “ሞኝነት” ማስተዋል የሌለው ሰው ወይም ፀባይ የሚገለጥበት መንገድ ነው።
ሞገስ እርሱን በተመለከተ ጥሩ አመለካከት ያለንን ሰው ለመጥቀም የሚደረግ ነገርን ያመለክታለ። “ሞገስ ያለው” ነገር ቀና ተቀባይነት ያለው ወይም ጠቃሚ ነው።
“ሥልጣን” የተሰኘው ቃል አንድ ሰው ሌላው ሰው ላይ ያለውን ተፅዕኖ የማሳደር ወይም የመቆጣጠር ኅይልን ያመለክታል
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ሥራዎች”፣ “ተግባሮች” የተሰኙት ቃሎች ጥቅም ላይ የዋሉት እግዚአብሔር ወይም ሰዎች ያደረጉትን በአጠቃላይ ለማሳየት ነው።
“ሥርዓት” ለተወሰኑ ግብረ ገባዊ መመሪያዎች እንዲታዘዙ ሰዎችን መሠልጠንን ነው የሚያመለክተው።
መጽሐፍ ቅዱስ ሥጋ ሲል ቃል በቃል የሰውን ወይም የእንስሳን ለስላሳውን የአካል ክፍል ያመለክታል።
ቃል በቃል፣ “ረቢ” – “ጌታዬ” ወይም፣ “መምህሬ” ማለት ነው።
“ርኅራኄ” ለሰዎች ማሰብ፣ አተለይም መከራ ለደረሰባቸው ሰዎች እነርሱ ቦታ ሆኖ ስሜታቸውን መጋራትን ያመለክታል። “ርኅሩኅ” ሰው ለሌሎች ሰዎች ያስባል እነርሱንም ይረዳል።
“ርኩሰት” የሚለው ቃል ትርጉም፣ “ኀጢአት” ከሚለው ጋር በጣም ተመሳሳይ ቢሆንም በተለይ፣ ሆን ተብሎ የሚፈጸም በደልን ወይም ታላቅ ዐመፃን ሊያመለክት ይችላል።
“ሰማይ” ተብሎ የተተረጎመው ቃል የእግዚአብሔር መኖሪያን ያመለክታል።
ሰንበት የሳምንቱ ሰባተኛ ቀን ነው፤ ይህ ቀን ምንም ሥራ የማይሠራበት የዕረፍት ቀን እንዲሆን እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አዝዞ ነበር።
ዲያብሎስ እግዚአብሔር የፈጠረው መንፈሳዊ አካል ነበር፤ በእግዚአብሔር መማመፁ የእግዚአብሔር ጠላት ሆነ። ዲያብሎስ፣ “ሰይጣን” እና፣ “ክፉው” ተብሎ ይጠራል
ሰዱቃውያን ፖለቲካዊ ተሳትፎ ያላቸው የአይሁድ ካህናት ነበሩ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ባገለገለ ዘመን የነበረውን የሮም አገዛዝ ይደግፉ ነበር። በሙታን ትንሣኤ አያምኑም
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስም በተለያዩ ምሳሌያዊ አነጋገርና ጥቅም ላይ ውሏል።
ስእለት አንድ ሰው ለእግዚአብሔር የሚገባው ቃል ነው። እግዚአብሔርን ልዩ በሆነ ሁኔታ ለማክበር ወይም ም ያህል ለእርሱ የተሰጠ መሆኑን ለማሳየት አንድ ሰው አንድ ነገር እንደሚያደርግ ለእግዚአብሔር ቃል ይገባል።
መጽሐፍ ቁስ ውስጥ፣ “ስድብ” እግዚአብሔርንና ሰውን በጣም በሚያንቋሽሽ መንገድ መናገርግን ያመለክታል። አንድን ሰው፣ “መስደብ” ሰዎች ሐሰት የሆነ መጥፎ ነገር እንዲያስቡ በዚያ ሰው ላይ ክፉ ነገር መናገር ማለት ነው።
“ስጦታ” የሚለው ለሌላው ወገን የተሰጠ ማንኛውንም ነገር ያመለክታል። ስጦታ የሚሰጠው በምላሹ ምንም ነገር ባለ መጠበቅ ነው።
“ቀናተኛ” እና “ቅናት” የተሰኙት ቃሎች አንድ ሰው የግል የማድረግ ጽኑ ፍላጎት ያመለክታሉ። አንድን ነገር ወይም ንብረት አጥብቆ የመያዝ ፍላጎትንም ያመለክታል።
“ቀኝ እጅ” የሚለው ምሳሌያዊ አነጋገር፣ በአንድ መሪ፣ ወይም ሥልጣን ባለው ሰው ቀኝ ያለውን የክብር ቦታ ያመለክታል።
“ቅንዓት” እና፣ “ቀናተኛ” የአንድ ሰው ወይም ሐሰብ ጠንካራ ደጋፊ መሆንን ያመለክታል።
ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “ቅዱሳን” – “ቅዱስ የሆኑ ሰዎች” ማለት ሲሆን፣ በኢየሱስ ያመኑ ወገኖችን የመለክታል
