1 ጳውሎስ ሲላስና ጢሞቴዎስ በተሰሎንቄ ከተማ ለምትኖሩ በእግዚአብሔር አባታችንና በኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን ለሆናችሁ አማኝ ወገኖች ይህን ደብዳቤ እንጽፍላችኋለን፡፡ 2 አባታችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእናንተ መልካም ማድረግ እንዲቀትና ሰላሙን መስጠቱን እርሱ እንዲቀጥል እኛ እንጸልያለን፡፡ 3 ወገኖቻችን፣ በጌታ ኢየሱስ ማመናችሁ እያደገገና እርስ በእርሳችሁ መዋደዳችሁ እየጨመረ በመምጣቱ እኛ ሁልጊዜም እግዚአብሔርን እናመሰግናለን ደግሞም ይህን ማድረግ ይገባናል፡፡ 4 ይህም በመሆኑ፣ የእግዚአብሔር ለሆኑ አማኝ ወገኖች ስለ እናንተ በኩራት መናገራችንን ቀጥለናል፡፡ ምንም እንኳን ከሌሎች መከራ ቢደርስባችሁም፣ ምን ያህል ትዕግስተኞች እንደሆናችሁና እንዴት በጌታ ኢየሱስ ባላችሁ እምነት እየቀጠላችሁ እንደምትገኙ ለወገኖች እንናገራለን፡፡ 5 መከራዎች ሁሉ በጽናት እስከተቀበላችሁ ድረስ፣ እግዚአብሔር ሁሉንም ሰዎች በጽድቅ እንደሚዳኝ በግልጽ እናውቃን፡፡ በእናንተ ጉዳይ፣ እርሱ እናንተን ለዘለዓም ሊመራ የተጋችሁ እንደሆናችሁ ለሁሉም ያሳውቃል ምክንያቱም በእርሱ ስታምኑ መከራን ዳግም ተቀበላችኋል፡፡ 6 በእናንተ ላይ መከራ በሚያደርሱ ላይ በእርግጥ ይፈርድባቸዋል ምክንያቱመ እርሱ ይህን ማድረጉ ጻድቅነቱን ያሳያ፡፡ 7 ውስጥ አልፋችሁ ለሽልማት ማብቃቱ ተገቢ እንደሆነ እርሱ ያውቃል፡፤ እርሱ ለእናንተና ለእኛ ሽልማት የሚጠንን ጌታችን ኢየሱስ ከሀያላን መላእክቱ ጋር ከሰማይ ተመልሶ ለእያንዳንዱ ራሱን ሲያሳይ ነው፡፡ 8 ለእርሱ ታማኝ ያልሆኑትን የጌታችንን የኢየሱስን የምስራች ለመቀበል እምቢ ያሉንን ሰዎች በቁጣው ዕሳት ይቀጣቸዋል፡፡ 9 ኢየሱስ እነዚህን እጅግ በታላቅ ሀይል ከሚገዛበት፣ ለዘለዓለም ወደሚጠፉበት በእርሱ ያባርራቸዋል፡፡ 10 ኢየሱስ ይህን የሚያደርገው እግዚአብሔር በወሰነው ጊዜ ከሰማይ ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ ነው፡፡ በውጤቱም፣ የእርሱ የሆንን ህዝቦች ሁሉ እርሱን እናመሰግናለን በእርሱም እንደነቃለን፡፡ የሰበክናችሁን አምናችኋልና እናንተም በዚያ ትሆናላችሁ፡፡ 11 እኛ ኢየሱስን ታመሰግኑ ዘንድ፣ እኛ ሁልጊዜ ለእናንተ እንጸልያለን፡፡ እግዚአብሔር እንድትኖሩበት በጠራችሁ አዲስ መንገድ ለመኖር የተገባችሁ እንዲያደርጋችሁ እንጸልያለን፡፡ እርሱ ሀያል ነውና፣ በማናቸውም በምትመኙት መንገድ መልካም የሆነውን ማድረግ እንድትችሉ እንዲያበቃችሁ እንጸልያለን፣ ደግሞም በእርሱ አምናችኋልና እርሱ ማናቸውንም አይነት መልካም ነገሮች ማድረግ እንድትችሉ ያስችላችኋል፡፡ 12 የምንጸልይበት ምክንያት ጌታችን ኢየሱስን እንድታመሰግኑ ስለምንፈልግና እርሱም እናንተን እንዲያከብር ስለምነፈልግ ነው፡፡ ይህ ይሆናል ምክንያቱም የምናመልከው እግዚአብሔርና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእናንተ በጎ ማድረግን ስለሚቀጥሉ ነው፡፡