1
1
2
1በዚህ መጽሐፍ የተፃፈው፣ እስራኤላውያን ድንኳናቸውን ከዮርዳኖስ በስተ ምስራቅ ከተከሉ በኋላ፤ በዮርዳኖስ አጠገብ በበረሃማው ሜዳ - ሱጳ በተባው ቦታ አቅራቢያ፣ በዮርዳኖስ በኩል ከዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ከሚገኘው ከፋራ መሃል እና በጦፌል፣ ላባን፣ ሐዴሮን እና ዲዛሃብ ከተሞች በወንዙ ሌላ ጎን ከሰፈሩ በኋላ ሙሴ ለእስራኤላውያን የተናገራቸው ቃል ነው፡፡ 2ተራራማ በሆነው ኤዶም በተባለው አገር በኩል ከሲና ተራራ ተነስተው ቃዴስ በርኔ ለመድረስ ሰዎች በእግር ለመጓዝ ብዙውን ጊዜ የሚወስድባቸው ጊዜ አስራ አንድ ቀናት ብቻ ነው፡፡
3
4
እስራኤላውያን ከግብጽ ከወጡ ከአርባ አመታት በኋላ፣ ሙሴ ለእስራኤላውያን ያህዌ ያዘዘውን ነገሮች በሙሉ ነገራቸው፡፡ 4ይህ የሆነው በሴናን ከተማ የሚኖረውን የአሞራውያንን ህዝቦች ንጉስ ሴዎንን ካሸነፉ በኋላ እና በአስታሮትና ኤድራይ ከተሞች የሚኖረውን የባሳንን አካባቢ ንጉስ ዐግን ካሸነፉ በኋላ ነበር፡፡
5
6
5ህዝቡ በዮርዳኖስ ወንዝ በስተምስራቅ በሚገኘው ሞአብ በተባለው ስፍራ በነበረ ጊዜ ሙሴ እነዚህን ነገሮች ለህዝቡ ተናገረ፡፡ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ለእነርሱ ገለጸላቸው፡፡ የነገራቸውም ይህንን ነው፡
6 “በሲና ተራራ በነበርንበት ጊዜ ያህዌ አምላካችን እንዲህ ሲል ተናገረን፣ ‹በዚህ ተራራ ግርጌ ለረጅም ጊዜ ቆያችሁ፡፡
7
8
7ስለዚህ አሁን ተነስታችሀሁ ጉዞአችሁን ቀጥሉ፡፡ አሞራውያን ወደሚኖሩበት ወደ ተራራማው አገር እና ወደ አካባቢው ስፍራዎች በዮርዳስ አጠገብ ወደሚገኘው ሜዳ፣ ወደ ተራራማው አገርና በስተምዕራብ ወደሚገኙት ኮረብታማ ስፍራዎች፣ ወደ ደቡባዊ የዮርዳኖስ በረሃዎች፣ ወደ ሜዲትራኒያን የባህር ዳርቻ፣ ወደ ከነዓን ምድር ሁሉ፣ ወደ ሊባኖስ ተራሮች እና ወደ ታላቁ የኤፍራጠስ ወንዝ ሰሜን ምስራቅ ሂዱ፡፡ 8ያንን ምድር ለእናንተ እሰጣለሁ፡፡ እኔ፣ ያህዌ፣ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፣ ለይስሃቅ እና ለያዕቆብ ይህን ምድር ለእነርሱ እና ለዘሮቻቸው እንደምሰጥ ቃል ገብቻለሁ፡፡ ስለዚህ ሂዱና ውረሷት፡፡›”
9
10
11
9እንደዚሁም ደግሞ ሙሴ ለህዝቡ እንዲህ አላቸው፣ ‹ገና በሲና ተራራ በነበረንበት ጊዜ፣ ለአባቶቻችሁ እንዲህ ብዬ ነበር፣ እናንተን ማስተዳደር ለእኔ በጣም ትልቅ የሀላፊነት ተግባር ነው፡፡ ብቻዬን ይህን ማድረግ አልችልም፡፡ 10አምላካችን እግዚአብሔር እኛን እስራኤላዊያንን በሰማይ እንዳሉ ከዋክብት አብዝቶናል፡፡ 11እናም ያህዌ፣ አባቶቻችን ያመለኩት አምላክ፣ አሁን ከበዛነው በላይ ሺህ ጊዜ እንደሚያበዛን ተስፋ አደርጋለሁ ደግሞም ሊያደርግ ቃል እንደገባው እንደዚያው ይባርከናል፡፡
12
13
14
12ነገር ግን ማጉረምረማችሁንና ክርክሮቻችሁን በሙሉ በእርግጥ ልሸከም አልችልም፡፡ 13ስለዚሀ አስተዋይ የሆኑና ጥሩ መረዳት ያላቸውን የተከበሩ ጥቂት ሰዎች ከየነገዶቻችሁ ምረጡ፡፡ ከዚያም እኔ መሪዎቻችሁ እንዲሆኑ እሾማቸዋለሁ፡፡› 14አባቶቻችሁ እንዲህ በማለት ምላሽ ሰጡ፣ ‹ይህ ያቀረብከው ሃሳብ እናደርገው ዘንድ ለእኛ መልካም ነው፡፡›
15
16
15ስለዚህ አባቶቻችሁ ከየነገዶቻችሁ የመረጧቸውን አስተዋይና የተከበሩ ሰዎች ወሰድኩ፣ ደግሞም መሪዎቻችሁ ይሆኑ ዘንድ ሾምኳቸው፡፡ አንዳንዶቹ በሺህዎች ላይ መሪ እንዲሆኑ ሾምኳቸው፣ አንዳንዶቹ በመቶ ሰዎች ላይ ስልጣን እንዲኖራቸው፣ አንዳንዶቹ በሀምሳ ሰዎች ላይ ስልጣን እንዲኖራቸው፣ አንዳንዶቹ በአስር ሰዎች ላይ ስልጣን እንዲኖራቸው ሾምኳቸው፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ከነገዶቻችሁ መሀል ሁሉ ሌሎች አለቆችን ሾምኩ፡፡ 16መሪዎቻችሁን እንዲህ በማለት መመሪያ ሰጠኋቸው፣ ‹በህዝባችሁ መሀል የሚነሱ ክርክሮችን አድምጡ፡፡ በእያንዳንዱ ክርክር ላይ ፍርድ ስጡ፣ በቅርብ ቤተዘመድ የሚነሳን ክርክር ጨምሮ፣ በህዝባችሁ መሀል በሚነሳ ጠብ እንዲሁም በመሀላችሁ በሚኖሩ የሌላ ሀገር ሰዎች መሀል በሚነሱ ክርክሮች ላይ ትዳኛላችሁ፡፡