Genesis 7
Genesis 7:1
ወደ መርከቡ የሚገቡት ሰባት ወንድና ሴት እንስሶች የትኞቹ ነበሩ?
ንጹሕ ከሆኑት እንስሳት ሰባት ወንድና ሴት እንዲሁም ወፎች ወደ መርከቡ መግባት ነበረባቸው
Genesis 7:4
እግዚአብሔር ዝናቡ በምድር ላይ ሳያቋርጥ የሚዘንበው ለምን ያህል ጊዜ ነው አለ?
እግዚአብሔር ዝናቡ ለአርባ ቀንና ሌሊት ሳያቋርጥ እንደሚዘንብ ተናገረ
Genesis 7:6
የጥፋት ውሃ በምድር ላይ በመጣ ጊዜ የኖኅ ዕድሜ ምን ያህል ነበር?
የጥፋት ውሃ በምድር ላይ በመጣ ጊዜ የኖኅ ዕድሜ ስድስት መቶ አመት ነበር
Genesis 7:8
ኖኅ እንስሶቹን ወደ መርከቡ ያመጣቸው እንዴት አድርጎ ነበር?
እንስሳቱ ወደ ኖኅ መጡና ወደ መርከቡ ገቡ
Genesis 7:11
የጥፋት ውሃ የመጣው ከየትኞቹ ሁለት መነሻዎች ነበር?
ውሃው የመጣው ከምድር ጥልቅና ከሰማይ ነበር
Genesis 7:15
ሰዎቹ ሁሉና እንስሳቱ ወደ መርከቡ ከገቡ በኋላ በሩን ማን ዘጋው?
እግዚአብሔር አምላክ በሩን ከበስተኋላቸው ዘጋው
Genesis 7:19
ውሃው ከምድር ምን ያህል ከፍታ ነበረው?
ውሃው ከተራራዎቹ ጫፍ በላይ አሥራ አምስት ክንድ ያህል ተነሣ
Genesis 7:21
በጥፋት ውሃው ምክንያት በምድር ላይ የሞተው ምንድነው?
በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረታት ሁሉና ሰዎች ሁሉ ሞቱ
Genesis 7:23
በምድር ላይ በሕይወት የቀሩት ብቸኞች ሰዎች እነማን ነበሩ?
ኖኅና ከእርሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩት ብቻ በሕይወት ተረፉ