1 “ያህዌ አምላካችን ፈጥናችሁ ወደምትገቡባትና ወደምትወርሷት ምድር ያመጣችኋል፡፡ ወደ ምድሪቱ ስትቃረቡ፣ ከእናንተ ይልቅ ይበልጥ ሀይለኛ የሆኑትንና በቁጥር ብዙ የሆኑትን ሰባት የህዝብ ወገኖች ከዚያ ምድር ያባርራቸዋል፡፡ እነዚህም ህዝቦች ኬጢያውያን፣ ጌርጌሳውያን፣ አሞራውያን፣ ከነዓናውያን፣ ፌርዛውያን፣ ኤዊያውያን፣ እና ኢያቡሳውያን ናቸው፡፡