“ቅዱሱ” የሚለው መጠሪያ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁሌም የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ነው።
“ቅዱስ ቦታ” ቃል በቃል እግዚአብሔር የሚቀደስበትና የሚመለክበት የተለይ ቦታ ማለት ነው። ከለላና ደኅንነት የሚገኝበትንም ቦታ ሊያመለክት ይችላል
“ቅዱስ” እና “ቅድስና” ኀጥእ ከሆነውና ፍጽምና ከሌለው ማንኛውም ነገር ፍጹም ልዩ የሚያደርገውን የእግዚአብሔርን ባሕርይ ያመለክታል።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ቅድስት” እና፣ “ቅድስተ ቅዱሳን” የተሰኙ ቃሎች መገናኛው ድንኳን ወይም ቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበሩ ሁለት ክፍሎች ያመለክታሉ። አንዳንዴ፣ “ቅድስት” ወይም፣ “ቅዱስ ቦታ” የሚለው በጠቅላላው ለእግዚአብሔር የለለየ ማንኛውንም ቦታ ያመለክታል።
“በመንፈስ ቅዱስ መሞላት” የሚለው አገላለጽ የእግዚአብሔር ፈቃድ ማድረግ እንዲችል መንፈስ ቅዱስ ለሰው የሚሰጠውን ኅይል የሚያመለክት ምሳሌያዊ አነጋገር ነው።
በግ ጥቅጥቅ ያሉ ለሱፍ መሥሪያ የሚያገለግሉ ጠጉሮች ያሉት ባለ አራት እግር እንስሳ ሲሆን፣ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ይቀርባል። እርሱ ለሕዝቡ ኃጢአት መሥዋዕት ሆኖ በመሞቱ ኢየሱስ፣ “የእግዚአብሔር በግ” ተብሏል።
ቤተ መቅደስ እስራኤል ለጸሎትና ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ለማቅረብ የሚሰበሰቡበት ዙሪያውን በተከበበ አደባባይ ውስጥ ያለ ሕንፃ ነው። ቤተ መቅደስ የነበረው ኢየሩሳሌም ከተማ ውስጥ ባለው የሞሪያ ተራራ ነበር።
በአዲስ ኪዳን መሠረት ቤተ ክርስቲያን የሚባለው ለመጸለይና የእግዚአብሔር ቃል ሲሰበክ ለመስማት ዘወትር የሚሰበሰቡ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምኑ ሰዎች ስብስብ ነው። “ቤተ ክርስቲያን” ብዙውን ጊዜ፣ ክርስቲያኖችን ሁሉ ያመለክታል።
“ቤዛ” የሚለው ቃል በምርኮ የተያዘ ሰውን ለማስለቀቅ እንዲከፈል የተጠየቀ ገንዘብ ወይም ሌላ ነገር ያመለክታል።
“ቤዛ” እና “ቤዛነት” ለሰው ልጆች ኃጢአት የሚከፈልና የእርሱን በኃጢአት መቆጣት የሚያበርድ መሥዋዕት እግዚአብሔር ያዘጋጀበትን ሁኔታ ያመለክታል
ተስፋ አንድ መልካም ነገር ይሆናል ብሎ መጠበቅና የተሻለ ነገር እንደሚመጣ መጠባበቅ ማለት ነው። ብዙውን ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት “ተስፋ” እግዚአብሔር ለሕዝቡ ቃል የገባውን እንደሚቀበሉ እርግጠኛ ሆ መጠበቅን ነው የሚያመለክተው። ይሁን እንጂ፣ አንድን ነገር እርግጠኛ ሆኖ ወይም በልበ ሙሉነት መጠበቅን የሚያመለክት በመሆኑ ULB በተሰኘው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጕም አብዛኛውን ጊዜ፣ “እምነት” ወይም፣ “ድፍረት” ተብሎ ተተርጕሞአል።
ተስፋ ቃል አንድን ነገር ለመስጠት ወይም ለማድረግ ቃል መግባት ማለት ነው። አንድ ሰው አንድ ነገር ለማድረግ ተስፋ ከሰጠ ያንን ለመፈጸም ይተጋል ማለት ነው።
“ተአምር”እግዚአብሔር ራሱ ካላደረገው በቀር ጨርሶ ሊሆን የማይችል አስደናቂ ነገር ነው።
