ምዕራፍ 3

1 በእግዚአብሔር የቁጣ በትር መከራ ያየ ሰው እኔ ነኝ። 2 አባረረኝ፥ በብርሃን ሳይሆን በጨለማ እንድሄድ አደረገኝ። 3 በእርግጥ ሊቃወመኝ ወደ እኔ ዘወር አለ፥ ቀኑን ሙሉ እጁን በላዬ መለሰ። 4 ሥጋዬንና ቆዳዬን ቀደደ፥ አጥንቶቼን ሰበረ። 5 ቅጥር በዙሪያዬ ገነባብኝ፥ በምሬትና በመከራም ከበበኝ። 6 ከሞቱ ረዥም ጊዜ እንደሆናቸው በጨለማ ስፍራ እንድኖር አደረገኝ። 7 በዙሪያዬ ቅጥርን ገነባ፥ ማምለጥም አልችልም። የእግሬን ሰንሰለት አከበደ። 8 ለርዳታ ብጮኽና ብጣራም ጸሎቴን ዘጋ። 9 ከጥርብ ድንጋይ በተሰራ ቅጥር መንገዴን ዘጋ፤የምሄድብት የትኛውም መንገድ ጠማማ ሆን። 10 መንገዴን ቀየረው። 11 ገነጣጠለኝ፥ብቸኛም አደረገኝ። 12 13 ቀስቱን ለጠጠ፥ ለፍላጻውም የዒላማ ምልክት አደረገኝ። 14 ለሰዎች ሁሉ መሳለቂያ፥ ዘወትርም ለሽሙጥጯ ዝማሬያቸው ምክንያት ሆንኩ። 15 ምሬት ሞላብኝ፥ እሬት እንድጠጣ አስገደደኝ። 16 ጥርሴን በድንጋይ ሰበረ፥ ወደ መሬት ውስጥ ረገጠኝ። 17 ሰላምን ከሕይወቴ አስወገድክ፤ ከእንግዲህ መቼም የትኛዉንም ደስታ አላስብም። 18 ስለዚህም« ጽናቴ ጠፍቷል፥ በእግዚአብሔር ላይ ያለ ተስፋዬም ሄዷል» አልሁ። 19 መከራዬንና እሬትና ምሬት ወደ አለበት መጥፋቴን አስባለሁ። 20 በእርግጥ አስበዋለሁ፥ተስፋ በመቁረጥ በውስጤ አቀረቀርኩ ። 21 ነገር ግን ይህን አስባልሁ፥ ተስፋ ሊኖረኝ የቻለውም ከዚህ የተነሳ ነው። 22 ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር የኪዳኑ ታማኝነት የተነሳ ነው፥ የምሕረቱ ሥራዎች አያልቁምና። 23 የምሕረቱ ሥራዎች ማለዳ ማለዳ አዲስ ናችው፤ ታማኝነትህ ምንኛ ታላቅ ነው! 24 ለራሴ እንዲህ አልኩ « እግዚአብሔር ዕጣ ክፍሌ ነው» ስለዚህ ተስፋ አደርገዋለሁ። 25 ለምጠብቀው፥ ለምትፈልገውም ሕይወት እግዚአብሔር መልካም ነው። 26 የእግዚአብሔርን ማዳን በዝምታ መጠበቅ መልካም ነው። 27 በወጣትነቱ ቀንበርን ቢሸከም ለሰው መልካም ነው። 28 እግዚአብሔር አሸክሞታልና ለብቻው ይቀመጥ ዝምም ይበል። 29 ምናልባት ተስፋ ሊኖር ይችላልና አፉን በአፈር ዉስጥ ያኑር። 30 ለሚመታው ጉንጩን ይስጥ። ዉርደትንም ይጥገብ፤ 31 እግዚአብሔር ለዘላለም አይጥለውምና! 32 ሐዘንን ቢያመጣም እንኳን ከታላቁ የኪዳኑ ታማኝነት በሚሆን ርኅራኄ ይራራል። 33 ምክንያቱም ከልቡ አይጨቁንም፥ወይንም የሰዎችን ልጆች አያሰቃይም። 34 በምድር ያሉ ምርኮኞችን ሁሉ ከእግሩ በታች ሲያደቅቅ፥ 35 በልዑል ፊት የሰውን ፍርድ ሲያጣምም፥ 36 ፍትህ ፈላጊውን ሲያፍን- ጌታ አያይምን? 