13

1ምናልባት ነብያት ነን የሚሉ ሰዎች ሊነሱ ይችላሉ፡፡ ህልሞችን መተርጎም ወይም የተለያዩ ተአምራትን ማድረግ እንችላለን ሊሉ ይችላሉ፡፡ 2እነዚያን ነገሮች የሚናገሩት አንተን ከዚህ በፊት በፍጹም የማታውቃቸውን አማልዕክት እንድታመልክ ለመገፋፋት ነው፡፡ ነገር ግን ይሆናል ያሉት ቢፈጸም እንኳን 3ለተናገሩት ነገር ትኩረት አትስጥ፡፡ ያህዌ አምላካችን እርሱን በውስጣዊ ማንነትህ ትወደው እንደሆነ ለማወቅ ይፈትንሃል፡፡