ምዕራፍ 1
1
የእግዚአብሔር ባሪያና፣የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነው ጳውሎስ፣ በእግዚአብሔር የተመረጡት ሰዎች እምነት እንዲጸና፣ እግዚአብሔርን ከመምሰል ጋር የሚስማማውን የእውነት እውቀት ለማፅናት፣
2
የማይዋሽ እግዚአብሔር፣ በተረጋገጠ ዘላለማዊ ሕይወት ከዘመናት በፊት ተስፋን ሰጠ፣
3
እንደ መድሃኒታችን እግዚአብሔር ትዕዛዝ፣ በትክክለኛው ጊዜ፣ ቃሉን ለእኔ አደራ በሰጠኝ መልዕክት ገለጠ፡፡
4
የጋራችን በሆነ እምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነ ለቲቶ። ከእግዚአብሔር አብ፣ከመድሃኒታችን ክርስቶስ ኢየሱስ ፀጋ፣ምህረትና ሰላም ለአንተ ይሁን።
5
አንተን በቀርጤስ የተውኩበት ምክንያት፣ ያልተጠናቀቁትን ነገሮች እንድታስተካክልና፣ በነገርኩህ መሠረት በየከተማው ሁሉ ሽማግሌዎችን እንድትሾም ነው፡፡
6
የቤተክርስቲያን ሽማግሌ፣ ነቀፋ የሌለበት፣የአንዲት ሚስት ባል፣ ከክፍዎችና ካልታረሙ ጋር ስማቸው የማይነሳ ታማኝ ልጆች ያሉት ሊሆኑ ይገባዋል።
7
የቤተክርስቲያን ሽማግሌ የእግዚአብሔርን ቤት የሚያስተዳድር መሪ ስለሆነ ነቀፋ የሌለበት፣ የማይጮህ፣ራሱን የሚገዛ ፣የማይቆጣ ፣ለወይን ጠጅ የማይገዛ፣ የማይጣላና ስስታም ያልሆነ ሊሆን ይገባል።
8
ነገር ግን እንግዳ ተቀባይ፣ መልካምን የሚወድ፣ ጠንቃቃ፣ ጻድቅ፣ መንፈሳዊና ራሱን የሚገዛ መሆን አለበት።
9
በጤናማ ትምህርት ሌሎችን ለማበረታታት፣ የሚቃወሙትን ለመገሠጽ እንዲችል እውነተኛውን ትምህር አጥብቆ መያዝ ይኖርበታል።
10
ሥርዓት የሌላቸው በተለይም ከተገረዙት ወገን የሆኑ ብዙዎች አሉ። ቃላቸው ከንቱ ነው። ሰዎችን ያስታሉ፣ በተሳሳተ መንገድም ይመራሉ።
11
እነዚህን ዝም ማሰኘት ይገባል። ለነውረኛ ትርፍ ብለው ማስተማር የማይገባቸውን እያስተማሩ፣ መላ ቤተሰብን ያፈርሳሉ።
12
ከነሱ ከራሳቸው ነብያት መካከል አንዱ፣ ''የቀርጤስ ሰዎች ዘወትር ውሸተኞች፣ ክፉና አደገኛ አውሬዎች፣ ሰነፍ ሆዳሞች ናቸው'' ብሏል፡፡
13
ይህም አባባል ትክክል ነው፣ ስለዚህ ጤነኛ እምነት እንዲኖራቸው አጥብቀህ ገሥጻቸው ።
14
ጊዜያቸውን በአይሁድ ተረትና፣ ከእውነት በራቁ ሰዎች ትዕዛዛት ላይ አያባክኑ።
15
ንጹሆች ለሆኑት፣ ሁሉም ንጹህ ነው፣ ለርኩሶችና ለማያምኑ ግን ንጹህ የሆነ ምንም የለም። ይልቁን፣ አዕምሯቸውና ሃሳባቸው እንኳ የረከሰ ነው፡፡
16
እግዚአብሔር እንደሚውያቁ ይናገራሉ፣ በሥራቸው ግን ይክዱታል። የሚያስጸይፉ የማይታዘዙና፣ ለመልካም ስራም የማይበቁ ናቸው፡፡