37 ጌታ ካላዘዘው በቀር የሚናገርና የሚፈጽመው ማን ነው? 38 ጥፋትና ስኬት ከልዑል አፍ የሚወጡ አይደሉምን? 39 ታዲያ ማንም ሕያው የሆነ ሰው እንዴት ሊያጉረመርም ይችላል? ማንም ሰው ስለ ኃጢአቱ ቅጣት እንዴት ሊያጉረመርም ይችላል? 40 መንገዳችንን እንፈትን እንመርምርም፥ ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ። 41 ልባችንንና እጃችንን በሰማይ ወደ አለው ወደ እግዚአብሔር እናንሣና እንዲህ ብለን 42 እንጽልይ፦ተላልፈናል በአንተም ላይ ዐምፀናል፥ስለዚህ ይቅር አላልከንም። 43 ራስህን በቁጣ ሸፈንክ አሳደድከንም። አረድከን፥ አራራህልንምም። 44 ራስህን በደመና ሸፈንክ፥ስለዚህም ማለፍ የሚችል ጸሎት የለም። 45 በአሕዛብም መካከል ቆሻሻና ውዳቂ አደረግኽን ። 46 ጠላቶቻችን በእኛ ላይ በማላገጥ አፋቸውን ከፈቱ። 47 የአሳር ጉድጓድ ፥የባዶነትና የጥፋት ፍርሃት መጣብን። 48 ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ጥፋት ዓይኔ ያለማቋርጥ ውኃ አፈሰሰች። 49 ዓይኖቼ ያፈሳሉ አያቆሙምም፥ለለቅሷቸውም ፍጻሜ የለውም፥ 50 እግዚአብሔር ውደ ታች እስኪመለከት ከሰማይም እስኪያይ ድረስ። 51 ከከተማዬ ሴቶች ልጆች የተነሳ ዓይኔ ጽኑ ስቃይ በሕይወቴ ላይ አመጣች። 52 ጠላቶቼ ያለ ምንም ምክንያት፥ያለመታከት እንደ ወፍ አደኑኝ። 53 ሕይወቴን በጉድጓድ ዉስጥ አጠፉ፥ ድንጋይንም በላዬ ከመሩ። 54 ውኆች በራሴ ላይ አለፉ፤እኔም፦ «ተቆርጬአለሁ!» አልኩ። 55 እግዚአብሔር ሆይ፥ ከጥልቅ ጉድጓድ ስምህን ጠራሁ። 56 «እርዳታ ፈልጌ ስጮህ፥እረፍት ፈልጌ ስጣራ ጆሮህን አትሰውር» ባልኩኝ ጊዜ ድምጼን ሰማህ። 57 በጠራሁህ ቀን ወደ እኔ ቀርበህ «አትፍራ» አልከኝ። 58 ጌታ ሆይ በተከሰስሁ ጊዜ ስለ ነፍሴ ተሟገትህ፤ ሕይወቴንም አዳንክ። 59 እግዚአብሔር ሆይ እንዴት እንደ ጨቆኑኝ አይተሃል፥ ክርክሬን በጽድቅ ፍረድልኝ። 60 በእኔ ላይ የዶለቱትን ሁሉ፥የበቀላቸውን ሥራ ሁሉ አይተሃል። 61 እግዚአብሔር ሆይ በእኔ ላይ የዶለቱትን ሁሉና እሽሙጥጫቸውን ሰምተሃል። 62 በእኔ ላይ የተነሱብኝን ከንፈሮች ሰምተሃል፤ቀኑን ሁሉ እኔን በመቃወም የሚያስቡትን ጥልቅ አሳቦች ሰምተሃል። 63 እግአብሔር ሆይ! ተመልከት፥ በመቀመጣቸውም ሆነ በመነሳታችው የስላቅ ዘፈናቸው ምክንያት ነኝ። 64 እግዚአብሔር ሆይ እጆቻቸው እንዳደረጉት ክፉ ነገር እንደዚያው መልሰህ ክፈላቸው። 65 ፍርሃትን በልባቸው አድርግ፥ ርግማንህንም በላይቸው አድርግ። 66 እግዚአብሔር ሆይ! በቁጣህ አሳድዳችው፥ከሰማይት በታች በየስፍራው አጥፋቸው።