1 ከንጉሥ ናቡከደነፆር፥በምድር ሁሉ ለሚኖሩ አሕዛብ፥ መንግሥታትና ልዩ ልዩ ቋንቋ ለሚናገሩ ሁሉ፦ «ሰላማችሁ ይብዛ። 2 ልዑል አምላክ ስላደረገልኝ ምልክቶችና ድንቆች እነግራችሁ ዘንድ መልካም ሆኖ ታየኝ። 3 ምልክቶቹ እንዴት ታላላቅ ናቸው! ድንቆቹም እንዴት ብርቱዎች ናቸው! መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥ ግዛቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል። 4 እኔ ናቡከደነፆር በቤቴ ደስ ብሎኝ፥ በቤተ መንግሥቴም በብልጽግና ፍሥሐ እያደረግሁ እኖር ነበር። 5 ነገር ግን የአስፈራኝን ሕልም አለምሁ፤ ተኝቼም ሳለሁ ያየኋቸው ምስሎችና የአእምሮዬ ራዕዮች አወኩኝ። 6 ስለዚህ ሕልሙን ይተረጉሙልኝ ዘንድ የባቢሎንን ጠቢባን ሁሉ በፊቴ እንዲያቀርቧቸው ትእዛዝ አወጣሁ። 7 በዚያን ጊዜ አስማተኞች፥ሙታን ሳቢዎች፥ጠቢባንና ኮከብ ቆጣሪዎች መጡ፤ ሕልሙንም ነገርኳችው፥ ነገር ግን ሊተረጉሙልኝ አልቻሉም። 8 በመጨረሻም፥ እንደ አምላኬ ስም ብልጣሶር ተብሎ የተጠራውና የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት ዳንኤል ገባ። ሕልሙን ነገርኩት። 9 «የአስማተኞች አለቃ ብልጣሶር ሆይ፦የቅዱሳን አማልክት መንፈስ እንዳለብህና የሚያስችግርህ ምሥጢር እንደሌለ አውቄአልሁና፤ በሕልሜ ምን እንዳየሁና ትርጉሙ ምን እንደሆነ ንገረኝ አልኩት። 10 በአልጋዬ ላይ ትኝቼ ሳልሁ በአእምሮዬ ያየኋቸው ራዕዮች እነዚህ ነበሩ፦ ተመለከትኩ፥ በምድርም መካከል ዛፍ ነበረ፥ቁመቱም እጅግ ታላቅ ነበረ። 11 ዛፉ አደገ፥በረታም። ጫፉ ሰማይ ደረሰ፥ እስከ መላው ዓለም ዳርቻ ድርስም ይታይ ነበረ። 12 ቅጠሎቹ ያማሩ፥ ፍሬዎቹም የተት ረፈረፉ ነበሩ፤ ለሁሉ የሚሆን ምግብም በላዩ ነበረበት። የዱር አራዊት ከበታቹ ጥላ አግኝተው ነበር፥ የሰማያት አእዋፍም በቅርንጫፎቹ ይኖሩ ነበር። ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ከእርሱ ይመገቡ ነበር። 13 በአልጋዬ ላይ ተኝቼ ሳለሁ በአእምሮዬ አየሁ፥ አንድ ቅዱስ መልእክተኛም ከሰማያት ወረደ። 14 እርሱም ጮኽ፥ እንዲህም አለ፦ ዛፉንና ቅርንጫፎቹን ቁረጡ፥ ቅጠሎቹን አራግፉ፥ ፍሬውንም በትኑ። አራዊቱ ከሥሩ፥ አእዋፍም ከቅርንጫፎቹ ይሽሹ። 15 16 የሥሮቹን ጉቶ፥ በሜዳው ለምለም ሳር መካከል በብረትና በናስ ማሰሪያ እንደታሰረ በመሬት ውስጥ ተውት። በሰማያት ጠል ይረስርስ፥ በምድር ዛፎች መካከል ከአራዊት ጋር ይኑር። አእምሮው ከሰው አእምሮ ይለወጥ፥ ሰባት ዓመታትም እስኪያልፉ ድረስ የአውሬ አእምሮ ይሰጠው። 17 በመልእክተኛው በተነገረው አዋጅ ይህ ውሳኔ ሆነ። ልዑሉ በሰዎች መንግሥታት ላይ እንደሚገዛና እነዚህንም መንግሥታት ለተናቁ እጅግ ትሑታን ለሆኑ ሰዎች እንኳን ሳይቀር፥ ሊያነግሠው ለወደደው ለማንም እንደሚስጥ ሕያዋን ሁሉ ያውቁ ዘንድ ይህ የቅዱሱ ውሳኔ ነው። 18 እኔ ንጉሡ ናቡከደነፆር ይህን ሕልም አልሜአለሁ። አሁንም አንተ ብልጣሶር፥ በመንግሥቴ ካሉ ጠቢባን ሰዎች አንዳቸውም ሊተረጉሙልኝ አልቻሉምና ትርጉሙን ንገረኝ። አንተ የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በውስጥህ ስላለ ልትተረጉም ትችላለህ።» 19 በዚያን ጊዜ ብልጣሶር የተባለው ዳንኤል፥ ለትንሽ ጊዜ እጅግ ታወከ፥ ሐሳቡም አስደነገጠው። ንጉሡም አለው፦ «ብልጣሶር ሆይ ሕልሙ ወይም ትርጉሙ አያስደንግጥህ።» ብልጣሶርም እንዲህ ሲል መለስ፥ «ጌታዬ ሆይ፥ ሕልሙ ለሚጠልህ፥ ትርጉሙም ለጠላቶችህ ይሁን። 