ምዕራፍ 1
1
እግዚአብሔር ስማያትና ምድርን ፍጠረ።
2
ምድርን በሚፈጥርበትም ጊዜ ምድር ቅርፅ የሌላት ባዶ ነበረች። ጨለማም በጥልቁ (ውቅያኖስ) ላይ ነበር፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሃው ላይ ይስፍ ነበር።
3
4
5
3እግዚአብሔርም አለ ''ብርሃን ይሁን'' ፤ብርሃንም ሆነ። 4እግዚአብሔርም፥ብርሃን በመሆኑ ተደሰተ።ስለዚህም እግዚአብሔር ብርሃንን ከጨለማ ለየ።5 ብርሃኑ ''ቀን'' ብሎ ጠራው፤ጨለማውንም ''ሌሊት'' ብሎ ሰየመው። ቀኑ መሸ፥ሌሊቱም ነጋ፤ ይህም መጀመሪያ ቀን ሆ፣
6
7
8
6ከዚህ በኃላ እግዚአብሔር ''ውሃውን ከውሃ የሚለይ ጠፈር ይሁን'' አለ፤7በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ጠፈርን ፈጠረ፤ከዚህም በኃላ እግዚያብሔር ''ከጠፈር በተና ከጠፈር በላይ ያሉት ውሆች ይለይዩ''አለ፤እንዳለውም ሆነ።8እግዚአብሔር ጠፈርን ''ሰማይ'' ብሎ ጠራው። ቀኑ መሸ፥ሌሊቱም ነጋ፤ ይህም ሁለተኛ ቀን ሆነ።
9
10
9 እግዚአብሔርም ''የብሱ ግልጥ ሆኖ እንዲታይ ከሰማይ በታች ያለውን ውሃ ሁሉ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ'' አለ፤እንዳለውም ሆነ።10የብሱን ''ምድር '' ብሎ ጠራው፤በአንድ ስፍራ የተሰበሰበውንም ውሃ ''ባሕር'' ብሎ ሰየመው፤እግዚአብሔር ይህ መልካም መሆኑን ተመለከተ።
11
12
13
11ከዚህ በኃላ እግዚአብሔር ''ምድር አትክልትን ፥የእህል አዝርእትንና ዘር በውስጡ ያለውን ፍራፍሬ የሚያስገኙ ተክሎችን በየዓይነቱ ታብቅል''አለ፤እንዳለውም ሆነ።12በዚህ ዓይነት ምድር አትክልትን፥በየዓይነቱ የእህል አዝርእትንና ዘር በውስጡ ያለውን ፍራፍሬ የሚያስገኙ ተክሎችን አበቀልች፤እግዚአብሔር ይህ መልካም መሆኑን ተመለከተ።13ቀኑ መሸ፥ሌሊቱም ነጋ፤ ይህም ሶስተኛ ቀን ሆነ።
14
15
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ''ቀንን ከሌሊት ለመለየት ልዩ ልዩ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ላይ ይሁኑ፤ለዕለታት፥ ለክፍላተ ዓመትና ለዓመታት መለያ ምልክት ይሁኑ፤ 15ለምድር ብርሃን ለመስጠት በሰማይ ጠፈር ላይ ሆነው ያብሩ'' አለ፤እንዳለውም ሆነ።
16
17
18
19
16 እግዚአብሔር ሁለት ታላላቅ ብርሃናትን ፈጠረ። ታላቁ ብርሃን ፀሐይ በቀን፥ ታናሹ ብርሃን ጨረቃ በሌሊት እንዲያበሩ አደረገ፤እንዲሁም ከዋክብትን ፈጠረ።17እነዚህን ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ላይ አኖራቸው፤ ይህንንም ማድርጉ ለምድር ብርሃንን እንዲስጡ፥18በቀንና በሌሊት ላይ ስልጣን እንዲኖራቸውና ጨለማን ከብርሃን እንዲለዩ ነው። እግዚአብሔር ይህ መልካም መሆኑን ተመለከተ። 19ቀኑ መሸ፥ ሌሊቱም ነጋ፤ ይህም አራተኛ ቀን ሆነ።
20
21