ለእግዚአብሔር፣ “ታማኝ” መሆን ዘወትር በእርሱ ትምህርት መኖር ማለት ነው። ለእርሱ በመታዘዝ እውነተኛነትን ማሳየት ማለት ነው ታማኝ ሆኖ የመገኘት ሁኔታ፣ “ታማኝነት” ይባላል።
ትሑት ሰው ከሌሎች ሁሉ የበለጠ እንደ ሆነ አያስብም። ትዕቢተኛ ወይም እብሪተኛ አይደለም።
ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “ትሩፋን” ማለት፣ በጣም ብዙ ከሆነው ክፍል ወይም ወገን “የተረፉ” ወይም፣ “የቀሩ” ሰዎች ወይም ነገሮች ማለት ነው።
“ትንሣኤ” ከሞት በኋላ ተመልሶ ወደ ሕይወት መምጣት ነው።
እነዚህ ቃሎች የሚያመለክቱት በእግዝአብሔር ቃል መሠረት ሰዎችን በአግባቡ መያዝን ወይም ማስተናገድን ነው። ትክክል የሆነውን የእግዚአብሔር መስፈርት የሚያንጸባርቁ የሰው ልጆች ሕጎችም ፍትሕ ይባላሉ።
“ኀይል” የሚለው ቃል የሚያመለክተው አብዛኛውን ጊዜ በታላቅ ብርታት ነገሮችን ማድረግን ወይም ነገሮች እንዲሆኑ የማድረግ ችሎታን ነው። “ኀይላት” የሚያመለክተው ነገሮች እንዲሆኑ የማድረግ ታላቅ ችሎታ ያላቸው ሰዎችን ወይም መናፍስትን ነው።
ኅሊና አንድ ሰው ኃጢአት እያደረገ መሆኑን እግዚአብሔር ለእርሱ የሚያሳውቅበት የሰውየው አስተሳሰብ አንድ ክፍል ነው።
አጠቃላይ በሆነ ደረጃ፣ “ኅብረት” ተመሳሳይ ፍላጎትና ልምምድ ያላቸው የአንድ ማኅበር አባሎች መካከል የሚደረግ የወዳጅነት ግንኙነትን ያመለክታል።
“ኅጢአት” የሚለው ቃል ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር የሚደረግ ተግባርን፣ ሐሳብንና ቃልን ያመለክታል። እግዚአብሔር ያዘዘውን አለማድረግም ኅጢአት ነው
“ነቀፋ የሌለበት” የሚለው ቃል በቃል፣ “ነውር፣ እንከን” የሌለበት ማለት ነው። በፍጹም ልቡ ለእግዚአብሔር የሚታዘዝ ሰውን የሚያመለክት ቢሆንም፣ ያ ሰው ምንም ኃጢአት የለበትም ማለት አይደለም።
“ነቢይ” የእግዚአብሔርን መልእክት ለሰዎች የሚናገር ሰው ነው። ይህን የምታደርግ ሴት ነቢዪት ትባላለች።
“ነጻ” የሚለው ቃል ወንጀል ከመፈጸም ወይም ከሌሎች በደሎች ነጻ የሆነ ማለት ነው። በጠቅላላው በማንኛውም ክፉ ነገር አለመሳተፉን ያመለክታል።
ነፍስ የሰው ውስጣዊ፣ የማይታይና ዘላለማዊ ክፍል ነው። የሰውን ቁሳዊ ያልሆነ ነገር ሁሉ ይጨምራል
ናዝራዊ የሚባለው ናዝርውያን የሚሳሉትን ስእለት የተሳለ ሰው ነው።
“ንስሐ መግባት” እና፣ “ንስሐ” ከኀጢአት ወደ እግዚአብሔር መመለስን ያመለክታል።
“ንጹሕ” መሆን እንከን የሌለው ወይም እዚይ ኣመገኘት ያልነበረበት የተቀላቀለ ነገር የሌለው ማለት ነው። አንድን ነገር ማንጻት ማለት ንጹሕ ማድረግና የሚያቆሽሸውንና የሚበክለውን ማንኛውንም ነገር ማስወገድ ማለት ነው።
ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “ንጹሕ” ምንም ቆሻሻ ወይም እድፍ የሌለበት ማለት ነው። ብዙውን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ቅዱስ” እና “ከኃጢአት የነጻ” የሚሉትን ለማመልከት በምሳሌያዊ አነጋገር ጥቅም ላይ ይውላል።
አሕዛብ የያዕቆብ ወይም የአሥራ ሁለቱ የእርሱ ልጆች ዘር ያልሆነ ሰው ነው። ስለሆነም አሕዛብ አይሁድ አይድለም ማለት ነው።
“አሜን” የሚለውለንድ ሰው የተናገረውን አጽንዖት ለመስጠት ወይም ትኩረት እንዲሰጠው ለማድረግ ጥቅም ላይ የሚውል ቃል ነው። ኢያሱስ ይህን ቃል ሲናገር ብዙውን ጊዜ አሜን ይሁን እንደ ማለት ነው።
