Genesis 6
Genesis 6:1
ሰዎች በምድር ላይ በበዙ ጊዜ የእግዚአብሔር ወንዶች ልጆች ምን አደረጉ?
የእግዚአብሔር ወንዶች ልጆች የሰዎችን ሴቶች ልጆች ለራሳቸው ሚስት አድርገው ወሰዱ
እግዚአብሔር፣ ስለ ሰዎች የሕይወት ዕድሜ ምን አለ?
እግዚአብሔር ሰው የሚኖረው 120 ዓመት ነው አለ
Genesis 6:4
በድሮ ዘመን ኃያላንና ስማቸው የታወቁ የሆኑት እነማን ናቸው?
በድሮ ዘመን ኃያላን የሆኑት ኔፍሊሞች፣ የእግዚአብሔር ወንዶች ልጆችና የሰዎች ሌቶች ልጆች ተጋብተው የወለዷቸው ነበሩ
Genesis 6:5
በዚያን ዘመን በሰዎች ልብ ውስጥ እግዚአብሔር አምላክ ያየው ምን ነበር?
እግዚአብሔር አምላክ የሰዎች ክፋት ታላቅ መሆኑንና አሳባቸውም ሁሉ ክፉ መሆኑን አየ
Genesis 6:7
እግዚአብሔር አምላክ በሰዎች ላይ የወሰነው ምን ለማድረግ ነበር?
እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ከምድር ላይ ለማጥፋት ወሰነ
ሆኖም በእግዚአብሔር አምላክ ፊት ሞገስን ያገኘው ማን ነበር?
ኖኅ በእግዚአብሔር አምላክ ፊት ሞገስን አገኘ
Genesis 6:9
ኖኅ ምን ዓይነት ሰው ነበር?
ኖኅ ጻድቅ፣ የማይነቀፍና አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገ ሰው ነበር
Genesis 6:13
እግዚአብሔር ሰውን ከማጥፋቱ በፊት ለኖኅ የነገረው ምን እንዲያደርግ ነበር?
መርከብ እንዲሠራ እግዚአብሔር ለኖኅ ነገረው
Genesis 6:16
እግዚአብሔር የሕይወት እስትንፋስ ያለበትን ሥጋ ሁሉ እንዴት አድርጎ እንደሚያጠፋ ተናገረ?
እግዚአብሔር በምድር ላይ የጥፋትን ውሃ እንደሚያመጣ ተናገረ
Genesis 6:18
ሆኖም እግዚአብሔር ቃል ኪዳኑን ያደረገው ከማን ጋር ነበር?
እግዚአብሔር ቃል ኪዳኑን ከኖኅ ጋር አደረገ
Genesis 6:20
እግዚአብሔር ለኖኅ የነገረው ወደ መርከቡ ማንን እንዲያስገባ ነበር?
ኖኅ ሚስቱን፣ ሦስቱን ወንዶች ልጆቹንና የልጆቹን ሚስቶች ወደ መርከቡ እንዲያስገባ እግዚአብሔር ነገረው
በሕይወት ይቆዩ ዘንድ ወደ መርከቡ መግባት የነበረባቸው እንስሶች የትኞቹ ናቸው?
ሕያዋን ፍጥረታት ከሆኑት ሁሉ ሁለት ሁለት ወንድና ሴት ሆነው ወደ መርከቡ መግባት ነበረባቸው
ለእግዚአብሔር ትዕዛዝ የኖኅ ምላሽ ምን ነበር?
ኖኅ እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