20ከዚህ በኃላ እግዚአብሔር ፤፤ውሃ ሕይወት ባለቸው በልዩ ልዩ ፍጥረቶች የተሞላ ይሁን፤እያንዳንዱም የሚባዛ ይሁን፤ወፎችም ከምድር በላይ ባለው በስማይ ጠፈር ይብረሩ፤እነዚህም ሁሉ ትውልድን የሚተኩ ይሁኑ''አለ።21በዚህ ዓይነት እግዚአብሔር ታላላቅ የባሕር እውሬዎችን፥ሌሎችንም በውሃ ውስጥ የሚኖሩና የሚንቀሳቀሱ ና ራሳቸውን የሚተኩ ፍጥረታትን ፈጠረ።ልዩ ልዩ ዝርያቸውን የሚተኩ አሕዋፋትን ፈጠረ።እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን ተመለከተ።
22
23
22እግዚአብሔር ''ብዙ ተባዙ፤ዘራችሁ የባህር ውሃ ይሙላ፤ወፎችም በምድር ላይ ''ይብዙ'' ብሎ ባረካቸው።23ቀኑ መሸ፤ሌሊቱም ነጋ፤ ይህም አምስተኛ ቀን ሆነ።
24
25
24ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ''ምድር ልዩ ልዩ የሆኑ ሕይወት ያላቸው ፍጥረቶች፥ማለትም ልዩ ልዩ የሆኑ እንስሳትን፥በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችና አራዊትን ታስገኝ'' አለ፤እንዳለውም ሆነ። 25በዚህ ዓይነት እግዚአብሔር አራዊትን በየዓይነቱ፥እንስሳትን በየዓይነቱ፥ምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቅሳቀሱ ፍጥረቶችን በየዓይነቱ ፈጠረ።እግዚአብሔር ይህ መልካም መሆኑን ተመለከተ።
26
27
26ከዚህ በኃላ እግዚአብሔር ''ሰውን በመልካችንና በአምሳያችን እንፍጠር፤ሰዎችም በባህር ውስጥ በሚኖሩት ዓሳዎች፥በሰማይ በሚበሩት ወፎች፥በእንስሳትና በምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች፥እንዲሁም በምድር ሁሉ ላይ ስልጣን ይኑራቸው'' አለ።27በዚህ ዓይነት እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክና በራሱ አምሳያ ፈጠረው፤እግዚአብሔር ሰዎችን ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ።
28
29
28እግዚአብሔር ''ብዙ ተባዙ፥ዘራችሁ ምድርን ይሙላ፤ ምድርም በቁጥጥራችሁ ስር ትሁን፤በባሕር ውስጥ በሚኖሩ ዓሳዎች፥ በሰማይ በሚበሩ ወፎችና በምድር ላይ በሚንቀሳቀሱ ሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ ላይ ስልጣን ይኑራችሁ'' ብሎ ባረካቸው።29እግዚአብሔር እንዲህ አለ፥''ምግብ እንዲሆኑአችሁ በምድር ገፅ ላይ የሚገኙትን የእህል አዝርእትንና ዘር በውስጡ ያለውን ፍራፍሬ የሚያስገኙ ተክሎችን ሁሉ ስጥቻችኃለሁ።
30
31
30እንዲሁም በምድር ላይ ለሚኖሩ እንስሳት ሁሉ፤በሰማይ ለሚበሩ ወፎች ሁሉ፤በምድር ላይ ለሚንቀሳቀሱ ሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ፥በአጠቃላይ የሕይወት እስትንፋስ ላለው ፍጥረት ሁሉ ምግብ እንዲሆናቸው ልምላሜ ያለውን ሳርና ቅጠል ሁሉ ስጥቻችዋለሁ።''እንዳለውም ሆነ።31እግዚአብሔር የፈጠረውን ሁሉ አየ፤እጅግ መልካም መሆኑንም ተመለከተ።ቀኑ መሸ፥ሌሊቱ ነጋ፤ ይህም ስድስተኛ ቀን ሆነ።