ምዕራፍ 9 32

1 ሰማያት ሆይ፥ አድምጡ እኔም እናገራለሁ፤ ምድር ሆይ፥ አንቺም የአፌን ቃል ስሚ። 2 ትምህርቴም እንደ ዝናብ ይውረድ፤ ቃሌም እንደ ጤዛ ይንጠባጠብ፤ በቡቃያ ሣር ላይ እንደ ካፊያ፥ ለጋ ተክልም ላይ እንደ ከባድ ዝናብ ይውረድ። 3 እኔ የእግዚአብሔርን ስም አውጃለሁ፤ የአምላካችንን ታላቅነት አወድሱ። 4 እርሱ ዐለትና ሥራውም ፍጹም፥ መንገዱም ሁሉ ትክክል ነው። የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፤ ቀጥተኛና ጻድቅ አምላክም እርሱ ነው። 5 በእርሱ ላይ ክፋት ፈጽመዋል። ከነውራቸው የተነሣ ከእንግዲህ ልጆቹ አይደሉም። ወልጋዳና ጠማማ ትውልዶች ናቸው። 6 እናንተ ተላላና ጥበብ የጎደላችሁ ሕዝብ፤ለእግዚአብሔር የምትመልሱለት በዚህ መንገድ ነውን? አባታችሁና ፈጣሪያችሁ የሠራችሁና ያበጃችሁእርሱ አይደለምን? 7 የጥንቱን ዘመን፥ የብዙ ዓመቶችን አስታውሱ፤ አባቶቻችሁን ጠይቁ ይነግሩማልም፥ ሽማግሌዎቻችንም ጠይቁ ያስረዱአችኋል። 8 ታላቁ አምላክ ለአሕዛብ ርስታቸውን በሰጠ ጊዜ የሰውንም ዘር በለያየ ጊዜ፤ በእስራኤል ልጆች ቁጥር ልክ፤ የአሕዛብን ርስት ድንበር ለየ። 9 የእግዚአብሔር ድርሻ የገዛ ሕዝቡ ያዕቆብ የተለየ ርስቱ ነውና። 10 እርሱን በምድረ በዳ፤ ባዶና ጭው ባለ በረሓ ውስጥ አግኘው፤እንደ ዐይኑ ብሌን ጠበቀው። 11 ንስር ጎጆዋን እንደትጠብቅ፤ በጫጩቶቿም ላይ እንደምትረብብ፥ እነርሱን ለመያዝ ክንፎቿን እንደምትዘረጋ በክንፎቿም እንደምትሸከማቸው፥ እግዚአብሔር ክንፎቹን ዘርግቶ፥ ተሸከሞ ወሰዳቸው። 12 እግዚአብሔር ብቻ መራው ምንም ባዕድ አምላክ ከእርሱ ጋር አልነበረም። 13 በምድር ከፍታ ላይ አስኬደው፤ የእርሻንም ፍሬ መገበው፤ ከዐለት ድንጋይ ማር አበላው፤ ከባልጩትም ድንጋይ ዘይት መገበው። በወንድና በሴት ልጆቹ ተቆጥቶአልና። 14 የላሙንና የበጉን መንጋ ቅቤና ወትት የሰቡትን በጎችና ፍየሎች፤ የባሳንን ሙኩት በግ፤ መልካም የሆነውንም ስንዴ ማለፊያውንም የወይን ጠጅ ጠጠህ። 15 ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፤ ስብ ጠገበ፥ ሰውነቱ ደነደነ፥ ለሰለሰም። የፈጠረውንም አምላክ ተወ፤ የመጠጊያ ዐለት የሆነውን አዳኙንም ናቀው። 16 በባዕዳን አማልክታቸው አስቀኑት፤ በአስፈያፊ ጣዖቶቻቸውም አስቆጡት። 17 አምላክ ላልሆኑ አጋንንት፥ ላላወቋቸው አማልክት፥ ከጊዜ በኋላ ለተነሡ አማልክት፥ አባቶቻችውም ላልፈሯቸው አማልክት ሠዉ። 18 አባት የሆናችሁን ዐለት ከዳችሁት፤ የወለዳችሁን አምላክ ረሳችሁ። 19 እግዚአብሔር ይህን አይቶ ተዋቸው፤ በወንድና በሴት ልጆቹ አስጥተውታልና። 20 እርሱም እንዲህ ብሎአል፦ ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ መጨረሻቸው ምን እንደሚሆንም አያለሁ፤ ጠማማ ትውልድ፤ የማይታሙንም ልጆች ናቸውና። 21 አምላክ ላልሆነው አስቀኑኝ፤ በከንቱ ጣዖቶቻቸውም አስቆጡኝ። እኔም ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋል፤ በማያስተውልም ሕዝብ አስቆጣቸዋለሁ። 22 በቁጣዬ እሳት ተቀጣጥሎአልና፤እስከ ሲኦል ዘልቆ ይነዳል፤ ምድርን እስከ ሰብሏ ይበላል፤ የተራሮችንም መሠረት ያቀጣጥላል። 23 በመዓት ላይ መዓት አመጣባቸዋለሁ። ፍላጻዬንም በእነርሱ ላይ እተኩሳለሁ። የሚያጠፋ ራብ፤በልቶ የሚጨርስ ቸነፈርና ከባድ መቅሠፍት እሰድባቸዋለሁ፤ 24 የአራዊትን ሹል ጥርስ፥ በምድር የሚሳብ የእባብ መርዝም እሰድባቸዋለሁ። 25 ሰይፍ መንገድ ላይ ያስቀራቸዋል፤ በመኝታቸውም ድንጋጤ ይነግሣል፤ጎልማሳውና ልጃገረዷ፤ ሕፃኑና ሽማግሌው ይጠፋሉ። 26 ከሰዎችም መካከል መታሰቢያቸውን አጠፋለሁ፥ እበትናቸዋለሁም፤አልሁ፤ 27 ድል ያደረገው እጃችን ነው ብለው፥ ጠላቶቻቸው በስሕተት እንዳይታበዩ፥ የጠላት ማስቆጣት እንዳይሆን እሠጋለሁ። 