ምዕራፍ 1
1
ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የወረዱት የያዕቆብ ልጆች እነኚህ ናቸው ፤ (እኒህ ሁሉ ከአባታቸው ያዕቆብ ጋር፤እና ከነ ቤተሰቦቻቸው ወደ ግብፅ የወረዱ ናቸው፡፡).የልጆቹም ስም ፡
2
ሮቤል፣ ሲሞን፣ሌዊ፣ይሁዳ፣
3
ኢሳኮር፣ዛብሎን፣ብንያም፣
4
ዳን፣ንፍታሌም፣ጋድ እና አሴር ናቸው፡፡
5
ከያዕቆብም ጋር ወደ ግብጽ የወረዱት ቁጥራቸው ሰባ ሰዎች ነበሩ፤ ዩሴፍ ግን በግብጽ ነበር፡፡
6
ከጥቂት ግዜም በኋላ ዮሴፍና ወንድሞቹ እንዲሁም ሌሎች በዚያ ትውልድ ይኖሩ የነበሩት ቤተሰቦች ሁሉ ሞቱ፡፡
7
ነገርግን የያዕቆብ ዘሮች ብዙ ልጆች ወለደው ነበር፡፡ የትውልዱም ቁጥር እጅ በጣም እየበዛና እየጨመረ ሄደ ከዚህም የተነሳ ትውለዱ በሁሉም የግብጸ ቦታዎች ላይ ይኖሩ በር፡፡
8
ይሁንና ዮሴፍ ለግብፅ በጎ ውለታ የዋላቸውን ምስጋና የሚገባቸውን ተገባራቱን የማያውቅ አዲስ ግብፅን የሚያስተዳደር ንጉስ ተነሳ፡፡እርሱም ለህዘቡ እንዲህ አላቸው፤
9
ተመልክቱ የእስራኤል ልጆች ቁጥር እንዴት እየበዛ እንደሆነና እንዴት ብርቱ በመሆን አስፈሪ እንደሆኑ ተመልከቱ አላቸው፡፡
10
እነሱን የምንቀንስበትን መንገድ መፈለግ ይኖርብናል ካለሆነ ግን ሌሎች የውጭ ጠላቶች በሚያጠቁን ግዜ ከእነሱ ጋር አበረው ለመውጋት በመነሳት ከግብፅ ለመውጣት ይችላሉ፡፡
11
ስለዚህም ንጉሱና አስተዳደሪዎች በእስራኤላዊያን ላይ መከራና ችግር እንዲያበዙባቸው ግብጻውያን ጌቶች በላያቸው ላይ ሾሙባቸው፡፡ እነሱም ለግብጽ ንጉስ ፊቱምናና ራምሴን ዕቃ ማሰቀመጪያ ግምጃ ቤት የሚሆኑ ከተሞች እንዲገነቡ አዘዟቸው፡፡
12
ነገር ግን ግብጻዊያኑ እስራኤላዊያኑን ባስጨነቋቸው ቁጥር እስራኤላዊያኑ እየበረቱና ቁጥራቸውም የግብጽን ምድር እስኪሞላ ድርስ እየበዛ ሄደ፡፡ ስለዚህም ግብፃዊያን እስራኤላዊያንን መፍራት ጀመሩ፡፡
13
እስራኤላዊያንም በባርነት ይኖሩ ሰለነበር ኑሯቸው እጅ በጣም አሳዛኝ ነበር፡፡
14
በጡብ እና ግንባታ ስራ በከባድና በማስጨነቅ ያሰሯቸው ነበርና፡፡
15
ሁለት ዕብራዊ አዋላጆችም ነበሩ አኒዲቷም ሲፓራ ሌላኛይቷም ፉዋ ይባሉ ነበሩ፡፡የግብጽ ንጉስም ሁለቱንም ዕብራዊ አዋላጆችን አላቸው፡፡
16
ዕብራዊያኑ በሚወልዱበት ወቅት በምትረዱበት ግዜ የሚወልዱት ወንድ ከሆነ ግደሉት፣ ነገር ግን ሴት ከሆነች በህይወት እንድትኖር ተዋት አላቸው፡፡
17
ነገር ግን አዋላጆቹ የግብጽ ንጉስን በመታዘዝ ወንዶቹን ቢገድሉ እግዚብሔር እንደሚቀጣቸው በመረዳት የግብጽ ንጉስ ያዘዘውን ባለመታዘዝ ወንዶችን አልገደሉም፡፡
18
ስለዚህም የግብጽ ንጉስ ዕብራዊያን አዋላጆቹን ጠርቶ፤ ይህን ያደረጋችሁት ለምንድር ነው? ለምንድነው ወንዶች በህይወት እንዲቆዩ ያደረጋቸሁት? በማለት ጠየቃቸው፡፡
19
ከአዋለጆቹም አንዷ እንዲህ ስትል መለሰችየዕብራዊያን እንስቶች እንድ ግብጽ እንስቶች አይደሉም፡፡ የዕብራዊያን እንስቶች በጣም ጠንካራ ስልሆኑ እኛ ለእነሱ እርዳት ከመሰጥታችን በፊት ወለደው እናገኛቸዋለን፡፡
20
ስለዚህም እግዚያብሔር በአዋላጆቹ በኩል በችሮታው ስለነበር እስራኤላዊያን እየበዙና እየጠነከሩ ሄዱ፡፡
21
አዋላጆቹ እግዚያብሄርን ይፈሩ ስለነበር እግዚያብሔር የራሳቸውን ልጆች ሰጣቸው፡፡
22
የግብጽ ንጉስም ዕብራዊያኑን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው ከዕብራዊያን የሚወለዱ ወንድ ህጻናትን ወደ አባይ ወንዝ ጣሏችው ሴቶች ህጻናትን ግን በህይወት እንዲኖሩ ተዋቸው፡፡