1ከዚያ ሙሴ ከዮርዳኖስ ወንዝ ባሻገር ኢያሪኮ ከሚገኘው ሞአብ አካባቢ ሜዳዎች ወደ ናባ ተራራ፣ ወደ ፈስጋ ተራራ ጫፍ ወጣ፡፡ በዚያም ያህዌ እስራኤላዊያን የሚወርሱትን ምድር ሁሉ አሳየው፡፡ የገለአድን አካባቢ እስከ ዳን ከተማ ሰሜን ድረስ አሳየው፤ 2የንፍታሌም ነገድ የሚወርሰውን ምድረ ሁሉ፤ የኤፍሬምና የምናሴ ነገዶች የሚወርሱትን ምድር፣ የይሁዳ ነገድ የሚወርሰውን ምድር እስከ ምዕራብ ሜድትራኒያን ባህር ድረስ 3በይሁዳ ደቡባዊ ክፍል በረሃማውን አካባቢ፣ እና በሰሜን እስከ ከኢያሪኮ በደቡብ እስከ ዞር ከተሞች የሚደርሰውን የዮርዳኖስን ሸለቆ አሳየው፡፡