ምዕራፍ 5

1 ንጉሥ ቤልሻዛር በሺህ ለሚቆጠሩ መኳንንቱ ታላቅ ግብዣ አደረገ፣ በሺሁም ፊት የወይን ጠጅ ይጠጣ ነበር። 2 ቤልሻዘር የወይን ጠጅ እየጠጣ ሳለ፣ አባቱ ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ ያመጣቸውን የወርቅና የብር መጠጫዎችን እርሱና መኳንንቱ፣ ሚስቶቹና ቁባቶቹ ይጠጡባቸው ዘንድ እንዲያመጡለት አዘዘ። 3 አገልጋዮቹም እነዚያን ከኢየሩሳሌም ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የተወሰዱትን የወርቅ ዕቃዎች አመጡ፤ ንጉሡና መኳንንቱ፣ ሚስቶቹና ቁባቶቹም ጠጡባቸው። 4 የወይን ጠጁንም እየጠጡ የወርቅና የብር፣ የናስ፣ የብረት፣ የዕንጨትና የድንጋይ አማልክቶቻቸውን አመሰገኑ። 5 በዚያን ቅጽበት የሰው እጅ ጣቶች ታዩ፤ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ በመቅረዙ ትይዩ ባለው በግድግዳው ልስን ላይ ጻፉ፤ ንጉሡም ይጽፍ የነበረውን እጅ አየ፤ 6 በዚያን ጊዜ የንጉሡ ፊት ተለዋወጠ በድንጋጤም ተሞላ፤ እጆቹና እግሮቹ ከዱት፤ ጉልበቶቹም ተብረከረኩ። 8 ከዚያም የንጉሡ ጠቢባን ሁሉ ገቡ፤ ነገር ግን ጽሕፈቱን ሊያነብም ሆነ ትርጉሙ ምን እንደሆነ ለንጉሡ ሊነግር የሚችል ማንም አልነበረም። 9 ንጉሥ ቤልሻዘር ፈራ ፊቱም እጅግ ተለወጠ፤ መኳንንቱም ግራ ግብቶአቸው ተደናገጡ። 11 በመንግሥትህ ውስጥ የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት አንድ ሰው አለ፤ ይህ ሰው በአባትህ ዘመን እንደ አማልክት ጥበብና ማስተዋል ዕውቀትም የሞላበት ሆኖ ተገኝቶአል፤ አባትህ ንጉሥ ናቡከደነፆርም የጠንቋዮች፣ የአስማተኞች፣ የኮከብ ቆጣሪዎችና የመተተኞች አለቃ አደረገው። 12 ንጉሡ ብልጣሶር ብሎ የጠራው ይህ ዳንኤል መልካም መንፈስ፥ ዕውቀትና ማስተዋል ያለው ሆኖ ተገኘ፤ ሕልምን የመተርጎም፣ እንቆቅልሽን የመፍታትና የተሰወረውን የመግለጥ ልዩ ችሎታም ነበረው። ስለዚህ ዳንኤልን አስጠራ፣ እርሱም የጽሕፈቱን ትርጉም ይነግርሃል።” 13 ዳንኤልንም ወደ ንጉሥ አቀረቡት፤ ንጉሡም እንዲህ አለው፤ “ንጉሡ አባቴ ከይሁዳ ማርኮ ካመጣቸው መካከል አንዱ የሆንኸው ዳንኤል አንተ ነህን? 14 የአማልክት መንፈስ በውስጥህ እንዳለ፣ ዕውቀት፣ ማስተዋልና ልዩ ጥበብ እንዳለህ ሰምቻለሁ፤ 15 ይህን ጽሕፈት አንብበው ትርጉሙ ምን እንደሆነ ይነግሩኝ ዘንድ ጠቢባንና አስማተኞች በፊቴ ቀርበው ነበር፣ ነገር ግን ሊገልጡት አልቻሉም። 