ምዕራፍ 1
1
እኔ ሕዝቅኤል ሠላሳ አመት በሆነኝ ጊዜ ከባቢሎን ደቡብ በሆነው በኬበር ወንዝ አጠገብ በእስራኤል ህዝብ መካከል እኖር ነበር፡፡ ባቢሎናውያን ከይሁዳ ምድር ወስደውን ወደዚያ አምጥተውን ነበር፡፡ ከአመቱ ከአራተኛው ወር በአምስተኛው ቀን ሰማይ እንደተከፈተ ሆኖ ከእግዚአብሔር ዘንድ ራዕይ አየሁ በአራተኛው ወር በአምስተኛው ቀን
2
ንጉሡ ኢዩአብን በተማረከ በአምስተኛው ዓመት ማለት ነው፡፡
3
እግዚአብሔር ለቡሊ ልጅ ለካህኑ ለህዝቅኤል በባቢሎናውያን በኮባር ወንዝ አጠገብ በነበረው ጊዜ መልዕክት ሰጠው፡፡ የእግዚአብሔርም ኃይል በርሱ ላይ ነበር፡፡
4
ከራዕዩቹም ከአንዱ ከሰሜን አውሎነፋስ ሲመጣ አየሁ፡፡ ከባድ ደመና ነበረ የማያቋርጥ ብልጭታ ነፀብራቅ ነበረ እና ደመናውም በታላቅ ብርሃን የተከበበ ነበር፡፡ ብርሃኑም በሚያንፀባርቅበት መሃል ቢሜ መልክ ያለው እሳት ነበር፡፡
5
በአውሎ ነፋሱም መካከል አራት ህያዋን ፍጥረታት የሚመልሱ አየሁ
6
ሆኖም እያንዳንዱ አራት ግፊቶችና አራት ክንፎች ነበራቸው
7
እግሮቻቸውም እንደ ሰው እግሮች ነበሩ መማሪያችሁ ግን ተወልውሎ እንደሚያብረቀርቅ የጥጃ ኮቴ ይመስል ነበር፡፡
8
በአራቱም የሳናቸው አካል በክንፎቻቸው ሥር የሰው እጅ የሚመስል ነበራቸው፡፡
9
አራቱም ፍጥረታት ክንፎቻቸው እርስ በርስ ተነካክተው ክብ ይሠሩ ነበር፡፡ ሲንቀሳቀሱም በቀጥታ ወደፊት ይሄድ ነበር እንጂ አይዞሩም፡፡
10
እያንዳንዱ ፍጥረት አራት ፊቶች ነበሯቸው፡፡ ከፊት ለፊት ያለው ፊት የሰው ፊት የሚመስል ነበር፡፡ በቀኝ በኩል ያለው ፊት የአንበሳ ፊት ይመስል ነበር፡፡
በግራ በኩል ያለው ፊት የበሬን ፊት ይመስላል በጀርባ በኩል ያለው ፊት የንስር ፊት ይመስላል፡ ፡
11
ሁለቱ እያንዳንዳቸው ክንፎች ወደ ላይ ከፍ ብለው በሁለቱም አቅጣጫ ያሉትን ክንፎች ይነኩ ነበር፡፡ ሌሎቹ ሁለት ክንፎች ግን ታጥፈው ሰውነታቸውን ይሸፍኑ ነበር፡፡
12
ፍጥረቶቹም በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ የሚቆጣጠራቸው የእግዚአብሔር መንፈስ ለመራቸው ወደ ሚፈልገው ወደ መራቸው ወደየትኛው እንደመራቸው አቅጣጫ ተራ ሳይቀይሩ በቀጥታ ወደ ፊት ይሄዱ ነበር፡፡
13
አራቱም ፍጥረታት የእሳት ፍም ወይም ችቦ ይመስል ነበር ፋና የሚያበራ እሳትም በፍጥረታቱ መካከል ወዲህና ወዲያ ይል ነበር ከእሱም መካከል መብረቅ ይመጣ ነበር፡፡
14
ፍጥረታቱም በፍጥነት አንድ መብረቅ ብልጭታ ወዲህና ወዲያ ይመላለሱ (ይንቀሳቀሱ) ነበር፡፡
15
