1 2 3 1. ከባለ ሥልጣን ጋር ለመመገብ አንድ ገበታ ላይ ብትቀርብ ማንነቱን አትዘንጋ፤ 2. ለመብላት ብትጓጓ እንኳ ብዙ እንዳትበላ ጉሮሮህ ላይ ካራ አጋድምበት 3. ምግቡ ሊያስትህ ስለሚችል የእርሱ ጣፋጭ መብል አያስጐምጅህ፡፡ 4 5 4. ሀብታም ለመሆን ብዙ አትድከም፤ ይልቁን ጠቢብ ሁን፤ መቼ ማረፍ እንደሚገባህም ዕወቅ፡፡ 5. እንዲህ ዐይነቱ ሀብት እያየኸው ወዲያውኑ ይጠፋል፤ ወደ ሰማይ እንደሚበር ንስር ድንገት ክንፍ አውጥቶ ይበራል፡፡ 6 7 8 6. የስስታምን ምግብ አትብላ ጣፋጭ መብሉም አያስጐምጅህ፤ 7. እርሱ የሚያስበው አንተ የምትበላውን ምግብ ዋጋ ነው፤ በአፉ ‹‹ብላ ጠጣ›› ይልሃል፤ ይህን የሚለው ግን ከልቡ አይደለም፡፡ 8. እውነተኛ ዓላማውን ስትረዳ፤ የበላኸውን ብታስወጣው ትፈልጋለህ፤ ስለ ጣፋጭ ምግቡ ያቀረብከው ምስጋና ባክኖ ይቀራል፡፡ 9 10 11 9. የምትነግረውን የጥበብ ቃል ስለሚያንኳስስ ከጅል ጋር በማውራት ጊዜህን አታባክን፡፡ 10. የቆየውን ድንበር አታፍልስ፤ አባትና እናት የሌላቸው ልጆችን መሬት አትቀማ፡፡ 11. ታዳጊያቸው ብርቱ ስለሆነ እርሱ ይፈርድላቸዋል፡፡ 12 12. ትኩረትህን ትምህርትህ ላይ አድርግ፤ የዕውቀትንም ቃል ከልብህ አድምጥ፡፡ 13 14 13. ልጆችህን ቀጥተህ ሥርዐት ከማስያዝ ወደ ኃላ አትበል፤ 14. በአርጩሜ ብትመታቸው አይሞቱም፤ እንዲያውም ሕይወታቸውን ከሞት ታድናለህ፡፡ 15 16 15. ልጄ ሆይ፣ ጠቢብ ብትሆን እኔን በጣም ደስ ይለኛል፤ 16. ተገቢውን ቃል በምትናገርበት ጊዜ ኩራት ይሰማኛል፡፡ 17 18 17. በኃጢአተኞች አትቅና፤ ይልቁን ቀኑን ሙሉ ያህዌን በመፍራት ኑር፡፡ 18. እርሱን ብትፈራ የወደ ፊት ኑሮህ ይከወናል ተስፋህም አይቋረጥም፡፡ 19 20 21 19. ልጄ ሆይ፣ እኔን አድምጥ ጠቢብም ሁን፤ እንዴት መኖር እንዳለብህ ረጋ ብለህ አስብ፡፡ 20. የወይን ጠጅ ከሚያዘወትሩና ከመጠን በላይ ከሚበሉ ጋር ጓደኛ አትሁን፤ 21. ሰካራሞችና ሆዳሞች ይደኸያሉ፤ እንቅልፍ ማብዛትም ቡቱቶ ያስለብሳል፡፡ 22 23 22. የወለደህን አባትህን አድምጥ፤ እናትህም ባረጀች ጊዜ አትናቃት፡፡ 23. ጥበብን ስትማር እውነትን ግዛት እንጂ አትሽጣት፤ ጥበብን፣ ተግሣጽና ማስተዋልን ገንዘብ አድርግ፡፡ 24 25 24. የጨዋ ልጅ አባት በጣም ደስ ይለዋል፤ ብልኅ ልጅ የወለደም ኩራት ይሰማዋል፡፡ 25. አባትና እናትህ በአንተ ደስ ይበላቸው፤ እናትህም በአንተ ሐሤት ታድርግ፡፡ 26 27 28 26. ልጄ ሆይ፣ የምነግርህን ልብ ብለህ አድምጥ፤ አኗኗሬም ምሳሌ ይሁንህ፡፡ 27. አመንዝራ ሴት በቀላሉ የሚወደቁበት፣ ሆኖም ለመውጣት እንደሚያዳግት ጥልቅ ጉድጓድ ናት፣ የሌላ ሚስት የሆነችውም ጠባብና አደገኛ ጉድጓድ ናት፤ 28. እንዲህ ያለች ሴት እንደ ወንበዴ ታደባለች፤ በሰዎችም መካከል ወስላቶችን ታበዛለች፡፡ 29 30 29. መከራ ለማን ነው? ሐዘንና ትካዜስ ለማን ነው? ጠብና ድብድብስ ለማን ነው? አለመግባባት ለማን ነው? በከንቱ መቁሰል ለማን ነው? የዐይን ቅላት ለማን ነው? 30. የወይን ጠጅ በመጠጣት ጊዜያቸውን ለሚያባክኑ ነው፤ እየዞሩ ድብልቅ የወይን ጠጅ ለሚያዘወትሩ ነው፡፡ 31 32 33 31. ስለዚህ መልኩ ቀይ ሆኖ፣ ብርጭቆ ውስጥ ሲያንጸባርቅ፣ ሲጠጡትም ሰተት ብሎ ቢገባ የወይን ጠጅ አያስጐምጅህ፡፡ 32. በመጨረሻ ግን እንደ መርዘኛ እባብ ይነድፍሃል፡፡ 33. ዐይንህ ብዥ ብዥ ስለሚልብህ ያልተለመዱ ነገሮችን የምታይ ይመስልሃል፤ በትክክል ማሰብም ሆነ መናገር ይሳንሃል፡፡ 34 35 34. ባሕር ውስጥ ወዲያ ወዲህ የምትዋዥቅ መርከብ ላይ ያለህ ይመስልሃል፤ መርከቡ ምሰሶ ጫፍ ላይ መተኛት እንደሚሞክር ሰው ትሆናለህ፡፡ 35. አንተም፣ ‹‹መቱኝ፤ ግን አልተጐዳሁም፤ ደበደቡኝ ግን አልተሰማኝም፣ መቼ በነቃሁና ጥቂት የወይን ጠጅ ጨምሬ በጠጣሁ!›› ትላለህ፡፡