Genesis 8
Genesis 8:1
ውሃው እንዲቀንስ እግዚአብሔር ምን አደረገ?
እግዚአብሔር ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ፣ የጥልቁ ውሃ ምንጮች ተደፈኑ፣ ዝናቡም ቆመ
ውሃው እንዲቀንስ እግዚአብሔር ምን አደረገ?
እግዚአብሔር ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ፣ የጥልቁ ውሃ ምንጮች ተደፈኑ፣ ዝናቡም ቆመ
Genesis 8:4
መርከቡ ያረፈበት ምድር የት ነበር?
መርከቡ ያረፈው በአራራት ተራሮች ላይ ነበር
Genesis 8:8
ለመጀመሪያ ጊዜ ኖኅ እርግቢቱን ከመርከቡ ወደ ውጭ በላካት ጊዜ ምን ሆነ?
በመጀመሪያው ጊዜ እርግቢቱ እግሮቿን የምታሳርፍበት ቦታ አላገኘችምና ወደ ኖኅ ወደ መርከቡ ተመለሰች
Genesis 8:10
ለሁለተኛ ጊዜ ኖኅ እርግቢቱን ከመርከቡ ወደ ውጭ በላካት ጊዜ ምን ሆነ?
በሁለተኛው ጊዜ፣ እርግቢቱ የለመለመ የወይራ ቅጠል ይዛ ተመለሰች
ለሦስተኛ ጊዜ ኖኅ እርግቢቱን ከመርከቡ ወደ ውጭ በላካት ጊዜ ምን ሆነ?
በሦስተኛው ጊዜ፣ እርግቢቱ ወደ ኖኅ አልተመለሰችም
Genesis 8:13
ኖኅ የመርከቡን ክዳን አንሥቶ ወደ ውጪ በተመለከተ ጊዜ ምን አየ?
ኖኅ የምድሪቱ ፊት መድረቁን አየ
Genesis 8:15
እግዚአብሔር በመርከቡ ውስጥ የነበሩት ፍጥረታት በሙሉ በወጡ ጊዜ ሄደው እንዲያደርጉ የፈለገው ምን ነበር?
እግዚአብሔር፣ ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ በምድር ላይ እንዲበዙና እንዲባዙ ፈለገ
Genesis 8:20
ኖኅ ከመርከቡ ከወጣ በኋላ ምን አደረገ?
ኖኅ ለእግዚአብሔር አምላክ መሠዊያ ሠራና በእርሱ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ሠዋበት
በዚህ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ለሰዎች የገባቸው ሁለት ቃል ኪዳኖች የትኞቹ ናቸው?
እግዚአብሔር ዳግመኛ ምድርን ላይረግማትና ሕያዋንን ሁሉ እንደገና ላያጠፋ ቃል ገብቷል
እግዚአብሔር፣ የሰው አሳብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ምንድነው አለ?
እግዚአብሔር፣ የሰው አሳብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፉ ነው አለ