1 "ከዚያም ያህዌ እንዲህ ሲል ተናገረኝ፣ ‹እንደ መጀመሪያዎቹ ያሉ ሁለት የድንጋይ ጽላቶችን አዘጋጅ፡፡ እነርሱን ለማስቀመጫ የእንጨት ሳጥን አዘጋ፡፡ ከዚያ ጽላቶቹን በዚህ ተራራ ላይ ወደ እኔ አምጣቸው 2አንተ በሰበርካቸውው በመጀመሪያዎቹ ጽላቶች ላይ የጻፍኳቸውን እነዚያኑ ቃላት በእነዚህ ጽላቶች ላይ እጽፋለሁ፡፡ ከዚያ አንተ በሳጥኖቹ ውስጥ ታስቀምጣቸዋለህ፡፡