ምዕራፍ 7

1 የባቢሎን ንጉሥ ቤልሻዘር በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት ዳንኤል በአልጋው ላይ ተኝቶ ሳለ ሕልም አለመ፤ ራእይም አየ፤ የሕልሙንም ዋና ሃሳብ ጻፈው። 2 ዳንኤል እንዲህ አለ፤ “ኣቱ የሰማይ ነፋሳት ታላቁን ባሕር ሲያናውጡት ሌሊት በራእይ አየሁ፤ 3 እርስ በርሳቸው የማይመሳሰሉ አራት ታላላቅ አራዊት ከባሕሩ ወጡ። 4 የመጀመሪያው አንበሳ ይመስል ነበር፤ የንስርም ክንፎች ነበሩት፤ ክንፎቹ እስኪነቃቀሉ ድረስ ትመለከትሁ፤ እንደ ሰው በሁለት እግር እንዲቆም ከመድር ከፍ ከፍ ተደረገ፤ ሰብዓዊ አእምሮ ተሰጠው። 5 እነሆም ሁለተኛው አውሬ ድብ ይመስል ነበር፤ በአንድ ጎኑ ከፍ ብሎአል፤ በአፉ ውስጥ በጥርሶቹ መካከል ሦስት የጎድን አጥንቶች ነበርት። እርሱም፤ “ተነሥ እስክትጠግብ ድረስ ሥጋ ብላ” ተባለ። 6 ከዚህ በኋላ ተመለክትሁ፤ በፊቱ በኩል ነብር የሚመስል ሌላ አውሬ ነበር፤ በጀርባውም በኩል የወፍ ክንፍ የሚመስሉ አራት ክንፎች ነበርት፤ ይህ አውሬ አራት ራስ ነበረው፤ ለመግዛትም ሥልጣን ተሰጠው። 7 ከዚህ በኋላ በሌሊት ራእይ አየሁ፤ በፊቴም የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ በጣም ኃይለኛ የሆነ አራተኛ አውሬ ነበር፤ ትልቅ የብረት ጥርሶች ነበሩት፤ ያደቅና ይበላ፣ የቀረውንም ሁሉ በእግሮቹ ይረጋግጥ ነበር። ከእርሱ በፊት ከነበሩት አራዊት ሁሉ የተለየ ሲሆን፤ አሥር ቀንዶች ነበሩት። 11 ቀንዱም ከሚናገረው የትዕቢት ቃል የተነሣ፣ መመልከቴን ቀጠልሁ፣ አውሬው እስኪታረድና እካሉድቆ ወደሚንበለበለው እሳት እስኪጣል ድረስ ማየቴን አላቋርጥሁም። 12 ሌሎቹም አራዊት ሥልጣናቸው ተገፎ ነበር፤ ነገር ግን ለተወሰነ ጊዜና ወቅት በሕይወት እንዲኖሩ ተፈቀደላቸው። 13 ሌሊት ባየሁት ራእይ የሰውን ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመና ጋር ሲመጣ አየሁ፤ ወደ ጥንታዌ ጥንቱ መጣ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት። 14 ሥልጣን፣ ክብርና ታላቅ ኃይል ተሰጠው፤ በልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች፤ መንግሥታትና ሕዝቦች ሰገዱለት፤ ግዛቱም ለዘላለም የማያልፍ ነው፤ መንግሥቱም ፈጽሞ የማይጠፋ ነው። 15 እኔ ዳንኤል በመንፈሴ ታወክሁ፤ ያየሁትንም ራእይ እጅግ አስጨነቀኝ። 16 በዚያ ከቆሙት ወደ አንዱ ቀርቤ የዚህ ሁሉ ትርጕም ምን እንደ ሆነ ጠየቅሁት። 17 “አራቱ ታላላቅ አራዊት ከምድር የሚነሡ መንግሥታት ናቸው፤ 18 ነገር ግን የልዑሉ ቅዱሳን መንግሥቱን ይወስዳሉ፣ ለዘላለምም ይይዙታል። 19 ከዚያም የሚያደቅቀውንና የሚበላውን የቀረውንም ሁሉ በእግሮቹ የሚረጋግጠውን የብረት ጥርሶችና የናስ ጥፍሮች የነበሩትን ከሌሎች የተለየና እጅግ አስፈሪ የሆነውን የአራተኛውን አውሬ ምንነት የበለጠ ማወቅ ፈለግሁ። 20 ደግሞም በራሱ ላይ ስላሉት አሥር ቀንዶች፣ ከመካከላቸው ብቅ ስላለው ቀንድና ከዚሁ ቀንድ ፊት ስለተነቃቀሉት ሦስት ቀንዶች፣ እንደዚሁም ከሌሎች ስለበለጠው የሰው ዓይኖች የሚመስሉ ዓይኖች በትዕቢትም የሚናገር አፍ ስለነበሩት ስለዚሁ ቀንድ ማወቅ ፈለግሁ። 21 እየተመለክትኩም ሳለሁ ይህ ቀንድ በቅዱሳን ላይ ጦርነት ዐውጆ አሸነፋቸው። 22 ይህም የሆነው ጥንታዌ ጥንቱ እስኪመጣና ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪፈርድላቸው ድረስ ነበር፤ ኪዝያም የልዑሉ ቅዱሳን መንግሥቱን የሚወርሱበት ዘመን መጣ። 23 እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “አራተኛው አውሬ በምድር ላይ የሚነሣ አራተኛው መንግት ነው። ከሌሎች መንግሥታት ሁሉ የተለየ ይሆናል፤ መላውንም ምድር እየረገጠና እያደቀቀ ይበላል። 24 ዐሥሩ ቀንዶች ከዚህ መንግሥት የሚወጡ ዐሥር ነገሥታት ናቸው፤ ከዚያም በኋላ ከእነርሱ የተለየ ሌላ ንጉሥ ይነሣል፤ ሦስቱንም ነገሥታት ያንበረክካል። 25 በልዑል ላይ የዓመፅ ቃል ይናገራል፤ የልዑልንም ቅዱሳን ያስጨንቃል፤ ለበዓላት የተመደበውን ጊዜና ሕግን ለመለወጥ ይሞክራል፤ እነዚህም ነገሮች ለዘመን፣ ለዘመናት፣ ለዘመን እኩሌታም ለእርሱ ዐልፈው ይሰጣሉ። 26 ነገር ግን የፍርድ ዙፋን ይዘረጋል፤ ሥልጣኑም ይወሰድበታል፤ ፈጽሞ ለዘላለም ይደመሰሳል። 27 ከዚያም ከሰማይ በታች ያሉ መንግሥታት ልዕልና፣ ሥልጣንና ታላቅነት ለልዑሉ ሕዝብ ለቅዱሳን ይሰጣል። መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ይሆናል፤ ገዦች ሁሉ ያመልኩታል ይታዘዙታልም። 28 የነገሩ ፍጻሜ ይህ ነው፤ እኔም ዳንኤል በሃሳቤ እጅግ ተጨነቅሁ፤ መልኬም ተለወጠ፤ ይሁን እንጂ ነገሩን በልቤ ጠበቅሁት።