1 1እኔ፣ ጳውሎስ ይህን ደብዳቤ እጽፍላችኋለሁ፡፤ ሲላስና ጢሞቴዎስ ከእኔ ጋር ናቸው፡፡ በእግዚአብሔር አብና በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሆናችሁ በተሰሎንቄ ከተማ ለምትኖሩ አማኝ ወገኖች ይህን ደብዳቤ ልከንላችኋል፡፡ የእግዚአብሔር በጎነትና ከእናንተ ጋር ይሁን ሰላሙንም ይስጣችሁ። 2 3 2በጸሎችን ስናስባችሁ ስለ እናንተ ሁልጊዜም እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡ 3በእርሱ ስለምታምኑ እግዚአብሔርን እንደምታገለግሉና ሰዎችን ስለምትወዷቸው በቅንት እንደምታገለግሉአቸው ይህን ሁልጊዜም እናስታውሳለን፡፡ ሰዎች መከራ ሲያደርሱባችሁም ታግሳችኋል፡፡ በመከራ የጸናችሁት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመከራ ሊያወጣችሁ! ከሰማይ በቶሎ እንደሚመለስ በልበ ሙሉነት ስለምትጠብቁ ነው፡፡ 4 5 4በእግዚአብሔር የተወደዳችሁ አማኝ ወገኖቼ፣ የእርሱ እንድትኑ እንደመረጣችሁ ስለምናውቅ እርሱን እናመሰግናለን፡፡ 5እርሱ እንደመረጣችሁ እናውቃለን ምክንያቱም የመስራቹን ስንሰብካችሁ በቃል ብቻ አልነበረም፡፡ መንፈስ ቅዱስ በመሀላችሁ በሀይል ይሰራ ነበር፣ ደግሞም መልዕክታችን እውነት እንደሆነ እጅግ ያረጋገጥልን ነበር፡፡ በተመሳሳይ መንገድ፣ ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ እናንተን ለመርዳት እነችል ዘንድ እንዴት በመካከላችሁ እንደተመላለስንና እንዳስተማርን እናንተ ታውቃላችሁ፡፡ 6 7 6በክርስቶስ በማመናችሁ ሰዎች መከራ ባደሩሱበት ጊዜ መጽናታችሁን አሁን ሰምተናል፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መከራን ሲቀበል እንደጸና እናተም ጸንታችኋል፤ እኛም ልክ ይህንኑ ነው ያደረግነው፡፡ በዚያን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ እጅግ ሀሴት ይሞላባችኋል፡፡ 7እናንተ በመከራ ስለጸናችሁ በመቄዶንያና በአካይያ አውራጃዎች የሚኖሩ አማኞች ሁሉ በመከራ ውስጥ ሲሆኑ እንዴት በእግዚአብሔር መታመን እንዳለባቸው ተምረዋል ፡፡ 8 9 10 8ሌሎች ሰዎች ከእናንተ የጌታ ኢየሱስን መልዕክት ሰምተዋል፡፡ ከዚያ እነርሱ ደግሞ በመቄዶንያና አካይያ በሙሉ ለሚኖ ህዝቦች የምስራቹን ሰብከዋል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን በብዙ ራቅ ያሉ ስፍራዎች የሚኖሩ ሰዎች እናንተ በእግዚአብሔር እንዳመናችሁ ሰምተዋል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር በእናንተ ህይወት ውስጥ የሰራውን ማውራት አላስፈለገንም፡፡ 9ከእናንተ ርቀው የሚኖሩ ሰዎች እኛ ወደ እናንተ ስንመጣ እንዴት የደመቀ አቀባበል እንዳደረጋችሁልን ለሌሎች እየተናገሩ ነው፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ጣኦታትን ማምለካችሁን እንደተዋችና ሁሉንም ማድረግ የሚችለውን እውነተኛ አምላክ የሆነውን እግዚአብሔርን ማመልክ እንደጀመራች እየተናገሩ ነው፡፡ አማኞች የሆናችሁት በእርሱ ነው! 10ልጁ ከሰማይ ተመልሶ ወደ ምድር እንደሚመጣ አሁን በጉጉት እየተጠባበቃችሁ እንደሆነም ደግሞ ነግረውናል፡፡ እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሙታን እንዳስነሳው በጽኑ ታምናላችሁ፡፡ ኢየሱስ በእርሱ የሚያምኑትን፣ እግዚአብሔር የዓለምን ህዝብ ሁሉ በሚቀጣበት ጊዜ ከመከራ እንደሚያወጣቸውም ታምናላችሁ፡፡