1 1 2 3 1. ዑፅ ተብሎ በሚጠራው አገር ኢዮብ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፡፡ እርሱም እግዚአብሔርን የሚፈራና ክፉ ነገሮችን ከማድረግ ራሱን ያራቀ ነበር፡፡ 2. ሰባት ወንዶች ልጆችና ሦስት ሴቶች ልጆች ነበሩት፡፡ 3. ሰባት ሺህ በጎች፣ ሦስት ሺህ ግመሎች፣ አንድ ሺህ በሬዎች፣ አምስት መቶ አህዮችም ነበሩት፡፡ ብዙ አገልጋዮችም ነበሩት፡፡ በዮርዳኖስ ወንዝ ምሥራቅ በነበሩት አካባቢዎች ሁሉ እጅግ በጣም ባለጠጋ ሰው ነበር፡፡ 4 5 4. የኢዮብ ወንዶች ልጆች ብዙ ጊዜ በቤቶቻቸው ግብዣ ያዘጋጁ ነበር፡፡ እያንዳንዱ ግብዣ በሚያዘጋጅበት ጊዜ፣ ተሰብስበው አብረው እንዲበሉ ወንድሞቹንና እኅቶቹን ሁሉ ይጋብዝ ነበር፡፡ 5. ከእንዳንዱ ግብዣ በኋላም፣ ኢዮብ ልጆቹን ይጠራና ካለባቸው ከማንኛውም ኃጢአት ወይም ነቀፋ እንዲያነጻቸው እግዚአብሔን ይለምን ነበር፡፡ በማለዳ ተነሥቶም ለልጆቹ ለእያንዳንዳቸው አንዳንድ እንስሳ በመሠዋት፣ በመሠዊያ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርብ ነበር፡፡ ኢዮብ ይህንን ያደርግ የነበረው ሁልጊዜም፣ ‹‹ምናልባት ልጆቼ ኃጢአት ሠርተው በልባቸውም ስለ እግዚአብሔር አንዳች ክፉ ነገር ተናግረው ይሆናል›› ይል ስለ ነበር ነው፡፡ 6 7 8 6. አንድ ቀን መላእክት መጥተው በእግዚአብሔር ፊት ተሰብስበው ሳሉ፤ ሰይጣንም ደግሞ መጣ፡፡ 7. እግዚአብሔርም፣ ሰይጣንን ‹‹ከወዴት መጣህ?›› ብሎ ጠየቀው፡፡ ሰይጣንም፣ ‹‹እየሆነ ያለውን ነገር ለማየት ወዲያና ወዲህ ስመላለስ ከነበርኩበት ከምድር ነው የመጣሁት›› ብሎ ለእግዚአብሔር መለሰለት፡፡ 8. እግዚአብሔር ሰይጣንን፣ ‹‹እኔን የሚያመልከውን ኢዮብን ልብ ብለህ ተመለከትኸውን? እንደ እርሱ የሚያከብረኝና በትክክለኛ መንገድ በምድር ላይ የሚኖር እንደ እርሱ ያለ የለም፡፡ እርሱ ምንጊዜም ማንኛውንም ክፉ ነገር ከማድረግ የተቆጠበ ነው›› ብሎ መለሰለት፡፡ 9 10 11 12 9. ሰይጣንም ለእግዚአብሔር እንዲህ ብሎ መለሰለት፡- ‹‹አንተ የምትለው እውነት ነው፤ ኢዮብ ግን አንተን የሚፈራህ ስላደረግህለት ነገርብቻ ነው፡፡ 10. አንተ ሁልጊዜ እርሱን፣ ቤተ ሰቡን፣ ያለውንም ነገር ሁሉ ከልለህለታል፡፡ ለመሥራት የሚሞክረውን ማንኛውንም ሥራ አሳክተህለታል፤ በርስቱ ላይም እጅግ ብዙ የቀንድ ከብት አለው፡፡ 11. ባለው ነገር ላይ ጉዳት ብታደርስበትና ብትወስድበት ግን፣ በሰው ሁሉ ፊት ይሰድብሃል፡፡›› 12. እግዚአብሔርም ሰይጣንን፣ ‹‹እንግዲህ እኔ ይህንን እንዳደርግ ፈልገሃል! እንግዲያውስ ይሁን ያለውን ሁሉ እንድትወስድበት