21

1 ለአብርሃም በሰጠው የተስፋ ቃል መሰረት እግዚአብሔር ሳራን አሰባት፤ እንደገባላት የተስፋ ቃልም አደረገ ፤ 2 ስለዚህም ሳራ አርግዛ በእርጅናው ጊዜ ለአብርሃም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ልጁም የተወለደው «በዚህ ጊዜ ይወለዳል» ብሎ እግዚአብሔር በተናገረበት ጊዜ ነው። 3 አብርሃም ሚስቱ ሳራ የወለደችለትን ልጅ «ይስሐቅ» ብሎ ስም አወጣለት። 4 ይስሐቅ ከተወለደ ከስምንት ቀን በኋላ እግዚአብሔር ባዘዘው መሰረት አብርሃም ገረዘው። 5 ልጁ ይስሐቅ በተወለደለት ጊዜ አብርሃም መቶ ዓመት ሆኖት ነበር። 6 ሳራም «እግዚአብሔር ሳቅ አደረገልኝ ስለዚህ ይህንን ነገር የሚሰማ ሁሉ ከእኔ ጋር ይስቃል»አለች። 7 ቀጥላም «ሳራ ለአብርሃም ልጆችን ወልዳ ታጠባለች» ብሎ የሚናገር ከቶ ማን ነበር አሁን ግን እነሆ በእርጅናው ዘመን ወንድ ልጅ ወለድሁለት» አለች። 8 ልጇም አድጎ ጡት መጥባት ተወ፤ ጡት ባስጣሉበትም ቀን አብርሃም ታላቅ ግብዣ አደረገ። 9 ግብጻዊትዋ አጋር ለአብርሃም የወለደችለት እስማኤል ከዕለታት አንድ ቀን በሳራ ልጅ በይስሐቅ ላይ ሲያሾፍበት ሳራ አየች። 10 ስለዚህ ሳራ አብርሃምን«ይህችን አገልጋይ ከነ ልጅዋ ወዲያ አባርልኝ የዚህች አገልጋይ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አብሮ መውረስ አይገባውም» አለችው። 11 እስማኤልም ልጁ ስለሆነ ይህ ጉዳይ አብርሃምን በብርቱ አስጨነቀው 12 እግዚአብሔር ግን አብርሃምን «ስለ ልጁና ስለ አገልጋይቱ ስለ አጋር አትጨነቅ። ዘር የሚወጣልህ በይስሃቅ በኩል ስለሆን እርሳ የምትልህን ሁሉ አድርግ። 13 የአገልጋይቱም ልጅ የአንተ ዘርያ ስልሆን ታላቅ ሕዝብ አደርገዋለሁ» አለው 14 አብርሃም በማለዳ ተነሳ ጥቂት ምግብ ውሃም በአቁማዳ ለአጋር በትከሻዋ አደረገላት። ልጁንም በጀርባዋ አሳዝሎ ከቤት አስወጣት፤ እርስዋም በቤርሳቤህ በረሃ ትንከራተት ጀመር። 15 በአቁማዳ የነበረው ውሃ ባለቀ ጊዜ ልጁን በቁጥቋጦ ስር አስቀምችጠችው። 16 እርስዋም «ልጄ ሲሞት ማየት አልፈልግም» በማለት ጥቂት ከልጅዋ ርቃ ተቀመጠች፤ እዚያም ሆና ድምጻን ከፍ አድርጋ ታለቅስ ጀመር። 17 እግዚአብሔሬም ልሉ ምርር ብሎ ሲያለቅስ ሰማ የእግዚአብሔርም መልአክ ከሰማይ አጋርን «አጋር ሆይ የምትጨነቂበት ነገር ምንድር ነው? እግዚአብሔር የልጂን ለቅሶ ሰምቶአልና አትፍሪ። 18 ተነሺ ሂንና ልጁን አንስተስ አባብይው፤ የእርሱንም ዘር አበዛለሁ ታላቅ ሕዝብም አደርገዋለሁ። 19 በዚህም ጊዜ እግዚአብሔር ዓይኖችዋን ከፈተላትና አንድ የውኃ ጉድጋድ አየች፤ ሄዳም በአቁማዳ ውሃ ሞላች ለልጅዋም አጠጣችው። 20 ልጁ እያደገ በሚሄድበት ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበር። 21 በፋራንም በረሓ ኖረ፤ ቀስት በመወርወርም የታወቀ አዳኝ ሆነ። እናቱም ከአንዲት ግብጻዊት ጋር አጋባችው። 22 በዚያን ጊዜ አቤሜሌክ ከሰራዊቱ አለቃ ከፊኮል ጋር ሄደና አብርሃምን «በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤ 23 እኔንም ሆነ ልጆቼን ወይም ዝርያዎቼን እንዳትዋሸኝ አሁን በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ። እኔ ለአንተ ታማኝነትን አሳይቻለሁ፤ አንተም ለእኔና ለዚህች ለምትኖርባትአገር ታማኝንትን እንደምታሳይ ማልልኝ» አለው። 24 አብርሃምም «እሺ እምላለሁ» አለ። 25 አብርሃም የአቢሜሌክ አገልጋዮች ስለ ወሰዱበት የውሃ ጉድጋድ ለአቤሜሌክ አቤቱታ አቀረበ፤ 26 አቤሜሌክም «ይህን ያደረገ ማን እንደሆን አላውቅም። አንተም አልነገርኸኝም ይህንን ነገር ገና ዛሬ መስማቴ ነው» አለው። 27 ከዚህ በኋላ አብርሃም ብዙ በጎችና ከብቶች አምጥቶ ለአቢሜሌክ ሰጠው፤ በዚያን ቀን ሁለቱም የስምምነት መሀላ አደረጉ። 28 በዚያን ጊዜ አብርሃም ሰባት እንስት የበግ ጠቦቶችን ከመንጋው ለየ፤ 29 አቤሜሌክም «እንዚህን ሰባት ጠቦቶች ለይተህ ያቆምሃቸው ለምንድር ነው?» አለው። 30 አብርሃምም «እነዚህን ሰባት እንስት ጠቦቶች ተቀበለኝ እነርሱን ከተቀበልከኝ ይህን ጉድጋድ የቆፈርሁ እኔ መሆኔን ምስክር እንዲሆን ነው» አለው፤ 31 ሁለቱ ተማምለው የተስማሙበት ስፍራ በመሆኑ የዚያ ቦታ ስም ቤርሳቤህ ተባል፤ 32 ይህን ስምምንት በቤርሳቤህ ተስማምተው ካደረጉ በኋላ አቤሜሌክና የሰራዊቱ አለቃ ፊኮል ወደ ፍልስጥኤም ምድር ተመለሱ 33 ከዚህ ብኃላ አብርሃም በቤርሳቤህ የታማሪስክ ዛፍ ተከልና የዘላለም አምላክ ለሆነው ሰገደ፤ 34 አብርሃም በፍልስጥኤም ምድር በእንግድነት ለረዥም ጊዜ ኖረ።