“አምላካዊ” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን በሚያስከብርና የእግዚአብሔርን ማንነት በሚያሳይ መንገድ የሚኖር ሰውን ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላል። የእግዚአብሔርን ፈቃድ በማድረግ እርሱን የማያከብር ሰው ባሕርይ አምላካዊነት ይባላል።
“አሥራ ሁለቱ” የቅርብ ደቀ መዛሙርቱ ወይም ሐዋርያቱ እንደሆኑ ኢየሱስ የመረጣቸው አሥራ ሁለት ሰዎች ናቸው። ይሁዳ ራሱን ከገደለ በኋላ፣ “አሥራ አንዱ ቀሩ።
“አካል” ቃል በቃል የሰው ወይም የእንስሳ ሥጋ ማለት ነው። ይህ ቃል አንድን ነገር ወይም በአንድ ቡድን ውስጥ ያሉ ግለ ሰቦችን ለማመልከትም ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።
አይሁድ በልጅ ልጁ በያዕቆብ በኩል የአብርሃም ዘር የሆኑ ሕዝብ ናቸው።
“አዳኝ” የሚለው ቃል ሌሎችን የሚያድን ወይም የሚታደግ ሰውን ያመለክታል። ለሌሎች ብርታትን ወይም የሚያስፈልጋቸውን የሚሰጥ ሰውንም ያመለክታል
በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት “አገልጋይ” እና፣ “አገልግሎት” የተሰኙት ቃሎች እግዚአብሔርን በተመለከተ ሰዎችን በማስተማር፣ ለመንፈሳዊ ሕይወታቸውም በማሰብ ሌሎችን መርዳት ማለት ነው። በዚህ መልኩ ሰዎችን የሚረዳ ሰው አገልጋይ ይባላል።
አጋንንት ያደሩበት ሰው የሚያደርገውንና የሚያስበውን የሚቆጣጠሩ አጋንንት ወይም ክፉ መናፍሳት ውስጥ ይኖራሉ።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ኢየሱስ ማለት፣ “ያህዌ ያድናል” ማለት ነው። “ክርስቶስ” “የተቀባው” የሚል ትርጉም ያለው ቃል ሲሆን፣ መሲህ የሚለው ሌላ ቃል ነው።
ኤፉድ እስራኤላውያን ካህናት ይለብሱት የነበረ መጎናጸፊያ ዐይነት ጨርቅ ነው። ትከሻ ላይ የሚገናኙ የፊትና የኋላ የሚባሉ ሁለት ክፍሎች ነበሩት፤ ከዚያም በጨርቅ መታጠቂያ ወገብ ላይ ይታሰር ነበር።
በአጠቃላይ ደረጃ “እምነት” የሚያመለክተው በእግዚአብሔር፣ በሰው ወይም፣ በነገሮች መተማመንን፣ መደገፍን፣ ወይም፣ መመካትን ነው።
እምነት የለሽ፣ እምነት የለሽነት
እስራኤል እግዚአብሔር ለያዕቆብ የሰጠው ስም ነው። እስራኤል፣ “ከእግዚአብሔር ጋር ታገለ” ማለት ነው።
ኢየሱስ፣ “እንደ ገና መወለድ” በሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሰው እግዚአብሔር አንድን መንፈሳዊ ሙት የሆነ ሰው መንፈሳዊ ሕያው እንዲሆን እንደሚለውጠው ለማመልከት ነበር። “ከእግዚአብሔር መወለድ” ወይም፣ “ከመንፈስ መወለድ” የተሰኙትም ቃሎች አዲስ መንፈሳዊ ሕይወት የተሰጠውን ሰው ያመለክታሉ።
“እውነት” የሚለው ቃል ይተረጋገጠ ፅንሰ ሐሳብን፣ በትክክል የተፈጸመ ሁኔታንና በእርግጥ የተነገረ ቃልን ያመለክታል።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር አጽናፈ ዓለሙን ከምንም ያስገኘው ዘላለማዊ ፈጣሪን ያመለክታል። እግዚአብሔር አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ በሚባሉ ሦስት አካሎች ተገልጧል። የእግዚአብሔር ተፀውዖ (መጠሪያ) ስም፣ “ያህዌ” ነው።