እፈቅድልሃለሁ፡፡ በሰውነቱ ላይ ግን ጉዳት አታድርስበት›› ብሎ መለሰለት፡፡ ሰይጣን በተነገረው ተስማምቶ ኢዮብን እንዴት እንደሚያጠቃው ለማቀድ ከእግዚአብሔር ፊት ሄደ፡፡ 13 14 15 13. ከዚያ በኋላ አንድ ቀን የኢዮብ ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆች በታላቅ ወንድማቸው ቤት እየበሉና ወይን ጠጅ እየጠጡ ነበር፡፡ 14. ይህን እያደረጉ ሳሉ አንድ መልእክተኛ ወደ ኢዮብ ቤት መጥቶ እንዲህ አለው፡- ‹‹በሬዎችህ በማሳ ላይ እያረሱ አህዮቹም በአቅራቢያው ባለው መስክ ላይ ሣር እየጋጡ ሳሉ፣ 15. የሳባ ሰዎች መጥተው አደጋ ጣሉብን፡፡ በማሳ ይሠሩ የነበሩትን አገልጋዮችህን ሁሉ ገደሉአቸው፤ በሬዎቹንና አህዮቹንም ሁሉ ወሰዱአቸው! የሆነውን ነገር ለአንተ ለመንገር አምልጬ የመጣሁት እኔ ብቻ ነኝ፡፡›› 16 17 16. እርሱ ገና ኢዮብን በማነጋገር ላይ እያለ፣ ሌላ መልእክተኛ መጣ እንዲህ አለው፡- ‹‹መብረቅ ከሰማይ ወርዶ በጎቹንና ይጠብቋቸው የነበሩትን ሁሉ ገደላቸው! የሆነውን ነገር ልነግርህ አምልጬ የመጣሁ እኔ ብቻ ነኝ፡፡›› 17. እርሱ ገና ለኢዮብ እየነገር ሳለ ሦስተኛው መልእክተኛ ደረሰ ኢዮብንም እንዲህ አለው፡- ‹‹በሦስት ቡድን የጠከፈሉ ከለዳውያን ዘራፊዎች መጥተው አደጋ ጣሉብን፡፡ ግመሎቹን ሁሉ ዘርፈው እነርሱን ይጠብቁ የነበሩትንም ሰዎች ሁሉ ገደሉአቸው፡፡ የሆነውን ነገር ልነግርህ አምልጬ የመጣሁት እኔ ብቻ ነኝ፡፡›› 18 19 18. እርሱ ገና ለኢዮብ እየነገረ ላይ እያለ አራተኛው መልእክተኛ ደረሰ ኢዮብንም እንዲህ አለው፡- ‹‹ወንዶች ልጆችህና ሴቶች ልጆችህ በታላቅ ወንድማቸው ቤት ይበሉነበር፡፡ 19. በድንገት ከበረሐ በጣም ብርቱ ነፋስ ተነሥቶ ቤቱን መታው፡፡ ቤቱ በወንዶች ልጆችህና በሴቶች ልጆችህ ላይ ተደርምሶ ሁሉንም ገደላቸው! የሆነውን ነገር ልነግርህ አምልጬ የመጣሁት እኔ ብቻ ነኝ፡፡›› 20 21 22 20. በዚያን ጊዜ ኢዮብ በጣም ዐዝኖ ስለ ነበር ተነሥቶ ቆመና ልብሱን ቀደደ፤ የታስ ፀጉሩንም ተላጨ፡፡ ከዚያም ለእግዚአብሔር ለመስገድ መሬት ላይ ተደፉ፡፡ 21. እንዲህም አለ፡- ‹‹እኔ ስወለድ ልብስ አልነበረኝም፡፡ ስሞትም ምንም ልብስ ይዤ አልሄድም፡፡ እግዚአብሔር የነበረኝን ሁሉ ሰጠኝ፤ አሁን ደግሞ ሁሉንም ወስዶታል፡፡ ነገር እኛ ግን ምንዚሜም እግዚአብሔርም ማመስገን አለብን!›› 22. እንግዲህ በኢዮብ ላይ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ቢደርሱበትም እርሱ እንደ ሞኝ ሰው አልተናገረም፤ እግዚአብሔር ያደረገውን ነገር ስሕተት ነበር በማለትም ኃጢአት አልሠራም፡፡