አራቱንም ፍጥረታት ስመለከት በእያንዳንዳችሁ አጠገብ በምድርህ ላይ መንኮራኮር (ተሽከርካሪ) አየሁ
16
አራቱም መንኮራኩሮች ተመሳሳይና እንደ ስዕሉ የሚያንፀባርቁ ነበሩ፡፡ እያንዳንዱ መንኮራከር በውስጡ አንድ መንኮራኩር ያለው ይመስል ነበር፡፡
17
ሲንቀሳቀስና ከአራቱ በአንዱ አቅጣጫ በቀጥታ ወደፊት ይሄዱ ነበር እንጂ ወደ ሌላ አቅጣጫ አይዞሩም ነበር፡፡
18
የመንኮራኩሮችም ክበብ ግርማ የለውም የሚያስፈራ በዓይኖችም የተሞላ ነበር፡፡
19
ህያዋን ፍጥረታቱ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ መንኮራኩሮቹና አብረዋችሁ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ፍጥረታቱም ከምድር ከፍ ብለው በመሰብሰብ በሚሉበት ጊዜ ሁሉ መንኮራኩሮችም አብረው ይነሳሉ፡፡
20
የሚቆጣጠራቸው የእግዚአብሔር መንፈስ ሊሄድ ወደሚፈልግበት ሁሉ ይሄዳሉ መንኮራኩሮቹንም የሚጣራቸው የእግዚአብሔር መንፈስ ስለሆነ መንኮራኩራቸው አብረው ይሄዳሉ፡፡
21
ፍጥረታቱም ወደሚሄድበት ሁሉ መንኮራኩሮችም ይሄዳሉ፡፡ ፍጥረታቱም ሲቆጩ መንኰራኩሮቹም ይቆጣሉ፡፡ ፍጥረታቱም ከመሬት ከፍ ብለው በሚነሱበት ጊዜ ሁሉ መንኰራኩሮቹ አብረው ይነሣሉ፡፡
22
ከፍጥረታቱም ራስ በላይ የሚያስፈራና የሚያንፀባርቅ በረዶ መልክ ያለው ጠፈር የሚመስል ነበር፡፡
23
ከጠፈሩም በታች ፍጥረታቱ ክንፎቻቸውን ዘርግተው ነበር እያንዳንዱ ሌላውን ፍጥረት የሚነካ ሁለት ክንፍ ነበረው በሁለቱ ክንፎች ደግሞ የራሱን አካል ይሸፍንበት ነበር፡፡
24
ፍጥረታቱ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ክንፎቻቸው እንደ ባህር ማዕበል ድምፅ እንደ ሁሉን ቻይ አምላክ ድምፅና እንደ ብዙ ሠራዊት ያለ ድምፅ ያሰው ነበር /ይመስል ነበር
25
ክንፎቻቸውን ዝቅ አድርገው በምድርም ላይ ሲቆሙም ከራሳቸው በላይ ብለው ከጠፈሩ ይሞታ ተሰማ (ይሰጣል)
26
ከጠፈሩም በላይ ከትልቁ በሰነፔር የተሠራ የሚመስል ግዙፍ ዙፋን ነበር፡፡ በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው ሰው የሚመስለው ነበር፡፡
27
ከወገቡም በላይ በእሳት እንደጋለ ከወገቡም በታች የሚያንፀበርቅ ብርሃን ከብቦት አየሁ፡፡
28
በዝናባማ ቀን በደመና ውስጥ እንዳሉ ቀስተ ደመና የበራ ነበር፡፡ ያም የእግዚአብሔርን መገኘት የሚያመለክት አንፀባራቂ ብርሃን ነበረ ባየሁትም ጊዜ ራሴን በምድር ላይ ተዘረርኩ አለቃም ሲነግረኝ ሰማሁ፡፡