ምዕራፍ 1

1 2 3 1 ከረጅም ጊዜ በፊት በተለያዩ ዘመናትና በተለያዩ መንገዶች እግዚአብሔር በነቢያት በኩል ለአባቶቻችን ተናግሮ ነበር። 2 አሁን ግን የሁሉም ነገር ወራሽ ባደረገው፣ ዓለምንም በፈጠረበት በልጁ ተናገረን። 3 ልጁ የክብሩ ነጸብራቅ ነው፤ እርሱ በባሕርዩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም አንድ ነው፤ በሥልጣን ቃል ሁሉን ደግፎ ይዞአል። የሰዎችንም ኃጢአት ካነዳ በኃላ በሰማይ በግርማው ቀኝ ተቀምጧል። 4 5 4 እርሱ የወረሰው ስም ከሰማቸው እጅግ የላቀ በመሆኑ፣ ከመላእክትም የበለጠ ሆኖአል። 5 ለመሆኑ፣ ከመላክት መካከል፣ 6 7 6 የበኩር ልጁን ወደ ዓለም ሲያስገባ እግዚአብሔር፣ “የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉ ይስገዱለት” ብሏል። 7 ስለ መላእክቱ ግን፣"መላዕክቱን ነፋሳት፥ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል ያደርጋል" ይላል። 8 9 8 ስለ ልጁ ግን፣ “አምላክ ሆይ፣ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ነው፤ የመንግሥትህም በትር የጽድቅ በትር ነው። 9 ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፅንም ጠላህ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ፣ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ” ብሏል። 10 11 12 10 እንዲሁም፣ “ጌታ ሆይ፣ በመጀመሪያ ምድርን ፈጠርህ፤ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው። 11 እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ትኖራለህ። ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ። 12 እንደ መጎናጸፊያ ትጠቀልላቸዋለህ፤እንደ ልብስም ይለወጣሉ። 13 14 13 በየትኛውም ጊዜ ነበር እግዚአብሔር ከመላእክቱ ለአንዱ፣ “ጠላቶችህን ከእግርህ በታች እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” ያለው? 14 ታድያ፣ መላእክት ሁሉ እኔን እንዲያመልኩና ድነት የሚወርሱትን ለመርዳት ተተላኩ መንፈሶች አይደሉምን?