1 ከዚያም መልአኩ፣ እንደ መስተዋት የጠራውን የሆነውን የሕይወት ውሃ ወንዝ አሳየኝ። ወንዙም የሚወጣው ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን ነበር 2 በከተማዋ ዋና መንገድ መካከል ያልፍ ነበር። በወንዙ ግራና ቀኝ አሥራ ሁለት ወር ሙሉ አሥራ ሁለት ዓይነት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበር። የዛፉ ቅጠሎች ሕዝቦችን ሁሉ ይፈውሱ ነበር። 3 ከእንግዲህ ምንም ዐይነት መርገም አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉ ዚፋን ከተማው ውስጥ ይሆናሉ፤ አገልጋዮቹም ያገለግሉታል። 4 ፊቱን ያያሉ፤ ስሙም ግንባሮቻቸው ላይ ይሆናል። 5 ከእንግዲህ ሌሊት አይሆንም፤ ጌታ አምላክ ስለሚያበራላቸው የመብራት ወይም የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም። ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ። 6 መልአኩም እንዲህ አለኝ፤ “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛ ናቸው። ጌታ፣ የነቢያት መናፍቅ አምላክ ቶሎ መሆን ያለበትን ለአገልጋዮቹ እንዲያሳያቸው መልአኩን ላከ።” 7 “እነሆ፣ ቶሎ እመጣለሁ! ለዚህ መጽሐፍ የትንቢት ቃሎች የሚታአእ የተባረከ ነው። 8 እነዚህን ነገሮች የሰማሁና ያየሁ እኔ ዮሐንስ ነኝ። እነዚህን በሰማሁና ባይብሁ ጊዜ እነዚህን ነገሮች ላሳየኝ መልአክ ለመስገድ በፊቱ ተደፋሁ። 9 እርሱ ግን፣ “እንዳታደርገው! እኔ ራሴ ከወንድሞችህ ከነቢያት ጋር፣ ለዚህ መጽሐፍ ቃል ከሚታዘዙት ጋር አብሬ አገልጋይ ነኝ። ይልቅ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ!” 10 እንዲህም አለኝ፤ ጊዜው በጣም ቅርብ ስለሆነ የዚህን መጽሐፍ የትንቢት ቃሎች በማኅተም አትዝጋው። 11 ዐመፀኛው ማመፁን ይቀጥል። ርኩሱም ርኩሰት ማድረጉን ይቀጥል። ጻድቁም ጽድቅ የሆነውን ማድረጉን ይቀጥል። ቅዱስም ቅዱስ መሆን ይቀጥል። 12 “እነሆ፣ ቶሎ እመጣለሁ። ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው የምከፍለው ዋጋ ከእኔ ዘንድ አለ። 13 እኔ አልፋና ዖሜጋ፣ ፊተኛውና ኋለኛው፤ የመጀመሪያውና የመጨረሻው ነኝ። 14 ከሕይወት ዛፍ ለመብላትና በበሮቿ ወደ ከተማዋ ለመግባት መብት እንዲኖራቸው ልብሳቸውን የሚያጥቡ የተባረኩ ናቸው። 15 ውሾች፣ ጠንቋዮች፣ አመንዝራዎች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ጣዖት አምላኪዎችና ሐሰትን የሚወዱና የሚያደርጉ ግን በውጭ አሉ። 16 እኔ ኢየሱስ ለእናንተ እንዲመሰክር መልአኬን ወደ አብያተ ክርስቲያናት ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርጥ ዘር ነኝ፤ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።” 17 መንፈሱና ሙሽራይቱ፣ “ና!” ይላሉ፤ የሚሰማ ሁሉ፣ “ና!” ይበል። ማንም የተጠማ ቢኖር ይምጣ፣ የሚፈልግ የሕይወትን ውሃ በነጻ ይውሰድ። 18 የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ለሚሰሙ ሁሉ እኔ እመሰክራለሁ፣ ማንም ትንቢቱ ላይ ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል። 19 ማንም ከዚህ መጽሐፍ ትንቢት ቢያጎድል እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ ከተጻፈው የሕይወት ዛፍና ቅድስት ከተማ ዕድሉን ያጎልበታል። 20 ለእነዚህ ነገሮች የሚመሰክር እርሱ፣”አዎን! ቶሎ እመጣለሁ” አሜን! ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና! ይላል። 21 የጌታ ኢየሱስ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን