ምዕራፍ 1
1
በሰላሳኛው ዓመት ክአመቱም በአራተኛው ወር ከወሩም በአምስተኛው ቀን በኬብሮን አጠገብ ከምርኮኞቹ ጋር አብሬ እየኖርኩኝ ሳለሁ ሰማያት ተክፍተው የእግዚአብሔርን ራዕይ አየሁ።
2
ንጉስ ኢዮአኬም በተማረከበት በአምስተኛው ቀን በከለዳዊያን አገር በኬብሮን ወንዝ አጠገብ
3
የእግዚአብሔር ቃል ወደ ካህኑ ወደ ኡዝ ልጅ ወደ ሕዝቅኤል በኃይል መጣ። የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረች።
4
እኔም በውስጡ የእሳት ነበልባል ያለበት ዙሪያውና ውስጡ የሚያበራ ታላቅ ደመና የሚመስል አውሎ ነፋስ ከሰሜን አቅጣጫ ሲመጣ አየሁ፣ በደመናው ውስጥ ያለው እሳት ቀለሙ ቢጫ ነበር።
5
መካከል ላይ የአራት ህያዋን ፍጡራን ምስል ነበር። ፍጥረታቱ የሰው መልክ ነበራቸው፣
6
ነገር ግን እያንዳንዳቸው አራት አራት ፊቶችና አራት አራት ክንፎች ነበሩዋቸው።
7
እግሮቻቸው ቀጥ ያሉ ነበሩ፣ ነገር ግን የእግሮቻችው ኮቴ እንደ ነሀስ የሚያበራ የጥጃ ኮቴ ያለ ነበር።
8
ከክንፎቻቸው ስር በአራቱም አቅጣጫ የሰው እጅ ነበራቸው።
9
በክንፎቻቸው ተነካክተው ወደ ኋላ ሳይገላመጡ ቀጥ ብለው ወደፊት ይራመዱ ነበር።
10
መልካቸውም በአንድ በኩል የሰው፥ በቀኝ በኩል የአንበሳ፣ በግራ በኩል የበሬና በሌላ በኩል ደግሞ የንስር ነበር።
11
መልካቸው ያንን ይመስል ነበር፣ ክንፎቻቸውም ተዘርግተው ነበር፣ በሁለት ክንፎቻቸው እርስ በርሳቸው ተነካክተው ነበር፣ በሁለት ክንፎቻቸው ደግሞ ሰውነታቸውን ይሸፍኑ ነበር።
12
እያንዳንዳቸው ሳይገላመጡ ወደፊት ይራመዱ ነበር፣ መንፈስ ወደመራቸው ሳይገላመጡ ይሄዱ ነበር።
13
ህያዋን ፍጡራን የከሰል ፍም እሳት ወይም ችቦ ይመስሉ ነበር፣ ከህያዋን ፍጡራኑ ጋር ደማቅ እሳት ይንቀሳቀስ ነበር፣ የመብረቅ ብልጭታዎችም ነበሩ።
14
ህያዋን ፍጡራኑ በዝግታ ወደ ኋላና ወደ ፊት ይንቀሳቀሱ ነበር፣ እንደ መብረቅም ነበሩ።
15
ወዲያውም ወደ ህያዋን ፍጥረታቱ ተመለከትኩ፣ በምድር ላይ ከእያንዳንዱ ፍጡር አጠገብ አንዳንድ መንኮራኩር ነበረ።
16
የመንኮራኩረቹ መልክ የሚከተለውን ይመስል ነበር፡ እንደ ብርሌ ያንጸባርቁ ነበር፣ አራቱም አንድ አይነት ነበሩ፣ አንዱም በአንዱ ላይ የተስካ ይመስል ነበር።
17
መንኮራኩሮቹ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ፍጡራኑ ወደየትኛውም አቅጣጫ ሳይገላመጡ ይሄዱ ነበር።
18
ዙሪያውን በዓይን የተሞላ ስለሆነ የመንኮራኩሮቹ ጠርዝ ርጅምና አስፈሪ ነበር።
19
ህያዋን ፍጡራኑ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ መንኮራኩሮቹ አብረው ይንቀሳቀሱ ነበር፣ ህያዋን ፍጥረታቱ ወደ ላይ ከፍ ሲሉ መንኮራኩሮቹም ከፍ ይሉ ነበር።
20
መንፈስ ወደሚሄድበት ሁሉ ይሄዱ ነበር፣ የህያዋን ፍጡራኑ መንፈስ ስላለባቸው መንኮራኩሮቹ አብረው ወደ ላይ ከፍ ይሉ ነበር።
21
የፍጡራኑ መንፈስ ስላለባቸው ፍጡራኑ ሲሄዱ መንኮራኩሮቹም ከአጠገባቸው ይሄዱ ነበር፣ ሲቆሙ እነርሱም ይቆሙ ነበር፣ ከምድር ወደ ላይ ከፍ ሲሉ እነርሱም ከፍ ይሉ ነበር።
22
ከህያዋን ፍጡራኑ ራስ በላይ ጠፈር የሚምስል ነገር ነበረ፤ ያም ጠፈር የሚመስል ነገር በህያዋን ፍጡራኑ ራስ በላይ እንደ አስፈሪ በረዶ ዙሪያቸውን ነበረ።
23
ከጠፈሩ በታች የእያንዳንዱ ህያው ፍጡር ክንፍ ቀጥ ብሎ ተዘርግቶ የአንደኛው ፍጡር ክንፍ ከሌላው ፍጡር ክንፍ ጋር ተነካክቶ ነበር። እያንዳምዱ ፍጡር ሰውነቱን የሚሸፍንበት ሁለት ክንፍ ነበረው።
24
ህያዋን ፍጡራኑ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ሁሉ የክንፎቻቸው ድምጽ ይሰማኝ ነበር፣ ድምጹም እንደ ውሃ ጎርፍ፣እንደ ህያው አምላክ ድምጽ፣ እንደ ሠራዊት ድምጽ፣ እንደ ዝናብ ውሽንፍር ነበረ ! በሚቆሙበት ጊዜ ክንፎቻችውን ያጥፉ ነበር።
25
በሚቆሙበትና ክንፎቻቸውን በሚያጥፉበት ጊዜ ከራሶቻቸው በላይ ካለው ጠፈር ድምጽ ይመጣ ነበር።
26
ከራሶቻቸው በላይ ከሚገኘው ጠፈር በላይ ዕንቁ የሚመስል የዙፋን አምሳያ ነበር፣ በዙፋኑም አምሳያ ላይ ሰው የሚመስል ተቀምጦ ነበር።
27
ከወገብ በላይ በእሳት የጋለ ብረት ከወገቡ በታች ደግሞ እሳት የሚመስል ምስል አየሁ።
28
በዝናብ ጊዜ እንደሚታይ ቀስተ ደመና ይመስል ዙሪያውም ደማቅ ብርሀን ነበረ። ባየሁትም ጊዜ በግንባሬ ተደፋሁ፣ ወዲያውም የሚያናግረኝ ድምጽ ሰማሁ።