1
1
ቂሮስ የፋርስን ግዛት በሚገዛበት በመጀመሪያው አመት ኤርምያስ የተናገረውን ትንቢት የሚያሟላ ነገር አደረገ፡፡ ያህዌ ቂሮስ ይህን መልዕክት እንዲጽፍ አነቃቃው፤ ከዚያም ቂሮስ ይህ መልዕክት በግዛቱ ሁሉ እንዲታወጅ አደረገ፡
2
“የፋርስን ግዛት የምገዛ እኔ፣ ንጉስ ቂሮስ ይህን እላለሁ፡ በሰማይ ያለ አምላክ፣ ያህዌ፣ በምድር ላይ ባሉ መንግስታት ሁሉ ላይ ገዥ አደረገኝ፡፡ ደግሞም የእርሱ ህዝቦች ይሁዳ ውስጥ በኢየሩሳሌም ለእርሱ ቤተ መቅደስ እንዲገነቡ ተገቢ የሆነውን እንዳደርግ እኔን ሾመኝ፡፡
3
የእግዚአብሔር የሆናችሁ ህዝቦች ሁሉ፣ በኢየሩሳሌም ለሚኖረው ለእስራአል አምላክ ለያህዌ ይህን ቤተ መቅደስ እንደገና ለመገንባት እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ሂዱ፡፡
4
ወደዚህ ተሰደው የነበሩ፣ አሁን እስራኤላዊያን በስደት በሚኖሩበት የሚኖሩት ሌሎቹ ሰዎች፣ ለእነዚያ ለሄዱት ብርና ወርቅ ያዋጡ፡፡ ደግሞም አይሁዶች ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ የሚያስፈልጋቸውን አቅርቦት ይስጧቸው፡፡ በኢየሩሳሌም ያለውን ቤተ መቅደስ ለመገንባት የቀንድ ከብቶችና የገንዘብ ስጦታም ይስጧቸው፡፡”
5
ለአገልጋዮቹ እንዲህ አለ፣ “ወደ ሐማ ሄዳች በፍጥነት እንዲመጣ ንገሩት፣ አስቴር የተናገረችውንም በፍጥነት አድርጉ!” ስለዚህ ንጉሱና ሐማ አስቴር ወዳዘጋጀችው ግብዣ ሄዱ፡፡
6
ወይን ጠጅ እየታደለ ሳለ ንጉሱ አስቴርን እንዲህ አላት፣ “አቤቱታሽ ምንድን ነው? እርሱ ይሰጥሻል፡፡ ጥያቄሽ ምንድን ነው? የምትጠይቂው የመንግስቴን እኩሌታ ቢሆን እንኳን እሰጥሻለሁ፡፡”
7
ናቡከደነጾር ወታደሮች በኢየሩሳሌም ከነበረው ከያህዌቤተ መቅደስ የወሰዱትንና በባቢሎን በጣኦቶቻቸው ቤተ መቅደስ ያስቀመጧቸውን ውድ ንብረቶች ንጉስ ቂሮስ አስወጣ፡፡
8
የፋርስ መንግስት ግምጃ ቤት ሀላፊ የሆነው ሚትሪዳጡ እነዚህን ሁሉ ንብረቶች እንዲቆጥርና ወደ ይሁዳ የሚመለሰው ቡድን መሪ ለሆነው ለሰሳብሳር እንዲሰጥ አዘዘ፡፡
9
ያበረከታቸው ዕቃዎች ዝርዝር ይህ ነው፡ ሰላሳ የወቅ ጎድጓዳ ሳኖች፣ አንድ ሺ ጎድጓ የብር ሳህኖችች፣ ሃያ ዘጠኝ ሌሎች ሳህኖች፣
10
ሰላሳ የወርቅ ሳህን፣ 410 ተመሳሳይ ባለግጣም የብር ሳህኖች፣ እና አንድ ሺህ ሌሎች ዕቃዎች ነበሩ፡፡
11
እና ከእርሱ ጋር የነበሩ ወደ ኢየሩሳሌም በተመለሱ ጊዜ ይዘዋቸው የወጡት የብርና የወርቅ ዕቃዎች በአጠቃላይ 5400 ነበሩ፡፡