“እግዚአብሔር አብ” እና፣ “ሰማያዊ አባት” የተሰኙት ቃሎች የሚያመለክቱት አንዱን እውነተኛ አምላክ ያህዌን ነው። ይህ ቃል በተለይም ኢየሱስ ሲጠቀምበት “አባት” ተብሎም ተጠርቷል።
ከርቤ ከተለየ ዐይነት ዛፍ ሙጫ የሚዘጋጅ ቅመም ነው።
ከፍ ማድረግ በከፍተኛ ደረጃ ማመስገንና ማክበር ማለት ነው። ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ማድረስንም ያመለክታል።
ኪዳን አንዱ ወይም ሁለቱም የሚፈጽሙት በሁለት ወገኖች መካከል የሚደረግ መደበኛ አሳሪ ስምምነት ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካህን ሕዝብን በመወከል ለእግዚአብሔር መሥዋዕት የሚያቀርብ ሰው ነው። “ክህነት” እንዲህ ላለው ሰው ተግባር የተሰጠ ስም ወይም ቦታ ነው።
ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከሄደ ጥቂት ጊዜ በኋላ ስዎች “ክርስቲያን” የሚለውን ስም አወጡ፤ ክርስቲያን የክርቶስ ተከታይ ማለት ነው።
“መሲሕ” ወይም፣ “ክርስቶስ” የሚለው ቃል፣ “የተቀባ” ማለት ሲሆን፣ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስን ነው የሚያመለክተው።
“ክብር” የሚለው ቃል ለእግዚአብሔር ወይም ለሰው ልጅ የሚሰጥ የላቀ ቦታ፣ ግምት ወይም አክብሮታዊ ፍርሃት ነው።
በአጠቃላይ “ክብር” ማለት ምስጋና፣ ውበትና የላቀ ታላቅነት ማለት ነው። ክብር ያለው ነገር “የከበረ” ይባላል።
“ክፉ” እና “ዐመጸኛ” የተሰኙት ቃሎች ሁለቱም የእግዚአብሔርን ቅዱስ ባሕርይና ፈቃድ የሚቃወም ማንኛውንም ነገር ያመለክታሉ።
ብዙውን ጊዜ ወንድም የሚባለው ቢያንስ ከወላጆች ከአንዱ የተወለደ ወንድ ልጅ ነው።
“ወንጌላዊ” የኢየሱስ ክርስቶስን የምሥራች(ወንጌል) ለሰዎች የሚናገር ሰው ነው።
“ወዮ” ከፍ ያለ ጭንቀትና ሐዘንን ያመለክታል። ስለሚመጣው ከባድ ጥፋት ማስጠንቀቂያም ይሆናል።
“ዋይታ” እና፣ “ሰቆቃ” የተሰኙት ቃሎች የከባድ ለቅሶ፣ ሕዘን ወይም ትኬ መገለጫዎች ናቸው።
ብዙውን ጊዜ፣ “ዓለም” የሚያመለክተው አጽናፈ ዓለሙ ውስጥ ሰዎች የሚኖሩበትን ማለትንን ማለትን ምድርን ነው። “ዓለማዊ” በዚህ ዓለም የሚኖሩ ሰዎችን ክፉ መንገድና አሠራር ያመለክታል።
“ዕብራውያን” በይስሐቅና በያዕቆብ ዘር ሐረግ በኩል የተገኙ የአብርሃም ዘሮች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ዕብራዊ” ተብሎ የተጠራ የመጀመሪያ ሰው አብርሃም ነበር። “ዕብራውያን” በይስሐቅና በያዕቆብ ዘር ሐረግ በኩል የአብርሃም ዘር የሆኑ ሕዝብ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ዕብራው” ተብሎ የተጠራ የመጀመሪያ ሰው አብርሃም ነው።
“ዘላለም” እና “ዘላለማዊ” በጣም ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን፣ የሚያመለክቱት ሁሌም የሚኖር ወይም ማለቂያ ማብቂያ የሌለውን ነገር ወይም ሁኔታ ነው።
“ዝሙት” አንድ ያገባ ሰው የትዳር ጓደኛው ካልሆነች ጋር ግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸምን ኃጢአት ያመለክታል። “ዘማዊነት”የዚህ ዐይነት ተግባርን ወይም ይህን ኃጢያት የሚያደርግ ሰው ድትጊት ያመለክታል።
“የመወለድ መብት” የተሰኘው ቃል ከቤተ ሰቡ የተወለዱ የመጀመሪያ ወንድ ልጅ ያለውን ክብር፣ ከቤተ ሰቡ መጠራትንና ሀብት መወሰድን መደበኛ መብት ያመለክታል።
