መዝሙር 1

1 በክፉዎች ምክር የማይሄድ በኃጢአተኞች መንገድ የማይቆም በፌዘኞች ወንበር የማይቀመጥ ምስጉን ነው፡፡ 2 ነገር ግን ደስ የሚሰኘው በያህዌ ሕግ ነው ሕጉንም ቀንና ሌሊት ያሰላስላል፡፡ 3 እርሱም ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፣ ቅጠሏም እንደማይጠወልግ፣ በወራጅ ውሆች እንድ ተተከለች ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል፡፡ 4 ኃጢአተኞች ግን እንዲህ አይደሉም ነገር ግን ነፋስ ጠራርጐ እንደሚወስደው ገለባ ናቸው፡፡ 5 ስለዚህ ክፉዎች በፍርድ ኃጢአተኞችም በጻድቃን ጉባኤ አይቆሙም፡፡ 6 ያህዌ የጻድቃንን አካሄድ ይጠብቃልና የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች፡፡