16 አንተ ግን መተርጎምና አስቸጋሪ የሆነውን ነገር መፍታት እንደምትችል ሰምቻለሁ። ይህን ጽሕፈት አንብበ ትርጉሙን ብትነግረኝ፣ ሐምራዊ መጎናጸፊያ ያለብሱሃል፣ የወርቅ ሐብል በዓንገትህ ያጠልቁልሃል፣ በመንግሥት ሥልጣንም ሦስተኛውን ማዕረግ እንድትይዝ ትደረጋለህ።” 17 ዳንኤልም ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ስጦታዎችህን ለራስህ አድርግ፤ ሽልማቶችህንም ለሌላ ሰው ስጥ፤ ይሁን እንጂ ጽሕፈቱን ለንጉሡ አነባለሁ፤ ትርጉሙ ምን እንደሆነም እነግረዋለሁ።” 18 “ንጉሥ ሆይ፤ ልዑል አምላክ ለአባትህ ለናቡከደነፆር ገናናነትንና ታላቅነትን፣ ክብርንና ግርማን ሰጠው። 19 ከሰጠው ታላቅ ሥልጣን የተነሣ ሕዝቦችና መንግሥታት፣ ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎችም ሁሉ ተንቀጠቀጡለት ፈሩትም። ንጉሡም ሊገድል የፈለገውን ይገድል፣ ሊያድን የፈለገውን ሊያድን፣ ሊሾም ይፈለገውን ይሾም፣ ሊያዋርድ የፈለገውንም ያዋርድ ነበር። 20 ነገር ግን ልቡ በትዕቢት በጸናና በእብሪት በተሞላ ጊዜ ከዙፋኑ ተወገደ፤ ክብሩም ተገፈፈ። 21 ከሰው መካከል ተሰደደ፤ የእንስሳም አእምሮ ተሰጠው፤ ከዱር አህዮች ጋር ኖረ፤ እንድች በሬም ሣር በላ፤ ልዑል አምላክ በሰዎች መንግሥት ላይ እንደሚገዛና እነርሱምን ለወደደው እንደሚሰጥ እስኪያውቅ ድረስ ሰውነቱ በሰማይ ጠል ረሰረሰ። 22 “ቤልሻዘር ሆይ፤ አንተ ልጁ ሆነህ ይሁ ሁሉ ብታውቅም፣ ራስህን ዝቅ አላደረግህም፤ 23 ይልቁንም በሰማይ አምላክ ላይ በመታበይ ራስህን ከፍ ከፍ አደረግህ፤ የመቅደሱን መጠጫዎች አስመጣህ፤ አንተና መኳንንትህ፣ ሚስቶችህና ቁባቶችህም የወይን ጠጅ ጠጣችሁባቸው፣ ማየት፣ መስማት፣ ማስተዋልም የማይችሉትን የብርና የወርቅ የናስና የብረት፣ የእንጨትና የድንጋይ አማልክትን አመሰገንህ። ሕይወትህንና መንገድህን ሁሉ በእጁ የያዘውን አምላክ ግን አላከበርህም። 24 ስለዚህ እርሱ ጽሕፈቱን ይጻፈውን እጅ ላከ። 25 የተጻፈውም ጽሕፈት፣ ‘ማኔ፣ ቴቄል፣ ፋሬስ’ ይላል 26 የቃሉም ትርጉም ይህ ነው፤ ‘ማኔ’ ማለት እግዚአብሔር የመንግሥትህን ዘመን ቆጠረው፣ ወደ ፍጻሜም አደረሰው ማለት ነው። 27 ‘ቴቄል’ ማለት በሚዛን ተመዝነህ ቀለህም ተገኘህ ማለት ነው። 28 ‘ፋሬስ’ ማለት መንግሥትህ ተከፈለ፣ ለሜዶናውያንና ለፋርስ ሰዎች ተሰጠ ማለት ነው።” 29 ከዚህ በኋላ በቤልሻዘር ትእዛዝ ዳንኤልን ሐምራዊ መጎናጸፊያ አለበሱት፣ የወርቅ ሐብል በዐንገቱ ኣይ አጠለቁለት፣ በመንግሥቱም ሥልጣን ሦስተኛውን ማዕረግ እንዲይዝ እንዲያደርጉት በዐዋጅ አዘዘ። 30 በዚያኑ ሌሊት የባቢሎናውያን ንጉሥ ቤልሻዘር ተገደለ፤ 31 የሥልሳ ሁለት ዓመት ዕድሜ የነበረው ሜዶናዊው ዳርዮስም መንግሥቱን ወሰደ።