ምዕራፍ 1
1
ዳርዮስ በፋርስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ስምንተኛው ወር የእግዚአብሔር ቃል ወደ አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ዘካሪያስ እንዲህ ሲል መጣ፡-
2
"በአባቶቻችሁ ተቆጥቼ ነበር፤
3
ስለዚህም ይህንን ለሕዝብ ተናገር ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡- “ወደ እኔ ተመለሱ፤ ከተመለሳችሁ እንደ ቀድሞው ከእናንተ ጋር እሆናለሁ፡፡
4
እንደ አባቶቻችሁ አትሁኑ፡፡ አባቶቻችሁ ከክፉ ሥራቸው እንዲመለሱ አሁን በሕይወት የሌሉ ነቢያቴ ነገሯቸው፡፡ ነገር ግን እነርሱ ጆሯቸውን አልሰጧቸውም፡፡
5
አባቶቻችሁ ሞተው አሁን በመቃብር ናቸው፡፡ እንኳን እነርሱ ነቢያቱም ለዘላለም አልኖሩም፡፡
“በነቢያቴ የተነገራቸውን ወግና ሥርዓት አልታዘዙምና ቀጣኋቸው፡፡
6
እነርሱም ተጸጽተው የሆነባቸው ነገር ሁሉ በኃጢአታቸው ምክንያት እንደመጣባቸው ተናገሩ፡፡”
7
በአስራ አንደኛው ወር ሃያ አራተኛው ቀን እግዚአብሔር ሌላ መልእክት ሰጠኝ፡፡
8
በምሽት ራእይ አየሁ፤ መልአክ በቀይ ፈረስ ላይ ተቀምጦ አየሁ፡፡ በጠባብ ሸለቆ ውስጥ በባርሰነት ዛፎች መካከል ቆሞ ነበር፡፡ ከኋላው ሌሎች መላእክት በቀይ፣ በቡኒና በነጭ ፈረሶች ላይ ተቀምጠው ነበር፡፡
9
አንደኛውን መልአክ ጠየቅሁት፡- “ጌታዬ ሆይ፣ ፈረሶቹ ላይ ያሉት መላእክት እነማን ናቸው?” እርሱም መለሰልኝ፡- “ማንነታቸውን አሳይሃለሁ፡፡”
10
ከዚያም በባርሰነት ዛፎች ስር ቆሞ የነበረው መልአክ እንዲህ አለ፡- “እነዚህ በመላው ዓለም እየተዘዋወሩ የሚጠብቁ መላእክት ናቸው፡፡”
11
ሌሎቹ መላእክት ከባርሰነት ዛፍ ስር ቆሞ ለነበረው መልአክ እንዲህ ብለው ነገሩት፡- “እነሆ በመላው ዓለም ዞርን፤ የንጉሠ ነገሥቱ ሠራዊት በዓለም ዙሪያ ያሉ አገሮችን ይዟል፤ አገሮቹም አቅመ ቢስ እና የደነዘዙ ሆነዋል፡፡”
12
መልአኩም እንዲህ ሲል ጠየቀ፡- “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ባሉት ላይ ምሕረት የማታደርገው እስከመቼ ነው? ለሰባ ዓመታት ተቆጣሃቸው!”
13
እግዚአብሔርም ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረው መልአክ በመልካምና በሚያጽናና ቃል ተናገረው፡፡
14
ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ፡- "ለኢየሩሳሌም ሕዝብ ተናገር፡፡ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጽዮን እና በተቀሩት የእየሩሳሌም አካባቢዎች ስላሉት ሕዝቦች ቀንቷል፡፡
15
በሚታበዩ እና በሚመኩት ዝቦች ላይ ተቆጥቷል፡፡ ስቃይ ባመጡባቸው በይሁዳ ሕዝቦችም ደስ አልተሰኘም፡፡
16
ስለዚም እግዚአብሔር ወደ እየሩሳሌም ተመልሶ ሕዝቡን ይረዳል፡፡ እርሱ እየሩሳሌምን አስቀድሞ በገመድ እንደለካ ሰው ያውቃታልና፡፡
17
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በይሁዳ ከተሞች ላሉት እንዲ ብለ ተናገር አለኝ፡፡ ደግመው በበጎ ነገር ይረካሉ፡፡ እግዚአብሔር እየሩሳሌምን ደግሞ ያጽጽናናታል፡፡ በድጋሚም የተለየች አድርጎ ይመርጣታል፡፡"
18
ከዚያም አይኖቼን አንስቼ ከፊት ለፊቴ አራት የእንሰሳት ቀንዶችን አየሁ፡፡
19
ሲያናጋግረኝ የነበረውን መልአክ "እነዚ ቀንዶች ምንድር ናቸው?" ብዬ ጠየቅሁት፡፡ እርሱም መለሰልኝ፡፡ "እነዚ የእየሩሳሌም፤ ይሁዳ እና እስራኤል ሕዝቦችን አስገድደው ወደ ሌሎች ሀገሮች የበተኗቸውን ይወክላሉ፡፡"
20
ከዚያም እግዚአብሔር አራት ጠራቢዎችን አሳየኝ፡፡
21
እኔም "እነዚ ሰዎች የመጡት ምን ሊሰሩ ነው?" ብዬ ጠየቅሁት፡፡ እርሱም መለሰልኝ፡፡ "በቀንዶቹ የተወከሉት ሕዝቦች የይሁዳን ሰዎች በትነዋልና ብዙ መከራ ይመጣባቸዋል፡፡ እነዚ ጠራቢዎችም የመጡት አነርሱን ለማስጨነቅና ለማጥፋት ነው፡፡ ሌሎቹንም የይሁዳ ሕዝቦች ያጠቁት ሁሉ ቀንዶቻቸውን እና ሥልጣናቸውን ይጥሉባቸዋል፡፡"