“የመጨረሻ ቀን” ወይም፣ “የመጨረሻዎቹ ቀኖች” በአጠቃላይ የሚያመለክቱት በአጠቃላይ ኢየሱስ ወደሚመለስበት ጊዜ የሚያደርሱ ወቅቶች ናቸው።
“የሚገባው” የሚለው ቃል ክብርና ምስጋና መቀበል ያለበትን ያመለክታል። “ዋጋ ያለው” ውድ ወይም ጠቃሚ ነገርን ያመለክታል። “ዋጋ ቢስ” ግን ለምንም የማይጠቅም ማለት ነው።
“የማእዘን ድንጋይ” የሚለው ሐረግ ልዩ በሆነ ሁኔታ ተጠርቦ የሕንጻው መሠረት አንድ ጥግ ላይ የሚቀመጥ ትልቅ ድንጋይ ነው።
ቃል በቃል የምሥራች ማለት ሲሆን፣ ሰዎችን የሚጠቅምና ደስ የሚያሰኛቸውን መልእክት ያመለክታል።
“የሰራዊት ጌታ ያህዌ” እና፣ “የሰራዊት ጌታ” የሚሉት ሐረጎች ለእርሱ በሚታዘዙ እጅግ ብዙ መላእክት ላይ እግዚአብሔር ያለውን ሥልጣን የሚገልጡ አባባሎች ናቸው።
የሰው ልጅ“የሰው ልጅ” የሚለው ሐረግ ብዙ ጊዜ ኢየሱስ ራሱን የሚጠራበት ስም ነበር። ብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ “የሰው ልጅ” ማንኛውም ሰው የሚታወቅበት ስም ነበር
ጥቅሶች እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን ያመለክታሉ
“የስርየት መክደኛ” ከወርቅ የተሠራ ጠፍጣፋ ነገር ሲሆን የታቦቱን የላይኛ ክፍል ለመሸፈን ጥቅም ላይ ይውል ነበር። አንዳንድ ትርጉሞች “የስርየት መሸፈኛ” ይሉታል
“በደል” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ኀጢአት ማድረግን ወይም ወንጀል መፈጸምን ነው።
“የተመረጠ” ወይም፣ “ምርጦች” የሚለው ቃል በቃል፣ “የተመረጡት” ወይም፣ “የተመረጠ ሕዝብ” ማለት ሲሆን አባባሉ የእርሱ ሕዝብ እንደሆኑ እግዚአብሔር የመደባቸውን ወይም የመረጣቸውን ያመልክታል። “የተመረጡ” ወይም፣ “በእግዚአብሔር የተመረጠው፣ የተመረጠ መሲሕ የሆነው የኢየሱስ መጠሪያ ነው።
“የተስፋ ምድር” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች እንጂ በጠቅላላው መጽሐፍ ቅዱስ አይደለም። ለአብርሃምና ለዘሮቹ እንደሚሰጥ እግዚአብሔር ቃል የገባላት የምድረ ከነዓን አማራጭ ቃል ነው።
ነቢይ፣ ትንቢት፣ ትንቢት ተናገረ፣ ተመልካች፣ ነቢዪት “ነቢይ” የእግዚአብሔርን መልእክት ለሰዎች የሚናገር ሰው ነው። ይህን የምታደርግ ሴት ነቢዪት ትባላለች።
“የተወደደ” በሌላው ሰው የተወደደና ውድ የሆነ ሰውን የሚያሳይ የፍቅር መገለጫ ቃል ነው
የአራተኛው ክፍል ገዥ የሚባለው የሮም መንግሥትን የተወሰነ ክፍል በመግዛት ላይ ያለ ባለ ሥልጣንን ነው። እያንዳንዱ የአራተኛው ክፍል ገዥ ከሮም ንጉሥ ሥልጣን ሥር ነበር።
“የእግዚአብሔር ልጅ” ሰው ሆኖ ወደ ዓለም የመጣውን ቃል ኢየሱስን ያመለክታል። ብዙውን ጊዜ፣ “ልጁ” ተብሎም ይጠራል
“የእግዚአብሔር ልጆች” በርካታ ትርጉሞች ያሉት ምሳሌያዊ አነጋገር ሊሆን ይችላል
“የእግዚአብሔር ሕዝብ” የተሰኘው ሐረግ ከእርሱ ጋር የተለየ ግንኙነት እንዲኖረው እግዚአብሔር ከዓለም የጠራውን ሕዝብ ነው።
