1 የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ከሞተ በኋላ፣ ያህዌ የሙሴ አገልጋይ ለነበረው ለነዌ ልጅ ለኢያሱ እንዲህ አለው፣ 2 "አሁን አገልጋዬ ሙሴ እንደሞተ አንተ ታውቃለህ፡፡ ስለዚህ አሁን የዮርዳኖስን ወንዝ ለመሻገር አንተና ይህ ህዝብ ሁሉ ተነሱ፡፡ ለእስራኤል ህዝብ ወደምሰጠው ምድር በቶሎ ግቡ፡፡ 3ለሙሴ ቃል እንደገባሁለት የምትረግጡትን ምድር ሁሉ እሰጣችኋለሁ፡፡