ምዕራፍ 1
1
የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋዮች ከሆኑት ከጳውሎስና ከጢሞቲዎስ፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ቅዱሳን ለሆኑ በፊልጵስዩስ ከተማ ከእረኞችና ከዲያቆናት ጋር ለሚኖሩ ሁሉ።
2
ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ስላም ለአናንተ ይሁን።
3
ስለእናንተ በማስብበት ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
4
ስለ ሁላችሁም በምጸልይበት ጊዜ ሁሉ በደስታ እጸልያለሁ።
5
ከመጀመሪያ ጀምሮ እስካሁን ወንጌል በሚሰበክበት ሥራ ስላሳያችሁት ትብብራችሁ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
6
ይህን መልካም ሥራ በእናንተ ውስጥ የጀመረው ኢየሱስ ክርስቶስ እስከሚመለስ ቀን ድረስ እንደሚፈጽም እርግጠኛ ነኝ።
7
እናንተ በልቤ ስላላችሁ ስለ ሁላችሁ እንዲህ ማሰብ ይኖርብኛል። በእስራቴና ስለ ወንጌል በመቆሜ ስለእርሱም በመመስከሬ ሁላችሁም በጸጋ ተባባሪዎች ሆናችኋል።
8
በኢየሱስ ክርስቶስ ባለኝ ጥልቅ ፍቅር ሁላችሁንም እንድምናፍቃችሁ እግዚአብሔር ምስክሬ ነው።
9
ፍቅራችሁ በዕውቀትና በሙሉ መረዳት የበለጠ እንዲበዘላችሁ እጸልያለሁ።
10
ይህን የምጸልይበት ምክንያት የተሻለውን ነገሮችን መርምራችሁ እንድታውቁ እንዲሁም ክርስቶስ ተመልሶ በሚመጣበት ቀን ንጹኃንና ነውር የሌለባችሁ ሆናችሁ እንድትገኙ ነው።
11
ይህ ደግሞ ከኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኘው የጽድቅ ፍሬ ተሞልታችሁ ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና እንዲሆን ነው።
12
ወንድሞች ሆይ፥በእኔ ላይ የደረሰው ሁሉ ወንጌል በጣም እንዲስፋፋ እንዳደረገ እንድታውቁ እወዳለሁ።
13
እኔም የታሰሁት በክርስቶስ ምክንያት መሆኑን የቤተ መንግሥት ጠበቂዎችና ሌሎችም እዚያ ያሉት ሰዎች ሁሉ እንዲያውቁ ሆኖአል።
14
በእኔ መታሰር ምክንያት በጌታ ወንድሞች ከሆኑት ብዙዎቹ የበለጠ ከቀድሞ ይልቅ የእግዚአብሔርን ቃል ያለ ፍርሃት ለመናገር ድፍረት አግኝተዋል።
15
በርግጥ አንዳንዶቹ የክርስቶስን ወንጌል የሚሰብኩት በቅናትና በፉክክር መንፈስ ነው፤ሌሎቹ ግን ክርስቶስን የሚሰብኩት በቅን ልቡና ነው።
16
እነዚህ የእግዚአብሔርን ቃል በቅን ልቡና የሚሰብኩት ከፍቅር የተነሳ ነው፤እነርሱም እኔ ስለወንጌል ቆሜ በመከራከርይ መታሰሬን ያውቃሉ።
17
እነዚያ ግን ስለ ክርስቶስ የሚሰብኩት በራስ ወዳድነትና ቅንነት በሌለበት አስተሳሰብ ነው። በእስራቴም ላይ ተጨማሪ መከራ ሊያመጡብኝ አስበው ነው።
18
ታዲያ ምን ይደረግ? በርግጥ በዚህ ደስ ይለኛል፤በማስመሰል ወይም በእውነት በሁሉም መንገድ ክርስቶስ ይሰበካል።
19
ምክንያቱም በእናንተ ጸሎትና በኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ርዳታ ነጻ እንደምወጣ አውቃለሁ።
20
እንደማላፍርበት በሙሉ መተማመ እጠባበቃለሁ። ነገር ግን ዘወትር እንደማደርገውና በተለይም ዛሬም በሕይወት ብኖር ወይም ብሞት ክርስቶስ በሰውነቴ ይከብራል ብዬ በድፍረት እናገራለሁ።
21
ስለዚህ ለእኔ ሕይወት ማለት በክርስቶስ መኖር ነው፤ ሞትም ማለት ማትፍረፍ ነው።
22
ነገር ግን በሥጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆን የትኛውን እንደምመርጥ አላውቅም።
23
ምክንያቱም በእነዚህ በሁለቱ አሳቦች መካከል ተወጥሬአለሁ። በአንድ በኩል ከክርስቶስ ጋር መሆን ከሁሉ የሚበልጥ ነገር ስለሆነ ከዚህ ሕይወት ተለይቼ ከክርስቶስ ጋር መሆንን እፈልጋለሁ።
24
ሆኖም በሥጋ መኖሬ ለእናንተ የበለጠ አስፈላጊ ነው።
25
እምነታችሁ እንዲያድግና ደስታን እንድታገኙ እንደምቆይና ከሁላችሁም ጋር እንደምቀጥል ስለዚህ ነገር እተማመናሉ።
26
በዚህ ምክንያት እኔም እንደገና ወደ እናንተ ስመጣት ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ በእኔ ትመካላችሁ።
27
እንግዲህ ከሁሉም በላይ ሕይወታችሁ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ይሁን፤ ይህም እኔ መጥቼ ባያችሁ ወይም ከእናንተ ብርቅ በአንድ መንፈስ ጸንታችሁ መቆማችሁንና ለወንጌልም እምነት በኅብረት መጋደላችሁን እሰማ ዘንድ ነው።
28
ተቃዋሚዎቻችሁንም በምንም ነገር አትፍሩአቸው፤ ይህም ለእነርሱ የመጥፋታቸው ምልክት ሲሆን፤ ለእናንተ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ የመዳናችሁ ምልክት ነው።
29
ምክንያቱም ከክርስቶስ የተነሳ ይህ የተሰጣችሁ አገልግሎት በእርሱ እንድታምኑ ብቻ ሳይሆን በእርሱ ምክንያት መከራ እንድትቅበሉም ጭምር ነው።
30
ስለዚህ አሁን ከእኔ ጋር የመከራ ተካፋዮች ሆናችኋል፤ ይህም መከራ ከዚህ በፊት ደርሶብኝ ያያችሁትና አሁንም እየደረሰብኝ መሆኑን የሰማችሁት ነው።