“የእግዚአብሔር መንግሥት” እና፣ “መንግሥተ ሰማይ” የሚሉት ሁለቱም የሚያመለክቱት በሕዝቡና በፍጥረት ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ያለውን አገዛዝ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “የእግዚአብሔር ቃል” የሚባለው እግዚአብሔር ለሰዎች የተናገረው ማንኛውንም ነገር ያመለክታል። ይህም ንግግርና በጽሑፍ የሰፈረ መልእክትን ይጨምራል። ኢየሱስ ራሱ፣ “የእግዚአብሔር ቃል” ተብሏል።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “የእግዚአብሔር ቤት” እና፣ “የያህዌ ቤት” የተሰኙት ሐረጎች የሚያመለክቱት እግዚአብሔር የሚመለክትበትን ቦታ ነው።
“አምሳያ” የሚለው ሌላውን የሚመስል፣ በጸባይም ሆነ በጥንተ ተፈጥሮው ሌላውን የመሰለ ማለት ነው። “የእግዚአብሔር አምሳል” የሚለው ሐረግ እንደ አውዱ ሁኔታ በተለያየ መንገድ ጥቅም ላይ ይውላል።
“የእግዚአብሔር ፈቃድ” የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ፍላጎትና እቅድ ነው።
የክርስቶስ ተቃዋሚ የሚለው አገላለጽ እየሱስ ክርስቶስንና ሥራውን የሚቃወም ሰውን ወይም ትምህርትን ነው የሚያመለክተው በዓለም ውስጥ ብዙ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች አሉ።
“የያህዌ ቀን” የተሰኘው የብሉይ ኪዳን አገላለጽ ከኀጢአታቸው የተነሣ እግዚአብሔር ሕዝቡን የሚቀጣበትን የተለየ ቀን ወይም ቀኖች ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል።
“የጌታ እራት” የሚለውን ቃል ሐዋርያው ጳውሎስ የተጠቀመበት በአይሁድ መሪዎች በተያዘበት ሌሊት ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የበላውን የፋሲካ ምግም ለማመልከት ነበር።
የጽዮን ሴት ልጅ የእስራኤልን ሕዝብ የሚያመለክት ምሳሌያዊ አነጋገር ነው። ብዙውን ጊዜ ትንቢት ውስጥ ጥቅም ላይ ውሏል።
“የፍርድ ቀን” እግዚአብሔር በማንኛውም ሰው ላይ የሚፈርድበት ወደፊት የሚመጣ ጊዜ ነው።
“ያህዌ” የእግዚአብሔር የተፀውዖ ስም ሲሆን፣ በሚቃጠለው ቁጥቋጦ ውስጥ እግዚአብሔር ራሱን ለሙሴ የገለጠው በዚህ ስሙ ነበር።
“ያልቦካ እንጀራ” የሚያመለክተው ያለ እርሾ ወይም እንዲቦካ የሚያደርግ ሌላ ነገር ሳይገባበት የተጋገረ እንጀራን ነው። ያልቦካ ዳቦ ኩፍ አይልም፣ ስለዚህ ጠፍጣፋ ነው።
አንድን ሰው ይቅር ማለት ከዚህ ቀደም ባደረገው መጥፎ ነገር ቂም አለመያ ማለት ነው። “ይቅርታ” ሌላውን ይቅር የማለት ተግባር ነው።
“ደም” ጉዳት ወይም ቁስል ሲኖር ከአንድ ሰው ቆዳ የሚወጣ ቀይ ፈሳሽ ነገርን ያመለክታል። ደም ለሰው አካል ሕይወት ሰጪ ምግብን ያመጣል።
“ደቀ መዝሙር” በቃልም ሆነ በሕይወት ምሳሌነት ከመምህሩ ለመማር ሲል ብዙ ጊዜውን ከመምህሩ ጋር የሚያሳልፍ ሰው ነው።
ዲያቆን ምግብን ወይም ገንዘብን በመሳሰሉ ተግባራዊ ነገሮች አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉትን በመርዳት የሚያገለግል ሰው ነው።
ድንጋይ አነስ ያለ ዐለት ነው። በድንጋይ መውገር አንድን ሰው ለመግደል እርሱ ላይ ድንጋዮች መወርወር ማለት ነው
ብዙ ጊዜ፣ “ጃንደረባ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የተኮላሸ ወንድን ነው በኋላ ግን ቃሉ አካላዊ ጉድለት ባይኖርባቸውም በአጠቃላይ ማንኛውንም የመንግሥት ባለሥልጣን የሚያመለክት ሆነ።
ገሃነም በእርሱ ላይ የሚያምፁትንና በኢየሱስ መሥዋዕትነት በኩል እነርሱን የማድኑን ዕቅድ ችላ የሚሉትን የሚቀጣበት የመጨረሻው የስቃይ ቦታ ነው። “የእሳት ባሕር” ተብሎም ይጠራል።