20 ያየኽው ዛፍ፥ ያድግ የነበረውና የበረታው፥ ጫፉም ወደ ሰማያት የደረሰው፥ እስከ መላው ዓለም ዳርቻ ድረስ የታየው፥ 21 ቅጠሎቹያምሩ የነበሩት፥ ፍሬዎቹም የተትረፈረፉት፥ ስለዚህም ለሁሉ የሚሆን መብል የነበረበት፥ ከበታቹም የምድር አራዊት ጥላ ያገኙበት፥ የሰማያት አእዋፍም ይኖሩበት የነበረ፥ 22 ያ ዛፍ፥ እጅግ ኃያል የሆንከው ንጉሥ አንተ ነህ። ታላቅነትህ እስከ ሰማያት፥ ሥልጣንህም እስከ ምድር ዳርቻ ደረሰ። 23 አንተ ንጉሥ ሆይ፥ አንድ ቅዱስ መልእክተኛ ከሰማይ ሲወርድና እንዲህ ሲል አየህ፦«ዛፉን ቁረጡና አጥፉት፥ ነገር ግን የሥሮቹን ጉቶ በሜዳው ለምለም ሣር መካከል በብረትና በናስ ማሰሪያ እንደታሰረ በመሬት ውስጥ ተውት። በሰማያት ጠል ይረስርስ። ሰባት ዓመታት እስኪያልፉ ድረስ ከአራዊት ጋር በሜዳ ይኑር። 24 ንጉሥ ሆይ ትርጉሙ ይህ ነው። ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ይህ በአንተ ላይ የወጣ የልዑሉ አዋጅ ነው። 25 ከሰዎች መካከል ተለይተህ ትባረራለህ፥ በሜዳም ከአራዊት ጋር ትኖራለህ። እንደ በሬ ሣር እንድትበላ ትደረጋለህ፥ በሰማያትም ጠል ትረሰርሳለህ፥ ልዑሉ በአሕዛብ መንግሥታት ላይ እንደሚገዛና እንዚህንም መንግሥታት እርሱ ለወደደው ለማንም ሊሰጣቸው እንደሚችል እስክታውቅ ድረስ ሰባት ዓመታት ያልፉብሃል። 26 የዛፉን የሥሩን ጉቶ ይተዉት ዘንድ እንደታዘዘው፥ እንዲሁ ሰማይ እንደሚገዛ ከተማርህ በኋላ መንግሥትህ ይመለስልሃል። 27 ስለዚህ ንጉሥ ሆይ ምክሬ በፊትህ ተቀባይነት ያግኝ። ኃጢአት ማድረግህን አቁምና ትክክል የሆንውን ሥራ። 28 - 29 ነገሮች ሁሉ በናቡከደነፆር ላይ ደረሱ። ከዐሥራ ሁለት ወሮች በኋላ በባቢሎን ቤተ መንግሥት ሰገነት ላይ ሲመላለስ፣ 30 “ይህች ለንግሥናዬ መኖሪያ፣ ለክብሬም ግርማ እንድትሆን የመሠረትኋት ባቢሎን አይደለችምን?” አለ። 31 ንጉሡ ይህን ገና ተናግሮ ሳይጨርስ እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ መጣ፣ “መንግሥትህ ከአንተ እንደ ተወሰደ ተነግሮአል፤ 32 ከሰዎች ትገለላለህ፤ መኖሪያህ ዱር ውስጥ ከአራዊት ጋር ይሆናል። እንደ በሬ ሣር ትበላለህ። ልዑል በሰዎች መንግሥት ላይ እንደሚገዛና እርሱ ለፈለገው እንደሚሰጥ እስክትገነዘብ ድረስ ሰባት ዓመታት ያልፉብሃል።” 33 ይህ ቃል ናቡከደነፆር ላይ የተፈጸመው ወዲያውኑ ነበር፤ ከሰዎች ተገለለ፤ እንደ በሬ ሣር በላ፤ ሰውነቱ ከሰማይ በሚወርድ ጠል ረሰረሰ፤ ጠጉሩ እንደ ንስር ላባ፣ ጥፍሩም እንደ ወፍ ጥፍር ሆነ። 34 ጊዜው ከተፈጸመ በኋላ እኔ ናቡከደነፆር ዐይኖቼን ወደ ሰማይ አነሣሁ፤ አእምሮዬም ተመለሰልኝ። “ልዑልንም ባረክሁት ለዘላለም የሚኖረውን እርሱን አመሰገንሁት አከበርሁት። እርሱ ለዘላለም ይነግሣልና መንግሥቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ዘመን ነው። 35 የምድር ሕዝቦች ሁሉ እንደ ኢምንት ይቆጠራሉ፤ በሰማይ ሰራዊትና በምድር ሕዝቦች መካከል የወደደውን ያደርጋል። የሚያስቆመው ወይም የሚከራከረው የለም። “ለምን እንዲህ አደረግህ?” የሚለውም የለም። 36 አእምሮዬ እንደ ተመለሰልኝ ወዲያውኑ ከመንግሥቴ ክብር ግርማዊነቴና ሞገስ ተመለሰልኝ። አማካሪዎቼና ሹማምንቴ ፈለጉኝ። ወደ ዙፋኔ ተመለስሁ፤ የበለጠ ታላቅነትም ተሰጠኝ። 37 እኔ ናቡከደነፆር አሁን የሰማይን ንጉሥ እባርካለሁ፤ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ። ሥራዎቹ ትክክል መንገዶችም ጽድቅ ናቸው። በትዕቢታቸው የሚራመዱትን ያዋርዳል።