Genesis 3
Genesis 3:1
እባቡ ለሴቲቱ ያቀረበው የመጀመሪያ ጥያቄ ምን ነበር?
እባቡ ሴቲቱን፣ "በእውነቱ እግዚአብሔር፣ 'በገነት ካለው ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ' ብሏችኋል?" በማለት ጠየቃት
Genesis 3:4
ሴቲቱ በገነት መካከል ካለው ዛፍ ከበሉ እንደሚሞቱ እግዚአብሔር እንደነገራቸው በተናገረች ጊዜ እባቡ ምን አለ?
እባቡ፣ "በእርግጥ አትሞቱም" አለ
እባቡ የተናገረው፣ ሰውየውና ሴቲቱ ከፍሬው ከበሉ ምን እንደሚሆኑ ነበር?
እንደ እግዚአብሔር እንደሚሆኑ፣ መልካምንና ክፉን እንደሚያውቁ እባቡ ተናገረ
ሴቲቱን ወደ ሕይወት ዛፍ የሳባት ምን ነበር?
ሴቲቱ ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደሆነ፣ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፣ ለጥበብም መልካም እንደሆነ አየች
ፍሬውን የበላው ማን ነበር?
ሴቲቱ በላች፣ ለባሏ ጥቂት ሰጠችውና እርሱም ደግሞ በላ
Genesis 3:7
ፍሬውን በበሉ ጊዜ ምን ሆኑ?
በበሉ ጊዜ ዓይኖቻቸው ተከፈቱና ራቁታቸውን እንደሆኑ አወቁ
Genesis 3:9
እግዚአብሔር ወደ አትክልቱ ስፍራ በመጣ ጊዜ ሰውየውና ሴቲቱ ምን አደረጉ?
ከእግዚአብሔር ተደበቁ
እግዚአብሔር ወደ አትክልቱ ስፍራ በመጣ ጊዜ ሰውየው ከእርሱ የተደበቀው ለምን ነበር?
ሰውየው ራቁቱን በመሆኑና በመፍራቱ ምክንያት ከእግዚአብሔር ተደበቀ
Genesis 3:12
ሰውየው፣ ፍሬውን ለእርሱ በመስጠቷ ምክንያት ተጠያቂ ያደረገው ማንን ነበር?
ሰውየው፣ ሴቲቱ ተጠያቂ ናት አለ
Genesis 3:14
ሴቲቱ፣ ፍሬውን ለእርሷ በመስጠቱ ምክንያት ተጠያቂ ያደረገችው ማንን ነበር?
ሴቲቱ፣ እባብ ተጠያቂ ነው አለች
እግዚአብሔር፣ በእባቡና በሴቲቱ መካከል ምን ዓይነት ግንኙነት እንዲኖር አደርጋለሁ አለ?
እግዚአብሔር እርስ በእርሳቸው እንዲጠላሉ እንደሚያደርጋቸው ተናገረ
Genesis 3:16
እግዚአብሔር ልጅ መውለድን አስመልክቶ ሴቲቱን ምን ብሎ ረገማት?
ሴቲቱ በምትወልድበት ጊዜ ሕመሟን እጅግ አበዛው
Genesis 3:17
ሰውየው ስለ ሠራው ሥራ እግዚአብሔር ምን ብሎ ረገመው?
ሰውየው በብርቱ ድካም ብቻ ከእርስዋ እንዲበላ እግዚአብሔር ምድርን ረገማት
Genesis 3:20
ሰውየው ለሴቲቱ ምን የሚል ስም ሰጣት? ለምን?
ሰውየው፣ የሕያዋን ሁሉ እናት ስለሆነች ሴቲቱን ሔዋን ብሎ ጠራት
እግዚአብሔር ለአዳምና ለሔዋን ምን አደረገላቸው? ለምን?
እግዚአብሔር ያለብሳቸው ዘንድ የቁርበትን ልብስ አደረገላቸው
Genesis 3:22
እግዚአብሔር፣ አሁን አዳም ከሕይወት ዛፍ መብላት የለበትም ያለው ለምን ነበር?
እግዚአብሔር፣ አዳም አሁን መልካምንና ክፉን አውቋልና ለዘላለም እንዳይኖር ከሕይወት ዛፍ መብላት የለበትም አለ
አዳም ከሕይወት ዛፍ እንዳይበላ ለመከላከል እግዚአብሔር ምን አደረገ?
እግዚአብሔር ሰውየውን ከገነት አስወጣው፣ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልን በዚያ አስቀመጠ