9
1እናንተ የእስራኤል ሰዎች፣ እኔን አድምጡ! በቶሎ ዮርዳኖስን ትሻገራላችሁ፡፡ በምትገቡባት ምድር፣ በዙሪያቸው ትላልቅ ቅጥሮች ያላቸው ታላላቅ ከተሞች አሉ፡፡ ከእናንተ ይልቅ በቁጥር የበዙና ሃይለኞች የሆኑ የህዝብ ወገኖች በዚያ አሉ፡፡ 2እነዚያ ህዝቦች በጣም ረጃጅሞች እና ጠንካሮች ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ የዔናቅ ዝርያ የሆኑ ግዙፎች ናቸው፡፡ አንተ ስለ እነርሱ ታውቃህ፣ ደግሞም ማንም የዔናቅን ዝርያ ሊያሸንፍ አይችልም ሲባል ሰምተሃል፡፡