እነዚህ ሁሉ የሚያመለክቱት አጋንንትን ሲሆን፣ አጋንንት የእግዚአብሔርን ፈቀድ የሚቀወሙ መንፈሳዊ ፍጥረቶች ናቸው።
እንዱ እውነተኛ አምላክን በተመለከተ እነዚህ ቃሎች ብሉይ ኪዳን ውስጥ ብዙ ጊዜ ተጠቅሰዋል።
“ጌታ” የሚለው ቃል ሰዎች ላይ ባለቤትነት ወይም ሥልጣን ያለውን ሰው ያመለክታል።
ብዙውን ጊዜ “ግርማ” ከንጉሥ ክብር ጋር በተያያዘ መልኩ ትልቅነትንና ውበትን ነው የሚያመለክተው።
“ግብዝ” የሚለው ልቡ ክፉና ጠማማ ሆኖ በሰዎች ፊት ግን መልካም ሰው መስሎ ለመታየት የሚሞክር ሰው ነው። “ግብዝነት” መልካምና እውነተኛ መስሎ ለመታየት አንድ ሰው የሚያደርገው ነው።
ግዛት ሰዎችን፣ እንስሳትንና መሬትን የመቆጣጠር፣ የመግዛት ኃይልና ሥልጣንን ያመለክታል።
“ጢቢባን” የተሰኘው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው የተለየ ዕውቀትና ችሎታ ያላችው ሰዎችን ለማመልከት ሲሆን፣ ብዙውን ጊዜ እነዚህ ሰዎች በንጉሡ አደባባይ ነበር የሚገኙት።
በዓለ ሃምሳ ከፋሲካ ሃምሳ ቀን በኋላ የሚከበረው የአይሁድ በዓል ግሪክኛ ስም ነው።
ጸሐፍት መንግሥታዊ ወይም ሃይማኖታዊ ሰንዶችን በእጅ ጽሑፍ የማርቀቅ ወይም የመገልበጥ ኅላፊነት የነበረባቸው ባለ ሥልጣኖች ናቸው
“ጸጋ” የሚለው ቃል ምንም ሳይለፋና ሳይደክም አንድን ሰው መርዳትን ወይም መባረክን ያመለክታል። “ባለ ጸጋ” ሌሎችን ጸጋ የሚያሳይን ሰው ይመለከታል።
“ጻድቅ” እና፣ “ጽድቅ” የእግዚአብሔር ፍጹም መልካምነት፣ ፍትሕ፣ ታማኝነትና ፍቅር ያመለክታል። እግዚአብሔር ጻድቅ ስለሆነ ኀጢአት ላይ መፍረድ አለበት።
መጀመሪያ ላይ፣ “ጽዮን” ወይም፣ “የጽዮን ተራራ” ተብሎ ይጠራ የነበረው ንጉሥ ዳዊት ከኢያቡሳውያን የያዝሰው ምሽግ ወይም መሸሸጊያ ቦታ ስም ነበር። የኢየሩሳሌም ከተማ በተመሠረተችባቸውና የዳዊት መኖሪያ ከሆነው ኮረብቶች አንዱ ላይ ነበር የሚገኘው።
ፈሪሳውያን ኢየሱስ በዚህ ምድር በነበረ ዘመን በጣም ታዋቂ የእስራኤል ሃይማኖት መሪዎች ነበር። አብዛኞቹ መካከለኛ ኑሮ ያላቸው ሠራተኞች ሲሆኑ፣ ጥቂቶቹም ካህናት ነበሩ።
ብዙውን ጊዜ፣ “ፈራጅ” ወይም፣ “ፍርድ” የተሰኙት ቃሎች የሚያመለክቱት ከግብረ ገብ አንጻር አንድ ነገር ትክክል መሆን አለመሆኑን በተመለከተ ውሳኔ መስጠት ነው።
“ፈተና” የሚለው ቃል የአንድን ሰው ብርታትና ድካም ለይቶ የሚያሳይ አስቸጋሪ ወይም አዳጋች ሁኔታ ያመለክታል።
ፋሲክ እግዚአብሔር አባቶቻቸው እስራኤላውያንን እንዴት ከግብፅ ባርነት እንዳዳናቸው ለማሰብ አይሁድ በየዓመቱ የሚያከብሩት ሃይማኖታዊ በዓል ስም ነው።
“ፍርሃት” እና፣ “ፈራ” የሚሉት በእርሱ ወይም በሌሎች ላይ ጉዳት ይመጣል ብሎ ሲያስብ የሚኖረው ደስ የማይል ስሜት ነው።
አንድን ሰው መውደድ ለዚያ ሰው ማሰብና መጠንቀቅ እንዲሁም ለእርሱ የሚጠቅመውን ነገር ማድረግ ነው። “ፍቅር” የተለያዩ ትርጕሞች አሉት፤ አንዳንድ ቋንቋዎች በተለያዩ ቃሎች ይገልጹታል። 1. ከእግዚአብሔር የሚመጣው ፍቅር ምንም እንኳ ራስን የሚጠቅም ባይሆንም ሌሎችን መጥቀም ላይ ያተኩራል። ምንም ያድርጉ ምን ይህ ፍቅር ለሌሎች ያስባል፣ ለሌሎች ይጠነቃቃል። እግዚአብሔር ራሱ ፍቅር ነው፤ የእውነተኛ ፍቅር ምንጭም እርሱ ነው።
“ፓስተር” የሚለው ቃል በቃል፣ “እረኛ” ከሚለው ጋር አንድ ነው። የአማኞች ስብስብ መንፈሳዊ መሪ ለሆነ ሰው የሚሰጥ ስም ነው።