ምዕራፍ 5

1 2 1የአዳም ዝርያዎች የስም ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፤እግዚአብሔር ሰዎችን በፈጠረ ጊዜ በብዙ መልክ እርሱን እንዲመስሉ በራሱ አምሳያ ፈጠራችው፤2ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።ባረካቸው፤በፈጠራቸውም ዕለት''ሰው'' ብሎም ሰየማችው። 3 4 5 3አዳም መቶ ሠላሳ ዓመት በሆነው ጊዜ በመልክ እርሱን የሚመስል ወንድ ልጅ ወለደ፤''ሤት'' የሚል ስም አወጣለት። 4ከዚህ በኃላ አዳም ከ800 ዓመት በላይ ኖረ፤ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤5ዕድሜው 930 ዓመት ሲሆነውም ሞተ። 6 7 8 6ሤት 105 ዓመት ሲሆነው ሄኖስን ወለደ፤7ከዚህ በኃላ ሤት 807 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤8እድሜው 912 ዓመት ሲሆነው ሞተ። 9 10 11 9ሄኖስ 90 ዓመት ሲሆነው ቃይናንን ወለደ፤10ከዚህ በኃላ 815 ዓመት ኖረ፤ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤11እድሜው 905 ሲሆነውም ሞተ። 12 13 14 12ቃይናንም 70 ዓመት ሲሆነው መላልኤልን ወለደ፤13ከዚህ በኃላ 840 ዓመት ኖረ፤ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤14ዕድሜው 910 ሲሆናውም ሞተ። 15 16 17 15መላልኤል 65 ዓመት ሲሆነው ያሬድን ወለደ፤ 16ከዚህ በኃላ 830 ዓመት ኖረ፤ሌሎችም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤ 17ዕድሜው 895 ሲሆነውም ሞተ። 18 19 20 18ያሬድ 162 ዓመት ሲሆነው ሔኖክን ውወለደ፤19ከዚህ በኃላ 800 ዓመት ኖረ፤ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤20ዕድሜው 962 ሲሆነውም ሞተ። 21 22 23 24 21ሔኖክ 65 ዓመት ሲሆነው ማቱሳላን ወለደ፤22ከዚህ በኃላ ሔኖክ የእግዚአብሔርን መንገድ በመከተል 300 ዓመት ኖረ፤ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤23ዕድሜው 365 እስኪሆነው ድረስ ኖረ፤24ይህን ያህል ዘመን የኖረውም የእግዚአብሔር መንገድ በመከተል ነበር፤ከዚህ በኃላ እግዚአብሔር ስለወሰደው አልተገኘም። 25 26 27 25ማቱሳላ 187 ዓመት ሲሆነው ላሜክን ወለደ፤26ከዚህ በኃላ 782 ዓመት ኖረ፤ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤27ዕድሜው 969 ሲሆነውም ሞተ። 28 29 28ላሜክ 182 ዓመት ሲሆነው ወንድ ልጅ ወለደ፤29''ይህ ልጅ እግዚአብሔር በረገማት ምድር ላይ ከብርቱ ሥራችን ያሳርፈናል'' ሲል ''ኖኅ'' ብሎ ጠራው። 30 31 30ከዚህ በኃላ ላሜክ 595 ዓመት ኖረ፤ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤31ዕድሜው 777 ሲሆነውም ሞተ። 32 32ኖኅ 500 ዓመት ከሆነው በኃላ ሶስት ወንዶች ልጆች ወለደ፤እነርሱም ሴም፥ካምና፤ያፌት ይባሉ ነበር።