28 እስራኤላውንም አእምሮ የጎደላቸው፤ ማስተዋልም የሌላቸው ናቸው። 29 አስተዋዮች ቢሆኑ ኖሮ ይህን በተገነዘቡና መጨረሻቸው ምን እንደሚሆን ባስተዋሉ ነብር። 30 መጠጊያ ዐለታቸው ካልሸጣቸው እግዚአብሔር ካልተዋቸው በቀር፥ አንድ ሰው እንዴት ሺሁን ያሳድዳል፥ ሁለቱስ እንዴት አሥር ሺሁን እንዲሸሹ ያደጋሉ? 31 የእነርሱ መጠጊያ ዐለታቸው እንደ እኛ መጠጊያ ዐለት አለመሆኑን፤ ጠላቶቻችንም እንኳ አይክዱም። 32 ወይናቸው ከሰዶም ወይን ከገሞራም እርሻ ይመጣል፤ የወይናቸው ፍሬ በመርዝ፥ ዘለላቸውም መራራ ነው። 33 ወይናቸው የእባብ መርዝ፤ መርዙም የጨካኝ እባብ ነው። 34 ይህስ በእኔ ዘንድ ተጠብቆ ያለ፤ በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን? 35 በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ፥ ጊዜው ሲደርስ እግራቸው ይሰናከላል፤ የመጥፊያቸው ቀን ቀርቦአል፤ የሚመጣባቸውም ነገሮች ይፈጥንባቸዋል። 36 ኃይላቸው መድከሙን ባሪያም ሆነ ነጻ ሰው አለመቅረቱን በሚያይበት ጊዜ፤ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል፤ ለአገልጋዮቹም ይራራል። 37 እንዲህም ይላል፦ መጠጊያ ዐለት የሆኗቸው፤ አማልክታቸው ወዴት አሉ? 38 የመሥዋዕታቸውን ስብ የበሉ፤ የመጠጥ ቁርባናችውንም የወይን ጠጅ የጠጡ አማልክት ወዴት ናቸው? እስቲ ይነሡና ይርዷችሁ! እስቲ መጠለያ ይስጧችሁ! 39 እኔ ራሴ እርሱ እንደ ሆንሁ እዩ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤እገድላለሁ፤ አድናለሁ፤አቆስላለሁ፤ እፈውሳለሁም፤ ከእጄም የሚያስጥል ማንም የለም። 40 እጄን ወደ ሰማይ አነሣለሁ፤ ለዘላለምም ሕያው እንደ ሆንሁ እናገራለሁ።። 41 የሚያብራቀርቅ ሰይፌን ስዬ እጄ ለፍርድ ስይዘው፤ ባላጋራዎቼን እበቀላቸዋለሁ፤ ለሚጠሉኝም እንደሥራቸው እከፍላቸዋለሁ። 42 ሰይፌ ሥጋ በሚበላበት ጊዜ፥ ፍላጾቼ በደም እንዲሰክሩ አደርጋለሁ፤ ደሙ የታረዱትና የምርኮኞች የጠላት አለቆችም ራስ ደም ነው። 43 አሕዛብ ሆይ ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ፤ እርሱ የአገልጋዮቹን ደም ይመልሳል፤ጠላቶቹንም ይበቀላል። ምድሪቱንና ሕዝቡን ይቤዣቸዋል። 44 45 ሙሴም ከነዌ ልጅ ከኢያሱ ጋር መጥቶ የመዝሙር ቃሎችን በሕዝቡ ጆሮ ተናገረ። ሙሴም እነዚህን ቃሎች ሁሉ ለመላው እስራኤል ተናገሮ ጨረሰ። 46 እርሱም እንዲህ አላቸው፦ የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ በጥንቃቄ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዟቸው እኔ ዛሬ በግልጥ የምነግራችሁን ቃሎች ሁሉ በልባችሁ አኑሩ። 47 ቃሎቹ ለእናንተ ሕይወታችሁ ናቸው፥ ባዶ ቃሎች አይደሉም፥ በእነርሱ ዮርዳንስን ተሻገራችሁ በምትወርሷትም ምድር ረጅም ዘመን ትኖራላችሁ። 48 በዚያችም ዕለት እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ 49 ከኢያሪኮ ማዶ ባለው የሞዓብ ምድር ከዓብሪም ተራሮች አንዱ ወደ ሆነው ወደ ናባው ተራራ ወጥተህ ለእስራኤላውያን ርስት አድርጌ የምሰጣትን የከነዓን ምድር አሻግረህ ተመልከት። 50 ወንድምህ አሮን በሖር ተራራ ላይ እንደ ሞተና ወደ ወገኖቹ እንደ ተስበስበ ሁሉ አንተም በወጣህበት በዚያ ተራራ ላይ ሙት፤ ወደ ወገኖችህም ተሰብሰብ። 51 ይህ የሚሆንበት ምክንያት ሁለታችሁም በሲን ምድረ በዳ በቃዴስ በምሪባ ውሃ አጠገብ በእስራኤላውያን መካከል በእኔ ላይ ባለመታመናችሁ፤ እንዲሁም በእስራኤላውያን መካከል የሚገባውን አክብሮት ባለመስጠታችሁ ነው። 52 ስለዚህ ምድሪቱን ከሩቅ ሆነህ ታያታለህ እንጂ ለእስራኤል ሕዝብ ወደምሰጣት ምድር አትገባም።