ምዕራፍ 1
ምዕራፍ 2
4
አራምም አሚናዳብን ወለደ፡፡ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፡፡ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፡፡
5
ሰልሞን እና እስራኤላዊ ያልሆነች ሚስቱ ረዓብ ቦኤዝን ወለዱ፡፡ ቦኤዝም ኢዮቤድን ወለደ፡፡ የኢዮቤድም እናት ሌላይቱ እስራኤላዊት ያልሆነች ሴት ሩት ነበረች፡፡ ኢዮቤድም የንጉሥ ዳዊት አባት የሆነው እሴይን ወለደ፡፡
6
እሴይም ዳዊትን ወለደ፡፡ ዳዊትም ሰሎሞንን ወለደ፡፡ የሰሎሞንም እናት ቀድሞ የኦርዮን ሚስት ነበረች፡፡
7
ሰሎሞንም ሮብዓምን ወለደ፡፡ ሮብዓምም ኢቢያን ወለደ፡፡ ኢቢያም አሳፍን ወለደ፡፡
8
አሳፍም ኢዮሳፍጥን ወለደ፡፡ ኢዮሳፍጥም ኢዮራምን ወለደ፡፡ ኢዮራምም ዖዝያንን ወለደ፡፡
9
ዖዝያን ኢዮአታሞን ወለደ፡፡ ኢዮአታምም አካዝን ወለደ፡፡ አካዝም ሕዝቅያስን ወለደ፡፡
10
ሕዝቅያስም ምናሴን ወለደ፡፡ ምናሴም አሞንን ወለደ፡፡ አሞንም ኢዮስያስን ወለደ፡፡
11
ኢዮስያስም የኢኮንያንና የወንድሞቹ አያት ነበር፡፡ እነርሱም ባቢሎናውያን እስራኤላውያንን ማርከው ወደ አገራቸው በወሰዱበት ጊዜ የኖሩ ናቸው፡፡
12
ባቢሎናውያን እስራኤላውያንን ማርከው ወደ ባቢሎን ከወሰዱ በኋላ፣ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፡፡ ሰላትያልም የዘሩባቤል አያት ነበር፡፡
13
ዘሩባቤል አብድዩን ወለደ፡፡ አብድዩም ኤልያቄምን ወለደ፡፡
14
ኤልያቄምም አዛርን ወለደ፡፡ አዛርም ሳዶቅን ወለድ፡፡ ሳዶቅም አኪምን ወለደ፡፡
15
አኪምም ኤልዩድን ወለደ፡፡ ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፡፡ አልዓዛርም ማታንን ወለደ፡፡ ማታንም ያዕቆብን ወለደ፡፡
16
ያዕቆብም ዮሴፍን ወለደ፡፡ ዮሴፍም ኢየሱስን የወለደች የማርያም እጮኛ ነበር፡፡
17
የኢየሱስን የትውልድ ሐረግ እንደሚከተለው አቅርቤዋለው፡- እንግዲህ ትውልዱ ከአብርሃም እስከ ንጉሥ ዳዊት አሥራ አራት ትውልድ፣ ከዳዊት ጀምሮ እስራኤላውያን ወደ ባቢሎን ምርኮ እስከ ተወሰዱበት ጊዜ ድረስ ሌላ አሥራ አራት ትውልድ፣ እንዲሁም ከባቢሎን ምርኮ ጀምሮ ክርስቶስ እስከ ተወለደበት ጊዜ ድረስ አሥራ አራት ትውልድ ነው፡፡
18
የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ታሪክ እንዲህ ነበረ፡፡ እናቱ፣ ማሪያም ለዮሴፍ ታጭታ ነበር፣ ዳሩ ግን ባልና ሚስት ሆነው አብረው ከመኖራቸው በፊት፣ እርስዋ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ፀንሳ ተገኘች፡፡
19
እጮኛዋ ዮሴፍ እግዚአብሔርን የሚታዘዝ ሰው ነበር፣ ስለዚህ ሳያገባት ሊተዋት ወሰነ፡፡ ነገር ግን በሰዎች ፊት ሊያሳፍራት አልፈለገም፡፡ በመሆኑም በስውር ሊተዋት ፈለገ፡፡
20
በዚህ አሳብ ላይ ሳለ፣ ከጌታ ዘንድ የተላከ መልአክ በሕልም ተገልጦ አስገረመው፡፡ መልአኩም እንዲህ አለው፡- “የንጉሥ የዳዊት ልጅ፣ ዮሴፍ ሆይ፣ ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ፡፡ እርሷዋ የፀነሰችው በመንፈስ ቅዱስ ነውና፡፡
21
ወንድ ልጅ ትወልዳለች፥ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው የሚያድናቸው ነውና፣ ስሙን ‘ኢየሱስ’ ትለዋለህ፡፡”
22
ይህ ሁሉ የሆነው ከረጅም ጊዜ በፊት እንዲጽፈው ጌታ ለነቢዩ ኢሳይያስ የተናገረው ነገር ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡
23
ኢሳይያስም እንዲህ ሲል ጽፎአል፡- “እነሆ፣ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ እነርሱም አማኑኤል ይሉታል፥ ትርጓሜውም ‘እግዚአብሔር ከእኛ ጋር’ ማለት ነው፡፡”
24
ዮሴፍም ከዕንቅልፉም ሲነቃ፣ የእግዚአብሔር መልአክ ያዘዘውን አደረገ፡፡ ከማርያምም ጋር መኖር ጀመረ፡፡
25
ዳሩ ግን የበኩር ልጅዋን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፡፡ ዮሴፍም ኢየሱስ ብሎ ጠራው፡፡