ምዕራፍ 1
1
ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ፡፡
2
በነብዩ በኢሳይያስ እንደተጻፈው እነሆ! መንገድን የሚያዘጋጅላችሁን መልዕክተኛዬን በፊታችሁ እልካለሁ፤
3
መንገድን አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ ብሎ በምድረበዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ፡፡
4
በምድረበዳ እያጠመቀና ለኃጢአት ይቅርታ የንሰሐን ጥምቀት እየሰበከ መጣ፡፡
5
ሁሉና በኢየሩሳሌም ያሉ ሁሉ ወደ እርሱ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ እየመጡ ኃጢአታቸውን በመናዘዝ ይጠመቁ ነበር፡፡
6
የግመል ጠጉር ይለብስና ወገቡን በቆዳ መታጠቂያ ይታጠቅ፣ አንበጣና የበረሃ ማርም ይበላ ነበር፡፡
7
የጫማውን ማሰሪያ ለመፍታት የማልበቃ ከእኔ ይልቅ ታላቅ የሆነ እርሱ ከበስተኋላዬ ይመጣል፡፡
8
በውሃ አጥምቄአችኋለሁ፤ እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል እያለ ይሰብክ ነበር፡፡
9
ቀናት ኢየሱስ ከገሊላ ናዝሬት በመምጣት በዮርዳኖስ ውስጥ በዮሐንስ ተጠመቀ፡፡
10
እንደወጣም ሰማይ ሲከፈት፣ መንፈስ ቅዱስም እንደ እርግብ በእርሱ ላይ ሲወርድ አየ፤
11
ልጄ አንተ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምጽም ከሰማያት መጣ፡፡
12
መንፈስ ቅዱስ ወደ ምድረበዳ መራው፡፡
13
በሰይጣን እየተፈተነም በምድረበዳ ለአርባ ቀን ቆየ፡፡ ከዱር አራዊትም ጋር ነበረ፤ መላዕክትም አገለገሉት፡፡
14
ታልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን የምሥራች ቃል እየሰበከ ወደ ገሊላ መጣ፡፡
15
ተፈጸመ፤የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንሰሐ ግቡ፤ በወንጌልም እመኑ ይል ነበር፡፡
16
ባህር ዳር ሲያልፍ ሳለ ስምዖን ጴጥሮስንና ወንድሙን እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባህር ሲጥሉ አያቸው፤ አሳ አጥማጆች ነበሩና፡፡
17
በኋላዬ ኑና ሰዎችን የምታጠምዱ አደርጋችኋለሁ አላቸው፡፡
18
መረቦቻቸውን ትተው ተከተሉት፡፡
19
እልፍ እንዳለም የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሐንስን እነርሱም በጀልባቸው ውስጥ መረቦቻቸውን ሲጠግኑ አያቸው፡፡
20
ጠራቸው፤ እነርሱም ዘብዴዎስ አባታቸውን ከተቀጣሪ ሰራተኞቻቸው ጋር በጀልባው ውስጥ ትተው ተከተሉት፡፡
21
ቅፍርናሆም ሔዱ፡፡ ወዲያው በሰንበት ቀን ወደ ምኩራብ ገብቶ አስተማራቸው፡፡
22
ጸሐፍት ሳይሆን ትምህርቱ እንደ ባለሥልጣን ስለነበረ በትምህርቱ ተገረሙ፡፡
23
ርኩስ መንፈስ ያለበት አንድ ሰው በምኩራባቸው ነበረ፡፡
24
የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ! ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደሆንክ አውቄሃለሁ፤ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱስ ብሎ ጮኸ፡፡
25
ዝም በል! ከእርሱም ውጣ ብሎ ገሰጸው፡፡
26
መንፈስ መሬት ላይ ጥሎ ካንፈራገጠው በኋላ በታላቅ ድምጽ ጮኾ ወጣ፡፡
27
ሁሉ በጣም ተገረሙና ይህ አዲስ ትምህርት ምንድነው? ርኩሳን መናፍስትን እንኳን በሥልጣን ያዛቸዋልና እነርሱም ይታዘዙለታል በማለት እርስ በርሳቸው ተጠያየቁ፡፡
28
እርሱም በገሊላ አውራጃና በዙሪያው ባሉ ሀገራት ሁሉ ዝናው ወጣ፡፡
29
እንደወጡ ወዲያው ከዮሐንስና ከያዕቆብ ጋር ወደ ስምዖንና እንድርያስ ቤት መጡ፡፡
30
ጊዜ የስምዖን አማት አተኵሷት ተኝታ ነበርና ወዲያው ስለ እርስዋ ነገሩት፡፡
31
እጇን ይዞ አስነሳት፤ ወዲያውኑ ትኵሳቱ ለቀቃትና አገለገለቻቸው፡፡
32
ጠልቃ በመሸ ጊዜም ብዙ በሽተኞችንና በአጋንንት የተያዙትን ወደ እርሱ አመጧቸው፡፡
33
ሰው ሁሉ በአንድነት በቤቱ ደጃፍ ተከማችቶ ነበር፡፡
34
በተለያየ በሽታ የታመሙትን ፈወሳቸው፤ ብዙ አጋንንንትንም አወጣ፡፡ አጋንንቱ ማን መሆኑን አውቀውት ነበርና እንዳይገልጡት አዘዛቸው፡፡
35
እጅግ በማለዳ ተነስቶ ለብቻው ወደ ምድረበዳ ሔደና ጸለየ፡፡
36
ከእርሱ ጋር የነበሩትም ተከተሉት፡፡
37
ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ይፈልጉሃል አሉት፡፡
38
የምሥራቹን ቃል እንድሰብክ ወደ ሌሎቹ ከተሞች ደግሞ እንሂድ፣ ስለዚህ ጉዳይ መጥቻለሁና አላቸው፡፡
39
ወዳሉ ምኩራቦቻቸው ሁሉ እየገባ ሰበከላቸው፣ አጋንንትንም አወጣ፡፡
40
ለምጻም ወደ እርሱ መጥቶ ሰገደለትና ብትፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላለህ ብሎ ለመነው፡፡
41
አዘነለት፤ እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና እፈቅዳለሁ፣ ንጻ! አለው፡፡
42
ለምጹ ለቀቀውና ንጹህ ሆነ፡፡
43
ለማንም እንዳይናገር አጥብቆ አዘዘውና ወዲያው ሲያሰናብተው ሳለ
44
ግን ራስህን ለካህን አሳይ፤ ስለመንጻትህ ምሥክር እንዲሆንባቸው ሙሴ ያዘዘውን መስዋዕት አቅርብ አለው፡፡
45
ግን ሄደና ኢየሱስ በግልጽ ወደ ከተማ ለመግባት እስኪሳነው ድረስ ስለዚህ ነገር አብዝቶ ሊያወራና ሊያሰራጭ ጀመረ፡፡ በመሆኑም በምድረበዳ አካባቢዎች እንዲቆይ ሆነ፤ ሰዎችም ከየአቅጣጫው ወደ እርሱ ይመጡ ነበር፡፡